“ጀሃዳዊ ሐረካት” ዘጋቢ ፊልም “በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ከሃሳብ ያለፈ እቅድ አላቸው” የተባሉት ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ገመና አንጠርጥሮ ሊያሳየን መሆኑን ሞቀ ደመቅ ደመቅመቅ ያለው የኢቲቪ ማስታወቂያ ልባችን አንጠልጥሎት ከርሟል ። ሳምንት በደመጽና በምስል በለፈፉትና በናኙት ማስታወቂያ የሙሰሊማን የመፍትሄ አፈላላጊ ኰሚቴ አባላት “አሸባሪ” አካሄድ በተጨባጭ መረጃ እንደሚያሳዩን የነገሩን የመንግሰት መገናኛ ብዙሃንን የተለመደ ስራ የማውቀው ሳይቀር ነፈሴ በአንገቴ እሰክትወጣ ጉጉት አሳድሮብኛል። ይህ መሰሉ ስሜት ለጊዜው ምንጩ ከየት እንደሆነ ባውቀውም ስሜቴን ተቆጣጥሬ በሰአቱ ደረስኩ፡፡ ተመሳሳይ ስሜት አድሮባቸው እንደሁ በሚል እዚህ ሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውንን እየደወልኩ ስሜታቸውን መጠየቅ ያዝኩ! (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)::
ጸሐፊውን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል: nsirak@gmail.com
Damtew Demeke says
it is stupid of the so cold Ethiopian bully weyanes
ብስራት says
በዚህ ጀሀዳዊ ሐረካት ላይ የታየው ከላይ ባለው ምስል ላይ ፊት ለፈት የቀረበው ሰው የኔ ቤተሰብ ነው ( እስማኤል አሰፋ ወይም በቤት ስሙ ወንድም አለም) ፍቅሩን እንጂ ክፋቱን በህይወቴ አላየሁም ፡፡ ምንም እንኳን እሱ ሙስሊም ቢሆንም እና ቤተሰባችን ክርስትያን ቢሆንም ማንም ግን ማንንም ገፍቶ አይደለም ክፉ እንኳን ተነጋግሮ አያውቅም፡፡ የክርስቲያን በዓል ሲሆን አብረን ያለንን ተካፍለን በልተን ተጫውተን ነው የምናሳልፈው፡፡ አሁንም ቢሆን ያቀረቡት ነገር እጅግ ውሸት እና እጅግ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለማወቅ የማንንም ማረጋገጫ አልፈልግም፡፡ ወንድም አለም አሁንም እጅግ የምንወድህ ቤተሰቦችህ ነን፡፡ ከኛ ስለተለየህ አዝነናል እጅግም ተደናግጠናል፡፡ አይዞህ ወንድማችን አባታችን፡፡ ይሄ ውሸት እና የሌለብህን ነገር የለጠፉብህ ክፉዎች እስኪነቀሉ በትእግስት ጠብቅ አብረንህ ነን፡፡ እጅግ እንወድሀለን!!
ሕሊና ብርሃኑ says
“ጂሃዳዊ ሃረካት” የተባለውን የመንግሥት የፕሮፓጋንዳ ፊልም፣ እኔም ረጋ ብዬ ተመልክቼዋለሁ። ሃገርና ዜጋን ሁሉ፣ ባጠቃላይ ኢትየጵያን በሙሉ የሚያዋርድ ሰነድ ነው።
በጨለማው ቤት የሚወርድባቸው ስቃዩና መዓቱ አነሰ ብሎ፣ ምርመራውን ራሱን ባደባባይ ያወጣ መንግሥት በዓለም ላይ ያለም አይመስለኝም። ያደባባይ ፍርድ ቤት ክንውን ይሆን እንደሆን እንጂ! ይህ ሁለት ሶስት ጊዜ አንድን ሰው የመግደል የናላ በሽተኞች /psychopaths / ሱስ ነው።
እንደዚህ ዓይነቶቹን፣ ሥልጣን ያሰከራቸውን ፍጡሮች ፣ ናላ የሌላቸው፣ የርህራሄ ስሜት ድንቁርና በሽተኞች /psychopaths/ናቸው ይላሉ፣ የስነ ልቦና ምርምሮች፣።
Exploring the minds of psychopaths and dictators:-
http://www.psychologytoday.com/blog/engineering-the-brain/201106/the-mind-dictator
ስለሆነም ፣ የሃገር ወዳዶች፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው፣ ከሁሉም በፊት መሰረት የሚያደርገው ሰብዓዊነት እስከሆነ ድረስ፣ እውነትን ለማወቅ ሰብዓዊነትን መሰረት ያላደረገ „መረጃ“ ወዲያም ወዲህ ሳይገለባባጥ፣ ህሊናቸው ሊቀበል አይገባም።
/”The End justifies the Means” /”ከየትም አምጪው ዱቄቱን ፍጪው” ፣ የሚባለው ነገር፣ ምን ጊዜም ቢሆን ሰብዓዊ ዘይቤ ሊሆን ስለማይችል፣ የአምባገነኖችን ፖሊስና የፍርድ ቤቶቹን ተረት ወደ ጎን መተው ብቻ ሳይሆን፣ ለህሊና ፍርድ የሚቀርብን ፋይልንም እንኳን ወድያውኑ ዘግተን ለስቃይ ከተዳረገው ሰው ጋር መቆም አለብን፣ ነው የምለው።
-የጠላቴ ጠላት ወዳጄ- የሚባለው ተንኮል ለሰብዓዊነት ስለማይሰራ፣ ወይንም በሌላ አማርኛ፣ “ቀንድ ካወጣ ሰይጣን ጋር ተባብሮ ጠላቱን የሚታገል“ ራሱ ሰይጣን እንጂ ፣ ምንጊዜም ቢሆን መላክ ሊሆን ስለማይችል፣ በስቃይ ላይ የተገኘን „መረጃ“፣ እንደዚህ ሊሆን ይችላል፣ ላይሆን ይችላል፣ እያልን፣ ፍሬ ከርስኪ ውስጥ ባንገባ መልካም ይመስለኛል።
ይልቅ፣ ስለ እዚህ ዓይነቱ ስቃይ ባለሙያዎች የሚሉትን እያገላበጥን፣ የሚፈጸመውን ወንጀል በህሊናችን እያሰብን፣ የሰብዓዊነት የረቀቀ የመንፈስ አንድነታችንን ብንገልጽላቸው እኛንም የበለጠ ሰብዓዊነት ተሰምቶን ወደፊት እንራምዳለን! እንዳው ለምሳሌ ያህል ምን ምን ዓይነት ገጽታና መዘዝ ይህ ስቅይ እንዳለው ይህን ሰነድ ብንመለከተው አንዳንድ ነገር መረዳት እንችላለን ፥http://samvak.tripod.com/torturepsychology.html
ይህችን ዓለማችንን ዛሬ ከግጭት ወደ ግጭት እያሰጠማት ያመጣው ጣጣ አንዱም፣ የ -”ከየትም አምጪው ዱቄቱን ፍጪው” – ዓይነት አመለካከት ነው። በኔ አስተያየት፣ የሞተው ቢን ላደን ራሱ፣ ከመቃብሩ ወጥቶ፣ በኢህአዴግ ናላቢስ ገራፊዎች/psychopaths/ ተገዶ መንግስት ልገለብጥ መጣሁ፣ ቢል እንኳን፣ የርሱ አክራሪነት ክርክር ውስጥ ሳይሆን የምገባው፣ እንደ ክርስቲያንም ሆነ እንደሰላማዊ ሙዝሊም ወይንም እንደማንኛውም ሰብዓዊ ሰላማዊ ሰው፣ የናላቢሱ መንግስት ኢሰብዓዊነት ጉዳይ ውስጥ ነው ።
ሌላው መቼም፤ ዛሬ ዓለም የገባችበት የሃይማኖት አክራሪነት፣ የሙዝሊምም ሆነ የክርስቲያን ወይንም ሌላ፣ እንደ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ፣ ሁለቱም ሃይማኖቶች በስፋት በቆዩበት ሃገር፣ ተከታይ ለማግኘት የማይገለብጡት ድንጋይ እንደማይኖር፣ እንኳን ለፖለቲካ ተዋናይ ቀርቶ፣ ለማንም ግልጽ ነው። እናም ይህ ስለሆነ መንግሥትን በቁጥጥር ያስገባቸውን ዜጎቹን የማሰቃየት ነጻ ሰርተፊኬት ይሰጠዋል ማለት ነው !!!???? ለነገሩማ ለዚህ ነበር አያሌ የሰብዓዊ ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች በየጊዜው የተደነገጉት። ያው የስምምነቶቹ „ቄሱም ፓፓሱም ሼኩም“ ይረጋግጧቸዋል እንጂ! ጉዋንታናሞንንም አይተናል! የማን ሆነሽ ትባረኪያለሽ ነው!
ለነገሩማ፣ እናንሳው ካልን ደግሞ፣ እነዚህን፣ በሁሉም በኩል ያሉትን አክራሪዎች በቀዳማዊነት በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ የሚመግቡት፣ እነማን ናቸው? ራሳቸው የሜሪካንና የሳውዲ ባለጸጎች መሆናቸው ያደባባይ ምስጢር ነው። ያልካዒዳ መዋቅር ውስጥ የሚረጨው ሃብትም፣ ከየት እንደሚመጣ ዊኪ ሊኪስ አንድ ሰሞን አዳባባይ አውጥቶታል፤ የሳውዲ ባለጸጎች! የኢትዮጵያን ገበሬና ደሃ ዜጋ በያለበት የሚያፈናቅሉት። ለማያውቋቸው ይታጠኑ እያልን፤ የኢትዮጵያውንም እግዜር ይወቀው፣ በደፈናው ማለት ይሻላል! የሳውዲ ባለጸጎች እራሱ ኢህአዲግ ጉያ ውስጥም አሉና።
ስለሆነም ፥ ይልቅ የኢህዴግን ተረት ትተን፣ ዛሬ በጀግንነትና በዘርም ሆነ በጥቃቅን የሆድ ጥቅም፣ ሳይከፋፈሉ በአንድነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመብታቸው፣ ለመብታችን በመቆም የሚታገሉት የሙዝሊም ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን፣ አርአያነት በማስተዋል፣
“ድምጻችን ይሰማ !” መሪዎቻችን ይፈቱ፣
የሚሉትን ያህል፣ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ!
እውነት! እውነቱም ይሰማ ! እውነቱ ሃገራችንን ዛሬ የሚያስተዳድሩት የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች ናቸው!
አንድ ህዝብ ነን ! አንድ ህዝብ ነን ! ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ !!!
ብለን እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ሃገር ወዳድ የሆን ሁሉ ድምጻችንን ከፍ አድርገን ለሰብዓዊነት ና ለነፃ ኢትዮጵያ እንጩህ ! ከተኛንበት በአእምሮም በተግባርም ከዳር እስከዳር እንነሳ !!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
nwba says
Nonsense….. how can Muslims build an Islamic state where more than half of the people and all it needs for a power is belong to other religious group. Have you heard of a Muslim country even having 3/4th of the whole population and having Islamic or the other way and having christian state? NOT POSSIBLE. This is politics!!