ጋምቤላን በረሃ አድርጎ፤ ሕዝቧን ገድሎ፤ በተለይ የአንድ ክልል “ዜጎችን” ብቻ ጠቅሞ በጋምቤላ የተተገበረው “ኢንቨስትመንት” ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ያህል የማይከፈል ዕዳ ውስጥ መዘፈቁን ህወሓት/ኢህአዴግ አመነ። ልክ የዛሬ 14ዓመት ነበር መለስ በመራው ስብሰባ ላይ “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለው ትዕዛዝ የወጣው። በዚህም መሠረት 424 ንጹሃን በግፍ ተጨፈጨፉ፤ መሬታቸው ተነጠቀ፤ ለባለሃብቶች በሃያ ብር (በወቅቱ 1 ዶላር) ሒሳብ ተቸበቸበ። ህወሓት ደርግን ሲወነጅልበት የነበረውን ግዳጅ ሠፈራና መንደር ምሥረታ በአኙዋክ ወገኖች ላይ ተፈጸመባቸው። ይህ ሁሉ የሆነው ለ"ልማት" ነው ተባለ። ሪፖርተር (8 November 2017) ባወጣው ዘገባ ላይ እንዳሰፈረው “ለጋምቤላ እርሻዎች የተሰጠው ብድር የልማት ባንክን መመለስ ያልቻሉ ብድሮች ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር … [Read more...] about ከ424 ዜጎች ጭፍጨፋ፤ ከ14 ዓመት መሬት ነጠቃ በኋላ የጋምቤላ “ኢንቨስትመንት” 9ቢሊዮን ብር ያህል ከስሯል
anuak
“እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”
እነዚህም የህወሓት ነፍሰበላዎች ይፈለጋሉ! የሰላም ሰዎች የሆኑት አኙዋኮች ከህወሓት ጋር መቃቃር ውስጥ የገቡት ገና ከጅምሩ ነበር። የቀድሞው የአኙዋክ ምክርቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ኦባንግ ሜቶ እንደሚሉት ችግሩ የተያያዘው ህወሓት የጋምቤላን ለም ምድር የራሱ ለማድረግ ከመፈለጉ ጋር ነው። ህወሓት ሥልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ የጋምቤላን ብቸኛ ጄኔሬተር በመንቀል ከመውሰድ አልፎ በአሎሮ ግድብ ላይ የነበሩትን ወደ 400 የሚሆኑ ማሽነሪዎች እና የእርሻ መሣሪዎች በምሽት ወደ ትግራይ ነቅሎ ወስዷል ይላሉ አቶ ኦባንግ። በመቀጠልም ተዝቆ የማያልቀውን የጋምቤላን ድንቅ ሃብት በረኸኞቹ ህወሃቶች ለመዝረፍ ውሳኔያቸው አደረጉ። “መሬቴን አላስነካም” በሚለው አኙዋክና ህወሓት መካከል ያለውን መቃቃር አንድ “ዕልባት” ላይ ለማድረስ በሚል አኙዋክን ማጥፋት የህወሓት ቀዳሚ ሃሳብ ሆነ እንደ አቶ … [Read more...] about “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”