• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተወልደ አስተዳደር ዘመን ለተሠራ ስህተት 425ሺ ዶላር ተቀጣ

December 14, 2024 01:44 am by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር ከ2011 ዓም እስከ 2022 ዓም በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመራ የነበረው ተወልደ ገብረማርያም ተስፋይ ከለቀቀ በኋላ በርሱ የአስተዳደር ዘመን ለተሠራ ስህተት አየር መንገዱ 425ሺህ ዶላር ተቀጣ።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (ሚኒስቴር) ትላንት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን 425ሺህ ዶላር፤ የአረብ ኤሚሬትሱ ኢትሃድ አየር መንገድ ደግሞ 400ሺህ ዶላር መቅጣቱን አስታውቋል።

አየር መንገዶቹ የቀጣው የአሜሪካው የትራንሰፖርት ሚኒስቴር ሲሆን ያቀረበባቸው ክስ ባልተፈቀደ የአየር ክልል የአሜሪካ አየር መንገዶችን ኮድ በመጠቀም መሆኑን ገልጾዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እኤአ ከየካቲት 2020 ዓም እስከ ታህሣሥ 2022 ዓም ባሉት ዓመታት የአሜሪካውን አየር መንገድ ዩናይትድ ኤርዌይስን ኮድ በመጠቀም በኢትዮጵያና በጂቡቲ መካከል ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆኑ በረራዎችን ማካሄዱን በምርመራ መገኘቱን የደንበኞችን መብት የሚያስጠብቀው የአሜሪካ መሥሪያ ቤት Department’s Office of Aviation Consumer Protection (OACP) አስታውቋል።

እነዚህ በጂቡቲና በኢትዮጵያ መካከል የአሜሪካንን አየር መንገድ ኮድ በመጠቀም በአየር መንገዱ የተደረጉት በረራዎች የአሜሪካው የአቪዬሽን አስተዳደር Federal Aviation Administration (FAA) በረራ እንዳካሄድባቸው ብሎ የከለከላቸው መስመሮች ናቸው። ከተካሄዱት በረራዎች አንዱ የተደረገው OACP በረራ እንዳይካሄድ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል።  

እነዚህ ሕገወጥ በረራዎች የተካሄዱትና ማስጠንቀቂያውም ተሰጥቶ ችላ የተባለው ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱን ከአቶ ግርማ ዋቄ በ2011 ዓም ተረክቦ እስከ 2022 ዓም ድረስ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመራ በቆየበት ዓመታት ነበር።

ኢትሃድም እንዲሁ የጄትብሉን ኮድ በመጠቀም በአረብ ኤምሬትስና በአሜሪካ መካከል በረራዎችን በማድረጉ መቀጣቱ መግለጫው ጠቅሷል።

የአሜሪካው የአቪዬሽን አስተዳደር (FAA) ክልከላ ባደረገባቸው መስመሮች የሚበሩ አየር መንገዶችን በተመሳሳይ መልኩ የመቅጣት አሠራር ያልተለመደ አይደለም።

በመስከረም 2024ዓም የካናዳ አየር መንገድ ከዩናይትድ ኤርዌይስ ጋር ኮድ በመጋራት በተከለከለ የኢራቅ መስመር ላይ በመብረሩ 250ሺህ ዶላር ተቀጥቷል።

እንደዚሁ ኤሚሬትስ አየር መንገድ በተተከለከለ የባግዳድ አየር ላይ የጄትብሉ ኤርዌይስን ኮድ ተጠቅሞ በመብረሩ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ተቀጥቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመቀጣቱ መረጃ እንደወጣ ጉዳዩ ልክ አሁን በአቶ መስፍን ጣሰው የአስተዳደር ዘመን የተፈጸመ ተደርጎ የተሰራጨው ዜና እጅግ እንዳሳዘናቸው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀሰ የጠየቁ የአየር መንገዱ ሹም ለጎልጉል አስታውቀዋል።

እንዲያውም ከዚህ በዘለለ አየር መንገዱ ወታደር ሲያመላልስ ተቀጣ ብለው የዘገቡ እንዳሉ የጠቆሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ከመቶ በላይ አውሮፕላን ለመግዛት ሲስማማ፣ ከስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ ታላቅ የአውሮፕላን ተርሚናል ዕቅድ መያዙ፣ ወዘተ አንድም ትንፍሽ የማይሉ የአየር መንገዱን ስም ለማጥፋት በዚህ ፍጥነት መሄዳቸው ዓላማቸውን በግልጽ የሚያሳይ ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የመንግሥት ኮሙኒኬሽንም ሆነ መንግሥት ከፍተኛ ዋጋ የተመነላቸው ፕሮፓጋንዲስቶች እንዲሁም የራሱ የአየር መንገዱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሥልጣናትና በዚህ ጥፋት ውስጥ እጃቸው የሌለበት አመራሮች የማኅበራዊ ሚዲያ አድናቂ ከመሆን በዘለለ በሚዲያ ወጥተው በዝርዝር ጉዳዩን አለማስረዳታቸውና በማን አስተዳደር ዘመን እንደተፈጸመ በመግለጽ ጫጫታውን ማምከን አለመቻላቸው ወይም አለመፈለጋቸው ትልቅ ጥያቄ እንደፈጠረባቸው አንድ የአቪዬሽን ባለሙያ ለጎልጉል በውስጥ መስመር በላኩት መልዕክት ገልጸዋል።

ይህ ዘገባ እስከታተመ ድረስ እንደ ቢቢሲ አማርኛና በተወልደ አገልጋይነቱ ኩራት የሚሰማው እንደ ኤሊያስ መሠረት ዓይነቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መቀጣቱን በተመለከተ አንዳች ነገር አለመጻፋቸው ለምን ይሆን ብሎ ለሚጠይቅ የዜናው ይዘት ስለገባቸውና “ዓሣ ጎርጓሪ” ላለመሆን በመፈለጋቸው እንደሆነ ለመረዳት ብዙም አይከብድም።

የአሜሪካው የትራንሰፖርት ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይገኛል፤

USDOT Fines Ethiopian Airlines and Etihad Airways for Operating Flights Carrying a U.S. Carrier’s Code in Prohibited Airspace

Thursday, December 12, 2024

WASHINGTON – The U.S. Department of Transportation (DOT) today fined Ethiopian Airlines $425,000 for operating flights carrying United Airlines’ designator code and Etihad Airways $400,000 for operating flights carrying JetBlue Airways’ designator code in regions in which a Federal Aviation Administration (FAA) flight prohibition was in effect for U.S. operators. The airlines were ordered to cease and desist from future similar violations.  

An investigation by the Department’s Office of Aviation Consumer Protection (OACP) revealed that between February 2020, and December 2022, Ethiopian Airlines operated a significant number of flights carrying the United Airlines code between Ethiopia and Djibouti in airspace prohibited by the FAA to U.S. operators. One of those prohibited flights took place after OACP issued an investigation letter to Ethiopian Airlines regarding this issue. By operating these flights in this manner, Ethiopian Airlines violated the conditions of its authority to operate and engaged in air transportation without the proper DOT authority.  

A separate OACP investigation revealed that between August 2022 and September 2022, Etihad Airways operated numerous flights carrying the JetBlue Airways code between the United Arab Emirates and the United States in airspace prohibited by the FAA to U.S. operators. Further, although OACP notified Etihad Airways of the problematic conduct in September 2022 and November 2022, OACP learned that between January 2023 and April 2023, Etihad Airways operated several additional flights carrying the JetBlue Airways code between the United Arab Emirates and the United States in airspace prohibited by the FAA to U.S. operators. By operating these flights in this manner, Etihad Airways violated the conditions of its authority to operate and engaged in air transportation without the proper DOT authority.  

The consent orders are available at www.regulations.gov, docket number DOT-OST-2024-0001.  

For information about airline passenger rights, as well as DOT’s rules, guidance, and orders, the Department’s aviation consumer website can be found at https://www.transportation.gov/airconsumer.   

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News Tagged With: Department of Transportation (DOT), Ethiopian Airlines, ethiopian terrorists, Federal Aviation Administration (FAA), operation dismantle tplf, tewolde gebremariam, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Bekele says

    March 30, 2025 06:19 am at 6:19 am

    Why is it necessary to mention the X CEO? Is it because he is from Tigray? Stop this narrow-mindedness. EAL was punished like many others.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule