• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ

March 6, 2013 06:56 am by Editor 3 Comments

እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን መነሻውን  ”ሃውፕትቫኸ” /Hauptwache/ ከሚባለው የከተማው ክፍል በማድረግ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ባንድራ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል።

– ”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!”

– ”የፕሬስ ነጻነት ይከበር!”

– ”ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብት ይከበር!”

– ”ጅሃዳዊ ሐረካት የወያኔ ፈጠራ ነው!”

– ”የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!”

–  ”በአለም ዙሪያ ያሉ የወያኔ ቆንስላ ፅ/ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክሉም!”

– ”የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ያቁም!”

– ”ከአባይ በፊት ሙስናና ዘረኝነት ይገደብ!” የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን

ከአንድ ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ተሰላፊው የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሲደርስ በከፍተኛ ጩኸት እና ፉጨት ተቃውሞውን ማሰማት ችሏል። በዚህም የተደናገጡት የወያኔ ቆንስላ ሠራተኞች የህንፃውን መስኮት በፍጥነት በመዝጋት ከፊሎቹ ህንፃውን እየለቀቁ የወጡ ሲሆን ቁጥራቸው ከአራት የማይበልጥ የቆንስላው ራተኞችም ከውስጥ በመሆን ሠልፈኞችን ለማስፈራራት በሚመስል መልኩ ፎቶ ሲያነሱ ተስተውለዋል። ሰልፈኛውም ተቃውሞውን ይበልጥ በማጠናከር ለአንድ ሰዓት ያህል መፈክሮችን በማሰማት፣ የሀገር ፍቅር ዜማዎችን በማዜም እንዲሁም ይህንን ሰልፍ በቅርብ ርቀት ይመለከቱ ለነበሩ የሀገሬው ዜጎች በጀርመን፣በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን በማደል የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እየደረሰበት ያለውን ግፍና መከራ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ አድርገዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተወካይ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች በአካል ተገኝተው አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎም ከኔዘርላንድ የላከው ደብዳቤ ተነቧል።

ይህ ከሶስት ሰዓት በላይ የፈጀው የተቃውሞ ሠልፍም በሠላምና በታላቅ ድምቀት መጠናቀቅ ችሏል።

By: Dawit Fanta /Engineer/

dawitfanta@yahoo.com

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Alem gebru says

    March 6, 2013 07:18 am at 7:18 am

    Yemaneam lekeakeam shentbeate terge hulea tesbsbeo bechue yeatme aydrsem…

    Reply
  2. zeru Alehubel says

    March 7, 2013 07:15 pm at 7:15 pm

    Alem you mustnot forget that your government is begging money from those ”shentbeate terge hulea” for Nile Dam. Lol!!! Alem you must be a b####

    Reply
  3. yemi taye says

    March 7, 2013 07:24 pm at 7:24 pm

    Poor Alem! one day you will face your trial in front of court of justice!!! Now you are running out of time and justice will be for all, not only for minorities!!!!!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule