• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሽብርተኛ ከሳሹ ሽብርተኛው የወያኔ መንግስት

March 8, 2013 02:11 am by Editor Leave a Comment

የመጨረሻ ግባቸው የእስልምናን መንግስት ማቆም ነው ብሎ የወያኔ አስተዳደር ያቀረበውን የተቀነባበረ ፊልም ( ጃሃዳዊ ሐረካ) በመደነቅ አየሁት። ወያኔ ማለቴ እስካሁን እራሱን ነጣ አውጪ እያለ የሚጠራው የትግራይ ቡድን ኢሃድግ የሚል ማወናበጃ ስም በመረከቡ ነው፡

የተሰጠው መረጃ ውሸት ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ባልችልም የመረጃ አቅራቢው ውሸታምነት በመረጃ በማስደገፍ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

መረጃቸውን በቴሌቭዥን የሚያቀርቡት አማን አሰፋ፣ አቡበከር አህመድ፣ ከሚል ሸምሱ፣ያሲን ኑሩ፣ ሙፍቲ አህመድ … የሚዘረዝሩት ታሪክ ወያኔ ራሱ ጥፎ ያቀረበላቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ከዚህ በፊት እነ ብርትኳን ሚደቅሳ፣ ፐርፌሰር መስፍን፤ ዶ/ር ያዕቆብ… ታላላቅ ልናከብራቸው የሚገቡ ጋዜጠኞች እንደነ እስክንድር ነጋ የመሳሰሉ ሁሉ በሽብርተኛነት በመታሰራቸው፤ ወያኔ የሚቃወመውን ሁሉ ያለህግ ለማጥፋት ሲያስብ ይህንን ውንጀላ መጠቀም ከጀመረ ውሎ በማደሩ ይህኛውም ውንጀላ ከዚህ ያልተለየ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም፡ ከሳሽ ፈራጅና ቀጪም ወያኔ ራሱ ነው አቀነባባሪውም የብሄራዊ መረጃ አገልግሎት ነው። በአገሪቱ ውስጥም የሕግ የበላይነት ባለመኖሩ ሁኔታውን መርምሮ ለሕዝብ ማቅረብም አይቻልም። የጸረ ሽብርተኛ ሕግ በማለት ወያኔ ከወነጀላቸው ጋር (ያለምንምንም መረጃ) ግኑኝነት ማድረግ ከ 10 እስከ 15 ዓመት ያስቀጣል ይላል።

ያወጣውን ሕገ መንግስት በመናድ ተወዳዳሪ የሌለው ወያኔ፤ በራሱ ሕገመንግስትና ባለራዕዩ መሪ ደጋግመው ፊልሙም ላይ እንዳስረዱት መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም እየተባለ ቢደሰኩርም በክርስቲያኑም ሆነ በእስልምናው ሃይማኖት ገብተው ሲፈተፍቱ እናያለን።

በክርስትናው ሃይማኖት ጳጳሱን ከአገር አባረው የራሳቸው ቢሾሙም ተሿሚው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ሌላ ጳጳስ ለወያኔ የሚያጎበድድ እስኪገኝ ሽር ጉድ እየተባለ ነው፡ “ አባይ ጸሐዬም የቀድሞውን ጳጳስ ማምጣት መንግስቱን እንደማምጣት ነው” ይህ አባባል ከመንግስት ተወካይ የተሰጠ ነው!! ሌላው የወያኔ ቁንጮ ሽማግሌው ስብሃት ነጋ “ የአማራና የክርስትያን አገዛዝ ቀብረነዋል ብሏል” እነዚህን መረጃዎች ይዘን መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ማለት የዋህነት ነው።

የአዲሱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የጳጳስ ምርጫ ካጤነው ስለመንግስት ያለንን ግንዛቤ ያጠናክርልናል።

መንግስት ሰለሚሰራቸው የፊልም መረጃዎች ለመጥቀስ

በሐውዜን (ረቡዕ june 1988) እንጀምር ፤ ይህ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ወያኔ ለፖለቲካ ትርፍ ሲል ወገኔ የሚላቸውን የትግራይን ሕዝቦች፤ ከከተማ እንዳይወጡ መውጫውን ዘግቶ፤ ለደርግ ቀኑን አስታውቆ ለፊልም ቀረጻ ያዘጋጃቸውን ፊልም ቀራጮች ቁልፍ ቦታ ካስያዘ በሗላ የደረሰውን የቦምብ ድብደባ በዕለቱ ከሱዳን እንዲተላለፍ አድርጓል።

ሁለተኛው ድራማ አኬልዳማ የተሰኘው ነው (2011)፡ ( አኬልዳማ በደም የተበከለ ምድር ማለት ነው) የቃሉን መሰረት ወንጌል ላይ የሐዋርያት ስራና ማቴዎስ ወንጌል ላይ ይመልከቱ፡ ወያኔ ግን ይህንን ፊልም የሰራው አንዳንድ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን እስር ለመክተትና ህገወጥ ድርጊቱን ሕጋዊ ልብስ ለማልበስ ነው።-….የኦነግ የሽብር ቅጣት በበደኖ 1984፣ በሐረር የወያኔ አካል በነበረው የኦሮሞ ተገንጣይ ቡድን አማራው ላይ ጭፍጨፋ ሲያካሄድ፣ እርጉዝ ሴቶች ከነሕይወታቸው ሆዳቸው እየተቀደደ ሽሉ ሲወጣና ከዚያም በሗላ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ መመሪያ ሲሰጥና ፊልም ሲያነሳ ከርሞ፤ ያንኑ ፊልም ከዓመታት በሓላ አሸባሪዎች እንዲህ አደረጉ ብሎ አሳይቶናል። ከዚህ ትያትር በሗላ እነ አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ አቶ ስለሺ ሃጎስ….በሽብርተኝነት ተፈርጀዋል። አቶ ዲማ ነገኦም የግዜው የኦነግ መሪ ስለበደኖ ጉዳይ ገለልተኛ ምርመራ እንዳይካሄድ ወያኔ መከልከሉን አሳውቀዋል። ( ሽግግር ምክር ቤት ጉዳዩ ተነስቶ ኦነግ እንዲጣራ ቢጠይቅም ጉዳዩ እንዳይጣራ ወያኔ ከለከለ ይላሉ) አርሲ እስላሞች ክርስታያኖችን ጨፈጨፉ ብሎ በቀረበው ዜና የእስላም ሽርጥ ያሸረጡ የወያኔ ወታደሮች ክርስትኖችን እያሳደዱ ሲገድሉ ታይተዋል ከሞቱትም ላይ የወያኔ የፖሊስ መታወቂያ ከኪሳቸው ተገኝቷል፡

ወያኔ ከ424 በላይ የተማሩ አኙዋኮችን መሬታችን እየተዘረፈ ለውጭ ሰዎች መቸብቸብ የለበትም ስለ አሉ ለአረብና ለሕንድ መሬቱን ለመቸብቸብ አይመቹኝም ሌላውንም ያስነሱብናል በሚል ያደረገባቸውን ጭፍጨፋ መረጃው በጄኖሳይድ ዎች እጅ ይገኛል፤ ይህን ያህል ሽብር የፈጠረ ሽብርተኛ ከወያኔ በስተቀር ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ ቡድን የለም።

በማንኛውም መመዘኛ በመንግስት ደረጃ ስልጣን ይዞ ሰላማዊ ሕዝብን እንደ እንስሳ ካልተገዛችሁልኝ የሚል ሽብርተኛ መንግሰት፤ የራሱን ወገን አንዱን ጎሳ ከሌላው ጎሳ በፖሊሲ የሚያጋጭ፣ ያ ሳይሳካ ሲቀር አሁን ደግሞ በሃይማኖት ሊያተራምስ የተቀመጠ መንግሰት ነው፤ ለስልጣኑ እስከተመቸው ድረስ ማንኛውንም ወንጀል ከመስራት ወደሗላ የሚል መንግስትም አይደለም።

መልዕክቴ መንግስት በሚያሰራጨው ከአሉባልታ ያልተሻለ መርዘኛ ዜና እርስ በርስ ልንጠራጠር አይገባም። መታገል ያለብን ይህንን ሽብርተኛ መንግስት ለማስወገድ ስለሆነ፤ በዘር፣በጎሳ በሃይማኖት…ልንከፋፈል አይገባም፤ ኢትዮጵያችን ሁላችንንም ልታስተናግድ የምትችልና ስታስተናግድም የኖረጭ አገር ናት።

ታዛቢው

ከሆላንድ

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule