የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስም ሲነሳ አቶ በረከት ስምዖን በግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ። የአቶ በረከት ንብረት ሆኖ የመለስን አመራር በታማኝነት ሲያገለግል የኖረው ይህ ተቋም ቆርጦ በመቀጠል፣ የዜጎችን ሃሳብ በማዛባት፣ ወሬን ባለማመጣጠንና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ የሚታወቅ ነው። ስለሚጠየፉት የማይመለከቱት እንዳሉ አፍ አውጥተው የሚናገሩም አሉ። ለሙያው ቅርብ የሆኑ አስተያየት ሰጪዎች “ወገንተኛ እንኳን ቢኾን መሰረታዊ የሙያው ግዴታ ሳይጣስ ሊሆን ይገባል። አንድ መገናኛ ማመጣጠን ካልቻለ በራሱ ሙት ነው። እያደር ብቻውን ይቀራል” ሲሉ ኢቲቪን ይገልጹታል። እንደነሱ አባባል ኢቲቪ ከህዝብ ሳይሆን ከራሱ ጌቶችም ጋር ተነጥሎ የአንድ ወገን (ግለሰብ) ሎሌ የሆነ በድርጅት ቅርጽ የሚከላወስ ሱቅ በደረቴ አይነት ነው። ኢቲቪ ሃሳባቸውን፣ ንግግራቸውን፣ አቋማቸውን፣ ጥቆማቸውንና … [Read more...] about ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!
ሽ – ሽ – ት …!
ሽ - ሽ - ት …! እንደዋዛ ሲከንፍ ዕድሜዬ እኔን ጥሎ ስም ያልዘራሁበትን ወኔዬን ጠቅልሎ እንደ ቀልድ ፤ እንደ ህልም ፤ ሲከስም ወዘናዬ ብ … ን … ! ሲል የኋሊት ጠጉሬ ከላዬ እንደው እንደ ዘበት ልጆች ሲሉኝ ጋሼ መናገር ያምረኛል ዕድሜዬን ቀንሼ፡፡ ይህንንም ግጥም ያገኘነው ከፌስቡክ ላይ ሲሆን ታዋቂው ገጣሚ አብዲ ሰኢድ ነው የገጠመው፡፡ ምስጋናችንን እንቸረዋለን፡፡ በሥራ መደራረብ እንደታሰበው በወቅቱ የግጥም ጨዋታችንን በማዘግየታችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ባለፈው “ህልመኛው” በሚል ርዕስ ላወጣነው ግጥም አጸፋ መልስ የሰጣችሁ የዘወትር ገጣሚዎቻችንን yeKanadaw kebede፣ inkopa፣ Tsinat፣ እና አሥራደው ከፈረንሳይ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ስለ “ሽሽት” ምን ትላላችሁ? ሽሹ! ሽሹ! ወይስ …? እስቲ ጨዋታውን አምጡት? … [Read more...] about ሽ – ሽ – ት …!
ከዚህም ከዚያም
በአለባበሳችሁ አትፈታተኑ በሜኔሶታ ጠቅላይ ግዛት የሜኔቶንካ ሁለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች የመቀመጫና የኋላ ክፍላቸውን የሚያሳይ አለባበስ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡ የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር የሆኑት ዴቪድ አድኔይ ለወላጆች በላኩት የኢሜይል (የጾዳቤ) መልዕክት ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን እንዲመክሩና የመቀመጫ ክፍላቸውን አወጣጥሮ እንዲሁም እግራቸውን በብዛት የሚያሳይ አለባበስ ሌሎችን የሚረብሽ በመሆኑ እንዳይለብሱ እንዲያደርጉ በማሳሰቢያው ጠቁመዋል፡፡ ርዕሰመምህሩ ለወሰዱት እርምጃ ከወረዳው ትምህርትቤት አስተዳደር፣ ከበርካታ ወላጆችና ከሌሎች ት/ቤቶች ድጋፍን አግኝተዋል፡፡ ውሳኔውን የተቃወሙ ተማሪዎች ሲኖሩ አንዳንድ ወላጆች ደግሞ “በየማስታወቂያው፣ በየቲቪው፣ በየመጽሔቱ፣ በሙዚቃው፣ … የሚሰራጨው የአለባበስ ዓይነት በየሱቁ ሲኬድ ከሚገኘው ጋር አንድ በመሆኑ ሰውነትን የማያሳይና … [Read more...] about ከዚህም ከዚያም
ከእሁድ እስከ እሁድ
የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች በማህበር ተደራጅተው እውቅና ጠየቁ! ባለአወልያዎችም ተደራጅተዋል በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች በማህበር ተደራጅተው ህጋዊ ፈቃድና የህጋዊነት ማረጋገጫ የምሰክር ወረቀት የጠየቁት “ይበራል ይከንፋል፣ አይሞትም ያርጋል” እየተባለ ሲመለክ የነበረው ታምራት ገለታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ነበር። የእምነቱ መሪዎች በ2002 ዓ ም ወልመራ ከተማ ቆቦ በምትባል ቀበሌ መስራች ስብሰባ አካሂደው እንደነበረ ያስታውሳሉ። ከሁለት ዓመት በፊት የወልመራ ወረዳ ከተማ በሆነችው ሆለታ የተደራጁት የዋቄፈታ ስርዓተ አምልኮ ተከታዮች የህጋዊነት ጥያቄ ያቀረቡት ለኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መሆኑን የሚጠቅሱት እነዚህ የእምነቱ ተከታዮች ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጹለት ከሆነ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል። መንግሥት በተደጋጋሚ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውና ማየት የሚፈልገው!
ባለፉት ዐመታት በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ምርጫዎች ተካሂደዋል። ከአምስት ዐመት በፊት በኬንያ የተካሄደውንና፣ በሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ደግሞ በናይጄሪያ የተደረገውን የፕሬዚደንትና የፓርላሜንት ምርጫ ትዝ ሳይለን አይቀርም። ከአንድ ዐመት በፊት ደግሞ በቱኒዚያ የተለኮሰው የሰሜን አፍሪካው የጥቢው አብዮት እየተባለ የሚጠራው ወደ ግብጽና ወደ ሊቢያ፣ ከዚያም ወደ የመን በመሸጋገር የስርዓት ለውጥ ሳይሆን የፕሬዚደንቶችን ለውጥ አስከትሏል። … … ከዚህ ስንነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘው፣ የሚያልመውና የሚጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ነው። የዛሬው የወያኔ አገዛዝ በአንዳች ነገር ቢወድቅ ምኞቴን የሚያሟላልኝ፣ ህልሜን ዕውን የሚያደርግልኝ፣ ነፃነቴን የሚያስከብርልኝና፣ ተከብሬና ተዝናንቼ በአገሬ ውስጥ ለመኖር የሚያስችለኝ የተደራጀ ኃይል አለ ወይ? ካለስ እንዴትና በምንስ ዘዴ ነው ስር የሰደደውን … [Read more...] about የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውና ማየት የሚፈልገው!
“ጥቁሩ ሰው” ይናገራል!
“ጥቁሩ ሰው” ይሉታል። ኢትዮጵያዊያን ለሚያሽከረከራት አስፈሪ ፈተና መፍትሄው ሰብአዊነትን ማስቀደም ብቻ ነው የሚል የጸና እምነት አለው። “ከጎሳ በፊት ሰብዓዊነት” በሚል መሪ ዓላማ ከሚመስሉት ጋር በመሆን ድርጅት አቋቁሞ መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባከናወናቸው ሥራዎች ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማው ያምናል። ኢትዮጵያዊያን ችግር ደርሶባቸዋል በሚባልበት ሁሉ ቀድሞ ደራሽ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በሰራቸው ስራዎቹ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ለማፍራት ቢችልም “ከጀርባው ድብቅ ዓላማና አጀንዳ አለው፣ ብቻውን ይሮጣል” የሚሉትን ጨምሮ በግል አቋሞቹ ዙሪያ ነቀፌታ የሚሰነዝሩበትም አሉ። የወደፊት ዕቅዱና የሚነቅፉት እንደሚሉት መቼ ፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ ይፋ ያደርጋል? በሚሉትና በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ኦባንግ ሜቶ ከጎልጉል … [Read more...] about “ጥቁሩ ሰው” ይናገራል!
የእምነትና የሞራል ግዴታ
በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስትና በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ያሉ ሰዎች ስለየሚያደርጓቸው ተደጋጋሚ በደሎች ዘወትር የሚነገሩትና የሚጻፉት ነገሮች እንደሚያሰለቹ የታወቀ ነገር ነው። በሆንም ቀድሞ በባህላችን ሲደረጉ አስገራሚና አስደንጋጭ የነበሩ ስህተቶች ተደጋግመው በመደረጋቸው እየተለመዱ፤ ስለነሱም በተደጋጋሚ የሚነገሩትና የሚጻፉት አሰልችተውናል። ቢሆንም፤ ሰልችተን ርግፍ አርገን ከተውናቸው፤ ስሀተተ ፈጻሚዎች በስህተታቸው ስለሚቀጥሉና ስህተቶችም የባህል ውርስ ሆኖነው እንዳሸገሩ፤ ስህተተኞችም ከስህተታቸው እንዲገቱ ለማሳሰብ፤ የእምነትና የሞራል ግዴታ በሚል ርእስ ይህችን ጦማር አዘጋጀሁ። (ሙሉው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የእምነትና የሞራል ግዴታ
“ለትግል እንነሳ”
በዛሬው እለት በ14/11/2012 በእስራኤል አገር በእየሩሳሌም ከተማ ቁጥራቸው ከ10000 እስከ 15000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን በተገኙበት የስግድ በአል በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። የበአሉ አብይ ትርጉም ኢትዮጵያዊ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ አምላካቸው ቅድስት አገር እየሩሳሌም ያደርሳቸው ዘንድ ተሰባስበው የምኞት ፀሎታቸውን ሲያደርሱ የነበረው በፀሎት ያሰሙት ልመና ፈጣሪ ሰምቷቸው በቅድስት አገር እስራኤል መሰባሰባቸውን ምክንያት በማድረግ በየአመቱ የምስጋና ፀሎት ከተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመምጣት ሲያከብሩት አመታት ተቆጥሯል። ሆኖም በተጠቀሰው የበአል አከባበር እለት የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዝ ባለ 14 ነጥብ የተቃውሞ ሀሳብ የያዘ “ለትግል እንነሳ” በሚል ርእስ በርካታ ወረቀቶች ተበትነው በበአሉ ታዳሚዎች እጅ የደረሱ ሲሆን በፅሁፉ ላይ … [Read more...] about “ለትግል እንነሳ”
እስራኤል ልጆቿን አሰረች
“አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስብ ይህንን ስርአት ጠብቀውም አድርገውም” ኦሪት ዘዳግም 16 – 12 የንግስት ሳባና የጠቢቡ የንጉስ ሰለሞንን ግንኙነት ተገን አድርጎ የተፈጠረው ሚኒሊክና ሚኒሊክን አጅቦ ከተስፋይቱ ምድር ወደ ታላቋ አገራችን የገባው የኦሪት እምነት አያሌ ሺህ ዘመናትን ማስቆጠሩን የሁለቱም አገር ሕዝቦችና መንግስታት ሊዘነጉት የማይችሉት የእምነት ትስስር ቁርኝቱ እስከ ዛሬ ድረስ አልተበጠሰም። የክርስትናው እምነት ገኖ በበላይነት እስከተስፋፋበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የኦሪት እምነትን ተከታይ እንደነበረችና በአገራችን ለእምነት ፅኑ መሰረት ወይም ትኩረት የማይሰጡ መንግስታት በተፈራረቁ ቁጥር ሕዝባችን ዛሬም “የእስራኤል አምላክ የተመሰገነ ይሁን” የሚለውን የምስጋና ቃል ከማስተጋባት አልቦዘነም። የዛሬዋ ነፃይቱ እስራኤል ገና የ64 አመት እድሜ ባለፀጋና … [Read more...] about እስራኤል ልጆቿን አሰረች
ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!!
ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የአቶ መለስን ሞት ደብቀው በመያዝና ማስተባበያ በመስጠት ጊዜ የወሰዱት ይኸው የተባለው የፖለቲካ ወለምታ እንዳይፈጠር ለማድረግ በማሰብ እንደነበር ዲፕሎማቱ ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ሁሉንም ጉዳይና ሃላፊነት ብቻቸውን ይዘውት ስለነበር በድንገት ማለፋቸው … [Read more...] about ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!!