አየር ኃይል
የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን አስተማማኝና ዘመናዊ አየር ኃይል የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ አየር ኃይሉ በሁሉም ረገድ በመዘመንና ስኬታማ በመሆን ሀገር የምትኮራበት ታላቅ ተቋም መሆኑንም ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሁን ላይ በውጊያ መሠረተ-ልማት፣ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና አጠቃቀም በአጭር ጊዜ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን በተቋሙ የተለያዩ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስተማማኝ የሀገር መከታ በመሆን ለየትኛውም ግዳጅ አፈጻጸም ብቁና ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን ዘመናዊ ተቋም የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
በአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል የሮተሪ ዲፓርትመንት ዊንግ መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር ሙሉቀን ደርሶ፤ አየር ኃይሉ የኢትዮጵያን ታላቅነት በሚመጥን መልኩ በሁሉም መስክ በዘመናዊ መልኩ እየተገነባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአየር ኃይሉ ለውጊያ፣ መለማመጃና ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ አውሮፕላኖችን አስተማማኝ እድሳትና ጥገና በማድረግ ላይ ስለመሆኑም አንስተዋል።
በአየር ኃይሉ ቀደም ሲል የነበሩ አውሮፕላኖችን ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የማሻሻያ ሥራ በማከናወን የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።
የአየር ኃይል የከባድ ጥገና ማዕከል የምርምር እና ልማት ክፍል ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ወንድማገኝ አርዓያ፤ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በማሻሻያ ሥራዎች ስኬታማ መሆኑን ገልፀዋል።
በከባድ የጥገና ማዕከል አውሮፕላኖችን የማዘመን፣ የዕይታና ዒላማ አቅማቸውን የማጎልበት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህም አየር ኃይሉ ያወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት መቻሉን ገልጸው፤ በቀጣይም ተጨማሪ ገቢዎችን ለማስገኘት እንሰራለን ብለዋል፡፡
በአየር ኃይል የአቪዬሽን ጥገና ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደረጄ አስታጥቄ፤ አየር ኃይል የውጊያ መሠረተ-ልማቶችን በመገንባት ያከናወናቸው ተግባራት ግዳጆችን በአስተማማኝ ብቃት መወጣት የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በአየር ኃይሉ የትራንስፖርት ሄሊኮፕተር ጥገና ስኳድሮን ኃላፊ ሻለቃ አንድነት ብርሃኑ በበኩላቸው፤ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአየር ኃይሉ በርካታ አመርቂ ሥራዎች ስለመከናወናቸው አብራርተዋል።
በአየር ኃይሉ የሄሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሌተናል ኮሎኔል አየለ ዳዊት እና ሻለቃ ፀጋዬ አሰፋ ፤ አየር ኃይሉ አሁን ላይ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምም ይሁን በግዳጅ አፈጻጸም አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በአስቸኳይ ተልዕኮና ግዳጅ በቀንም ይሁን በሌሊት በመብረር ያሰብነውን ማሳካት የሚያስችል ቁመና ላይ እንገኛለንም ነው ያሉት።
እስከ 122 ሚ.ሜ ድረስ ያሉ የሮኬት ተተኳሾችን የሚያመርተው መከላከያ ኢንጂነሪንግ
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ቢሾፍቱ በሚገኘው የሞተር ቬሂክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ተገኝተው በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተከናወኑ የፈጠራ፣ የምርምር ውጤቶችን እና ምርቶችን ተመልክተዋል።
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እንደ አዲስ ከተደራጀ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ነባር እና አዲስ ኢንዱስትሪዎችን በመያዝ የተለያዩ የአርማመንት ቴክኖሎጂ ውጤቶችን የማምረት እና የማዘመን፤ የቀላል እና የመካከለኛ መሣሪያ ተተኳሾችን እንዲሁም እስከ 122 ሚ.ሜ ድረስ ያሉ የሮኬት ተተኳሾችን ያመርታል።
ኮርፖሬሽኑ BRDM-2 ፣ PTR -60ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን፣ T-55 እና T-72 ታንኮችን የመጠገን፣ የማደስ እና ኦቨር ሆል የማድረግ አቅም የገነባ ሲሆን በተጨማሪም የመከላከያ ሠራዊታችንን የማድረግ አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ የምርምር እና የፈጠራ ስራዎችን ያከናውናል።
የትጥቅ ዝግጁነትና ሎጅስቲክስ
የመከላከያ ሰራዊት የሪፎርም ስራ በሁሉም መስክ የላቀ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ የዝግጁነት አቅምና የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።
በዚሁ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ በኢትዮጵያ የትጥቅ ዝግጁነትና ዘመናዊ ጦር የማቋቋም ስራ በሂደት ቀጥሎ ዛሬ ላይ በእጅጉ መዘመኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ከዛሬ 116 ዓመት በፊት ዘመናዊ ሰራዊት ለማቋቋም የተደረገውን ጥረት መነሻ በማድረግ የሰራዊት ቀን መከበር መጀመሩን አንስተው ዘንድሮም በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል።
የኢትዮጵያንና የሰራዊቱን ታሪክ በማጥናት የሰራዊቱ ቀን ታሪኩን በሚመጥን መልኩ በድምቀት የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል።
በመከላከያ ሎጅስቲክስ መምሪያ የተሰሩ ፈጠራና የዝግጁነት ሥራዎችም የሰራዊቱን አቅም የሚያጎለብቱና ለሰራዊቱ ቀን ልዩ ድምቀት የሚሰጡ ናቸው ብለዋል።
ባለፉት አራት ዓመታት የአገር መከላከያ ሰራዊትን አቅም ማጎልበት ያስቻለ ተቋማዊ የለውጥ ስራ ተከናውኖ የላቀ ውጤት መመዝገቡንም አንስተዋል።
የአየር ኃይል፣ ሎጅስቲክስ መምሪያ፣ መከላከያ ኢንዱስትሪና መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሪፎርሙን ተከትሎ እምርታዊ ለውጥ አምጥተዋል ብለዋል።
በመሆኑም አሁን ላይ በአስተማማኝ መልኩ ግዳጅ መፈፀም የሚችል ዘመናዊና የሀገር አለኝታ የሆነ ሰራዊት ተገንብቷል ብለዋል።
የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አብዱራህማን እስማኤል፣ የሰራዊቱን የግዳጅ አፈፃጸም ውጤታማነት የማስቀጠል ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። (ኢዜአ እና የመከላከያ ቴሌግራም ገጽ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Abebe says
Ye Oromo Mekelakeya Bel Ethiopia Dersha Yelatem Ethiopuanema Eyewegwat New Afar Amara Gurage Eelayeta Ethiopiawiyan Nachew Eyetegodum New Yemiwegachewm Oromuma Yetebalew New .Mekelakeya Atibel