በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቅንጅት በተከናወነ ኦፕሬሽን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡ ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና በተለያየ መልኩ ባደረገው ጥናት መነሻነት በየካ፣ በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ሺሻ በሚጨስባቸው ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በተከናወነ የኦፕሬሽን ስራ እርምጃ ተወስዷል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ወረዳ 3 በተለያዩ አካባቢዎች በአጠቃላይ … [Read more...] about ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ