“አንድ በሬ ሸጬ ስድስት ዓመት በመቀሌ የታሰረውን የልጅ ልጄን በደከመ አቅሜ ሄጄ አስፈትቻለሁ። ከተፈታ በኋላም አፋኙ የህወሓት ጁንታ በሚደረግበት ጫናና ክትትል ተማሮ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዷል። የልጅ ልጄ ያለበትን ቦታና ምን እንዳጋጠመው ስለማላውቅ የበረሃ ራት ሆኖ ይሆን ብዬ እየተጨነኩ ነበር። አምና ግን ሳውዲ መግባቱን ስለሰማሁ ደስታዬ ወደር የለውም” የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው።
ቃፍታ ሁመራ ከተማ ከሀዲው የህወሓት ጁንታ ነጻ ከወጣች ሶስት ሳምንት ሁኗታል። ከተማዋ ነጻነቷን በመቀናጀቷ እፎይታ ከተሰማቸው ነዋሪዎች መካከል አንዷ ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። አፋኙ ቡድኑ በማንነታቸው ምክንያት በእኚህ አዛውንት ላይ ከፍተኛ ማንገላታት፣ ሰቆቃና ግፍ ፈጽሞባቸዋል።
ማንነቴን አልሸጥም እኔ የወልቃይት አማራ ነኝ አባቴ፣ አጎቶቼ ይግባኝ ሲኖራቸው መቀሌ ሳይሆን ደባርቅና ዳባት ሄደው ሲያስፈጽሙ ነበር ብዬ በአደባባይ በመናገሬ እያረስኩና እያሳረስኩ ልጆቼን ያሳደኩበትን መሬቴን ተነጥቄያለሁ ይላሉ ። (ኢፕድ)
Leave a Reply