ከኤርትራ ሰሞኑን የሚወጡ መረጃዎች ከጉዳዩ ባለቤቶች ማረጋገጫ ወይም ማስተባበያ ባይቀርብበትም ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አቋምና ተስፋ ባላቸው ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል። አንዳንድ በብሎግ ሂሳብ የሚጫወቱ የኤርትራ መንግሥት አገልጋዮች ለጉዳዩ ጆሮ ዳባ ቢሉም በዋና በተቃዋሚነት የሚታወቁት የኢሳያስ ባላንጣዎች ለወሬዎቹ ሽፋን በመስጠት ግንባር ቀደም ሆነዋል። የ1997 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት “ህወሃት ሰራዊቴን በመያዝ ጓዜን ጠቅልዬ ወደ ትግራይ ምድር እገባለሁ” ማለቱን አስነብቦ የነበረው ኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተር ሰሞኑን የህወሃት ሊቀመንበርን ጠቅሶ ኤርትራ ላይ ጦርነት የማወጅ ፍላጎት እንዳለ ይፋ አድርጓል። ኢንዲያን ኦሽን ከውስጥ አዋቂዎች አገኘሁ በማለት ሌላ ያሰነበበው ዜና የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ ካናዳ ጥገኝነት … [Read more...] about “የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም”
Eritrea
ጥፋቱ የማን ነው?
ኤርትራዊ ሆነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት የተሸከሙት አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈርድ፣ ዜጎችን የሚያሸማቅቅ፣ ለአገራቸው የተሰውትን የሚያናንቅና በተለይም በውድ አገራቸው የሚመኩ ወገኖችን የሚያኮስስ ንግግር ማድረጋቸው በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ ቅሬታ ማስነሳቱ ታወቀ። አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ እነ አቶ ተወልደን በስም በመጥራት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ ያደረጉት አቶ በረከት “አንድነትና አንድ አገር” የሻዕቢያ መዝሙር መሆኑን በመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠል ለሚፈልጉ ጊዜው ሲደርስ እንደ ኤርትራ መገንጠል መብታቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሚኒስትር ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ይህንን የተናገሩት Eritrean Oppositions Arabic Paltalk በሚሰኝ የኤርትራ ተቃዋሚዎች የፓልቶክ መወያያ ክፍል … [Read more...] about ጥፋቱ የማን ነው?


