ባለፉት 21 ዓመታት በልዩነት ላይ የተመሰረተው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተነዛው የዘረኝነት መርዝ ቀላል አይደለም። መላ ኢትዮጵያን ቀስ በቀስ እየወረረው መጥቶ ማሰብ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅበትን፣ ጥቂት ያልሆነ “ምሁር” የሚባለውን ሁሉ ሳይቀር በነጻ ጭንቅላት እንዳያስብ እያደረገው ነው። ሰለሆነም ነው፣ ማሰብ የሚገባው እንደዚህ ካሰባ፣ የፖለቲካና የስለላ ማዕከሎች ጥናቶች፣ አልፈው ተርፈው ረዥም ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከእንግዲህ በሃያ ዓመታት ውስጥ ከሚወድቁት መንግስታት ተርታ ውስጥ ያስገቧት። ይህ መቼም፣ ሆነም አልሆነም፣ እራሱ መገመቱ እንኳን፣ እያንዳንዱን የዛሬውን የኢትየጵያ ሃገር ወዳድ ሊያሳስበው ብቻ ሳይሆን፣ ራሱን አስይዞ የሃሳብ ያለህ አሰኝቶ ሊያስጮኽው ይገባል። ደግሞም የመንግሥትንና የአባሪዋቹን ታሪካዊ አካሄድና ዛሬ የሚወስዱትን ኢትዮጵያን የማፈራረስ እርምጃዎች ላስተዋለ አይሆንም ብሎ መከራከር አይቻልም። ስለሆነም የችግሩን ስረ መሰረታዊ መንስኤ መረዳት ብቻ ሳይሆን፤ ሀገር ወዳድ ነኝ የሚል ሁሉ ከዳር እስከዳር አንድ ሆኖ መነሳትም አለበት።
የወንዝ ውሃ እያሳሳቀ ነው የሚወስደው !
ይህ እንዳይሆን፣ በዘረኝነት የተበከለውን የሰው ደካማን አስተሳሰብ፣ በመሰረታዊ ትክክለኛ ሃሳብ ለማደስም ጭምር፣ በዚህ በኩል በተጨባጭ ልምዶች የተደገፉ ለምሳሌነት የሚያግዙ እርማጃውችን ደግሞ ደጋግሞ ማስተጋባት ያስፈልጋል፣ ይጠቅማል። – ኢትዮጵያ ለዘላለም እንድትኖርና ህዝባችን በፍትህ፣ በሰላምና በአንድነት እንዲበለጽግ ለምናደርገው ትግል !
በዚህ አኳያ፣ እኔ የማደንቀው፣ የወንድሜ የኦባንግ ሜቶ ልምድና ሃሳቦች እንደምሳሌዎች የሚቀርቡ ናቸው እላለሁ። ስለሆነም ነው፣ እዚህ እንደገና (ሰንበት ያለም ቢሆን) ላንባቢ ለማሳሰብ የምወደው። (አባሪውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
ኢትዮጵያ ሃገራችንን፣ በሃያ ዓመታት ውስጥ ይደርሳል ከተባለው አደጋ ለማዳንና ፣ መልሶ ለማቋቋም ዘሬውኑ መነሳት አለብን!
ሕሊና ብርሃኑ
Save-Ethiopia says
በቅዱስ መፅሀፍ ውስጥ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም እንዳለው ፈጣሪ ማንኛውም ነገር ዘላለማዊ አይደለምና በእርግጥ እንኳንስ ሀገራትና መንግስታት እራሷ ምድራችንም ከተወሰነላት ጊዜ ገደብ በኋላ አላፊ ነች፡፡ነገር ግን ይህንን የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ትንበያና ትንተና የሚሰጡት ምእራባውያን በተለይም አሜሪካና እንግሊዝ ይህንን አይንት ትንበያና ትንተና የሚሰጡት አስቀድሞ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ስሟን ዥግራ ይሏታል አይነት ምእራባውያን በታዳጊው አለም ላይ የሚሰሩትን የዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ለማስፈፀም እንዲረዳቸው አስቀድመው የዘየዱት መሰሪ ስልት ነው፡፡ስለዚህም ይህ አይነት የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ትንበያና ትንተና ለአንድ ሰው አደገኛ መርዝ ግቶ እከሌ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሞታል ብሎ የመተንበይ ያክል ነው፡፡ይህንን ትንበያና ትንተና የሚሰጡት ምእረባውያን አስቀድመው ይህ እንደሚሆን ከተረዱና እራሳቸውንም ለተቀረው ታዳጊው አለም የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጠበቃና አርአያ እንደሆኑ አድርገው የሚያስቀምጡ ስለሆነ ለምን ይህ እንዳይሆን አስቀድመው በቀናነት ተገቢውን መልካም ስራ አይሰሩም?ምእራባውያን የእነሱን የውሸት ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ለታዳጊው አለም ለመጋት ብለው እንደ ሊቢያ አይነት የተረጋጉና በልማት የበለፀጉ ሀገራትን ጭምር የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጠበቃና አርአያ እንደሆኑ አድርገው በማራገብ በቀጥታ የኔቶ ወረራ ለምን ፍርስርሳቸው እንዲወጣ አደረጉ?በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ትግበራ ለታዳጊው አለም የሚሰበከው ዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ከበስተጀርባ ያለው ቅኔው የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ወይንም ኢምፔሪያሊስታዊ ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ነው፡፡በተባበሩት መንግስታት የኮፊ አናን ዋና ፀሃፊነት ወቅት የረቀቀው የR2P (Responsibility To Protect) ዋና ቅኔውም የምእራቡን አለም አፍሪካንና መላውን ታዳጊውን አለም ነፍስ እንዳላወቀ ህፃን ልጅ በሞግዚት አስተዳደር የማስተዳደርና የመጠበቅ ሃላፊነትን በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ የሚያጎናፅፍ ዘመናዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ወይንም Neo-Colonialism ነው፡፡እንደሚታወቀው አሜሪካንን የአለም ብቸኛ የበላይ ልእለ ሃያል ሀገር የሚያደርገው PNAC(Plan for New American Century) ወይንም አዲሱ የአለም ስርዓት New-World Order ከዚህ በፊትና አሁንም ያሉትን ሉአላዊ ሀገራትን Sovereign Nation State ቀስ በቀስ የሚያዳክምና የሚያፈራርስ የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት አሰራር ነው፡፡
በዚህ እቅድ አሰራርና አካሄድ የተነሳ ደግሞ በሂደት ቀስ በቀስ የማይፈራርስ ሉአላዊ ሀገር አይኖርም ማለት ነው፡፡በምእራቡ አለምና በእኛም ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ጥራዝ-ነጠቅ ምሁራን የሚኮነነው ዘመነ ኮሚኒዝምና ቀዝቃዛው ጠርነት አሁን ካለው የማስመሰልና የውሸት ዘመነ ዲሞክራሲ(Fantasy of The Day) ነገር ግን በተቃራኒው በተግባር ካለው የዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት(Order Of The Day) በአንፃራዊነት የተሻለ የአለም ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ነበር፡፡ጋዳፊ በምእራባውያን የጦር ወረራ በአሳዛኝና አሳፋሪ ሁኔታ የተወገደው AFRICOM የተባለውን የአሜሪካንን አፍሪካዊ የወታደራዊ ግብረ ሃይል ስለተቃወመ ነበር እንጂ ምእረባውያን የውሸት ዲሞክራሲ ባያገኝም ቅሉ ግን የተረጋጋ ሰላማዊ ህይወት የሚኖረውን የሊቢያ ህዝብ የተሻለ ዲሞክራሲ መልካም አስተደዳርና ልማት ሊሰጡት አስበው አልነበረም፡፡አሁን በማሊ አሸባሪነትን ሽፋን አድርጎ እየተፈጠረ ያለውም የቅኝ ግዛት ወረራ የሊቢያን ቀውስ ተከትሎ ጭምር የተፈጠረ ነው፡፡አሁን ባለው የአለማችን ሁኔታ የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State(Not Failed Governments or Regimes) እንዲፈጠሩ የሚሆነውም አሸባሪነት የተባለውን በቦታና በጊዜ ወሰን የሌለውን(Open Ended and Omnipresent) መናፍስት(Ghost) እንደ ሽፋን በመጠቀም መላውን ታዳጊውን አለም አጠቃላይ አለመረጋጋትና ቀውስ ውስጥ በመክተት እንደሆነ ብዙዎቻችን አልተረዳንም፡፡እረ ለመሆኑ አንድ ወሳኝና ምክንያታዊ ሎጂካል ጥያቄ እናንሳ::እንዴት ነው በአንድ በስልጣኔ ብዙም ያልገፋ ነው ከሚባለው የአረቡ አለም ከወጣው ኦሳማ ቢላደን ከተባለ አንድ እስላም ግለሰብ አማካኝነት የሚመራው አልቃይዳ የተባለ አሸባሪ ቡድን ለዘመናት የሰለጠነና ሃያል የሚባለውን አሜሪካንንና የምእራቡን አለም ይህንን ያህል በትሪሊዮን ዶላር የሚያስወጣ አለም አቀፍ ጦርነትና ፈተና ሊከት የቻለው?ይህ ሁል ጊዜ አእምሮዬን የሚኮረኩረኝ ቅኔ ነው፡፡በሀገራችን ያለው አገዛዝም አስቀድሞ ሊያጠቃ የሚፈልገውን ተቃዋሚ ግለሰብና ቡድን ሁሉ አሸባሪ እያለ ነው የሚፈርጀው፡፡
ከታሪክ እንደምንረዳው በአለም ላይ ያሉ ብዙ መሰሪ አገዛዞችና ልሂቃን ስልጣናቸውን (Power) በዚህም አማካኝነት ህልውናቸውን ጥቅማቸውን ፍላጎታቸውን በዘላቂነትና በአስተማማኝ ለማስጠበቅና ለማስቀጠል ሲሉ አንድን ሀገርና ህዝብ በራስ የመተማመን መንፈሱ ተኮላሽቶ ሁልጊዜ እንደ ህፃን ልጅ በፈርሃት እየራደና እየተረበሸ የእነሱን ተገቢና ጤናማ ያልሆነ ጥበቃ በመሻት ዘላለም የእነሱ ጥገኛ እያደረጉት እንደፈለጋቸው በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የግድ አንድ የሆነ ጠላት (External Enemy) እንደሚፈጥሩ የታወቀ ነው፡፡እነዚህ አገዛዞችና ልሂቃን ይህንን አይነት መሰሪ ስራና ስልት ተግባራዊ የሚያደርጉበት ዋና ስልት ደግሞ State-Terrorism በመጠቀም ነው፡፡እንደዚሁም እነዚህ መሰሪ አገዛዞችና ልሂቃን ሌላውን ለፍላጎታቸው የማይመቻቸውን ደካማ ሀገር ለማጥቃትና ለመውረር የግድ ይህንን ተመሳሳይ ሁኔታ በመጠቀም የሚገዙትን የሀገራቸውን ህዝብ አሳምነው ወደ ጦርነት ውስጥ ለመግባት የግድ አንድ የሆነ ሰበብ (Casus-belli) በተጠቂው ሀገርና መንግስት ላይ መሸረብ አለባቸው፡፡እነዚህ መሰሪ አገዛዞችና ልሂቃን ይህንን አይነት መሰሪ ስራና ስልት ተግባራዊ የሚያደርጉበት ቅድመ ሁኔታና ስልት ደግሞ አስቀድመው Mainstream ሚዲያውን በመጠቀም ሊያጠቁት የሚፈልጉትን ሀገርና አገዛዝ ሃጢያት የተጋነነና የተዛባ እውነታ በመፍጠር ሰለባ የሚሆነውን ሀገርና አገዛዝ የተወገዘና የተረገመ (Demonize) እንዲሆን በማድረግ ነው፡፡The first casualty of war is truth የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ጋዳፊ የምእራባውያን ሰለባ ከመሆኑ በፊት አስቀድሞ 42 አመት ያስተዳደረውን የገዛ እራሱን ህዝብ እንደ ጭራቅ የሚበላ ፍጡር ተደርጎ ነበር በMainstream ሚዲያው የተሳለው፡፡ከዚያ ግን ምን ተፈጠረ?አዎ ምእራባውያን በኔቶ አማካኝነት የሊቢያን በተለይም የጋዳፊን የትወልድ አካባቢ ነው የሚባለውን መሰረተ ልማት በቦምብ እንዳልነበረ አድርገው አፈራረሱት እንደዚሁም ጣልቃ-ገብነታችን ለሰብዓዊነት(Humanitarian Mission) ነው እንዳልተባለ ጋዳፊንም ለርፍድ እንኳን ሳይቀርብና አጠፋ የተባለው ጥፋትና ወንጀል ለአለም ህዝብ ይፋ ሳይሆንና ሳይረጋጋጥ አሳዛኝና አሳፋሪ በሆነ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ገደሉት እንደዚሁም ይህንን ወረራ ተከትሎ ብዙ ወዘተ ወዘተ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ነገሩን መዘርዘር ስለሚከብድ ነገር ግን ቢያንስ አንድ ወሳኝ ነገር ላንሳ፡፡ለመሆኑ ጋዳፊ በውጪ በምእራቡ አለም ባንኮች አስቀመጠው የተባለውና በጦርነቱ ወቅት እንዳይንቀሳቀስ የተደረገ የነበረው በመቶ ቢሊዮነች ዶላር የሊቢያ ህዝብ ገንዘብ እጣ ፈንታው ምን ሆነ?ነው ወይነስ ይህ ገንዘብ ምእራባውያን ለሊቢያ ወራራ ላወጡት ገንዝብ ካሳ የሚከፈልና የሊቢያንም መሰረተ ልማት በቦምብ ስላፈራረሱት መልሰው ለመገንባት የእነሱ ሀገራት አለም አቀፍ ኩባንያዎች ለሚወስዱት ውድ የፕሮጀክት ኮንትራት እንደ ማካካሻ የሚከፈል የጦር ካሳ ማለት ነው?አዎ በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት አሰራር ስንሄድ ደካማ ተዳጊ ሀገራትን በጠርነት መውርርና የተፈጥሮ ሀብታቸውንና ኢኮኖሚያቸውን መቆጣጠር ነፃ-ገበያ ተብሎ ይጠራል፡፡ብዙ የአለም ጦርነቶችን ታሪክ ስናጠና አንዱ ዋናው የስር መሰረቱ መነሻ መንስኤ እራሱ ግሎባል ካፒታሊዝም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡አንዳንድ የፖለቲካ ጠበብት እንደሚናገሩት ከሆነም በማሊ ያለው የእርስ በርስ ግጭትና ይህንንም አሸባሪነት የተባለ መናፍስት ሰብብ አድርጎ እየተፈፀመ ያለው የውጪ ወረራ ዋናው መንስኤ በራሱ በምእራቡ አለም ካለው የግሎባል ካፒታሊዝም የፋይናንስ ቀውስ ጋር በተያያዘ በማሊ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በተለይም ወርቅ ፍለጋ ነው፡፡እንግዲህ ይህች ናት የግሎባል ካፒታሊዝም ዲሞክራሲና ነፃ-ገበያ ሰምና ወርቅ ቅኔ፡፡የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ትንበያና ትንተናም ከዚህ የታዳጊውን አለም የተፈጥሮ ሀብትና ኢኮኖሚ ያለማንም ሃይ ባይ እንደፈለጉ ለመቀራመትና ለመዝረፍ ከታለመ የረቀቀና የተቀነባበረ መሰሪ ስልት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ምክንያቱም የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation State) ስላልሆኑ የገዛ ህዝባቸውንና ሀብታቸውን ከውጪ ሃይል ለመከላከልና ለመቆጣጠር አይችሉም ማለት ነው፡፡ስለዚህም ለምሳሌ አፍሪካውያን ቀስ በቀስ AFRICOM በሚባለው የአሜሪካ ወታደራዊ የውጪ ባእድ የሞግዚት አስተዳደርና ጥበቃ ስር ሆነው ነገር ግን ከውስጥ ባሉ እንደ ጠንካራ መንግስት በማይታዩ ሀገር በቀልና ሃላፊነት በማይሰማቸው ቅጥረኛ የሆኑ ወሮበላና ሆዳም ልሂቃንና አገዛዞች ነው የመተዳደሩት ማለት ነው፡፡የR2P(Responsibility To Protect) ቅኔው ይህ ነው፡፡Yes the civilized West has the responsibility to protect and rule the rest uncivilized world.አዎ R2P ተግባራዊ እንዲሆን ደግሞ የግድ ሃላፊነት የማይሰማቸውና ሀገራቸውና ህዝባቸውን የማያከብሩ የማይወዱ የማይታመኑ አድርባይና ሆዳም ወሮበላ የሆኑ ቅጥረኛ ሀገር በቀል ልሂቃንና አገዛዞች በራሳቸው በምእራባውያን እየተደገፉ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ስልጣን ላይ እንዲወጡ ይደረጋል፡፡ሀገርና ህዝብ በእነዚህ ቅጠረኞች በአለቆቻቸው እርዳታ ጭምር አበሳውን እያየ የእርስ በረስ ጦርነት እልቂትና መበታተን(የከሽፈ መንግስት Failed-State) ውስጥ ሲገባ ምእራባውያን ደግሞ እንደ አዳኝ መሲህ(Holly Savior) ሆነው ነፃ ሊያወጡንና ሊጠብቁን ይመጣሉ ማለት ነው፡፡
አዎ የታዳጊው አለም ህዝብ በሁለት ጨካኞች(ሀገር በቀል እና ውጪ) መካከል ዘላለም አበሳውን ያያል ማለት ነው፡፡ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ እንዲሁም መላው ታዳጊው አለም በዚህ በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት የተነሳ አበሳቸውን እያዩ ሳለ ስለግለሰቦች ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ብቻም ሳይሆን እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State)አንድ ሀገርና ህዝብ እንዴት ተከብሮና ታፍሮ የጋራ ህልውናውና ደህንነቱ(Collective Security and Common goods) ተጠብቆ ለመቀጠል እንደሚቻል እጅግ ፈታኝ እየሆነ ነው፡፡የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዲሁም ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ እንዲሉ ደርሶ በዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያችን የጋሪና የፈረሱ ቅድም ተከተል ተምታቶብን ያለአካሄዱ ስለ ግለሰብ ነፃነትና ዲሞክራሲ ያን ያህል በከንቱ ተጨነቅን እንጂ ከዚህ በባሰ ግን እንደ ሀገር የመቀጠል ትልቅ አደጋው ግን ብዙ የታየን አልሆነም፡፡
በዘመነ ቅኝ ግዛት አበሳውን ሲያይ የነበረውና አሁንም በዚያው ተመሳሳይ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውስጥ ለሚዛብቀውና እንደ ህፃን ልጅ ዳዴ የሚለው ታዳጊው አለም የጋራ ህልውናውና ደህንነቱ (Collective Security and Common goods) ተጠብቆ እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State) ለመቀጠል የሚችለው ይበልጥ በጋራ ጉዳዩ (Socialistic) ላይ በማተኮር እንጂ የምእራቡን አለም አይነት የግለሰብ ነፃነትን(ሊበራል ዲሞክራሲ) በማቀንቀን አይደለም፡፡በታዳጊው አለም ውስጥ የግለሰብ ነፃነት(ሊበራል ዲሞክራሲ) በዘላቂነትና በአስተማማኝ ተግባራዊና ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ታዳጊው አለም ቅድሚያ የጋራ ህልውናውና ደህንነቱ (Collective Security and Common goods) ተጠብቆ እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State) ለመቀጠል ሲችል ነው፡፡ዛሬ ወደ ልእለ ሃያልነት ደረጃ የደረሰችው ቻይናም ለዚህ የበቃችው ዋና ምክንያት ይህንን የጋራ ህልውናና ደህንነት (Collective Security and Common goods) ተጠብቆ የምእራቡን አለምና የጃፓንን ቅኝ ግዛት ጫና በመቋቋም እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State) ለመቀጠል ስለቻለች ነው፡፡ታዳጊው አለም ይህንን እንዲያደርግ የተፈጥሮ ህግም ጭምር ያስገድደዋል፡፡ምክንያቱም የግለሰብ ነፃነትን በተገቢው ሁኔታ በመቀነስና ይህንንም በጋራ ህልውናውና ደህንነት (Collective Security and Common goods) ላይ በማዋል ነው የውጪውን ጫናና ወረራ ለመመከት የሚቻለውና በዚህም የከሽፈ መንግስት Failed-State ከመሆን መታደግ የሚቻለው ፡፡We have to be so wise so that we achieve such a viable and working stable and balanced equilibrium point where we can survive both as an individual as well as a society in our nation-statehood. Failed-State becomes inevitable whenever such viable and working stable and balanced equilibrium point is destabilized. So here it is very important to properly discern the nature of our social fabric and class structure in our nation-state so that we shall not become failed-state.
So as long as it has the power to destabilize the equilibrium point of our social fabric and class structure not only savage dictatorship that has the power to render failed-state but also externally imposed westernized bogus democracy has also similar tantamount role to cause same effect of failed-state. Because we have live witnessed bogus democracy becoming the very source of conflict, violence and ensuing chaos that has been destabilizing 3rd world nations. And that is why Bogus democracy and humanitarian mission is serving as a Joker card by West in order to systematically destabilize 3rd world nations. Any way be it trough direct and blatant dictatorship (as is in Monarchical Arabic GCC Nations) or be it through bogus democracy (as is in Ethiopia and many other 3rd world nations) however what Global Capitalism aspires and thrives is to have installed stooge client-regimes who serve its Neo-Liberal and Neo-colonialism Imperialistic projects. And hence neither Dictatorship nor Democracy is its agenda (and never ever will it be) as long as its interest are maintained.
So the irony behind Failed-State hype is like the irony behind terrorism hype.
Because both happen mainly because it is systematically and insidiously maneuvered by global master elites to happen likewise.So when we are doomed by others to become failed-State in prediction, we have to be aware that they also want us to be like that and it is also their wish so for it not to happen on us as a reality we have to work hard. One of the great means is to honestly and audaciously expose both the lies and the truth to the public for public awareness and enlightenment.
God Bless Ethiopia!!!
Kinfe Michael Abay says
Save-Ethiopia!
*
God bless You too!
እውነት! እውነት!
እንዲህ ባጭር ዘጋባ፣ የሚባለውን ሁሉ ብለህ፣ የልብ ትርታዬን ነው ያገኘኽው!!!
ኢትዮጵያ ታበጽእ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ሕሊና ብርሃኑ says
ለ ሃገር ሰው፣
„መድሃነ፥ኢትዮጵያ„ ልበልህ መሰለኝ …. Save-Ethiopia
እውነቱን ለነገ ሳትል እንዲህ በማፈራረጥህ፣ ምስጋና ይድረስህ። እስከመቼ እውነቱ ሳይወጣ ሊቀር ነው? እርግጠኛ ነኝ በብዙው ዘንድም መወለድ አቅቶት የሚጉላላው የዚህ ዓይነቱ ሃሳብ ነው፣ እላለሁ! አዎ! “እያንዳንዱን የዛሬውን የኢትየጵያ ሃገር ወዳድ ሊያሳስበው ብቻ ሳይሆን፣ ራሱን አስይዞ የሃሳብ ያለህ አሰኝቶ ሊያስጮኽው ይገባል፣” ና እንዲህ ዓይነቱ እውነትም ከንግዲህ ለነገ ሳይባል ባደባባይ ካልወጣ፣ ከገባንበት ጭቃ ሳንወጣ ክፉዎች የደገሱልን ማጥ ውስጥ ሰጥመን እንቀራለን።
የውጭ ሃይሎች ለዓለም አቀፍ የእጅ አዙር አገዛዝ ተንኮላቸው ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የተገለገሉበት ዋና መሳሪይ፣ ለመብታቸው የቆሙ ቅን ዜጎችን እያፈላለጉ በዘረኝነት ስነልቦና እያጠመቁ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አገልጋዮቻቸው ማድረግ ነበር፤ ነውም። በዚህ ተንኮላቸው ለይተው ይበልጥ የሰሩበት፣ጉልበትና ሃብት ያፈሰሱበት፣ በኢትየጵያ ታሪካዊ የመንግሥት ተፈጥሮአዊ እድገት *Ethiopian State formation“ ውስጥ በተለይ ዓይነተኛ ቦታ ባላቸው፣የአማራ፣ የትግራይና የኦሮሞ ብሄረሰቦች ውስጥ ነው። አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ፣አንዱን ካንተ ወዲያ አንዱን የሌላው ደበኛ፣ ሌላውን ወዳጅና አገልጋይ ወዘተ እያደረጉ ሲያተራምሱ ናላቸውን ውሃ ባልያዘ የተለያየ አክራሪ ርዕዮተ ዓለምና ሃይማኖት እያዞሩ አጋጨተው ዛሬ ያለንበት የዕብዶች ዘመን ከተውናል።በመሆኑም የብዙ ወገኖቻችን አፈቀላጤዎች ሆነው የወጡ የታወቁ መሪዎችን ሆነ አጃቢዎቻቸውን፣ እያወቁም ሆነ በስሜት ብቻ ተገፍተው ዞሮ ዞሮ በነርሱ ፉጨት የሚንቀሳቀሱ አገልጋዮቻቸው አድርገዋቸዋል። ይህ በክፋትና የሃገር ጠቅምን ዓይን ላፈር ብሎ በራስ መውደድ ላይ የሚሽከረከር ፈሪሃ እግዚአብሄር አይሉ ህሊና የማያውቅ፣ የመጋጨት የመባላት ስነልቦና፣ መንግሥት አይል ተቃዋሚ፣ ልጅ አይል አዋቂ፣ ማህበረሰባችንን ከዳር እስከዳር እያጥለቀለቀው ነው። የዚህ ዓይነቱን የዘረኝነት ስነልቦና ለማስፋፋት፣ በቅድሚያ፣ በተለይ እነዚህ ብሄረ ሰቦች ፣ የአማራው፣ትግራይና የኦሮሞው ማህበረሰቦች ላይ ያተኮሩትም፣ እነሱ ከነ አፈ ቀላጤዎቻቸው ሆድና ጀርባ ከሆኑ፣ ውሎ አድሮ መጋጨት ብቻ ሳይሆን መላ የኢትዮጵያ መንግሥታዊ ተፈጥሮን በሂደት እንደሚያንኮታኮት ስላወቁት ነው። – – ባባቶቻችንና እናቶቻችን ብልህነት፣ እንደሌላው አብዛኛው የአፍሪቃ ምድር፣ አልበላም ሲል አሸገራቸው እንጂ፣ የኢትዮጵያ ስነመንግሥት ታሪካዊ አጀማመርና እድገትን፣ እያጀቡት እየጎነተሉት ሲመጡ ሰለኖሩ ። ስለሆነም፣ ዛሬ የዘረኝነቱ ስነልቦና ጫፍ የደረሰ ሰለመሰላቸው፣ እነሆ የ failed state ተረታቸውን በመንዛት፣ ሃገርቤት እሹሩሩ እያሉ ለ21 ዓመት ባሳደጉት መንግሥት አማካይነትም፣ በሚያሳምን ተግባር እያጀቡት ነው።
ሰለሆነም ነው፣ ዛሬ አንዱን ትልቁን እውነት፣ እነዚህ የእጅ አዙር ገዥዎች፣ ለደገሱልን ዓላማቸው፣ የተንኮሎቻቸው አስኳል የሆነውን፣ በተለይ የአማራውን፣ የትግሬውንና የኦሮሞውን ማህበረሰብ በጥቅምም ሆ ነ በስነልቦና ፣ ከስረ መሰረቱ ተጋጭቶ እንዲቆይ ማድረግ መሆኑን መናገር ያለብን። የጅ አዙር ገዥዎቹ፣ እነዚህ ማህበረሰቦች ላይ ያተኮሩት፣ እነዚህ ሆድና ጀርባ ከሆኑ፣ በነበራቸው የኢትዮጵያ ታሪክ ስነ መንግስታዊ አስተዳደግና በተለያየው ዓይነተኛ ሚናቸውና ተጽዕኖዋቸው፣ በሰላምና በትብብር እየበለጸጉ መኖር የሚፈልጉት ሌሎች የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ውስጥም ሆ ነ፣ በአጠቃላይ በመላ ሃገሪቱ ላይ የሚያስከትለውን ማህበራዊ ናዳ ስለሚያውቁ ነው። ይህን እውነት ከፍ አድርገው፣ ሃገር ወዳዶች ሁሉ ዛሬ ውሎ ሳያድር እንዲሰማ፣ እንዲታወቅ፣ እንዲጋለጥ ማድረግ ያለባቸው ለዚህ ነው። ይህ ከልሆነ እሩቅ ሳንሄድ በሌሎች የአፍሪቃ ሃገሮችና ጎረቤቶች የታየው መዘዝ አፍጦ መጥቷል።
ነገር ግን፣ ይህን ብዙ እድሜ ያለው የእጅ አዙር ገዥዎች፣ የተንኮሎች ተንኮል ያልተረዳ፣ መንግሥት አካባቢ ጉድ ጉድ አለ፣ አደፈጠ፣ በተቃውሞ ለሰላማዊ ዓመጽ ተነሳ አልተነሳ፣ መንግስትን አምርሮ ለመቀየር ጦር አነሳ አላነሳ፤ ይህን ዛሬ ሆድና ጀርባ የሆነን የተለያየ ማህበረሰብ ለማስታረቅ ከልተነሳ፣ የትኛውም የፖለቲካ ሃይል ፣ ወይ በማደንቆሪያው ድንቁሯል፣ ወይ በጥቅም ተተብተቧል፣ ወይንም ያችን በህዝቦች ዓይነት የሸበረቀችውን ኢትዮጵያ ሃገራችንን አብሮ ከነሱ ጋር ሊያፈራርስ ለመንደር ወይንም ለግል ጥቅሙ እያወቀ ወገን ለይቷል ማለት ነው።
ስለሆነም ፥ ዛሬ በጀግንነትና ሳይከፋፈሉ በአንድነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመብታቸው፣ ለመብታችን በመቆም የሚታገሉት ሙዝሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ አርአያነት በማስተዋል፣ “ድምጻችን ይሰማ !” የሚሉትን ያህል፣ እንደዚህ ዓይነቱም፣
“እውነት! እውነት ! ይሰማ !”
„አንድ ህዝብ ነን፤ አንድ ህዝብ ነን“ !!!
„ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ“!!!
ብለን እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ድምጻችንን ከፍ አድርገን ለነጻ ኢትዮጵያ መጮህ አለብን!
ከተኛንበት በአእምሮም በተግባርም መነሳት አለብን !!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
Save-Ethiopia says
Dear Reader how are you.
Thanks for your attention and sober understanding on my comment.
ዲሞክራሲያዊ መብታችን ለመጠየቅና ለማስከበር ቅድሚያ ዲሞክራሲያዊ መብታችንን የምንጠይቅባት የምናስከብርባት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ቅድሚያ እንደ ሀገር መኖር አለባት፡፡ስለዚህም እንደ ግለሰብ ሃይማኖት ያለሀገር ሊኖረን ቢችልም ቅሉ ግን የምናምንበትን ሃይማኖት ለመከተልና ለማራመድ የሚያስችል የዜግነት መብት ሊያጎናፅፈን የሚችለው አካሄድ ግን የእኛ የምነለው ሀገር ሲኖረን ነው፡፡
ላለፉት 21 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ የፈረደበት የምእራቡ አለም ዲሞክራሲ የሚባል ነገርና ስልጣን ላይ ያለውም አገዛዝ ከሚከተለውን የዘር ፖለቲካ ከማቀንቀን ውጪ ሀገር የሚባለው ትልቅ ፅንሰ-ሃሳብና ስሜት ግን ቀስ በቀስ ከኢትዮጵያውያን አእምሮና ስሜት ውስጥ እየከሰመ የመጣ ነገር ነው የሆነው፡፡ለዚህም ነው አፄ ቴዎድሮስ አሉት እንደተባለው የኢትዮጵያዊነትን ሀሁ ምን ብለን ብናስቆጥራቸው ነው የሚገባቸው ያሉት፡፡መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በተባለው የፕሮፌሰር መስፍን መፅሀፍ ውስጥ እውቀትና እውነት በአንድ በኩል የተገለጠ በሌላ በኩል በምርምር የተገኘ ተብሎ ተከፍሎ ቀርቧል፡፡ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንደኔ እይታ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በዋናነት የተገለጠ እውነትና እውቀት ሆኖ በመኖሩና በምርምር እውቀት ጭምር ያልታገዘ ስለነበር ከዚህ በኋላ ግን ይህ ታሪካዊ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በምርምር እውቀት ጭምር ካልታገዘ በስተቀር በሂደት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እየወደቀ የሚመጣ ነገር ነው የሚሆነው፡፡ላለፉት 21 ዓመታትም የታየው ይህ ነው፡፡
በምርምርና ፍልስፍና የተገኘውን ዲሞክራሲ የሚባለውን የምእራቡን አለም አስተሳሰብ እንደ ሸቀጥ እቃ አስገብተን መሰረት በሌለው ነገር ላይ ለማስቀመጥ ፈለግን፡፡በዚህ የተነሳም ላለፉት 21 ዓመታት ያህል በቅጡ ያልገባንን ባእዳዊና መጤ የሆነውን ዲሞክራሲ የሚባል የፋሽን ቃልና ፅንሰ-ሃሳብ ባራገብንበትና ባቀነቀንበትን መጠን በተቃራኒው ደግሞ በእጃችን ለዘመናት የቆየውን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚባለውን ብሄራዊ ስሜትና አስተሳሰብ እያዳከምነው መጣን፡፡ይህም ምንም መሰረት በሌለው ነገር ላይ ፎቅ ለመገንባት የማለም ያህል ነው፡፡የባህር በራችን ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ሞራላዊ በሆነ መንገድ ሲወሰድና አንገታችን ሲታነቅ ብዙዎቹ ፖለቲከኞቻችንና ምሁራኖቻችን ምንም ሳያስጭንቃቸው በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ እንዲሉ አልሰሜን ግባ በለው አይነት ስልጣን ላይ ካለው አገዛዝ ጋር ወደፊት ስለሚገኘው ስለ ስልጣናቸው እያሰቡ የዲሞክራሲ ዳንኪራና ፌሽታ ከአገዛዙ ጋር አብሮ ለመርገጥ ሲያሽቃብጡ ነበር፡፡የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዲሉና ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ እንዲሉ በቅጡ ያልገባንን እና የማናውቀውን የምእራቡን አለም ዲሞክራሲ ስናቀነቅንና ስናሯሩጥ በእጃችን የነበረውን ጥንታዊውንና ታሪካዊውን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ግን ከእጃችን እያፈተለከ እንዲወጣ አደረግነው፡፡ከሁለት ያጣ እንዲሉ አሁን ግን ከሁለቱም አይደለንም፡፡ይህ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የዘመኑ ኮሜዲ-ትራጄዲ ነው፡፡ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊና አፍሪካዊ ወጣት የፖለቲካ ልሂቃንና ምሁራኖች ያልገባን ነገር የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምና የሶሻሊስቱ ብሎክ በጊዚያዊነት መውደቅ በቃ ወዲያውኑ የዲሞክራሲ ምእራፍ መጀመሪያ እንደሆነ አድርገን ነበር የተረዳነው፡፡በእርግጥም ላለፉት 21 ዓመታት ያህል ሲራገብና ሲቀነቀን የነበረው ዲሞክራሲ የውሸት ዲሞክራሲ ነበር፡፡ነገር ግን ያለፉትን 21 ዓመታት ስንቃኝ ትክክለኛ እውነታው መሰረቱን በምእራቡ አለም በተለይም አሜሪካና እንግሊዝ ያደረገው ግሎባል ካፒታሊዝም በአሸናፊነት ወጥቶ ይህ ሰርዓት በዘመነ ቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የደከመበትን የጦር ግዳዩን ያለአንዳች ተቀናቃኝ የሚሰበስብበት የዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ትግበራ እንደገና ሀ ብሎ በአዲስ መንፈስ የሚጀምርበት መሆኑ ነው፡፡እድሜ ለአሜሪካ የማርሻል ፕላን እርዳታ አውሮፓም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የእርስ በርስ እልቂት አሁን ሙሉ በሙሉ አገግሟል፡፡ስለዚህም የምእራቡ አለም በአሜሪካ ዋና መሪነት ዳግም ዘመናዊ ቅኝ ግዛትን በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ አሸባሪነትን ዲሞክራሲንና ሰብዓዊ መብትን ሽፋን አድርጎ መላውን አፍሪካንና ታዳጊውን አለም ዳግም ዘመናዊ ባርነትና ኢኮኖሚያዊ ምዝበራ ውስጥ ለመክተት በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ይህንን ደግሞ ተግባራዊ ለማድረግ በዋናነት እየተጠቀመ ያለው ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንዲሉ በከፋፍለህ ግዛው መሰሪ ስልት ሀገር በቀል አድር-ባይና ባንዳ ልሂቃንና ምሁራንን በጥቅምና በስልጣን አስሮ በመያዝ ነው፡፡ባእዳን ሃይሎች ቅኝ ግዛትን ለማስፋፋት ሁል ጊዜ እንደ መንደርደሪያና መነሻ ነጥብ(Stepping-Stone) የሚጠቀሙት ጥቂት ሀገር በቀል አድር-ባይና ባንዳ ልሂቃንንና ምሁራንን ነው በጥቅምና በስልጣን አስሮ በመያዝ ነው፡፡ከዚያ በኋላ እነዚህ ባእዳን ሃይሎች እነዚህን ሀገር በቀል አድር-ባይና ባንዳ ልሂቃንንና ምሁራንን በፖለቲካው በኢኮኖሚው በሚሊታሪው በደህንነቱ በሚዲያው በኢንተርቴይንመንት እንደስትሪው በቴክኖክራቲክ ቢሮክራሲው ወዘተ በመሰግሰግና ከዚያም የእውቀትና የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት የአንድን ሀገር አጠቃላይ ስርዓት በቁጥጥር ስር ያደርጋሉ፡፡አሁን በሀገራችን ያለው አገዛዝም በዚህ ቅኝት ነው ደርግን አሸንፎ ስልጣን ላይ እንዲወጣ የሆነውና እስካሁንም ድረስ እንዲገዛ እየተደረገ ያለው፡፡ላለፉት 21 ዓመታትም ለዚህ አገዛዝ የውጪ እርዳታና ብድር እንደ ጉድ የጎረፈለትም ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ተገኘ የሚባለውም የኢኮኖሚ እድገትና የኢኮኖሚው እድገትም ዋና ተጠቃሚዎች ጥቂት ልሂቃን የመሆናቸው ምስጢር በዋናነት ከዚህ የመነጨ ነው፡፡በመሰረቱ ትክክለኛ የኢኮኖሚ እድገት ዝም ብሎ የተለመደውን GDP ብቻ በመቁጥርና በማስላት አይደለም፡፡ሌሎች ብዙ ነገሮች ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡ለምሳሌ በዋናነት የህዝብ ብዛት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል የሰዎች ጤናማ ግለሰባዊና ማህበራዊ ህይወት (quality of life) የተፈጠሮና የአካባቢ ደህንነትና ጥበቃ ወዘተ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ደግሞ ይህ ሁሉ ግምት ውስጥ ሲገባ ተገኘ የተባለው የኢኮኖሚ እድገት Zero-Sum Game ብቻም ሳይሆን ከዚያም አልፎ Negative sum-game ሊሆን ይችላል፡፡ ብቻ ላለፉት 21 ዓመታት ስልጣን ላይ ላለው አገዛዝ የተሰጠው ብድርና እርዳታ በዋናነት የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ ተብሎ ነው እንጂ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታስቦ አይደለም፡፡
There is no free lunch እንደሚባለው ማንም ዝም ብሎ እርዳታና ብድር ለሌላ ለማንም ዝም ብሎ አይሰጥም፡፡የተከበሩት ሼህ አላሙዲንም በሚሰጡት ለጋስነት ያለውንም በሚመለከት ይኸው ነው፡፡ብዙውን ጊዜ አርዳታና በድር ተመዘበረ ተዘረፈ ይባላል ነገር ግን ቀድሞውኑ ምእራባውያን እኛን ወይንም ስልጣን ላይ ያለውን አይነት አገዛዝ ለምንድን ብለው ነው የሚረዱን የሚለውን ዋና መሰረታዊ ጥያቄ ማንም አያነሳም አይመልስም፡፡ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ቢነሳና ምላሽ ቢያገኝ ኖሮ ግን ከበስተጀርባ ያለው ነገር ይገባን ነበር፡፡ለምሳሌ አሜሪካ ከሁለተኛው ጦርነት በኋላ በማርሻል ፕላን መሰረት ወደ 20 ቢሊዮን ዶላር ለምእራብ አውሮፓ መልሶ ማቋቋም ስትሰጥ አንዱ ዋና ምክንያት የሶቭየት ህብረትን የኮሙኒዝም ስርዓት ወደ ምእራብ አውሮፓ ከመስፋፋት ለመመከት ጭምር ነበር፡፡
ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላም እስከ ቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም ድረስ በራሷ በአሜሪካና መላው ምእራብ አውሮፓ ጭምር መላውን ህዝብ ጭምር የኢኮኖሚ እድገት ዋና ተጠቃሚ እንዲሆን ያደረገው ለነበረው የWelfare-State አሰራር ዋና አስተዋፅኦ ያደረገው የሶቭየት ህብረትና በምስራቅ አውሮፓ ያለው ህዝብ ማእከል ያደረገ የሶሻሊስት ስርዓት አሰራር እንደ Check and Balance ሆኖ ስላገለገለ ነበር፡፡ይህንን ያነሳሁት አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በራሱ በምእራባውያን ዋና ድጋፍ ደርግን ጥሎ ስልጣን ላይ እንዲወጣ የሆነበት ዋና ምክንያት በአንድ በኩል ከጥንቱ ኮሎኒያሊዝምና ፀረ-ኮሊኒያሊዝም ታሪክ ጋር በሌላ በኩል ደግሞ ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር ታሪካዊ ትስስር ስላለው ነው፡፡
መለስና ወያኔ የሚከተለው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው የሚባለው ነገር ፍፁም ማታለያ ጭንብል ነው፡፡
አብዮታዊም ሆነ ዲሞክራሲያዊ የሚያሰኘው ምንም ይዘት(Substance) የለውም፡፡ይህንን ለመረዳት ደግሞ ፖለቲካውን ብቻ ሳይሆን የተዘረጋውን የኢኮኖሚ ስርዓት በጥሞና መረዳት ይገባል፡፡ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ የሚያራምደው የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት፡፡የብዙሃኑ ህዝብ ህይወት ከእለት ወደ እለት ወደ ድህነት አረንቋ መገፋትና የጥቂቶች በብርሃን ፍጥነት የሀብት ጣሪያ ላይ መቆናጠትና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለግል ባለሃብቶች በርካሽ ዋጋ መቸብቸብ የሚያሳየው አገዛዙ የሚከተለው የኢኮኖሚ ስርዓት ኒዎ-ሊበራል ካፒታሊዝም መሆኑን ያሳያል፡፡በዘር ላይ የተመሰረተው ፌዴራሊዝምና የሚያራምደው የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲና አንድን ብሄር በሌላው ላይ በፍፁም የበላይነት የማንገስ አካሄድና የሀገር ብሄራዊ ስሜትና አስተሳሰብ መጥፋት ደግሞ ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም መሆኑን ያሳያል፡፡ ስለዚህም የኢትዮጵያ ችግር ዝም ብሎ የምርጫ ዲሞክራሲ ችግር አይደለም ወይንም አሁን ስልጣን ላይ ያለው ወርዶ ሌሎች ተመሳሳይ ቅጥረኞች ስልጣን ላይ ቢወጡም ቶሎ የሚፈታ ችግር አይደለም፡፡ስለዚህም የስርዓት ለውጥ ያስፈልጋል፡፡በሂደት የሚተገበር ስር-ነቀል የስርዓት ለውጥ፡፡ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ዘረኛ ነው የሚል አስተያየት በተሰጋጋሚ ይስተጋባል ይህ ግን የሚታወቅ ነውና ነገር ግን ለምን ዘረኛ ሆነ የሚለው በጥሞና መመርመር አለበት፡፡ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ዘረኛ የሆነበት ምክንያት ዝም ብሎ በተፈጥሮው ዘረኛ ስለሆነ አይደለም፡፡ዘረኛነቱን የውጪ ባእዳን ሃይሎች በእከክልኝ ልከክልህ አካሄድና በከፋፍለህ ግዛው አሰራር የራሳቸውን ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ለራሳቸው የውስጥ አላማና ፍላጎት እንዲመች አድርገው ሊጠቀሙበት ስለሚፈልጉና ስለቻሉ ነው፡፡ስለዚህም ባእዳን ሃሎች ጥቂት አድርባይና ከሃዲ የሆኑ የትግሪኛ ተናጋሪውን ልሂቃንና ምሁራንን መርጠው ደካማ ጎናቸውን በመጠቀም የዘረኝነት መርዛቸውን በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እርስ በርሱ እንዲናከስ ይህንን የዘር ጥላቻ በሰፊውወና በጥልቀት እንዲዘሩት ባእዳን ሃይሎች እነዚህን ሀገር በቀል ልሂቃን ቀጥቅጠው አሰለጠኗቸው እርዳታም ሰጧቸው፡፡እነዚህ ጥቂት ሀገር በቀል ልሂቃንም የተቀረውን ትግሪኛ ተናጋሪ ህዝብ አማራ ሲረግጥህ ሲዘርፍህ ኖሯልና ቁጥር አንድ ጠላትህ አማራ ነው ብለው የጥላቻ ዘራቸውን በገዛ ትግሪኛ ተናጋሪው ወገናቸው ላይ እንደወረደ ዘሩባቸው፡፡ለዚህም መሰሪ ስራ ባእዳን ሃይሎች ስልጣን ላይ ላለው አገዛዝ ብድርና እርዳታ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም አጎረፉለት፡፡ነገር ግን ብድርና እርዳታው መጨረሻ ላይ ለምን እንደሚውል የታወቀ ነው፡፡በዚህ እይታም እነዚህ ልሂቃን ለትግሪኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ እኛ ስልጣን ላይ ስለወጣን ይኸው አሁን በእኛ ትግልና መስዋእትነት የተነሳ አንተ የተለየ ጥቅምና ስልጣን አገኘህ እያሉ የወጡበትን የትግሪኛ ማህበረሰባቸውን የተለየ ስሜትና አመለካከት ውስጥ ከተቱት፡፡በዚህ የተነሳም ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የትግሪኛ ማህበረሰቡን አንድ የሆነ አጣብኝ ውስጥ ሊከቱት ቻሉ፡፡
ምክንያቱም በአንድ በኩል በዘረኝነት ላይ የተመሰረተው ጊዚያው ጥቅምና ስልጣን ዘላቂነት እንደሌለውና ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘለቄታው የሚያቃቅርና የሚያናክስ እንደሆነ ውስጣቸው ያውቀዋል በሌላ በኩል ደግሞ በአድሎ የሚገኘው ጥቅምና ስልጣን ደግሞ ስጋቸውን አሸነፈው፡፡
ይህ አይነት ጥቂቶችን በብዙሃኑ ላይ በበላይነት የማሰልጠን ችግር በሩዋንዳ ውስጥ በዘመነ ቤልጂየም ቅኝ ግዛት ወቅት በሁቱና ቱትሲዎች መካከል የተፈጠረ ሁኔታ ነው፡፡ኢትዮጵያ ግን የቅድስና ሀገር ስለሆነች ያ አይነት የሩዋንዳ መከራ ግን እስካሁን ድረስ አልሆነም እንጂ፡፡ዞሮ ዞሮ ግን ኢትዮጵያን ከጥፋት ማዳንና እንደተሟረተብን Failed-State እንዳንሆን መታደግ ታሪካዊ ግዴታችን ነው፡፡ማንም በሌላው መቃብር ላይ ቤተ-መንግስት ለመገንባት የሚያደርገው ከንቱ መፍገምገም ግን የትም አያደርሰንም፡፡ባእዳን ሃይሎች ደግሞ ወዳጃቸው ጥቅማቸውና ጥቅማቸው ብቻ እንጂ ማናችንም አይደለንም፡፡ሁላችንንም እንደ ማስቲካ ወይንም ሸንኮራ አደጋ አላምጠውን ጣእማችን ሲያበቃ ወደ ሌላው አዲስ ማስቲካ ወይንም ሸንኮራ አደጋ ነው የሚዞሩት፡፡በስተመጨረሻ ግን የምለው ኢትዮጵያውያን ልሂቃን ምሁራንና ፖለቲከኞች ለጊዚያዊ ጥቅምና ስልጣን ተሸንፈው በፈቃደኝነት የባእዳን ሃይሎች ቅጥረኛ ካልሆኑ በስተቀር ይህች ሀገር ህልውናዋና ደህንነቷ ብዙም አደጋ ላይ አይወድቅም፡፡ምክንያቱም የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ያለነዚህ ሀገር በቀል ልሂቃን(Comprador Elite) ተባባሪነት ድልድይነትና ቅጠረኛነት በታዳጊው አለም ውስጥ በአስተማማኝ ተግባራዊ ከቶውንም ሊሆን አይችልም፡፡ምክንያቱም እነዚህ ሀገር በቀል ልሂቃን (Comprador Elite) የግሎባል ካፒታሊዝም Class Structure ዋና አገናኝ ሰንሰለቶች ናቸው፡፡በሃይማኖት በዘር በፆታ ወዘተ የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲም የዚህ የግሎባል ካፒታሊዝም Class Structure ዋና አካል ነው፡፡ይህንን የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ሳነሳ ግን እንደ ኢትዮጵያዊ እንደ አፍሪካዊ እንደ ታዳጊው አለም ህዝብ እይታ ሁሉንም ስር የሰደደና የተስፋፋ የዘመናት ዘርፈ ብዙ የውስጥ የራሳችንን ችግር በውጪው አለም ላይ ለመላከክ ወይንም ከውጪው አለም ጋር በመከባበርና በመተማመን ላይ የተመሰረተ የጋራ አለም አቀፍ ጥቅምና ፍላጎት የለንም ለማለት ሳይሆን ይህንን የግሎባል ካፒታሊዝምን ጉዳይ እንደ አንድ አለም አቀፍ ስርዓት እንደ አንድ ዋና መሰረታዊ የችግሮች መንስኤ በሆኑን በቅጡ አለመረዳታችን ለመጠቆም ነው፡፡በእርግጥ ኒዎ-ሊበራል ግሎባል ካፒታሊዝም በ Austerity Measure and Bank Bailout የተነሳ በራሱ በሰለጠነው አለም ህዝብ ውስጥ ጭምር ቀላል የማይባል ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ቀስ በቀስም ፖለቲካዊ ቀውስ እየፈጠረ እንደሆነ የሚታወቅ ጭምር ነው፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!
Hilina Berhanu says
መድሃነ-ኢትዮጵያ ልበልህ ብያለሁ፥
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!
አንተንም ለሰጠኽን ማብራሪያ እግዜር ይባርክህ!
ጉልጉል እንዳውም፣ እንዳው ቢሆንለት ፣ አንድ ቀን፣ አንድ ዓምድ ከፍቶልህ፣ እዚህ ውስጥ ገረፍ እያደረግህ ምታነሳቸውን ጉዳዮች እንድታስተምርበት ብፈቅድልህ ምንኛ መልካም በሆነ ነበር፤ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የባእድ ሃይሎች የደገሱልንን የማፈራረስ መዓትን መልሶ ለመቋቋም፣ በሚደረገው የገንቢ ትግል ውስጥ ብርሃን ይፈነጥቅ ዘንድ።
ያም ሆ ነ ይህ፣
ለሰጠኽን የሚያመረቅንና ፍርጥም፣ ፍርጥርጥ አርጎ እውነቱን፣ የእውነታችንን/Reality ጀርባን ለሚያወጣው ማብራሪያ ኣመሰግናለሁ። ያነሳኻቸው ነጥቦች ሁሉ ስለሚገቡኝና ከሞላ ጎደል የኔም ኣመለካከት ስለሆኑ። ነገር ግን እንደሚታወቀው፣ በዘመነ ቀዝቃዛው ጦርነት በኮምኒስቱ ዓለም ውስጥ በሰው ልጅ መብቶች ላይ የተፈጸሙት ወንጀሎችና የነበሩት የአስተዳደር ትርምሶች፣ በሃገራችን ዜጎችም ሆነ በዓለም ህዝቦች ክፉ ትዘታ ገና ትኩስ ስለሆኑ፣ ባለኣንድ ፥ዓይናሞቹ ብቻቸውን እንደልባቸው ባገራችን ላይና ባለም ላይ የሚዘሉትን ጎደሎነት፣ አንተ እንደምታየው አልታይ ስለሚላቸው፣ የሰውን ግንዛቤ እንደገና ለማስተካከልም ሆነ አመዛዛኝ እንዲሆን ለማድረግ ያለው መንገድ ቀላል እንዳልሆነ ግን ይገባኛል። ሰለሆነም በዚህ መንገድ ውስጥ በተለይ መቼም ዲሞክራሲ የምትባለዋ ሁሉን አድን፣መድሃኒት የምትመስል ነገር፣ ንድፈ ሃሳቧ፣ ላይ ላይዋን ተቀንጅባ ያደነቋቆረችንን ያህል፣ በሚያጠግብ ይዘት/substance / ተሞልታም ቢሆን፣ እንዲሁም ላገራችን በሚበጅ መንገድ፣ ከመኮነን ኣልፈን የሚያመረቅን አማራጭ ማሳየቱ ከሁሉም ይበልጥ ዓቢይ ጉዳይ ይመስለኛል፤ እንዲህ ባበደና በዞረበት የውድ ሃገራችን ዘመን።
በነገራችን ላይ፣ ይህች የዲሞክራሲ ጉዳይ እንዳው እንዲሁ ስላደኖቆረችኝ፣ አንድ ጊዜ ረጋ ብዬ የእንግሊዝኛ ሆሄዋቶቹን እንኳን ስመለከታቸው፣ እብደት ከሚባለው ቃል የሚለያት አንድ ሆሄ ብቻ እንደሆን አስተውዬ ከደካም ፈገግታ ጋር ለካስ የሚያተራምሰን ይኽ ነው ስል፣ በቀልድና በቁም ነገር ተገርሜ፣ ማስታወሻ ብጤ ወስጄ ነበር:-
Demo – cra – c -y ……Demo – cra -z-y!
ሶስተኛውን ሆሄ ….A …..B …ብሎ ….”C”ን…. ከመጨረሻው ሆሄ፣ ከ”Z” መለየት አቅቶን፣ በቅጡ ሳንማረው፣ ማለቂያችንን -Z- ን አንግበን ሆያ ሆዬ እንል ገባን!
ያም ሆኖ ከሆያ ሆዬ አልፈን፣ አቅመ ኣዳም ደርሰን፣ አሳብዶ አገራችንን ገደል ከመክተቱ በፊት ማን ያውቃል፣ እንደርስበት ይሆናል ። ተስፋ መርህ ነው! እኔም ለፈገግታም ሆነ ለማሰብ ከአንድ ሁለት የማስታወሻዎቼ ስንኞች ጋር ፣ በዚሁ እሰናበታለሁ!
*
እራሳችንን እንድንቀይር፣ “Change Your Mind” እያሉ በሚማጠኑ ተመሳሳይ ጩኽቶች ውስጥ፣ እንዲህ ይሉ ነበር፥
It is You, the DEAD ENDS,
THE DEAD HEADS.
Africa needs, not a shift
In Para-DIGM,
Is a shift and shuffle of your kinds,
That it lacks.
Call it, if you like, Demo-Cracy,
But Attention! Demagogy,
“Z” and “c”, Philology.
At times and History,
Demo-craCy goes craZy…
…
At such moments,
Stop TIME,
Go and Go ahead,
To the SOURCE….the best b-reed,
The Origin, the best c-reed.
For its peace, for its fate,
Rich in bread.
Healthy child, best mind…
እግዜር ከተጨመራበት የማይሆን ነገር የለምና ያበርታን!
ኢትየጵያ ለዘላለም ትኑር!