• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

January 16, 2023 08:50 am by Editor Leave a Comment

በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቅንጅት በተከናወነ ኦፕሬሽን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡

ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና በተለያየ መልኩ ባደረገው ጥናት መነሻነት በየካ፣ በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ሺሻ በሚጨስባቸው ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በተከናወነ የኦፕሬሽን ስራ እርምጃ ተወስዷል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ወረዳ 3 በተለያዩ አካባቢዎች በአጠቃላይ በ24 ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽት ጀምሮ ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 8ቱ ሺሻ ሲያስጨሱ ተገኝተዋል፡፡

293 የሺሻ ዕቃዎች ከእነዚሁ ቤቶች ውስጥ የተያዙ ሲሆን አዋኪ ድርጊቱን ሲፈፅሙ እና ሲያስፈፅሙ የተገኙ 118 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው በንግድ ቤቶቹ ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች በተከናወነው የኦፕሬሽን በሁለቱ ክፍለ ከተሞች ፍተሻ ካደረጉባቸው 23 ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች መካከል በ7ቱ ላይ ሺሻ ሲጨስባቸው እንደተገኙ ተናግረዋል።

ከእነዚህ 7 ቤቶች ውስጥ 207 የሺሻ ማጨሻ ዕቃዎች እና በህገ ወጥ ተግባሩ ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 61 ግለሰቦች ተይዘው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ እንደሚገኝ ምክትል ኢንስፔክተር አባይ ባህሩ ገልፀዋል፡፡

በቂርቆስ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች እርምጃ የተወሰደባቸው፤

1. ሪቮ አዲስ ላወንጅ :- 87 የሺሻ ዕቃና በድርጊቱ ተሳታፊ 200 ወጣቶች

2. አቤም ሆቴል 22 የሺሻ ዕቃና 8 ወጣት

3. ናሽናል ሆቴል 16 የሺሻ ዕቃና 67 ወጣቶች

4. ሞሲሳ ሆቴል 7 የሺሻ እቃ

በቦሌ ክ/ከተማ

5.ቀነኒሳ ሆቴል 35 የሺሻ እቃ

6.ዘባንክ ላውንጅ 28 የሺሻ እቃ

በተመሳሳይ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ በተደረገ ፍተሻ 86 የሺሻ ማጨሻ ዕቃዎች እና በአዋኪ ድርጊቱ ላይ ተሳትፈው የተገኙ 57 ግለሰቦች እንደተያዙ የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሃላፊ ኮማንደር አስፋው የሺዳኜ ተናግረዋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ እርምጃ የተወሰደበት፤

7.ቤልቪው ሆቴል 86 የሺሻ ዕቃ እና 54 ሠው ነው።

በህጋዊነት ሽፋን ህገ ወጥ ተግባር እንዲፈፀም በመፍቀድ በከተማችን ለሚከናወነው የፀጥታ ስራ እንቅፋት የሚሆኑ አንዳንድ ሆቴሎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች ፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች እና መሰል የንግድ ተቋማት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጣይነት እንዳለው የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህብረተሰቡ መረጃ እና ጥቆማ በመስጠት ትብብሩን እንዲያጠናክር ጥሪውን አቅርቧል፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8፤ አዲስ ሚዲያ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Social Tagged With: Ethiopia Night Clubs, operation dismantle tplf, Revo Addis, shisha ethiopia

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule