እኛ የኦጋዴን፣ የኣማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግራይና የደቡብ ብሄር ተወላጆች ኣዲስ ኣበባን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ የሚገኙ ድሃ የኦሮሞና ሌሎች ገበሬዎችን ግፍ በጥብቅ የምናወግዝ ሲሆን በቅርቡ በሃረማያ፣ በኣምቦ እና በሌሎች ኣካባቢዎች የሚኖሩ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን ግድያና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሊገልጹ በወጡ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የድብደባና የማጉላላት ዘመቻ በጥብቅ እናወግዘዋለን። ገዳዮቹም የጊዜ ጉዳይ እንጂ በፍትህ ፊት ቀርበው የእጃቸውን እንደሚያገኙ ኣንጠራጠርም። እኛ ኢትዮጵያዊያን ልብ ልንል የሚገባው ጉዳይ ባለፉት ዘመናት እንደታዘብነው የኢህዓዴግ መንግስት ሲያሻው ብሄር እየለየ ሲያሻው በጅምላ ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊ ዜጎችን ሲያሰቃይ ሲገድል ቆይቷል። ኣንዴ ኦሮሞን፣ ኣንዴ ደቡብ ሲዳማን፣ ኣንዴ … [Read more...] about ያምማል! አፍንጫን ሲመቱት ዓይን ያለቅሳልና!
Archives for May 2014
“ኢንሔሊ ተቃርኖተ ጽድቅ”
እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም በተከታታይ ያቀረብኳቸው ጽሁፎች፤ አንባቢ በግልጽ ወደሚያያቸው ክስተቶች ቀጥታ ዘልዬ በመግባት አይደለም። ይህም ባለመሆኑ፤ ከነገረ መለኮት ውስጥ ሳልገባ ህዝባውያን የሆኑትን ነገሮች ብቻ ባቀርብ ላንባቢ እንደሚቀል የተለያዩ ምክሮችና ሀሳቦች ከተለያያችሁ ወገኖቼ ቀርበውልኛል። እንደናንተ ሀሳብ ቢሆን ኖሮ ፤ ላንባቢ ጥልፍልፍ ከሚሆንበት ነገረ መለኮት ከመግባት ይልቅ፤ ወቅታውያን የሆኑትን ነገሮች ብቻ እንደክር በመምዘዝ ለማሳየት በቀለለኝ ነበር። ምክራችሁ ትክክል ቢሆንም፤ ለመቀበል ከዚህ በታች በገለጽኳቸው ምክንያቶች እንደምቸገር ተረዱልኝ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “ኢንሔሊ ተቃርኖተ ጽድቅ”
በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረረ ስጋት ፈጥሯል
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት በሞከሩና ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ሰልፍ በወጡ ወገኖች ላይ አገዛዙ የ"ከፋ" ነው የተባለ ሃይል መጠቀሙ ተሰማ። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ታስረዋል። ለተቃውሞ መነሻ በሆነው አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ኦህአዴድ ተመሳሳይ አቋም መያዝ አልቻለም። ችግሩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ያልቻለው ኢህአዴግ ጉልበት መምረጡ አገሪቱ ውስጥ ካለው የተከማቸ ብሶቶች ጋር ተዳምሮ አለመረጋጋቱን ያሰፋዋል የሚል ስጋት አለ። ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት በአቀራረቡ ቢለያይም ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሙት ዜናዎች ሊስተባበሉ የሚችሉ አይደሉም። በታችኛው እርከን የሚገኙትን ጨምሮ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጥቅሉ፣ ገሃድ አይውጣ እንጂ በመዋቅር ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ካድሬዎች የተቃውሞው ተሳታፊና ደጋፊ … [Read more...] about በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረረ ስጋት ፈጥሯል
የሕግ አምላክ የሞተባት አገር፤ በሕገ መንግሥት ሳይሆን በወያኔ የጫካ ሕግ ለሃያ ዓመታት
ለከት ያጣው የወያኔ ጭካኔ እና የማይነጥፈው የሕዝብ ትእግስት ኢትዮጵያን ወዴት እየወሰዷት እንደሆነ አገሪቱ ዛሬ ያለችበት ውጥንቅጥ ሁኔታ በግላጭ ያሳያል። በመግደል አባዜ የተለከፉት የወያኔ ተጋዳላዮች ዛሬም መግደላቸውን ቀጥለዋል። ለይስሙላ በወረቀት ላይ የሰፈረው ሕገ-መንግስት እና በውስጥ የያዛቸው መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች ለወያኔ ተጋዳላዮች ምናቸውም እንዳልሆነ በተደጋጋሚ እያሳዩን ነው። በአገሪቱ ውስጥ ያለው የሕግ ማእቀፍ (አንዳንዶቹ ሕጎች በራሳቸው የማፈኛ መሳሪያ ተደርገው የተቀረጹ መሆኑ ሳይረሳ) ለወያኔ ተጋዳላዮችና ተራ ካድሬዎች ሳይቀር ምናቸውም አይደለም። ሲሻቸው ይገድላሉ፣ ያፍናሉ፣ ይሰውራሉ፣ ባደባባይ ይደበድባሉ፣ ሺዎችን በየማጎሪያው ያሰቃያሉ፣ ያዋርዳሉ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ ይሞስናሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ያስፈራራሉ፣ ሴቶችን ይደፍራሉ፣ ህዝብን … [Read more...] about የሕግ አምላክ የሞተባት አገር፤ በሕገ መንግሥት ሳይሆን በወያኔ የጫካ ሕግ ለሃያ ዓመታት
Open Letter to Political Leaders in Ethiopia
SMNE’s Call to Ethiopian Political Leaders in Ethiopia: A Viable Alternative to a New, Better and More Inclusive Ethiopia Will Not be Delivered by Foreigners like Humanitarian Aid! Are Ethiopians Ready to Discard Ethnic Politics and Embrace Inclusion in Preparation for the 2015 National Election? Dear political leaders in Ethiopia, Warmest greetings to you from the (SMNE) http://www.solidaritymovement.org. We are writing to you because we believe you are among those who have shown … [Read more...] about Open Letter to Political Leaders in Ethiopia
መቀየር የሚያስፈልገው ራስን ወይስ ሃይማኖትን?
እኅቴ ወ/ሮ ሚሊ ተስፋዬ እንደምን አለሽ በዚህ ዘመን የሚሠሩት የሀገራችን ፊልሞችና ድራማዎች (ምትርኢቶችና ትውንተ-ድርሰቶች) ከሞላ ጎደል ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ደርዝ፣ ጭብጥ፣ ትልም ያላቸው አይደሉምና፤ ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ከሀገር ጥቅም አንጻር በጥልቀትና በብስለት የሚዳሰስባቸው አይደሉምና ተከታታይ አይደለሁም፡፡ በመሆኑም በዚህ ኢንደስትሪ (ምግንባብ) ባለሽና በነበረሽ ሚና አላውቅሽም ነበር፡፡ በእንጨዋወት የኢ.ቢ.ኤስ የቴሌቪዥን (የምርዓዬ ኩነት) ትዕይንተ-ወግ (ቶክ ሾው) ዝግጅት ላይ እንግዳ ሆነሽ ቀርበሽ ያደረግሽውን ወግ ስመለከት ሃይማኖትሽን ስለ መቀየርሽ ስታወሪ “ክርስቲያን ሆንኩኝ፤ ክርስቲያን ከሆንኩ በኋላ…” እያልሽ የገለጽሽው አገላለጽ በጣም ስለገረመኝና የሠራሽው ስሕተት ከብዶ ቢታየኝ ነው ይህችን መልእክት ልጽፍ … [Read more...] about መቀየር የሚያስፈልገው ራስን ወይስ ሃይማኖትን?