“ሊሆን የማይችል ነገር ነው” ባለፈው ማክሰኞ የተከናወነው የአሜሪካ የፕሬዚዳንት ምርጫ ተጠናቅቆ ባራክ ኦባማ ማሸነፋቸው ግልጽ በሆነበት ጊዜ የሚት ሮምኒ የምርጫ ዘመቻ ኃላፊዎች በተወሰኑ ግዛቶች የድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ መፈለጋቸው ተገለጸ፡፡ በተለይ በኦሃዮ፣ ፍሎሪዳና ቨርጂኒያ ግዛቶች የተደረገውን የድምጽ ቆጠራ ለማስደገም አራት አውሮፕላኖች የሪፓብሊካን ፓርቲ ሰዎች ለመላክ በወሰኑበት ጊዜ ሚት ሮምኒ “ሊሆን የማይችል ነገር ነው” በማለት ጉዳዩ እንዲቆም ከልክለዋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መሠረት ኦባማ ሦስቱንም ግዛቶች በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸው ይፋ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል ሮምኒ ምርጫውን ያሸንፋሉ በሚል እሳቤ ተዘጋጅቶ የነበረ የእጩ ፕሬዚዳንት ድረገጽ ለተወሰኑ ጊዜያት ተለቅቆ እንደነበር ሮል ኮል የተሰኘ የፖለቲካ ድረገጽ አስታውቆዋል፡፡ ይኸው … [Read more...] about ድህረ ምርጫ አሜሪካ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግ በ “ልማት ሠራዊት” ግንባታ ችግር ገጠመኝ አለ ኢህአዴግ በልማት ሠራዊት ግንባታ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ። ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በብአዴን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት አሁን የተፈጠረው ስሜት “መነቃቃት ነው” ካሉ በኋላ “መነቃቃት በመፈጠሩ የተሰራው ስራ የዘመቻ ነው” ብለዋል። አቶ ደመቀ “የአመለካከት ችግር አለ” በማለት የልማት ሰራዊት ግንባታው ችግር እንደተጋረጠበት አመልክተዋል። የብአዴንን ግምገማ ከፋፍሎ ካሳየው የአማራ ቴሌቪዥን ለመረዳት እንደተቻለው አቶ በረከት ስምኦንም አቶ ደመቀን አግዘዋል። ከ2003 ጋር ሲነጻጸር በተጠናቀቀው ዓመት የተሰራው ስራ የተሻለ መሆኑን ጠቁመው “የልማት ሰራዊት ግን አልፈጠርንም” ብለዋል። የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና ምክትል ር/መስተዳድር አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው “የተጀመረው ልማት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
”እናቴ አልዳነችም!…….’’
እናት ለልጇ ያላትን ፍቅር መለኪያ፣ ወሰን፣ ድንበርና ግዜ ይኖረው ይሆን?……. በእግዚአብሄር ፈጣሪነትና ፈቃድ፤ ዘጠኝ ወር በመሀጸኔ ተሸክሜ፣በጭንቅና በጣር አምጨ ወለድኩት። አርባ ቀን ሲሞለው እምነታችን በሚያዘው መሰረት ክርስትና አስነሳሁት። በክርሰትና ስሙ ኅይለማርያም ብዩ ስም አወጣሁለት። ጡቶቸን እያጠባሁ፣ የምችለውን ሁሉ እያደረኩና የማይጠገበውን የእናትነትን ፍቅር እየመገብኩ አሳደኩት። ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤትም ላኩት። ልጀም ለቁምነገር በቃ። ከስልጣን ወደ ስልጣን ተሸጋገረ። ከትልቅ ደራጃም ደረሰ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒሰተርም ተባለ። ኅይለማርያም ደሳለኝ፤ የኔ ልጅ። መቼም የእናት ፍቅርና ስቃይ መሳ-ለመሳ ነው። ትልቅ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚያስድስተኝን ያህል፤''ምን ይሆን? ወይስ ምን ይደርስበት ይሆን?....''የሚለው የሌት-ተቀን ሀሳብና ጭንቀቴን እናት ብቻ ነው … [Read more...] about ”እናቴ አልዳነችም!…….’’
ኢትዮጵያዊው ዑሴይን ቦልት የራሱን ሪከርድ አሻሻለ!
ለለውጥ ያህል ለምን አንባቢን ፈገግ ልታደርግ በምትችል የአዲስ አበባ ዘመነኛ ቀልድ አልጀምርም? አንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሲዝናና ያመሻል፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ወደቤቱ ሊሄድ ቄንጠኛ ፕራዶ መኪናውን ሊያስነሳ ቢሞክር ያልታሰበ ብልሽት ያጋጥመውና ሞተሩ ለመነሣት እምቢዬው ይለዋል፡፡ ቢለው፣ ቢለው አልሆነለትም፡፡ ከዚያም ሌላ ምርጫ ሲያጣ ላዳ ታክሲ ያስጠራና ወደቤቱ እንዲያደርሰው ሹፌሩን ይጠይቀዋል፡፡ በቅድሚያ ግን በስንት እንደሚያደርሰው ሒሳቡን ለማወቅ ይፈልግና “ለቡልጋሪያ ማዞሪያ ነው ቤቴን፣ በስንት ነው እንዴ’ምታደርሰኝ?” ይለዋል፡፡ ይህ ባለታክሲም ብዙም ሳያቅማማ “150 ብር ይከፍላሉ፤ ይግቡ” ይልና ጋቢናውን ይከፍትለታል፡፡ ይሄኔ ባለሥልጣኑ ተገርሞ “ቧይ! ለቡልጋሪያ ማዞሪያ ለዚህን ያህል ቡዙ ገንዘብ ማለተይ ለሞቶ ሃምሳ ብር … [Read more...] about ኢትዮጵያዊው ዑሴይን ቦልት የራሱን ሪከርድ አሻሻለ!
ሞተ ያለው ማነው?
ፕ/ር አስራት አስራት ወልደየስን ሞተ ያለው ማነው? በረከቱን ያጣ የሞተ መለስ ነው፣ ፕ/ር አስራት አልሞተም ውሸት ነው፣ ኢትዮጵያን ሲቆርሷት ቁጭብየ እንደ ግርማ አላይም ነው ያለው፣ ታሞነው የሞተው? ማነው የገደለው? ያለ ይመስለኛል ስሙን ቀይረውት አለማየሁ ብለው፡፡ ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል … [Read more...] about ሞተ ያለው ማነው?
“ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?
የአሜሪካ ምርጫ ሲጠናቀቅ ተሸናፊው ሚት ሮምኒ ደጋፊዎቻቸው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፡- “… ሁለታችንም ለምንወዳት አገራችን የምንመኘውን ለማድረግ በተለያየ አቅጣጫ ሞከርን፤ … ሕዝባችን ደግሞ የሚፈልገውን መሪ መረጠ፤ … ስለዚህ ፕሬዚዳንቱን ደውዬ አነጋሬያቸዋለሁ፤ ባገኙትም ድል እንኳን ደስ አለዎ ብያቸዋለሁ፤ … በተለይ ለእርሳቸው፣ ለቀዳማዊ እመቤት እና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካሙን እመኛለሁ፤ … አገራችን ከባድ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል፤ … ባለቤቴና እኔ ለፕሬዚዳንቱና ቤተሰባቸው ከልብ እንጸልያለን፤ በሥራቸው ስኬት እንዲያገኙና ታላቋን አገራችንን በመምራት የሚያከናውኑት ሁሉ የተሳካ እንዲሁን እመኛለሁ፡፡” ይህንን ካሉ በኋላ ወደተለመደው ህይወታቸው ሄዱ - የፖለቲካ ገዳም ገቡ፡፡ ይህ ንግግር ወደራሳችን እንድንመለከት የሚያደርግ ነው፡፡ የእኛስ ፖለቲከኞች … [Read more...] about “ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?
ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ
“የሙስና መርከብ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አሉ። ከተቋቋመ ጀምሮ አንድም ቀን ስለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተገልጾ አያውቅም። ከአገሪቱ ባንኮች ትልቁ ተበዳሪ ነው።የወጋጋን ባንክ ትልቁ ባለድርሻ ነው። በአንዳንድ ከፍተኛ የንግድ ተቋማት ውስጥ የንግድ ሽርክና እንዳለው ይታማል። የወርቅ ማዕድን ፍለጋው ሰምሮለታል። የግል አስመጪዎችን በመፈታተን አነካክቶ ጥሏቸዋል። አገሪቱ ላይ የገነባው የንግድ ኢምፓየር በበርካቶች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ የተቋቋሙትን የንግድ ተቋማት በመደፍጠጥ በፖለቲካው የበላይነቱ ሳቢያ ልዩ ተጠቃሚ በመሆኑ አይወደድም። ይህ ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ነው። የትግራይ ህዝብ “ያንተ ነው” ስለሚባለው ታላቅ የንግድ ኢምፓየር የሚያውቀው ነገር እምብዛም የለም። አስራ ሶስት ሰፋፊና ስትራቴጂክ ኩባንያዎችን ያቀፈው ኤፈርት በቅርቡ የእህት … [Read more...] about ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ
ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!
ታዋቂው የጋና ምሁር ጆርጅ አዪቴ በተደጋጋሚ እንደሚሉት ከአምባገነናዊ ስርዓት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሽግግር የትኛውንም ዓይነት ተሃድሶ ከማድረግ በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የእውቀት ተሃድሶ ነው፡፡ ሕዝብ እንደሚገባው በእውቀት ከነቃ የዴሞክራሲና የመብቱን ጉዳይ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ይህንን ተከትሎ የሚከሰተው የእውቀት ተሃድሶ ወደ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊ፣ ሕገመንግሥታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ … ተሃድሶ ይመራል፡፡ የእውቀት ተሃድሶ ሳይደረግ ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር አንዱን አምባገነን በሌላ የመተካት ሂደት እንጂ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣ አይደለም ይላሉ፡፡ ሕዝብ የእውቀት ተሃድሶ ካካሄደ በሥልጣን ላይ ከተቀመጠው አምባገነን ያልተሻሉትን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ማንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይችላል፡፡ በፖለቲካ ብልጣብልጥነት ሊያካሂዱበት የሚችሉትን አሻጥር አስቀድሞ ያውቃል፤ … [Read more...] about ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!
ማን ጸሎት ያሳርግ
ወ/ሮ ለምለም ጸጋው በእስልምና ሃይማኖትም ሆነ መብታቸውን ለማስጠበቅ በመናገራቸው በእስር ቤት ለሚማቅቁ ሁሉ በፎቶ አስደግፈው የጻፉትን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about ማን ጸሎት ያሳርግ
“በአገራችን ባይተዋር ከመሆን በላይ ውርደት የለም”
ይህንን ዘገባ ሳሰናዳ በ1997 ምርጫ ወቅት አዲሱ ገበያ አካባቢ አልሞ ተኳሾች የገደሉባቸውን ልጃቸውን ስም እየጠሩ “ምን አደረካቸው? ምን አጠፋህ? አንተኮ ትንሽ ነህ? ማንን ልጠይቅ? ማንን ላናግር? ልጄ … የኔ ባለተስፋ፣ እኔ ልደፋ፣ እኔ መንገድ ላይ ልዘረር፣ ምነው ለኔ ባደረገው? የማን ያለህ ይባላል…” የሚሉ ልብን ዘልቆ የሚገባ ሃረግ እየደጋገሙ እብደት የተቀላቀለው ለቅሶ አልቅሰው ያስለቀሱን እናት ታወሱኝ፤ ብዙዎች በተመሳሳይ አንብተዋል።ደረታቸውን ደቅተዋል። አሁን ድረስ የልጅ፣ የአባት፣ የወንድም፣ የእህት፣ የዘመድና ወዳጅ ብሎም የአገር ልጅ ሃዘን የሚያቃጥላቸውን ቤታቸው ይቁጠራቸው። “ኢትዮጵያ ለእኛ አስፈላጊ አገር ናት። ኢትዮጵያዊ በመሆናችን ለአገራችን ትልቅ ቦታ መስጠት አለብን። ምክንያቱም አስፈላጊ ናትና። እዚያ እስከተወለድን ድረስ /መሰረታችን ኢትዮጵያ እስከሆነች … [Read more...] about “በአገራችን ባይተዋር ከመሆን በላይ ውርደት የለም”