“የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ ርዕዩተ ዓለምና የትግል ግብና ዕቅድ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ አቶ ጋሻው ዓለሙ ጥሩ የመወያያ ሃሳብ አቅርበውልናል። ማለፊያና ብዙ የምስማማባቸውን ነጥቦች የያዘ በመሆኑ፤ ላመሰግንና ድጋፌን መስጠት እፈልጋለሁ። መቼም ብዕሬን ያነሣሁ ተስማምቻለሁ ለማለት ብቻ አይደለም። የተስማማሁባቸውን መደረቱም አንባቢን ማድከም ነው። የማቀርበው ለየት ያለ አቀራረብ ሊኖረው ይገባ ነበር ያልኳቸውን ላመላክት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በኔ በኩል ድክመት ሳይሆን ልዩነት ነው ያለው። በርግጥ በተለያዬ መልክና ቦታ ይኼ ጉዳይ በጽሑፉ ውስጥ ተጠቅሷል። ነገር ግን ማዕከላዊ ቦታ መያዝ የሚገባው ጉዳይ ተለጣፊ በመሆን ቀርቧል ባይ ነኝ። እንዲህ ነው። የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎችን አንድ ተግባር እንዲፈፅሙ እንፈልጋለን። ይኼም ተግባር የዘረኛውን አምባገነን የወያኔ … [Read more...] about የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና እቅድ ልዩነት
Opinions
The role of higher education and Ethiopia
My beautiful and brilliant niece graduated from college a few days ago. We are all proud and happy with her accomplishment. It gave the whole family an opportunity to get together. Believe me the festival was preserved on video and camera, posted on Facebook, published on Instagram and micro blogged on tumblr. That is how important it was. No question it was a proud moment for her parents and an early Christmas present to the whole clan. We were lucky and our daughter was strong and focused and … [Read more...] about The role of higher education and Ethiopia
አቶ መለስ ዜናዊ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ ይሁኑን?
በ2012 በኢትዮጵያውያን ትዝታ ውስጥ በጉልህ የሚታወሰው የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ነው። አቶ መለስ በጠና ታመዋል የሚለው ዜና ተንጠባጥቦ መሰማት ከጀመረበት ከጁላይ 15 ጀምሮ በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳር ውስጥ ከፍተኛ መናወጥ ተጀመረ። ነዉጡ አላቆመም። አሁንም ቀጥሏል። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about አቶ መለስ ዜናዊ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ ይሁኑን?
የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት
በዓለም የተበተንነው ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጣም ብዙ ነው። አሁንም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ዓለም ለመውጣት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖቻችን ቁጥር ቀላል አይደለም። በውጭ የምንኖረው፤ በየምንኖርበት ሀገር፤ የሀገሩን ዜግነት በተለያዬ ምክንያት የወሰድንና ያልወሰድን አለን። ይኼ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ግን፤ እኔም ሆንኩ እኔ የማውቃቸው ኢትዮጵያዊያን፤ ሀገራችን በልባችን ቋጥረን ነው የምንጓዘው። እኔ ቁጥሬ፤ በንጉሠ ነገሥቱ ጊዜ ተወልደው አድገው፣ የንጉሠ ነገሥቱን አገዛዝ ኋላ ቀር ነው ብለው ተቃውመው፣ በደርግ ጊዜ ግብግብ ገጥመው፣ አሁንም የወያኔን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ በመቃወም ከሀገር ውጪ ካሉት ወገን ነው። በአስተዳደጋችን ሆነ በእምነታችን፤ ሀገራችን ከማንም ሀገር አሳንሰን ተመልክተን አናውቅም። የገዢዎቻችን ተግባር እንጂ፤ የሀገራችን ጉዳይ ላንዳፍታም እንኳ ጥያቄ ውስጥ … [Read more...] about የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት
የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች
1. መግቢያ የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊን ህልፈተ-ህይወት ተከትሎ በኢህአዴግ እና በተቃዋሚ ኃይሎች የሚታየው የመረበሽና ትርምስምስ በመሰረታዊነት ምንጮቹ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቢሮክራሲያዊ ስልጣኖችን በአጠቃለለ ሁኔታ ጠ/ሚ መለስ በእጃቸው ማስገባታቸውና በእሳቸው ህልፈተ-ህይወት ምክንያት የተከፈተውን የስልጣን ክፈተት የሚሞላ ተቋማዊ አቅም አለመገንባቱና ሁለተኛ ግለሰብ በስርአቱ ውስጥ አለመኖር ናቸው:: ስለዚህም በእርሳቸው ህልፈተ-ህይወት የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት... (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች
የማፍረስ አባዜ
በአለፉት ሃያ አንድ ዓመታት፣ በተለይም ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ልዩ መታወቂያው ያደረገው እያፈረሱ መገንባትን ነው፤ ማፍረስ ቀላል ሥራ ነው፤ ጭንቅላትም፣ ማሰብም አይጠይቅም፤ ልብም፣ ስሜትም አይጠይቅም፤ የሚጠይቀው የዝሆን አካልና ጉልበት ብቻ ነው፤ አንድ ቤተሰብ ስንት ዓመት በዚያ ቤት ውስጥ ኖረ? ጎረቤቶች ምን ዓይነት ትስስር አላቸው? በማኅበር፣ በእድር፣ በዝምድና በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተ መስጊድ፣ በመቃብር፣ በሥራ፣ በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ከልደት ጀምሮ የተፈተለበትና የተደራበት ውስብስብ የኅብረተሰብ አካል መኖሪያ ነው፤ ይህንን አካል ለማፍረስ ትንሽ ጭንቅላትና ግዙፍ ጡንቻ ያለው አይቸግረውም፡፡ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ፣ መቃብሮችን ማፍረስ፣ የንግድ ድርጅቶችን ማፍረስ፣ ትምህርት ቤቶችን ማፍረስ፣ … ማፍረስ… ማፍረስ… ማፍረስ! ሳያለቅሱ … [Read more...] about የማፍረስ አባዜ
አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!
ኅዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በሥራ ጉዳይ ወደ ጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ለሁለት ቀን ተኩል የሚበቃኝን ሸክፌ ከመሥሪያ ቤቴ በተመደበልኝ መኪና ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ለሚነሳው በረራ ለመድረስ ወደቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ በቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ወደ ቦሌ የሚወስደውን መንገድ ይዘን ስንጓዝ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ ላይ የተደረደሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት አቀባበል ወይንም ሽኝት የሚደረግለት ባለሥልጣን/እንግዳ እንዳለ ስለጠቆመኝ መንገዱ ሳይዘጋ ቦሌ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርግ ለሹፌሩ ጠቆምኩት፡፡ ብዙም ሳንጓዝ አትላስ ሆቴል የትራፊክ መብራት ላይ ስንደርስ በስፍራው የነበሩት የትራፊክ ፖሊሶች ወደ ቺቺንያ ወይንም ወደ ቦሌ ሩዋንዳ የሚወስደውን መንገድ እንድንጠቀም አስገደዱን፡፡ ወዲያውኑ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ ለሰባት … [Read more...] about አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!
የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የወያኔን ቡድን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረገው ትግል አሁንም ቀጥሏል። ይህ ትግል አንድነት የለውም። ይህ ትግል አንድ ማዕከል የለውም። ይህ ትግል አንድ መሪ የለውም። ያለንበትን መርምረን ወደፊት እንዴት እንደምንሄድ መወያየት አለብን። ለዚህ ይረዳ ዘንድ፤ በኔ በኩል መደረግ አለባቸው የምላቸውን እጠቁማለሁ። ይቺ ሀገር ያንቺም፣ ያንተም፣ የነሱም፣ የኛም የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ሀገር ናት። ስለሆነም ሁላችንም ለወደፊቷ እኩል ባለጉዳዮች ነን። ማንም የነገዋን ሀገራችን እድል ሲወስን፤ እኛ የበይ ተመልካች መሆን አይገባንም። “ከወያኔ የተሻለ እስከመጣ ድረስ እኔ ምን ቸገረኝ!” ብለን ለሌሎች ጉዳዩን የምንተወው ሊሆንም አይገባም። አዎ የሚሻል ይኖራል። ያባሰም አለ። የሚሻለውም ሆነ የባሰው ሲመጣ የራሱን አጀንዳ ይዞ ስለሆነ የሚመጣው፤ እኛም ሆነ የሀገራችን ጉዳይ … [Read more...] about የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።
“ቤ/ክናችን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች”
የዘመናት ታሪክ ባለቤትና ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ፤ ወደፊትም ለዘለዓለም የምትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ ማደሪያ የምትባለው ዛሬ ኖሮ ነገ ለማይኖረው አምባ ገነንና ዘረኛ አገዛዝ መሣሪያ ሳትሆን ከተበደለውና መብትና ነጻነቱን ከተገፈፈው የኢዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆም የቻለች እንደሁ ብቻ ነው። (ሙሉው ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “ቤ/ክናችን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች”
ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የ2012 ዓመተ ምህረቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ
እንደማንኛውም የአሜሪካ ኅብረተሰብ ሁሉ፤ በኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን፤ ማንኛውንም ምርጫ ከራሳችን ጥቅም አንፃር መመልከቱ ለሕልውናችን አስፈላጊ ጉዳይ ነው። እናም የ2012 ዓመተ ምህረቱን የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ምርጫ የምንመለከተው፤ ከዚህ ተነስተን ነው። እኛ ምን ሠራን? ምን ተጠቀምን? ምን ተጎዳን? ምን አገኘን? ምን ቀረብን? ምን ማድረግ ነበረብን? በመጨረሻ ደግሞ፤ ምን ትምህርት ወሰድን? ይህ ነው ለምርጫው ግምጋሜ ጠቅላላ ይዘቱ፤ ከኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን አንፃር ሲታይ። የባራክ ኦባማ ከጥቁር ዝርያ መሆኑ ወይንም የሚት ራምኒ ነጭ መሆን ቦታ አልነበረውም። የዴሞክራቲክ ፓርቲው ማቸነፍ ወይንም የሬፑብሊኩ ፓርቲ መቸነፍ፤ ለኛ ትርጉሙ በፓርቲነታቸው ሳይሆን፤ የኛን ጉዳይ በሚመለከት ባላቸው አቁዋም ነው። በአሜሪካን ፓርቲ ስሌት ደግሞ፤ የምንፈልገውን ለማግኘት፤ የሚተማመኑበት የአንድ … [Read more...] about ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የ2012 ዓመተ ምህረቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ