
- አትሸወዱ! የትግራይ ደህንነት(Security) ከእጃችን አልወጣም። ያ ሲባል ግን መቼም ቢሆን ጦርነትን ምርጫ አናደርግም። በሆነ አጋጣሚ ጦርነት የግድ ከሆነና appetite ካለን ግን ማን ያግደናል? ሰራዊታችን እንደሆነ ከኛ ጋር ነው ያለው።
- ትጥቅ በመፍታትና መሳሪያ በማስረከቡ ዙሪያ ላይ ምንም መደናገር አያስፈልግም። እነሱ የፈለጉት ሌላ ነበር። የሆነው ሌላ ነው። በዚህ ዙሪያ ብዙ መናገር አልፈልግም -sensitive material ነው። እርግጥ በትጥቅ ማስፈታት ዙሪያ የሚሰሩ የቴሌቪዢን ፕሮግራሞችን ሲመለከቱ ስጋት የሚገባቸው አንዳንድ የኛ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ።
- አሁን ለምሳሌ መንግስት ደብዳቤ ሲፅፍልን “የትግራይ አካታች ጊዜያዊ መንግስት” እያለ ነው የሚፅፍልን። ይሄ ለምን ሆነ? የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ለምን አልተባለም? ስንላቸው “አይ ካቢኔው ከበፊቱ የተቀየረ ለመሆኑ ለህዝብ ለማሳየት ነው” ይሉናል። ይሄ ደግሞ እኛን ይጠቅመናል እንጂ አይጎዳንም። እነሱ ይቺን ሲሉ ኦኮ “ትግራይ ውስጥ ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ሁሉም ነገር በህወሐት እየተፈፀመ ነው” የሚለውን ትችት ከወዲሁ ለማስቀረት እንደ “ታኮ” ነው የሚጠቀሙባት። እውነታው ግን አሁን ያሉት የካቢኔው አባላት ያው በፊት የተመረጡት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ናቸው። ደብረፂዮን ብቻ ነው የተቀየረው። እሱንም እኔ ነኝ የተካሁት። እኔ ደሞ የህወሓት ስራአስፈፃሚ ነኝ።
- አሁን ለምሳሌ ዶ/ር አቢይንም ሆነ አቶ ኢሳያስን በጄኖሳይድ ወንጀል ለመክሰስ ጊዜውም ሆነ ሁኔታዎች ለኛ አይፈቅዱልንም። ሌላው ቀርቶ አሜሪካ እንኳን በትግራይ ህዝብ ላይ ጄኖሳይድ ተፈፅሟል ብላ ለመፈረጅ ጫፍ ከደረሰች በኋላ ግራ በሚገባ ሁኔታ ፍረጃውን ትታ ጭራሽ እኛንም በወንጀሉ ተጠያቂ እንደሆንን በመጥቀስ በቆቦና በጭና ወንጀል ፈፅማችኋል የሚል allegation ሰነዝራብናለች።
- ጌታቸው ንግግሩን የቀጠለው ማንኛውም የአንድ አገር ወንጀለኛ መሪ የዘገየውን ያህል ቢዘገይ ከመጠየቅ እንደማይድን ቻርለስ ቴለርንና ዑመር አልበሽርን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ነበር። በዚህ ንፅፅራዊ ማጣቀሻው ላይ ቻርለስ ቴለር በICC ከተከሰሰ ከ10 አመት በኋላ በወንጀሉ እንደተጠየቀ ጠቅሷል።
- ጌታቸው በዚህ ንግግሩ ላይ ይህ የተጠያቂነት ጉዳይ እንደሌሎቹ ወንጀለኞች ሁሉ 10 እና ከዛ በላይ አመታት መጓተት እንደሌለበት ጠቅሶ አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ ምክንያት ግን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም ሆነ ህወሓት የተጠያቂነትን ጉዳይ በአጀንዳነት አንስቶ ንቅናቄ መፍጠር ስለሚያዳግተው በአክቲቪዝሙ ላይ የሚሳተፉ የትግራይ አክቲቪስቶች አጀንዳውን ማስተጋባት እንዳለባቸው አሳስቧል።
- በንግግሩ መጨረሻ ላይ እነ ዶ/ር አቢይን ለመወንጀል በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ ላደረገላቸው የትግራይ አክቲቪስቶች “ስራ መከፋፈል አለብን” ሲል ትዕዛዝ “ወ” ምክር ቢጤ አስተላልፏል።
ትርጉም፤ በአስፋው አብርሃ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply