በዋዜማ ዝግጅቶች ሲታጀብ ከርሞ፣ ቅዳሜ የተከበረውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎችን በማሳተፍ “አንቀጽ 39 ለዘላለም ይኑር” ብሎናል። እኛም ለዚህ ውለታ ማንን ማመስገን እንዳለብን ለመጠየቅ ተገደድን። ለመልካሙና “የህዝቦች አብሮ የመኖር አለኝታ” ስለሚባለው አንቀጽ 39! የሶማሌ ብሄር አባል ናቸው። አቶ አብዱላሂ አብዱራሂም ይባላሉ። ዘጠነኛውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘው በቴሌቪዥን ብቅ አሉ “… አቅማችሁ ካደገ በኋላ፣ ልጆቻችሁን አስተምራችሁ አቅም ስታዳብሩ ለአንቀጽ 39 ትደርሱበታላችሁ…” እንዳሉዋቸው አቶ መለስን ጠቅሰው ተናገሩ። ትዝታቸው መሆኑ ነው። ወዲያው አቶ መለስ በወቅቱ እንገነጠላለን ያሉትን የሶማሌ ህዝቦች ሰብስበው ሲናገሩ ታዩ።እንዲህ አሉ “አስራ ዘጠኝ ዓመት … [Read more...] about ስለ “አንቀጽ 39” ማንን እናመስግን?
ከእሁድ እስከ እሁድ
የጉራ ፈርዳ አማሮች መሬታቸው በሃራጅ ተሸጠ ቪኦኤ ሰለባዎችን በማነጋገር እንደዘገበው የጉራ ፈርዳ ነዋሪ አማሮች መሬታቸውን እንዳያርሱ ከተከለከሉ በኋላ መሬታቸው በሃራጅ እየተሸጠባቸው እንደሆነ ይፋ አድርጓል። መሬታቸውን በህጋዊ መንገድ የግላቸው እንዳደረጉና ግብር እየከፈሉ የሚኖሩት ተበዳዮች ርምጃው የተወሰደባቸው ቅንጅትን በመምረጣቸውና ለመኢአድ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል እንደሆነ ተናግረዋል። በተደጋጋሚ መታሰራቸውንና በከሰሳቸውን የተናገሩት የጉራ ፈርዳ ነዋሪ ከእስር ከተፈቱ በኋላ “መሬታችሁን የያዛችሁት በህጋዊ መንገድ ነው” በማለት ለመኢአድ መረጃ መስጠታቸው እንደ ጥፋት እንደተወሰደባቸው አመልክተዋል። በ1997 ምርጫ ወቅት በምስጢር የድምጽ መስጫ ክፍል ውስጥ የጤና ባለሙያዎችን በማስቀመጥ ማንን እንደመረጡ መሰለላቸውንም አመልክተዋል። የሚሸጠውን መሬት የወረዳ፣ የቀበሌ፣ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ውለታ የማታውቅ ሀገር
• ያ የኮሜዲ አውራ “እብድ” ተብሎ ጎዳና ላይ “ቆሼ” ይለቅማል! • እርሱን ያፈራው ኅብረተሰብ የወደቀን ቀና ከማድረግ እንዳይቃና ይተጋል • ስለዚህ ኅብረተሰቡ እንደ ድመት የራሱን ልጆች ይበላል! ይኸውልህ ወዳጄ የተመለከትኩትን፣ የታዘብኩትን እና ያስተዋልኩትን እንደወረደ ላጫውትህ፡፡ ያ ጉምቱ የጥበብ ሰው፣ ያ የኮሜዲ-የጭውውት አውራ፣ ያ ጥበብን የተቀባው ባለትልቅ ተሰጥዖው ሰው፣ ያ ከሥነ-ሠብዕ ጥበብ ተሻግሮ የአዕዋፋትን ዝማሬ ምስጢር፣ የንፋስን ሿሿታ፣ የበር-መስኮት ሲጥሲጥታ ሳይቀር በጥበብ ሥራው ላይ አክሎ የሚከውንልህ ተዋናይ ልመንህ ታደሠ፣ ከፒያሳ ወረድ ብሎ ከሚገኘው ቢስ መብራት አደባባይ ላይ፣ እንደ ማንም ቆሼ ሲለቅም ተመለከትኩት፡፡ ልመንህን ያየ፣ እኔን-አንተን አየ፤ እኔን-አንተን ያየ ኅብረተሰቡን አየ፤ ኅብረተሰቡን ያየ-ተቋማቱን አየ ነው እያልኩህ ያለሁት … [Read more...] about ውለታ የማታውቅ ሀገር
“ዲቪ አልቀረም!! ቀረ ያለው ማን ነው?”
የዲቪ ሎተሪ እድለኛ ነው። ባገኘው እድል መሰረት አሜሪካ ለመግባት ማሟላት የሚገባውን ሁሉ እያከናወነ ይገኛል። በአካል አዲስ አበባ፣ በሃሳብ አሜሪካ ያለው ወጣት ስራውን በገዛ ፈቃዱ ተሰናብቷል። እቃውን ለሚወዳቸው ማከፋፈል ጀምሯል። አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍሮ የብስና ውቂያኖስ አልሰነጠቀም እንጂ በምኞት በየቀኑ በረራ ያደርጋል። አሜሪካ!! “ማርና ወተት የምታፈሰው አሜሪካ እንደገባሁ” እያለ ቃል የሚገባላቸው ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ ስንቅ እያዘጋጁለት ነው። ስጦታ ያበረከቱለትና ድንገት ካልተገናኘን በማለት የተሰናበቱት አሉ። እንዳኮበኮበ ያለው ወጣት ላሊበላ ሬስቶራንት ጫማ እያስጠረገ የአጭር የስልክ መልዕክት ይደርሰዋል። መልዕክቱ “ዲቪ ቀረ” የሚል ነበር። ወዲያው “ማን ነው ቀረ ያለው” ሲል መልሶ ጠየቀ። ደነገጠ። ብርክ ያዘው። ህልሙ፣ ውጥኑ ሁሉ ሲተን፣ ከእጁ ሲያመልጠው ታየው፡፡ … [Read more...] about “ዲቪ አልቀረም!! ቀረ ያለው ማን ነው?”
ኢህአዴግ ኦነግን እያሰበ አስመራ ላይ አነጣጥሯል!
ኢህአዴግ ከወትሮው በበለጠ አስመራ ላይና አስመራን ተገን ያደረጉ ተቃዋሚዎች አስመልክቶ የተንጠለጠሉ ጉዳዮችን አንድም በሰላማዊ መንገድ፣ አለያም በሃይል ለመቋጨት ፍላጎት እንዳለው ከተለያዩ ምንጮች ይሰማል። ይህንኑ መረጃ የሚያጠናክሩ መግለጫዎችና ዜናዎችም በቀጥታና በተዘዋሪ እየተደመጡ ነው። ድርድሩ የሚካሄደው ኦነግን ጨምሮ ከተለያዩ ድርጅት አመራሮች ጋር በተናጠል ስለመሆኑ ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ጠቁመዋል። ኦነግንና ኢህአዴግን ለማስማማት ከላይ ታች የሚሉት የአገር ሽማግሌዎች የሚባለውን ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ኮሚቴ የሚመሩት ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅን ጨምሮ የቀድሞው የኦነግ አመራር አባቢያ አባጆቢር፣ የኢትዮጵያ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የነበሩት ቄስ ኢተፋ ጎበናና ከሳቸው ጋር የሚሰሩት ኮሚቴዎች፣ በአሜሪካ የወንጌላዊት ሉትራን ቤ/ክ የአፍሪካ ብሔራዊ … [Read more...] about ኢህአዴግ ኦነግን እያሰበ አስመራ ላይ አነጣጥሯል!
ሉዓላዊነትና መብት
ሶርያ አሮጌ አገር ነው፤ ታሪኩ ረጅም ነው፤ ከሶርያ ጋር ሲወዳደር አሜሪካ ሕጻን ነው፤ ነገር ግን ለብዙ ወራት በሶርያ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነትና በቅርቡ በአሜሪካ የተደረገውን ምርጫ ስንመለከትና ስናነጻጽራቸው፣ የሶርያ ሕዝብ እርስበርሱ ሲጨራረስ አሜሪካኖች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሐዝቡ ድምጹን ሰጥቶ ምርጫው ተጠናቅቆ በሰላም የሥልጣን ርክክብ ተደረገ፤ ዕድሜ የመብሰል ምልክት ላይሆን እንደሚችልና ፍሬ-አልባ እንደሚሆን መረዳት እንችላለን፤ ከርሞ ጥጃ እየሆኑ ዕድሜ መቁጠር፤ በሶርያ የሚካሄደው ጦርነት ግን አንድ ሰው፣ በሺር አላሳድ፣ እስቲሞት ድረስ መጋደሉና አገር መፈራረሱ ይቀጥላል፤ ዓለምም፣ የተባበሩት መንግሥታትም፣ የአረብ ማኅበርም ሁሉም ከንፈሩን እየመጠጠ የሶርያን ሕዝብ ስቃይ ያያል፤ የፍልስጥኤማውያንንም ስቃይ እንዲሁ፡፡ ለምን አንዲህ ይሆናል? ምክንያቱ ሉዓላዊነት የሚባል ነገር … [Read more...] about ሉዓላዊነትና መብት
ማነው ተጠያቂው?
ማነው ተጠያቂው? ለኅሊናችን፣ ለትወልድ፣ ለሀገር ሰው - ስለ ሰው ብሎ፣ እስቲ ሰው ይናገር፤ በዚች ዓለምችን፣ መለኪያው ምንድን ነው ከገዥና ተገዥ፣ ተጠያቂው ማነው? ጥቂቶች በቡድን፣ ብዙሀኑን ገፍተው የሰውን ስብዕና፣ ማንነቱን ገፈው፤ በጥይትም ይሁን፣ በታንክ ደፍጥጠው እነሱ እንዲገዙ … ማነው የፈቀደው? ሰለኅሊናችን፣ ስለ እውነት በሀቅ ሰው - ለራሱ ብሎ፣ ‘ራሱን ይጠይቅ። ብዙ በልተው - ብዙ ‘ለማበት’ ብዙ ተግተው - ብዙ ለመሽናት፤ …ለጮማ - ቅርናታቸው… …ለውስኪ - ቅርሻታቸው… …ለእኩይ - ምግባራቸው፤… እንደ አንድ ሰው ሆነው፣ሲቆሙ በአንድነት ለክቡር አላማ፣ ሌላው ሲሆን “ኩበት’’፤ እነሱ ምን ያ’ርጉት?... ምንስ ያቅርቡለት…? ሰው ነኝ የሚል ዜጋ፣ ከተነዳ እንደ ከብት። ሀገርን አፍርሰው፣ ትውልደን አጥፈተው እንድ ቅርጫ ስጋ፣ ህዝብንም … [Read more...] about ማነው ተጠያቂው?
በሳቅ ፍርስ አሉ
በሳቅ ፍርስ አሉ አገራቸውን በመክዳት ወገናቸውን ለመጉዳት ያልነበረ ሕግ ጥሰው በነስብሐት ነጋ – በነ መለስ ተከሰው ሽብርተኛ ሲባሉ ‘በሳቅ ፍርስ አሉ’ አሉ፡፡ ሽ-ሽ-ት በሚል ርዕስ ላቀረብነው የአብዲ ሰኢድ ግጥም ግሩም የሆነ ምላሽ በመስጠት ጨዋታው ሞቅ ደመቅ ላደረጋችሁት dawit፣ ሽማግሌው፣ በለው፣ yeKanadaw kebede እና ዱባለ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ በዚህ የግጥም ጨዋታችን የዘወትር ተሳታፊ የሆኑት የካናዳው ከበደ (yeKanadaw kebede) “ለሚቀጥለው የግጥም ጨዋታ አድርጓት” ብለው “በሳቅ ፍርስ አሉ” በሚል ርዕስ “አሸባሪ” በመባል ተከስሰው በእስር የሚማቅቁት ወገኖቻችንን በተመለከተ የላኩልንን ግጥም ነው ላሁኑ ጨዋታችን ያቀረብነው፡፡ እስካሁን ግጥም ስናቀርብ የነበረው ከሌሎች ቦታዎች ነበር አሁን ግን የካናዳው ከበደ የራሳቸውን … [Read more...] about በሳቅ ፍርስ አሉ
የጎልጉል ቅምሻ
ስኳር ለስኳር በሽታ ያጋልጣል “ጣመኝ ድገመኝ” የምንላቸው ዓይነት ብስኩቶች፣ የቸኮሌት ውጤቶች፣ አይስክሬም፣ ብርታት ሰጪ መጠጦች፣ … በከፍተኛ ሁኔታ ለስኳር በሽታ እንደሚያጋልጡ ሳይንስ ደርሼበታለሁ ይለናል፡፡ በእነዚህ የምግብ ውጤቶች ውስጥ የሚገኘው የበቆሎ ስኳር (fructose corn syrup - HFCS) ምግቦቹን ለማጣፈጥ የሚጨመር በመሆኑ ይህንን ተመጋቢ የሆኑ 20በመቶ ለስኳር በሽታ መጋለጣቸው የማይቀር ነው ይላል ውጤቱ፡፡ ከምዕራባውያን አገራት መካከል አሜሪካ በጣፋጩ አወሳሰድ ቀዳሚውን ስትይዝ በአማካይ አንድ ሰው በዓመት 24.78ኪሎ የበቆሎውን ስኳር በተለያዩ ምግቦች አማካኝነት ወደ ሆዱ ይጭናል፡፡ አንድ ካናዳዊ በዓመት 9.13ኪሎ ሲጭን አንድ ጣሊያናዊ ወይም እንግሊዛዊ ከግማሽ ኪሎ በታች እንደሆነ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ግብጻዊያን 1.6ኪሎ በአማካይ እንደሚጭኑ ያስረዳው … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!
ከአቶ መለስ መለየት በኋላ ወደ አደባባይ የወጡት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ እንደሚችሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ግምታቸውን ሰጡ። አገር ቤት ተቀምጠው በኢህአዴግ ላይ የሰላ ትችት በማሰማት ቀዳሚውን ስፍራ የያዙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህርና እንደ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የአደባባይ ምሁር በመባል የሚታወቁት ዶ/ር ዳኛቸው ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይፋ እንዳደረጉት ለግምታቸው ምክንያት ሰጥተዋል። አቶ መለስ በህይወት እያሉ የስልጣን ክፍፍሉን በሶስት ለመመደብ መታሰቡን ሰምተው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሃሳቡ ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ አመልክተዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ ቀደም እንደነበረው ስልጣኑ በአንድ ሰው ላይ ተጭኖ ሊቀጥል እንደማይችል … [Read more...] about ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!