ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱዛን ራይስ ወደ ኬኒያ እና ኢትዮጵያ ስለሚደረገው ጉብኝት መግለጫና ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሸ ሰጥተው ነበር፡፡ የጉብኝት ዝርዝር መርሃ ግብር በማስረዳት ንግግር የጀመሩት ራይስ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢህአዴ ሹማምንትና ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች እንዲሁም ከአህጉሪቱ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አስረድተዋል፡፡ ከጠያቂ ጋዜጠኞች መካከል ተራው የደረሰው አይዛክ አምባሳደር ራይስን ስለ ጉዞው የጸጽታና ደኅንነት ጉዳይ ከጠየቀ በኋላ ከዚህ በፊት ሌላኛዋ ጋዜጠኛ (ክሪስቲ) ያነሳችውን ሃሳብ በማጠናከር “ፕሬዚዳንት (ኦባማ) የኢትዮጵያና የኬኒያ መሪዎች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ አድርገው ይቆጥሯቸዋል?” በማለት ጠየቀ፡፡ ሱዛን ራይስ ማስረዳት ጀመሩ የጸጥታውና የደኅንነቱ … [Read more...] about የሱዛን ሳቅ
የነጻነት ትግል መጀመሪያው የቀና ልቦና ባለቤትነት ነው
አፄ ቴዎድሮስ ያሠሩትን መድፍ (ሴባስቶፖል) ወደ ተራራው አናት ለማውጣት እየተጣደፉ ነው። እሳቸው ጭምር በጉልበት እያገዙ ሲገፋ ውለው ረፋዱ ላይ ከሰፈር ደርሰው ሲመለሱ አንዱ መድፉን ከሚገፉት ተለይቶ ወደ ሰፈር ሲወርድ መንገድ ያገኙትና ቆም ብለው ወዴት ነው ሥራ ትተህ የምትሄድ? ብለው ይጠይቁታል። “ወደ ሰፈር፣ ወደ ሰፈር እየወረድኩ ነው ንጉሥ ሆይ!” “ምነው ደህናም እማይደለህ?” “ጣቴን ድንጋይ ቀርጥፎኝ ነው ንጉሥ ሆይ!”፤ ትንሽዋን ጣቱን በጨርቅ ነገር ጠቅሎ አንከርፏል። “ና እስቲ! ቀረብ በልና የተጎዳኸውን አሳየኝ”፤ ሰውየው ንጉሡ ጋ ቀርቦ የቋጠራትን ጨርቅ ፈቶ ጣቱን ሲያሳይ ንጉሡ ትንሽ ጭረት ቢጤ ብቻ ያያሉ። “ሌላ ቦታም ተጎተሃል እንዴ?” “የለም! ይሄው ብቻ ነው።” “እና! ይቺን ቁስል ናት! ብለህ ነው ሥራ ትተህ የምትሄድ?” “ይችኑስ ቢሆን በማን ልላካት … [Read more...] about የነጻነት ትግል መጀመሪያው የቀና ልቦና ባለቤትነት ነው
ኦባማ ባዲሳባ፣ የሚጠበቁ ምጸቶች
(ሀ) ፕሬዚደንት ኦባማ ነገ እሑድ አዲስ አበባ ይገባሉ (ከመግባታቸው በፊት የተጻፈ ነው)። አንዱን ቀን - እንደደንቡ ሰኞ - በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ራት እንደሚኖር ይጠበቃል። የታሪክ ምጸቱን ከዚያ ጀምረን እናደንቃለን። ራቱ ምኒልክ በሠሩት፣ ዛሬም በስማቸው በሚጠራው ቤተ መንግሥት ይሆናልና፤ መቼም ለራት ሼራተን፣ አለዚያም መቀሌ - አዳማ - ባህርዳር - አዋሳ - አሳይታ--- አይወስዷቸውም ብዬ ነው። ራቱንም ቦታውንም መቃወሜ አይደለም። አገር የመሥራት ሙከራ ቀልድ አይደለም፣ የሙከራው ሒደትና ውጤት ምንም ይሁን የሞካሪዎቹ ስም ድንገት ተንኖ አይጠፋምና እንዲህ ያለውን ታሪካዊ ምጸት ይጋብዘናል ለማለት ነው። (ኦባማ ከጋዜጣዊ መግለጫ በስተቀር የፖሊሲና የፖለቲካ ጉዳዮችን በስፋት የሚናገርበት መድረክ ስለመኖሩ አላወቅንም። ከኖረ ግን፣ አድዋን ማንሳቱ ሳይታለም የተፈታ ነው፣ ምኒልክንም … [Read more...] about ኦባማ ባዲሳባ፣ የሚጠበቁ ምጸቶች
ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ
ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ውጤት ቢሰጥ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው በንግግር (በወሬ) ደረጃ A በተግባር ግን D እንደሚሰጧቸው ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡ አፍሪካውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ምዕራባውያን ዕንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ አስረዱ፡፡ በአሜሪካ ድምጽ የStraight Talk Africa አዘጋጅ ሻካ ሳሊ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን የአፍሪካ ጉብኝት በተመለከተ ከሁለት ቀናት በፊት ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ሦስት አፍሪካውያንን ተጋብዘው ነበር፡፡ ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ የሴራሊዮኑ ፕሮፌሰር አብዱል ካሪም ባንጉራ፣ የአፍሪካ ስደተኞች ስብስብ ኃላፊ ጋናዊው ኒ አኩቴ እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር ኢትዮጵያዊው ኦባንግ ሜቶ ነበሩ፡፡ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው ለፕሬዚዳንቱ ምን ውጤት ትሰጣላችሁ በማለት ሻካ ላቀረበው ጥያቄ ዶ/ር አብዱል D … [Read more...] about ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ
ዝዋይ እስር ቤት
ሐምሌ 16/2007 ዓ.ም. ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየውን ጋዜጠኛ፣ ተመስገን ደሳለኝን (ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ዝምድና የለውም፤) ለመጠየቅ ወደዝዋይ ወህኔ ቤት ሄጄ ነበር፤ የወሕኒ ቤቱ ባለቤቶች ማረሚያ ቤት ይሉታል፤ ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ እንዴት እንደሚያጎብጡት ላሳያችሁ፤-- 1. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሰዎች በመሆናቸው ሰብአዊ ደኅንነታቸውና ክብራቸው ሁልጊዜም እንዲጠበቅላቸው ያስፈልጋል፡፡ 2. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሁሉ ከመሰቃየትና ከመጉላላት በጸዳ አያያዝ እንዲጠበቁ ይደነግጋል፤ 3. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ … [Read more...] about ዝዋይ እስር ቤት
መቶ ብር ከየት ወዴት?
ትናንት ኣመሻሽ ላይ፤ ከYohanes Molla ጋር ተቀጣጥረን ተገናኘን ፡፡ካልዲስ ገብተን እኔ ኣንድ ፍንጃል ቡና ሳዝዝ ፤ ዮሀንስ ሲያቀብጠው ኣንድ ቡና እና የባራክ ኦባማን ጆሮ የሚያህል ቦምቦሊኖ ኣዘዘ፡፡ በመጨረሻ ኣስተናጋጂቱ የእዳችንን ደረሰኝ ኣምጥታ ጠረጴዛው መሀል ላይ ኣኖረችው ፡፡እሱ እኔ እስክከፍል ሲጠብቅ እኔ እሱ ይከፍላል ብየ ስጠብቅ ካብ ለካብ እየተያየን በጣም እረጅም ጊዜ ተጎለትን፡፡ በመካከሉ የኢትዮጵያን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ርእሰ ጉዳይ ጨርሰን "ፌንጣ ስንት እግር ኣላት? ስድስት ነው ኣራት?" በሚል ጉንጭ ኣልፋ ክርክር ተጠመድን፡፡ ወሬ ኣልቆብን ካጠገባችን ከተቀመጡ ተስተናጋጆች ወሬ እየተበደርን ስናወራ ቆየን፡፡ በመጨረሻ ካፌው ጭርር ብሎ ኣስተናጋጆች እንድንወጣላቸው እግራችን ስር መጥረጊያ ኣስገብተው ይጠርጉ ጀመር፡፡ ድንገት በብሄረሰቦች ላይ የሚነገረው ቀልድ … [Read more...] about መቶ ብር ከየት ወዴት?
ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
ለረጅም አመታት፣ ለብዙ ዘመናት፣ ፓርቲ ሲጠልዘኝ፣ መንግስት ሲረግጠኝ፣ ፖሊስ ሲነርተኝ፣ ሕጉ ሳይደግፈኝ፣ ዳኛው ቢፈርድብኝ፣ በቡድን ተካፍለው፣ በስም ተሸንሽነው፣ የሚጠልዟት ኳስ፣ የሚነርቷት ኳስ፣ ምትለጋዋ ኳስ፣ እኔ ራሴን መስላኝ፣ ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ። … [Read more...] about ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ . . .
"…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው። ጊዜው ተቀይሯል። ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም። ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ … " ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የተናገሩት የአስመራ ጉዟቸው ከመሰማቱ ጥቂት ቀናት በፊት ነበር። ንግግሩ ለብዙዎች ግርታ መፍጠሩ አልቀረም። ከቀናት በኋላ የኤርትራን ምድር ሲረግጡ "ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ..." ማለታቸው ግልጽ ሆነ። ከምርጫ 97 በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በፖለቲካ ስብእናቸው የሚታወቁት ለሰላማዊ ትግል ባላቸው የከረረ አቋም ነበር። በእስር ቤት ሆነው በጻፉት "የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፤ ..." መጽሐፋቸው ሰላማዊ ትግል ያለውን የሞራል፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ምሳሌ እያስቀመጡ ዘርዝረዋል። ለዚህም ነበር ከሰላማዊ ትግል ወጥተው "ሁለገብ … [Read more...] about የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ . . .
ብርሃኑ ነጋ “… ዱር ወጡ …”
* የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ብሏል ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሃደው የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የፓርቲው የአመራር አባላት የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ታጣቂዎቻቸው ወደሚንቀሣቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለው መሄዳቸውን የአመራር አባላቱ አስታወቁ፡፡ ብርሃኑ አስመራ መግባታቸው ከተሰማ በኋላ የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ማለቱና ከአገር ውስጥ ግምባሩን ለመቀላቀል የሚፈልገው ሕዝብ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ቁጥራቸው ይፋ ያልተደረገ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአመራር አባላትን ይዘው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ኤርትራ ያመሩት ሌሎች አማራጮችን ጨምሮ በብረት ትግልና በሕዝባዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ገዥ ፓርቲ ለማስወገድ መሆኑን የአመራር አባላቱ ይናገራሉ፡፡ “ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ጓዶቻቸው ትግል ወደሚካሄድባቸው አባባቢዎች ያመራሉ” ሲሉ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል ዶ/ር ታደሰ ብሩ … [Read more...] about ብርሃኑ ነጋ “… ዱር ወጡ …”
“ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”
በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት ላይ ኅብረተሰቡ የሚያሰማው እሮሮ ኤሌክትሪኩ መጥፋቱ ብቻ አይደለም፡፡ መብራቱ ሄዶ ሲመጣ የሚያደርሰው ጥፋት የትየለሌ ነው፡፡ የኤሌክትሪኩ ኃይል መጠን ከመደበኛው ውጭ ከፍና ዝቅ ሲል የሚያደርሰው ጥፋት ቤት ይቁጠረው፡፡ ማቀዝቀዣው፣ ቴሌቪዥኑ፣ አምፖሉ፣ ልዩ ልዩ "ቻርጀሮች" የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ተቃጠሉብን የሚል የሕዝብ እሮሮ በየጊዜው ይሰማል፡፡ የሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፈጣን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አገልግሎት የማይሰጠውን "905" ላይ ደውላችሁ አስመዝግቡ ከማለት ያለፈ መልስ የለውም፡፡ "የኤሌክትሪክ ምሰሶው ሊወድቅብን ነው፣ ዘሟል፣ ኧረ ድረሱልን" እያሉ ለሚወተውቱም ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዳልተቻለም ማስረጃ ከሚሆኑ ትዕይንቶች (በፎቶዎቹ የሚታዩት) መካከል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 እንደራሴ አካባቢ ያሉ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች … [Read more...] about “ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”










