የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር ከ2011 ዓም እስከ 2022 ዓም በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመራ የነበረው ተወልደ ገብረማርያም ተስፋይ ከለቀቀ በኋላ በርሱ የአስተዳደር ዘመን ለተሠራ ስህተት አየር መንገዱ 425ሺህ ዶላር ተቀጣ። የአሜሪካ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (ሚኒስቴር) ትላንት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን 425ሺህ ዶላር፤ የአረብ ኤሚሬትሱ ኢትሃድ አየር መንገድ ደግሞ 400ሺህ ዶላር መቅጣቱን አስታውቋል። አየር መንገዶቹ የቀጣው የአሜሪካው የትራንሰፖርት ሚኒስቴር ሲሆን ያቀረበባቸው ክስ ባልተፈቀደ የአየር ክልል የአሜሪካ አየር መንገዶችን ኮድ በመጠቀም መሆኑን ገልጾዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እኤአ ከየካቲት 2020 ዓም እስከ ታህሣሥ 2022 ዓም ባሉት ዓመታት የአሜሪካውን አየር መንገድ ዩናይትድ ኤርዌይስን ኮድ በመጠቀም … [Read more...] about የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተወልደ አስተዳደር ዘመን ለተሠራ ስህተት 425ሺ ዶላር ተቀጣ