• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዝዋይ እስር ቤት

July 24, 2015 09:24 am by Editor 1 Comment

ሐምሌ 16/2007 ዓ.ም. ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየውን ጋዜጠኛ፣ ተመስገን ደሳለኝን (ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ዝምድና የለውም፤) ለመጠየቅ ወደዝዋይ ወህኔ ቤት ሄጄ ነበር፤ የወሕኒ ቤቱ ባለቤቶች ማረሚያ ቤት ይሉታል፤ ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ እንዴት እንደሚያጎብጡት ላሳያችሁ፤–

1. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሰዎች በመሆናቸው ሰብአዊ ደኅንነታቸውና ክብራቸው ሁልጊዜም እንዲጠበቅላቸው ያስፈልጋል፡፡

2. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሁሉ ከመሰቃየትና ከመጉላላት በጸዳ አያያዝ እንዲጠበቁ ይደነግጋል፤

3. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ አንድ እስረኛ ዘመዶቹና ወዳጆቹ ከሚኖሩበት በጣም ርቆ አይታሰርም፤

4. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ የታመመ እስረኛ ሙሉ ህክምናና አስፈላጊውን መድኃኒት ሁሉ ማግኘት አለበት፤

5. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች በአእምሮና በመንፈስ የሚያድጉበት ትምህርትን የማግኘት፣ መጻሕፍትን የማግኘት መብቶች አሏቸው፤

6. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ማንኛውም እስረኛ በእምነቱ መሠረት አምልኮቱን የመፈጸምና የሃይማኖቱን መጻሕፍት የማንበብ መብት አለው፤

7. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ማንኛውም እስረኛ ዘመዶቹና ወዳጆቹ እንዲጎበኙት መብት አለው፤

8. እስረኞች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ከወህኒ ቤት ሲወጡ ትክክለኛ የማኅበረሰቡ አባሎች ሆነው እየሠሩ ለማኅበረሰቡ እድገት ድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ማሰናዳት ያስፈልጋል፤

በዝዋይ እንዳየነውና እንደተነገርነው የእስረኞች ሁኔታ በጣም የሚያሳዝንና ከላይ የተዘረዘሩትን የሰብአዊ መብቶች የሚጥስ ነው፤ ጤንነት ዋና ነገር ነውና በሱ እንጀምር፤ ተመስገን ደሳለኝ ወንጀል የተባለበት የፖሊቲካም ሆነ የማኅበረሰብ እምነቱን እያፍረጠረጠ በመጻፉ ነው፤ (በ1992 ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባደረግሁት ንግግር ‹‹አትፍሩ›› ብለሃል ተብዬ ተከስሼ ነበር!) እንዲያውም ክሱን አስቂኝ የሚያደርገው መንግሥትን ነቅፈሃል የሚል መሆኑ ነው፤ ሦስት ዓመት እስራት ተፈረደበት፤ ይግባኝ ተከለከለ፤ አሁን ከታሰረ አሥር ወራት ሆኑት፤ ተመስገን በጣም ከታመመ ጥቂት ቆየ፤ አንደኛ አንዱ ጆሮው በጭራሽ አይሰማም፤ ሁለተኛ ከባድ የወገብ ሕመም ስላለበት መተኛትና መቀጥም በጭንቅ ሆኖበታል፤ ሆኖም አሳሪዎቹ ወደሀኪም ቤት ሊወስዱት ፈቃደኛ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ መድኃኒት ከውጭ ሲመጣለት ይከለክላሉ፤ እኔም የወገብ ሕመም ስላለብኝ የወገብ ሕመሙን የሚያቀልለትን መድኃኒት ወስጄለት ነበር፤ አንድ አሥር አለቃ መድኃኒቱን አየና ከለከለ፤ መልሼ ይዤው መጣሁ፤ እንዲህ ያለውን ውሳኔ የሚያደርጉ ሁሉ ወያኔዎች ናቸው፡፡

ከተመስገን ጋር ትንሽ ጊዜ ቆይተን በዚያው በዝዋይ የታሰሩ ሌሎች ጋዜጠኞችን ለመጠየቅ መጀመሪያ ተፈቅዶልን ስለነበረ ወደዚያ ስናመራ አንድ ሹም መሳይ መጥቶ ወታደሮቹን ለብቻ ለብቻ በስም እየጠራ በመንሾካሾክ ትእዛዝ ይሰጣል፤ እየተንሾካሾከ ለአንዱ ትእዛዝ ሰጥቶ ሌሎቹን እንዳናይ ከለከለንና ተመለስን፤ ምክንያቱን ብንጠይቅ በአንድ ጊዜ መጠየቅ የሚቻለው አንድ እስረኛ ብቻ ነው ተባልን፤ ቅን መንፈስ ለጎደለውና ለሙስና ለተጋለጠ አሠራር ጥሩ ምሳሌ ነው፤ በመንሾካሾክ የሚሰጠውም ትእዛዝ ዓላማው ያው ይመስላል፤ ወያኔ በሰዎች ላይ እንዲህ ያለ ጭካኔ ማሳየት የሚፈልገው ለምንድን ነው?

በዝዋይ እስር ቤት ትምህርትም እንደመድኃኒት የተጠላ ነገር ነው፤ ለተመስገንም ሆነ ለሌሎች መጻሕፍት አይገቡላቸውም፤ ለምን? ብዬ ስጠይቅ አንዱ ጠባቂ ‹‹ለእውቀት የሚሆን መጽሐፍ ይገባል፤›› አለኝ፤ የእውቀትን ፍቺ ለመጠየቅ ስሞክር ቶሎ ግራ መጋባቱን አየሁና ተውሁት፤ እሱም እንዳያውቅ ስለሚፈልጉ፣ አለቆቹ የእውቀትን ፍቺ ጠበብና ቀለል አድርገው አስተምረውታል፤ ሎሌ ትእዛዝን በሹክሹክታ እየተቀበለ ማስፈጸም እንጂ፣ እውቀት አያስፈልገውም፤ እዚህ ላይ ምናልባት በደርግ ጊዜ በእስር ቤቶች የነበረውን የትምህርት መስፋፋት ማንሣት ይጠቅም ይሆናል፤ በደርግ ዘመን ብዙ የተማሩ ሰዎች ታስረው ስለነበረ እረስበርሳቸው እየተማማሩ አንዳንድ ሰዎች ጀርመንኛና ፈረንሳይና ቋንቋዎች፣ ግእዝና ታሪክ እየተማሩ ወጥተዋል፤ በተለይ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወህኒ ቤቶች አንደኛ ሲወጡ እንደነበረ አስታውሳለሁ፤ ዛሬ በወህኒ ቤቶች ትምህርት ክልክል ነው፤ በቃሊቲ ሁለት የትምህርት ሙከራዎች ከሽፈውብናል፤ አንድ ጊዜ ኦሮምኛ ለመማር የፈለግን ሰዎች ተሰባስበን ተከልክለናል፤ ሕግ ለመማርም ጀምረን ታግደናል፤ እንዲሁም ጂምናስቲክ በቡድን መሥራት ክልክል ነበር፤ ማናቸውም እውቀት አደገኛ ነው! ታዲያ ማረሚያ ቤት የሚሉት ማንን ለማታለል ነው? ማረሚያ ቤት እንዲሆን በመጀመሪያ አሳሪዎቹ መታረም አለባቸው!

እንደተመስገን ደሳለኝ፣ እንደአብርሃ ደስታ፣ እንደእስክንድር ነጋ፣ ከዞን ዘጠኝም በፈቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ወበላ፣ አጥናፉ ብርሃኔ ገና አልተለቀቁም፤ በተጨማሪም ከእስልምና በኩል የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባሎች ዛሬም እንደታሰሩ ነው፤ የመፍትሔ አፈላላጊዎችን ማሰር ነገሩም ግራ ነው፡፡

በመጨረሻም መነሣት ያለበት አንድ አደገኛ አዝማሚያ አለ፤ ፖሊስ የሚባለው ፍርድ ቤት ከሚባለው ጋር ያለው ግንኙነት ሕግ የሚባለውን ከጨዋታ ውጭ አድርጎታል፤ ፍርድ ቤት የሚባለው እስረኛ እንዲፈታ ፖሊስ የሚባለውን ሲያዝ እንደማይፈጸም በተደጋጋሚ ታየ፤ ይህ የመጨረሻው የውድቀት ምልክትይመስለኛል፤ቆም ብሎ ማሰብና አስፈላጊውን የለውጥ እርምጃ መውሰድ የሚያስፈልገው አሁን ነው፡፡

ሐምሌ 17/2007

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    July 25, 2015 03:31 am at 3:31 am

    ሊ/ጠበብት መስፍን ወልደማርያም..ወይ እኔ! ቤት ወይንስ ‘ወያኔ’ ‘ማረፊያ’ ‘ማፈሪያ ቤት?
    …” የእኛን እንተወውና ሲሉ!?
    –የእኛ ሀገር ሕግ የተፃፈ የሚነበብ የሚፎከርብት እንጂ የማይተገበር ስለሆነ ነውን?
    – እኛ ለእኛ በእኛ ስለእኛ መልካም ነገር አያስፈልጋቸውም ተብሎ ተፈርዶብናል ማለት ነውን?
    >> ሕዝቡ ይመርጠናል ምን ማራጭ አለው ሲሉ.. ካልተቃወመ ተስማምተነዋል ማለታቸው አደለምን?
    >> ልመደው ሆዴ፣…. ልመደው ሆዴ፣…. ኢህአዴግ ሁለት ትውልድ አምክኖ/አባክኖ የለም እንዴ!?
    ” በዝዋይ እስር ቤት ትምህርትም እንደመድኃኒት የተጠላ ነገር ነው፤ ለተመስገንም ሆነ ለሌሎች መጻሕፍት አይገቡላቸውም፤ ለምን? ብዬ ስጠይቅ አንዱ ጠባቂ ‹‹ለእውቀት የሚሆን መጽሐፍ ይገባል፤›› አለኝ፤ የእውቀትን ፍቺ ለመጠየቅ ስሞክር ቶሎ ግራ መጋባቱን አየሁና ተውኩት፤ እሱም እንዳያውቅ ስለሚፈልጉ፣ አለቆቹ የእውቀትን ፍቺ ጠበብና ቀለል አድርገው አስተምረውታል፤ ሎሌ ትእዛዝን በሹክሹክታ እየተቀበለ ማስፈጸም እንጂ፣ እውቀት አያስፈልገውም፤ – ኀይለመለስ ያሉት ትዝ አለኝ…” የተማረው ወጣት ኮብል እስቶን ፈላጭ ሆኗል ወጣቱ በተማረው ዕውቀት ሥራ ማግኘት አልቻለም” ቢሏቸው ሲመልሱ” እኛ አለንበት ደረጃ ለመድረስ ማናቸውም ሰው መጀመር ያለበት ከዚያ ነው ብለው ነበር” እኛ የሚለው ግን ይህ ከውጭ ተቀፍሎ የተገዛውን የትምህርት ማስረጃ ማለታቸው ይሆን? የወይኔ/የወያኔ ቤት የተውሶ ትምህርትና ውጤቱን ተመልከቱ “ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ –
    ** በኢህአዴግ መልካም አስተዳደር ጎለበተ..በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ብሔር ብሔረሰቦች ሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች.. ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው…ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ናቸው ይልና…ዳኛው በነፃ ያሰናበቱት ተከሳሽ ፖሊስ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ብሎ ከፍረድ ቤቱ አጥር ውጭ አፍኖ ወሰደው….ዳኛው በቤተሰቡ የመጎብኘት መብቱ ይከበር ብለው አስጠነቀቁ..ተረኛው የእሥርቤቱ ፖሊስ የተከሳሽን ጠያቂ ዘመድ በዱላ ደበደበ!…የዋስ መብቱ ይከበር ተባለው ተከሳሽ ፖሊስ 14 ቀናት መረጃ ማሰባሰቢያ ግዜ ይገባኛል ሲል ወህኒ ቤት ላከው!… ዳኛው በነፃ ያሰናበቱት ተከሳሽ በሌላ ክስ ይፈለጋል ተብሎ 5ሺህ ብር ዋስ ተጠየቀ!… ፖሊስ የሚባለው ፍርድ ቤት ከሚባለው ጋር ያለው ግንኙነት ሕግ የሚባለውን ከጨዋታ ውጭ አድርጎታል፤ ፍርድ ቤት የሚባለው እስረኛ እንዲፈታ ፖሊስ የሚባለውን ሲያዝ እንደማይፈጸም በተደጋጋሚ ታየ፤ ይህ የመጨረሻው የውድቀት ምልክትይመስለኛል፤ቆም ብሎ ማሰብና አስፈላጊውን የለውጥ እርምጃ መውሰድ የሚያስፈልገው አሁን ነው፡፡ድሮም የኅብረት አመራር (በደቦ) ? ወቃው በለው! ያዢ ያጣች ሀገር!?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule