Whether or not we Ethiopians can work together until all our remaining political prisoners are freed, will be the greatest proof as to whether or not we are ready for inclusive transformational change in Ethiopia. Thousands of Ethiopian political prisoners have been released from jails, prisons and detention centers in Ethiopia in the last two weeks. Who could not celebrate this unprecedented release of such large numbers of Oromo and Amhara leaders as well as some others like the … [Read more...] about NO ONE IS FREE UNTIL ALL ARE FREE: LET US NOT STOP OUR EFFORTS UNTIL ALL OUR POLITICAL PRISONERS ARE FREE!
“የመጨረሻዋ ጥይት” የወያነ ጣት ከምላጩ ላይ!!
ያልተጠበቀ ባይሆንም እንዲህ ተጣድፎ የሚጠፋበትን ፈንጂ ለመርገጥ ማሰቢያ ያጣል ብየ አልገመትኩም ነበር፤ ግን ሆነ፤ ወያኔ የቀረችውን የመጨረሻ ጥይት ለመተኮስ ሌባ ጣቱን ምላጩ ላይ አስረግጧል። ቀድሞም ከቦታ ጠባቂነት የዘለለ ድርሻ ያልነበራቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ገፋ አድርጎ በትረስልጣኑን የነጠቀው ወራሪው የወያኔ ጦር መሪዎች ቡድን እንደ ዘመነ መሳፍንቱ ሚካኤል ስሁል የፈቀደውን ሊያነግስ የጠላውን ሊያወርድ ከምንይልክ ቤተ መንግስት ገብቷል። ቀድሞውንም በራሱ በፈጣሪው የተናቀውና የተናደው የይስሙላ “ህገ መንግስት “ ተብየ ባዶ ሰነድ ሙሉ በሙሉ በጠመንጃ ነካሾቹ የሰራዊት መሪዎች በፈረሰበት አገር የወያኔ ሰራዊት የሚከላከለው ሰነድ ሳይኖረው ቤት መንግስቱን መውረሩ የመሪዎቹን የዘረፋ ንብረት ከመከላከል የዘለለ ህዝባዊ ተለዕኮ የለውም። በፈረሰና ህልውና በሌለው ሚንስትሮች ምክር ቤት … [Read more...] about “የመጨረሻዋ ጥይት” የወያነ ጣት ከምላጩ ላይ!!
ወርቅነህ አሜሪካኖችን “ምረጡኝ፤ አስመርጡኝ” ያለበት የጠ/ሚ ምርጫ ተውኔት ይፋ ሆነ
እነ ለማ የሚያራምዱት የጽንፍ ፖለቲካ ነው - ወርቅነህ ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ለአሜሪካኖች “እኔ እንድመረጥ ድጋፍና ጫና ብታደርጉ የናንተን ፍላጎት ለማሳካት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነኝ” በማለት አሜሪካኖችን ሲወተውት እንደነበር ታወቀ። እርሱን እንዲመርጡ ድጋፍ ለመጠየቅ መነሻ አድርጎ ያቀረበው ሃሳብ “እነ ለማ ‹ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ› ቢሉም የሚያራምዱት የጽንፍ ፖለቲካ ነው፤ ከአማራው ጠቅላይ ሚኒስትር ቢመደብ ወደ አማራ ማድላቱ አይቀርም፤ ከሁለቱም ያልሆነ እንደእኔ ያለ ሰው መመረጥ አለበት” የሚል ነው። በግልጽ በማይነገር የጄኔራልነት ማዕረግ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበረው ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ይህንን ያለው ሰሞኑን በአሜሪካ ቆይታው ከፖሊሲ አውጪዎችና የዓለምአቀፍ ግንኙነት ባለሙያዎች ጋር ተገኝቶ ስለወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታና መፍትሄ ማብራሪያ ሲሰጥ ነው። … [Read more...] about ወርቅነህ አሜሪካኖችን “ምረጡኝ፤ አስመርጡኝ” ያለበት የጠ/ሚ ምርጫ ተውኔት ይፋ ሆነ
ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ህወሃት ወስኗል
ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን በህወሃት ተሹሟል። ይህ ከታማኝ ምንጭ የደረሰን መረጃ ነው። መረጃው እንደሚጠቁመው፤ እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ሹመቱን ያጸደቁለት፤ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገና በስልጣን ላይ እንዳሉ ነበር። የህወሃት ሰዎች፤ "የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ሃገሪቱ አሁን የገባችበትን አስከፊ ችግር ይፈታል" የሚል ቅኝት ይዘው ወደ ምዕራቡ አለም እንዲሰማሩም ተደርጓል። ከሀገሬው ሕዝብ ይልቅ የአሜሪካ እና የአውሮፓን ልብ መግዛት ከቻሉ ለተለመደው የበጀት ድጎማ ዋስትና ያገኛሉ። ሁሉም ወገኖች ሳይስማሙበት በሸፍጥ የተፈጸመው ይህን ሹመት ከአሜሪካ ባለስልጣናት ይሁንታ አግኝቷል ተብሏል። የአሜሪካ መንግስት ይህንን ሹመት ለመቀበል ሁለት ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ምክንያት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሮሞ ስለሆነ የተቀሰቀሰውን የቄሮ አመጽ ሊያስቆም ይችላል በሚል … [Read more...] about ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ህወሃት ወስኗል
የከረረው የአሜሪካና የህወሓት “ወዳጅነት ተበጥሷል”
አጋራችን ብትሆኑ ኤምባሲችን ወደየሩሳሌም እንዲዛወር ድምፅ ትሰጡ ነበር - አሜሪካ ለህወሓት ህወሓት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳያውጅ በጌቶቹ ከተነገረው በኋላ በራሱ መንገድ መሄዱ የግንኙነት “ገመዱን እንደበጠሰው” ተነገረ። አሜሪካ ኤምባሲዋ ወደየሩሳሌም እንዳይሄድ የተቃወሙ አገራትን ዋጋ ትከፍላላችሁ ያለችውን በህወሓት ላይ ተግብራዋለች። አውሮጳውያን የጠነከረ ተቃውሟቸውን በህወሓት ላይ በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል። በባራክ ኦባማ አስተዳደር የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት ቶም ማሊኖውስኪ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የአገሪቱን ሁኔታ የገለጹበትን አስመልክቶ ጎልጉል ይህንን መዘገቡ ይታወሳል። “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቸኛ ሃላፊነት ነው፤ … በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ … [Read more...] about የከረረው የአሜሪካና የህወሓት “ወዳጅነት ተበጥሷል”
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የግል አስተያየት
የሃገራችን ፖለቲካ በፍጥነት በሚለዋወጡና አቅጣጫቸውን ለመተመን በሚከብዱ ሁኔታዎች ውስጥ ይዋኛል። ለእነዚህ በፍጥነት ለሚለዋወጡ ፖለቲካዊ ክስተቶች ገፊው ነገር (driving force የምንለው) ምንድን ነው? ካለን በተለይም ላለፉት ሶስት ዓመታት በተከታታይ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ኣመጽ ነው። ይህ ኣመጽ በከፍተኛ ሁኔታ በፖለቲካው ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው። በብዙ ሃገራት ህዝቦች በአምባገነን ስርዓት ላይ ሲያምጹ 5 ዋና ዋና ክስተቶች ይፈጠራሉ። ህዝብ እምቢኝ ሲል አገዛዙ መረረኝ ብሎ ሲያምጽ አመጹ ተጽእኖ ፈጥሮበት የሚከሰቱት እነዚህ 5 ጉዳዮች፦ በገዢው ፓርቲ ውስጥ መሰንጠቅ፣ መፈረካከስና አለመረጋጋትን ያመጣል። ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያጠነክራል፣ ያበረታታል፣ ያደራጃል፣ ወኔ ይሰጣል። አዳዲስ መሪዎችን ከአመጹ መሃል ያወጣል:: የለሂቁን ልዩነት ያጠባል። … [Read more...] about በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የግል አስተያየት
ብሔራዊ የመረጋጋትና የሰላም ጥሪ፤ ከሕጋዊው ሲኖዶስ
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ብሔራዊ የመረጋጋትና የሰላም ጥሪ፤ ከሕጋዊው ሲኖዶስ
ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የትኛው ኦህዴድ?
በደም ወይስ በድርጅት አባልነት? ወርቅነህ ገበየሁ ወዴት ወዴት? ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ፍላጎት መኖሩን፣ እሱም ቦታውን እንደሚፈልገው የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች ጠቆሙ። ወርቅነህ ቀደም ሲል ከነበረው ሃላፊነት፣ ኦሮሞ አይደለም በሚል የሚቀርብበት ክስ፣ በ1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለተካሄደው ግድያ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው በሚል ስለሚወነጀል ኢህአዴግ ራሱ የበጠሰውን የሕዝብ እምነት ሊቀጥል አይችልም የሚል ስጋት መኖሩንም አመላክተዋል። ቀደም ሲል በጄኔራል ማዕረግ የፌደራል ፖሊስ አዛዥ የነበረው፣ ከዚያም በጁነዲን ሳዶ እግር ተተክቶ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር የሆነው በኦሮሚያ ማሊያ ለትግራይ የሚጫወተው ወርቅነህ፣ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነትም የታጨው የኦሮሞን ሕዝብ ለማባባበል ነበር። እንደታሰበው ሳይሆን ግን በተሾመ ማግስት … [Read more...] about ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የትኛው ኦህዴድ?
ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ኢ.ቢ.ሲ. በሰበር ያስተናግደውን የኃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ፤ ዞምቢዎቹ ተሯሩጠው ለማጽደቅ ግዜ አልወሰደባቸውም። እሳቸውም ልክ ስልጣን እንደነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር "ስልጣን አስረክቢያለሁ" ሲሉ እፍረት የሚባል ነገር ፊታቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር። ሹመት እንጂ ሕገ-መንግስቱ የሚፈቅደው ስልጣን እጃቸው ላይ እንዳልነበር ሕጻናትም ያውቁታል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መልቀቅያቸውን በብርሃን ፍጥነት ሲያጸድቀው፤ ድርጊትዋን ከደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዙማ ክስተት ጋር ለማመሳሰል የተተወነች ድራማም አስመስሏታል። ስልጣን ሳይኖር “ሰላማዊ ሽግግር” የሚሏት ፌዝ … ኃይለማርያም ደሳለኝ ተሸክመውት የነበረው ሹመት ይሁን ስልጣን ሲለቅቁ፤ "ከደሙ ነጻ ነኝ" ብለው ለተሰራው ወንጀል ሁሉ እንደ ጲላጦስ እጃቸውን ሊታጠቡ እንደማይችሉ ግን እርግጥ ነው። ከዚህ ባለፈ ግን የእሳቸው መውረድ … [Read more...] about ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ዘብረቅራቃው የባህር ዳር “ቅጠል ሰፈር” ጉድ!
ልብ-ወለድ ታሪኮችን አብዝቶ መጻፍ፣ ዕውነታዉን በግማሹም ቢሆን አስቶ፣ በራስህ የህልም ዓለም ዉስጥ እንድትዋኝ ያደርግሃል፡፡ የCreative writing ኪኑ ከአምላክ ቢሰጥህም፣ ጭቆናንና መገፋትን-ድህነትንና መቆራመድን በጠራ-ገለጥለጥ ባለ አማርኛ ከመግለጽ ግን አትታጎልም፡፡ የኔ ሁለት የሃሳብ ጽንፎች እንደዚህ ሲጓተቱ ቆይተው፣ በስተመጨረሻ "ዕውነታን በኪነት" አሉና ተስማሙ፡፡ ሰፈሬ ከከተማዋ (ከባህር ዳር) አንዷ ክፍል ሆና በመጠራት ትታወቃለች፡፡ በአሁኑ የቀበሌ አወቃቀር፣ "ክፍለ-ከተማ" ተባለች፤ "ሽምብጥ ክፍለ-ከተማ"! አብዛኛው ነዋሪዎቿ በዝቅተኛ የአኗኗር መደብ ዉስጥ ይካተታሉ፡፡ ጠላና አረቄ በመሸጥ የሚተዳደሩ ባልቴቶች በእልፍዓእላፋት መዝገብ ውስጥ ሊመዘገቡ አንድ ሃሙስ የቀራቸው ናቸው፡፡ የህወሃት "እያደኸዩ መግዛት" ፖሊሲ በትክክል ውጤት ያመጣው (በባህርዳር ደረጃ) … [Read more...] about ዘብረቅራቃው የባህር ዳር “ቅጠል ሰፈር” ጉድ!










