ጋምቤላን በረሃ አድርጎ፤ ሕዝቧን ገድሎ፤ በተለይ የአንድ ክልል “ዜጎችን” ብቻ ጠቅሞ በጋምቤላ የተተገበረው “ኢንቨስትመንት” ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ያህል የማይከፈል ዕዳ ውስጥ መዘፈቁን ህወሓት/ኢህአዴግ አመነ።
ልክ የዛሬ 14ዓመት ነበር መለስ በመራው ስብሰባ ላይ “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለው ትዕዛዝ የወጣው። በዚህም መሠረት 424 ንጹሃን በግፍ ተጨፈጨፉ፤ መሬታቸው ተነጠቀ፤ ለባለሃብቶች በሃያ ብር (በወቅቱ 1 ዶላር) ሒሳብ ተቸበቸበ። ህወሓት ደርግን ሲወነጅልበት የነበረውን ግዳጅ ሠፈራና መንደር ምሥረታ በአኙዋክ ወገኖች ላይ ተፈጸመባቸው። ይህ ሁሉ የሆነው ለ”ልማት” ነው ተባለ።
ሪፖርተር (8 November 2017) ባወጣው ዘገባ ላይ እንዳሰፈረው “ለጋምቤላ እርሻዎች የተሰጠው ብድር የልማት ባንክን መመለስ ያልቻሉ ብድሮች ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር አድርሷል”።
በጋምቤላ የአኙዋክ ተወላጆች ተጨፍጭፈውና ከመሬታቸው ተፈናቅለው “ለሰፋፊ እርሻ” በሚል ሲቸበቸብ ከነበረው መሬት “ወደ ሥራ የገባው” 15በመቶው ብቻ መሆኑን ህወሃት/ኢህአዴግ ማስታወቁን ጎልጉል የዛሬ ዓመት ዘግቦ ነበር። የጎልጉል ዘገባ ሲቀጥል፤ ለ“እርሻ ልማት” በሚል በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ብድር ተሰጥቷል። የመሬት ካርታ “ከቢሮ ውጪ በመኖሪያ ቤቶችና በጫት ቤት ውስጥ” ሲሰራ ቆይቷል። በብድር አሠጣጡ ላይ ቁልፍ የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊ ኢሳያስ ባህረ ከሥልጣኑ ለመነሳት ምክንያት የሆነው “ብድር በመስጠቱ ሂደት ለተወሰኑ የባለሃብቶች ቡድን (ለትግራይ ተወላጆች) በማድላቱ ነው” መባሉን ጨምሮ ዘግቦ ነበር።
በጋምቤላ ይህ ነው የማይባል ግፍና የዘር ማጽዳት ተካሂዶ ከምስኪን ረዳተቢሶች የተነጠቀው መሬት ከጥቅም ውጪ ሆኗል። ገና ከጅምሩ አሠራሩ ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ በተለያዩ ሪፖርቶች ሲነገረው የነበረው ህወሃት/ኢህአዴግ የጋምቤላ አኙዋኮችን ከምድራቸው ላይ በማጥፋት መሬታቸውን ከነጠቀ በኋላ “ሰፋፊ እርሻ” በሚል አንዱን ሔክታር መሬት በሃያ (20) ብር ሲቸበችበው ቆይቷል። በኢትዮጵያ እስከ 3ሚሊዮን ሔክታር መሬት ከነዋሪዎች እየተነጠቀ፣ ደን እየተጨፈጨፈ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ የህወሃት/ኢህአዴግ ደጋፊዎችን ኪስ ሲያደልብ፤ ድርጊቱ ሊታሰብበት እንደሚገባ ሲነገር፤ “እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልሸጥነው መሬት ነው” በማለት ሞት እንደ ቡሽ ክዳን በድንገት የነቀለው መለስ ተናግሮ ነበር።
ዓመታት ተቆጥረው፣ የሰው ነፍስ ከትንኝ ያነሰ ደረጃ ወርዶ፣ በግፍ ተጨፍጭፎ፣ ቀሪው ኑሮው ተመሳቅሎ፣ መሬቱ ተነጥቆ፣ ወደማይፈልግበት ቦታ በግዳጅ ሰፈራ ተወስዶ፣ የተፈጥሮው ደን ተጨፍጭፎ፣ ኑሮው ከሞት በታች ከሆነ በኋላ ህወሃት/ኢህአዴግ አደረግሁ ባለው ጥናት መሬቱም፣ ብድሩም ከንቱ ሆኗል፤ “ኢንቨስተሮቹ” ገንዘቡን አባክነውታል፤ “ለመንግሥት” የገባ ጥቅም የለም፤ ትርፉ ኪሣራ ነው ብሏል።
ሰሞኑን የብሔራዊ ባንክ ገዢ የሆነው ተክለወልድ አጥናፉ እነ ኢሳያስ ባህረ እንደፈለጉ ሲያዙበት የነበረው ልማት ባንክ “አጠቃላይ የማይመለስና መመለሱ አጠራጣሪ የሆነ ብድር ከአጠቃላይ 38 ቢሊዮን ብር” መስጠቱን ሪፖርተር ዘግቧል። ከዚህ ብድር ውስጥ “25 በመቶ ወይም 8.6 ቢሊዮን ብር እንዲደርስ ያደረገው፣ በጋምቤላ ለተጀመሩ ሰፋፊ እርሻዎች ልማት የተሰጠው ብድር” በማለት ተክለወልድ መናገሩ አብሮ ተዘግቧል።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የዛሬ ዓመት “በጋምቤላ የከሸፈው ኢንቨስትመንት” በሚል ርዕስ ባወጣው የዜና ዘገባ ላይ ይህንን ብሎ ነበር፤
‹‹በጋምቤላ በሰፋፊ እርሻ ስም ከተሰጠው “630 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ወደ ስራ የገባው ከ15.5 በመቶ” ብቻ ነው። ከዚህ በፊት በእርሻ ንግዱ ላይ የተሰማሩ ተብለው የተጠቀሱት “ባለሃብቶች” 780 የነበሩ ቢሆንም አሁን በፋና ላይ ወጣ በተባለው ሪፖርት 623 ብቻ ናቸው ተብሏል። 157ቱ እንደ ኮንዶሚኒየም ጠፉ ባይባልም “በመረጃ ልውውጥ ክፍተት” ያልተገኙ ተብለው በሙያዊ ቃል ተገልጸዋል። እነዚህ 157 “ባለሃብቶች” ብድር ይወሰዱ፤ መሬት ይረከቡ፤ የፋና ዜና አልጠቀሰም።
‹‹ባለፈው “የጋምቤላ እርሻ ባለሐብቶች የሕብረት ሥራ ማኅበር” አቤቱታ አሰሙ በተባለበት ወቅት የማህበሩ ኃላፊ አቶ የማነ አብዛኛው በጋምቤላ በእርሻ የተሰማራው “ባለሃብት ባጋጣሚ የትግራይ ተወላጅ” መሆኑን ማስረዳታቸው ይታወሳል።
‹‹የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ላለፉት ስምንት ዓመታት ሲገዛ የነበረው ኢሳያስ ባህረ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ከ623ቱ “ባለሃብቶች” መካከል 200ው 4.96 ቢሊዮን ብር ከባንኩ ወስደዋል። ከእነዚሁ “623 ባለሃብቶች ውስጥ ለ381 ባለሃብቶች ከ45 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ተደራርቦ” የተሰጠ ሲሆን ባንኩም ለእነዚሁ ድራቢ መሬት ለወሰዱ “ባለሃብቶች” ድራቢ ብድር ሰጥቷል።
‹‹ብድሩ ሲፈቀድ በብድሩ ማመልከቻ ላይ ብድሩ የሚውልበት ዝርዝር ይጠቀሳል፤ ይህም ማለት ብድሩ የተሰጠው “ለመሬት ልማት፣ ለማሽነሪ ግዥ፣ ለካምፕ ግንባታ እና ለስራ ማስኬጃ የተሰጠ ሲሆን፥ ከአጠቃላዩ ብድር ውስጥ” 2 ቢሊየን ብሩ “ለመሬት ልማት ተብሎ ለ194 ባለሃብቶች ተሰጥቷል” በማለት ሪፖርቱ ማስረዳቱን ፋና ዘግቧል።
“ባለሃብቶቹ በዚህ ገንዘብ 314 ሺህ 645 ሄክታር መሬት እንዲያለሙ ቢጠበቅም (እነርሱ) ያለሙት ግን 55 ሺህ ሄክታሩን” ብቻ ነው። እንዲሁም ሰፋፊ እርሻ እናለማለን ብለው መሬትም ብድርም ሲወስዱ ከነበሩት 623 “ባለሃብቶች” መካከል 40 በመቶ ያህሉ (242ቱ) “ከቀረጥ ነጻ ተጠቃሚዎች ናቸው”።››
ከዚህ ሁሉ በኋላ አሁን ወደ 9ቢሊዮን የሚደርስ ብር የማይከፈል ዕዳ ሆኖ ቀርቷል የተባለው። ኢሳያስ ባህረ “ብድር በመስጠቱ ሂደት ለተወሰኑ የባለሃብቶች ቡድን በማድላቱ ነው” በሚል ነበር ከስምንት ዓመት ምዝበራ በኋላ ከሥልጣኑ የተነሳው። አሁን ተክለወልድ ባቀረበው ዘገባ የገንዘቡ መጠን 9ቢሊዮን ብር ነው። የጋምቤላ እርሻ ልማቶች ማኅበር ሊቀመንበር የሆኑት የማነ በተናገሩት መሠረት መሬቱንም ብድሩንም የወሰዱት “ባጋጣሚ የትግራይ ተወላጅ” ናቸው። አእምሮ ላለው የገንዘቡ ስሌትና በእነማን ኪስ ውስጥ ገንዘቡ እንደገባ ነጋሪ አያሻውም።
ከጋምቤላ ጋር በተያያዘ ጎልጉል በተደጋጋሚ ሲዘግባቸው የነበሩትን መነበብ የሚገባቸው ሪፖርቶች ከዚህ በታች ሰፍረዋል፤
በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”
“የመሬት ካርታ ጫት ቤት ተሠርቷል”
ጋምቤላ ልጆቿ በጥይት የተጨፈጨፉበት ምክንያት ይፋ ሆነ!
የካሩቱሪ መሬት ለትግራይ “ባለሃብቶች” ሊሰጥ ነው
ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!
ህወሃት በስጋት ትጥቅ እያስፈታ ዜጎችን ለምን ያስጨርሳል?
የጋምቤላ ክልል በህንድና በሳዑዲ ኩባንያዎች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ
የህንዱ ኩባንያ “ከቆመለት ዓላማ በተቃራኒ ከአካባቢው ደን ጣውላ በማምረት ሲያጓጉዝ በተጨባጭ ተይዟል”
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Ezira says
አዎ! ይህ የትግሬ ማፊያ ቡድን የአኙክ ወገኖቻችንን፣ ከአባት እናቶቻቸው እንዲሁም ከአያት እና ቅደም አያቶቻቸው እርስት እና ጉልታቸው አፈናቅለው መሬቶቻቸውን በመወረር በትግሬ ጉልተኞች እንዲያዝና እንዲሠፍሩበት ማድርጉን ከአገር አቀፍ ሚዲያዎች አንስቶ እስከ ዓለማቀፍ የሚዲያ ተቋማት በሰፊው ሲዘገብና ሲጋለጥ ቆይቷል። ከ 400 በላይ የሆኑ የአኙዋክ ወገኖቻችን ደም እንደጅረት ፈሶ በትግሬ ወራሪዎች መሬታቸውን ሲነጥቁና ወገኖቻችን ከርስቶቻቸው ሲፈናቀሉም ኢትዮጵያዊያን በተከታታይ ሳያቋርጡ ለመላው ዓለም የትግሬው ወያኔ ወራሪዎች የሚያደርጉትን የመሬት ቅርምት (ወረራ) በማጋለጥ እና በማውገዝ በሠላማዊ ሠልፍ ለዓለም ሲያስተጋቡ ቆይተዋል። አሁን ግን ዛሬ የትግሬው ወራሪ እብሪት ተንፈሶ ቀኑ ጨልሞበት፣ የትግሬ የበላይነት ያክትም ፣ Down Down WEYANE በሚል በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ (ከትግሬ በስተቀር) ህዝብ ወራሪው ወያኔ ከሥልጣን እንዲወርድ እየጠየቀ ነው። እብሪተኘው የትግሬ ወያኔም የህዝቡን በቃህኝ፡ አንፈልገህም የሚለዉን ሕዝባዊ እምቢተኝነትን በአጋዚ ጦሩ ሊቀለብስ (አይሳካለትም እንጅ) ሕዝብ እየፈጀ ነው። ግን ለትግሬው ወያኔ ቀኑ አልቆበታል ። ቀኑ ጨልሞበታል፤ ሰማይም ተደፍቶበታል። ህዝቡ በመላ (ከትግረው በስተቀር) የትግሬ ወያኔን ማፊያ ቡድን በመጣባት እገሩ እንዲመለስ እና ከነኮተቱ እንዲነቅል ህዝቡ እጅ ለእጅ ተያይዞ Down Down WEYANE ! yetgree yebelaynet ያክትም በማለት በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ተጋድሎ እያደረገ ነውና ወራሪው የትግሬ ወያኔ ጭንቅ ላይ ነው። ያኙዋክ ወገኖቻችችን ደም እና እንባ ፈሶ አይቀረም እንባቸው ይታበሳል! እርስታቸውም ይመለሳል። ማዲንጎ አፈወርቅ በሙዚቃው እንዳለው፥
አምላክ ስለ ሠራት – ምድርን በክብነት፤
ዞሮ አይመጣ የለም – ወደነበረበት።
ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ይመለሳል። Down ! Down ! Weyanee አራት ነጥብ !
Down Down WEYANE! አራት ነጥብ
aradw says
Our Casa Nostra (Casa Adwa):
Most of you I believe watched movies, read books, and followed news regarding the world mafias such as the old and the traditional Italian Casa Nostra, the Ndrangetha for that matter the Japanese Yakuzu or the Chinese Triads and the new comers the Russian Mob, Mexican Cartel, the list goes on. These are the most powerful collegial bodies with sophisticated organization. The mafias are known for their cruel, violent intimidation, infiltration to extract what they want. You remember once the woyane prime minster claiming that some businesspersons with their own prison. Aha. May be they are Casa Adwa. To control and hold power they use the court, intimidating or bribing judges, witnesses. Their secrecy and sacred code of silence, fraternization, brotherhood and ours are abide by ” የሰማዕታተ አጥንት” which is a mechanism to keep members obliged to keep secret, absolute duty and giving their lives. The casa nostra or casa Adwa extend their power in conglomerate business enterprise and their “EFFORT” effort to infiltrate business, big contracts, and bidding process, collaboration with government officials, politicians and greedy business people to extort big money. Casa Adwa besides are different from the usual Mafioso in their openly holding political power, army, commerce and the whole economy using the traditional mafia style organization, composition, action and strategies. They are not tolerant for journalists. They exterminate them. How many sacrificed their life when they tried to expose their evil deeds. Ours are the leading exterminators for journalists. They exercise power over their members and similarly over the community. They are engaged in terrorism to demonstrate a national power. The Casa Adwa is very notorious for their sophisticated work to start wars among different communities. Our political situation became a fertile ground for their divide and rule and dirty work, they make one group to kill the other. The big family chief known as commissioner or “Sebhat and extended family (the powerful bodies) set up the house straight by violence and intimidation against members and public officials (like Obbo Lemma). They hate confrontation they will have a big tantrum until they get what they want.
They have the lower group ተርፍራፊ ለቃሚ the tolerated who are involved in smaller crimes contraband that we have seen these days, the driver of the Prime Minster and petty army officers that are caught with sugar and coffee.
They are so much greedy and they do not know enough is enough and continues with their criminal and evil deeds. There came time for the demise of the strong Italian Mafioso’s. ሌባ ሲካፈል አንጂ ሲሰርቅ ኣይጣላ the same demise is brewing with the Casa Adwa. May be it is time for their end. Let us all pull the string and choke them out.
Araya says
The Adwa Tigres may well be the bedrock of the Woyane occupation forces. But assigning the blame only on Adwa’s descendants of mercenaries, would trivialize the overwhelming support the the criminal entity enjoys from virtually every Tigre both in and outside Ethiopia. Save a few exceptions, Tigres and their lackeys from other linguistic groups, are avowedly ant-Ethiopian.
For the record, the TPLF occupation forces had declared genocidal war on Amaras at its very inception as early as 1967 ( Ethiopian calendar). The sanctioned murder, eviction and wholesale violation of all sorts of human rights violation, has been raging since.
The massacres of genocidal proportion had since been extended to decimate Anuaks, Afars, Oromos, Somalis and Konsos besides the millions of Amaras exterminated across the whole nation. That is why the Tigrean brand of fascism should be seen for what it is, regardless of the fact that Woyanes’ leadership allegedly emanates from a band of Adwa Tigres that had indeed been sired by despicable Tigre mercenaries in Italian uniform.
History amply reminds us of one brutal reality. It was Tigres in fascist Italian uniform who killed over a million Ethiopians between 1928-1933 (Ethiop Cal). It is Tigres again who are pulling triggers at the broad Ethiopian masses. The only distinction is that our killer Tigres are ironically clad in our national uniform.