‹‹እኔ ጆርጅ ቡሽን (ፕሬዚዳንት) አላደንቅም፤ ጠፈር ላይ የወጡትንም አላደንቅም፡፡ የማደንቀው እነዚህን ሰዎች ለትልቅ ደረጃ ያደረሷቸው መምህራንን ነው፡፡›› መምህራን የሀገር ምሰሶዎች... መምህርነት የሙያዎች አባት... መምህር የእውቀት ብርሃን...ይህ እውነት ነው፡፡ እውነቱ ግን ዛሬ ላይ ተጋርዷል፡፡ መምህርነትም ሆነ መምህራን የነበራቸው ክብር ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ መሬት በአስደንጋጭ ፍጥነት እየወረደ ይገኛል፡፡ መምህራን በሙያቸው እያፈሩ ነው፡፡ እውቀታቸውን እየሰሰቱ ነው፡፡ አዎ፣ መምህራን ጫንቃቸው ጎብጦ ነገን በደበዘዘ ተስፋ የሚጠባበቁ ‹ምስኪኖች› እየሆኑ ነው፡፡ ግን እንዴት? ካድሬነት Vs መምህርነት ወጣት ነው፤ ገና ለስራው ዓለም ብዙ አበርክቶት የሚጠበቅበት፡፡ ወጣቱ በአዲስ አበባ አብዮት ቅርስ መሰናዶ ት/ቤ የኬሚስትሪ መምህር ነው፡፡ በስራው ዓለም ለአራት ዓመታት … [Read more...] about የመምህራን ፍዳ
Opinions
የኔ ሃሳብ
የደብተራው አምሳሉ ጡዘት!!!
ደብተራው አምሳሉ የቅድመ አያቶቹን ታሪክ ይዞ ፉከራና ቀረርቶውን ያስነካዋል፡፡ ነጻነትህ ጥሩ ሆኖ ሳለ፤ ደብተራነትህ ሳይጎዳህ የቀረ አልመሰለኝም፡፡ ግድ የለህም ጎድቶሃል፡፡ ምላሽ ይሁናችሁ ብለህ የደገምከው የመሰል አያቶችህን ተረት ነው፡፡ የዛን ዘመን ተረት ደግሞ ታሪክ እንዲሆን ትወዳለህ፡፡ በሌላ ወገን ያለውን ለማመን ግን አሻፈረኝ ባይነትህ ገርሞኛል፡፡ በመሠረቱ የወደዱትን ጽፈው ታሪክ አስብለው ያለፉት ያንተው ነገስታት እነሆ ዛሬ ላይ ታሪክ አልባ ሀገር ብትኖረን ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስባለሁ፡፡ የእራሳቸውን ማንነት ለማግዘፍ ሲሉ፤ ቅራቅንቦዋቸውን ሁሉ በመዝገብ ሲያኖሩ ከርመው፤ አንዳች እውነት ፍለጋ ምን ያህል እያደከሙን እንዳሉ ሳስብ አዝናለሁ፡፡ ነገስታቱ በረባ ባልረባው ሁሉ የእነርሱን ጀብድና መልካምነት አስፍረው አልፈዋል፡፡ አንዳንዴም ሳስበው በንግስናቸው ወራት ጦርነት … [Read more...] about የደብተራው አምሳሉ ጡዘት!!!
ኢህአዴግ እንደ ናቡከደነፆር
በአንድ ወቅት የዓለም ገናና ንጉስ የነበረው የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር ለ43 ዓመታት ባቢሎንን ገዝቷል፤ በስተሰሜን ሶሪያ በምዕራብ በፍልስጤም እስከ ግብፅ ግዛቱን አስፋፍቷል፡፡ ይህ ንጉስ ህጎችን ከመቀፅበት ይደነግጋል፣ ይለውጣል፡፡ ለእሱ ስርዓት ተገዥ ያልሆኑትን ያስራል፣ ይገርፋል፡፡ ንጉስ ናቡከድነፆር በጣም የሚፈራ እና ኃይለኛ ንጉስ ቢሆንም ከመውደቅ ግን አልዳነም፡፡ ለማንኛውም የዚህ ንጉስ ታሪክና የሀገራችን መንግስት ስርዓት ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገሮች ስላሉ እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡፡ ንጉስ ናቡከድነፆር በዘመኑ በጣም የሚፈራ እና የማይደፈር እንደመሆኑ መጠን የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው፡፡ በዚህም መሰረት ነው የሌለባቸውንና መልክ መልከኞችን ጥበብና ዕውቀት የሞላባቸውን በብልሀት ዳኞችንና አስተዋዮች የሆኑትን በንጉሱም ቤት መቆም የሚችሉ ብላቴናዎችን በእስራኤል ልጆች … [Read more...] about ኢህአዴግ እንደ ናቡከደነፆር
የክልል እና የፌዴራል ምርጫ!
ምርጫ 2005 የአካባቢ (የክልል ቀበሌ፣ ወረዳ እና ከተሞች) እንዲሁም የእራስ ገዞቹ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ምክር ቤቶች ምርጫ ነበር። ብዙ የተወራለት የ33ቱ ተቃዋሚዎች ህብረት ቢያንስ ቢያንስ በአዲስ አበባ ከተለመደው የተቃዋሚዎች ምርጫ ሽሽት የተሻለ ነገር ሊሰራ ነው ብለን በተስፋ ስንጠብቀው ምርጫው ሲቃረብ ስለ ህውሃት/ኢህአዴግ አምባገነንነት የማናውቅ ይመስል እንደ አዲስ ዜና በህውሃት/ኢህአዴግ ስር ምርጫው ነፃ አይሆንም አለን። ወዲያው እራሱን ከምርጫ ማግለሉን ገለጸለን። በዚህ አይነት የአዲስ አበባን ምክር ቤት 138 መቀመጫ እና የከንቲባውን ቦታ ካለምንም ፉክክር ተቃዋሚው በነፃ ለህውሃት/ኢህአዴግ በማስረከቡ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እውቅና ለማግኘት ሳይቀር በዚህ ምክር ቤት ስር በመጉላላት ላይ ይገኛል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የክልል እና የፌዴራል ምርጫ!
ነገረ ኢትዮጵያ
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about ነገረ ኢትዮጵያ
ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ፈጠረ ወይስ የትግራይ ሕዝብ ወያኔን?
እንደሚታወቀው በሕወሓት የትጥቅ ትግል ዘመን የትግራይ ሕዝብ ከሞላ ጎደል ሊባል በሚችል ደረጃ ለሕወሓ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ያደርግ ነበር፡፡ ይሄንን ዓይነት ገደብ የለሽ ድጋፍ የትግራይ ሕዝብ ለሕወሓት እንዲሰጥ ያደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች ተብለው ሲጠቀሱ የምንሰማቸው፡- የሕወሓት ታጋዮች ልጆቹ የአብራኩ ክፋይ ስለሆኑ፡፡ ወያኔ የትግራይ ሕዝብ ለደርግጥላቻ እንዲኖረውና ከጎኑ እንዲሰለፍ ለመድረግ ደርግ በሕዝቡ ላይ የፈጸመው አስመስሎ የፈጸማቸው የግፍ ሴራዎች ስለሰመሩለት ሕወሓት ለትግራይ ሕዝብ ‹‹ወደፊት እንዲህ እንዲህ አደርጋለሁ›› ብሎ ቃል በመግባቱና በሕዝቡም በመታመኑ፡፡ እንደነሱ አገላለጽ “ኢትዮጵያ ውስጥ ለሺህዎች ዓመታት በነበረው አገዛዝ ተረግጠው፣ ተንቀው፣ በማንነታቸው እንዲያፍሩ፣ እንዲሸማቀቁ፣ የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው በመደረጉ እንደዜጋ ባለመታየታቸው … [Read more...] about ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ፈጠረ ወይስ የትግራይ ሕዝብ ወያኔን?
“አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ።”
ወንድሜ ህይ! በመጀመሪያ አነሳስህ ታሪክ መሰረተ አድርገህ ነው የተንቀሰቀስከው። አሁን ግን ሰበካውን፣ ፖላቲካውን፣ ታሪኩን (ተረት-ተረት)፣ የትምክህትና የንቀት ቀለቶችህ ተበውዘው ሊክ እንደካርታ ጨዋታ አኬር (ጆከር) ፍለጋ የሚባዝን ሰው መሰልከኝ። አሁን በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንድ ያኔው 19ኛ ክፍለ ዘመን ብዙ የተናገራ እንድሚያሸንፍ አይደለም። አማሪኛችሁን ስለ ከሸንክና በጥሩ ቃላቶች ነገሮችን ስለ ሸፋፈንክ (ቅኔም) እንበለው፣ ሃቁ ተደብቆ አይቀርም። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) አቶ ቃሉ ኩሣ ይህንን ምላሽ የጻፉት አቶ አምሳሉ ገ/ኪዳን “መልሳቹህ” በማለት ለሰጡት ምላሽ ነው። … [Read more...] about “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ።”
“ኅብረ ሐመልሚል”
“የአረንጓዴ፤የቢጫ፤ የቀይ፤ የነጭና የጥቁር ነጠብጣብ፤ የብዙ አይነት ቀለማት ህብር፤ በማይዝግ በብር ሰሌዳ ላይ በባለሙያ የተሰሩ የወርቅ፡ ያልማዝና የዕንቁ ፈርጦች እና ጉብጉባቶች” የአቶ መላኩ አሰፋን የህይወት ታሪክ ለመግለጽ “ኅብረ ሐመልሚል ቀይህ ወጸዓድዒድ አርአያ ኮሰኮስ ዘብሩር”ብለን ውበት የምንገልጽበትን የግዕዝ ቋንቋ ሐረግ መነሻ ማድረጉ ተስማሚ ይመስለኛል። ይሁን እንጅ ያቶ መላኩን ሁለንተና ለመግለጽ ወደዚህ ውበት ገላጭ ሀረግ ከመግባቴ በፊት፤ በሩቅና በቅርብ ላሉት ዘመዶቹና ወዳጆቹ ህልፈቱን ለማርዳት ስለሚረዳ፤ ተወልዶ እትብቱ ከተቀበረባት መንደር ጀምሬ የረገጣቸውንና የቆየባቸውን ቦታወች ማስቀደሙ ተገቢ እንደሆነ እገምታለሁ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “ኅብረ ሐመልሚል”
ዲና ሙፍቲ ይመችዎት – “በነጻው ፕሬስ” ስም
ለምሳሌ አንድ አናጢና ግንበኛ የነበረ ሰው ጊዜ ረድቶት ወይም ተምሮ ወይም እድገት አግኝቶ ወይም …. በቃ በሆነ ነገር የጦር ጄኔራል ቢሆንና ተመልሶ ግንበኛ ቢሆን ምን ተብሎ ሊሰየም ነው? ግራ ያጋባል። ግን ደግሞ ላያጋባም ይችላል። የዛሬዎቹ ጄኔራሎች ኢንቨስተር ስለሆኑ ነዋ!! ለምሳሌ አንድ አምባሳደር ተብሎ የ"ተመደበ" ሰው፣ በግምገማ በሉት በገገማ "በቃህ" ቢባልና ቀድሞ ወደነበረው ሙያ ወደ ነርስነቱ ቢመለስ ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? “አምባሳደር፣ ነርስ፣ እገሌ …”? ቀጭኑ ዘ-ቄራ ነኝ። በውል በማይገባችሁ ምክንያት ተሰውሬ ነበር። ዛሬ እግር ጣለኝና "ላሸብር" መጣሁ። ሰላምታዬ መሆኑ ነው። መለስ ድንጋዩ ይቅለላቸው፣ አርማታው ስፖንጅ ይሁንላቸውና ብዙ አይነት የሰላምታ ቋንቋና ስታይል "አውርሰውን" አልፈዋል። ታላቁና አርቆ አስተዋዩ መሪያችን!! ህወሃቶች በዚህም ይቀኑ ይሆናል … [Read more...] about ዲና ሙፍቲ ይመችዎት – “በነጻው ፕሬስ” ስም
ትግል እምቢታ እንጅ አቤቱታ አይደለም
ምንም እንኳን ወያኔን እንቃወማለን የሚሉ ድርጅቶች ሁሉ ተቃዋሚ ሃይሎች በመባል በአንድ ጎራ ተጠቃለው ይታወቁ እንጅ በውስጣቸው የተሰሉፉት ሃይሎች አንድ አይነት የትግል ስልትም ሆነ ብሄራዊ ራዕይ ያላቸው እንድልሆኑ ግልፅ ነው። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በጥገና ለውጥ ስርዓቱ እንዲሻሻል ማስገደድ ይቻላል የሚሉ፣ ሌሎች ደግሞ ስርዓቱ መቀየር አለበት የሚሉ፣ ነገር ግን የሃገሪቱን ሉአላዊነት ግምት ውስጥ የማያስገቡና የባዕዳንን የቆየ ተፅዕኖ በአዲስ ቀለም ለማስቀጠል የሚፈልጉና ዴሞክራሲን ከይስሙላ ምርጫ ጋር ቀላቅለው የሚያዩ፤ ጥቂቶች ደግሞ መገንጠልን በግልፅ እሚያራምዱ ወይም ይህንኑ ዓላማ በአዲስ ቋንቋ አለዝበው ሁኔታው እስኪመቻች የሚጠብቁና ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ነን ቢሉም እነዚህኑ ክፍሎች የሚያግዙና የሚያበረታቱትንም ያጠቃልላል። ከነዚህ ሁሉ ተለይተው የቆሙት ሃይሎች ደግሞ፣ ያለው … [Read more...] about ትግል እምቢታ እንጅ አቤቱታ አይደለም








