• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ያምማል! አፍንጫን ሲመቱት ዓይን ያለቅሳልና!

May 2, 2014 12:08 am by Editor Leave a Comment

እኛ የኦጋዴን፣ የኣማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግራይና የደቡብ ብሄር ተወላጆች ኣዲስ ኣበባን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ የሚገኙ ድሃ የኦሮሞና ሌሎች ገበሬዎችን ግፍ በጥብቅ የምናወግዝ ሲሆን በቅርቡ በሃረማያ፣ በኣምቦ እና በሌሎች ኣካባቢዎች የሚኖሩ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን ግድያና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሊገልጹ በወጡ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የድብደባና የማጉላላት ዘመቻ በጥብቅ እናወግዘዋለን። ገዳዮቹም የጊዜ ጉዳይ እንጂ በፍትህ ፊት ቀርበው የእጃቸውን እንደሚያገኙ ኣንጠራጠርም።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ልብ ልንል የሚገባው ጉዳይ ባለፉት ዘመናት እንደታዘብነው የኢህዓዴግ መንግስት ሲያሻው ብሄር እየለየ ሲያሻው በጅምላ ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊ ዜጎችን ሲያሰቃይ ሲገድል ቆይቷል። ኣንዴ ኦሮሞን፣ ኣንዴ ደቡብ ሲዳማን፣ ኣንዴ ኣማራን፣ ኣንዴ ኦጋዴንን፣ ኣንዴ ጋምቤላን ወዘተ ሲያጠቃ ተላላ ሆነን የተጠቃው ቡድን ብቻ ለብቻው ትንሽ ጮሆ ዝም ስለሚል የግፉ ጊዜ ሊረዝምብን ችሏል። ኣሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የመንግስትን የከፋፍለህ ግዛው ዘዴ ሊነቃበትና ኣፍንጫን ሲመቱት ኣይን ያለቅሳል እንደሚባለው ኣንዱ ሲጠቃ ሌላውም ሆ! ብሎ በመነሳት ይህንን ኣስከፊና በዓለም የሌለ ብሄርተኛ ኣገዛዝ ኣሽቀንጥሮ መጣል ይገባዋል። በሌላ በኩል የኦሮሞ ወገኖቻችን ያነሱትን የፍትህ ጥያቄ ለማጣመምና ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት የኢህዓዴግ ካድሬዎች ሊሯሯጡ እንደሚችሉ እየተገነዘብን ይህንን ጉዳይ የኦሮሞ ተማሪዎች ይስቱታል ብለን ኣናምንም። መንግስት በተለይ በኣሁኑ ሰዓት የቀለም ዓብዮት ሊነሳብኝ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት ስላለበት ህዝቡን በሃይማኖትና በብሄር በመከፋፈልና ከፍተኛ የሆኑ የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በጋራ እንዳይነሱ ስለሚፈልግ ብሄርተኝነትንና ጠባብነትን ለብሶ እንደለመደው እያጋጨ በስልጣን ለመቆየት መፍጨርጨሩ ኣይቀርምና በማናቸውም ተቃውሞዎቻችን ውስጥ ለወያኔ እድል ፈንታ መስጠት የለብንም።

በሌላ በኩል ለውጥ ለማምጣት የሚታገሉ ዴሞክራት የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ኣንድ ብሄር ተለይቶ ሲጠቃ ሁሉን የማንቀሳቀስና ለጋራ ትግል ቆራጥ የጥሪ ደወል የማሰማት ሃላፊነት ኣለባቸው ብለን በጽናት እናምናለን።

የጀግናው ብእረኛ እስክንድር ነጋ ነገር፣ በቅርቡ ደግሞ ወደ ዘብጥ የወረዱት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ጉዳይ እንቅልፍ የነሳን ጉዳይ ነው። እነዚህ ወጣት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን በሰፊው እስር ቤት የሚገኘውን የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት እጦት ኑሮ ተምሳሊት ኣድርገው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ለጋ ወጣቶች ወደ እስር ቤት መውረዳቸው ከሰፊው እስር ቤት ወደ ጠባቡ መግባታቸውን ከማሳየቱም በላይ የታሰሩት ግለሰቦቹ ብቻ ሳይሆኑ ኣላማቸው በመሆኑ ሌላው የዞን ዘጠኝ እስረኛ የሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ መንግስት የነጻነት ጥያቄውን ወደ ወህኒ መወርወሩን የሚያሳይ በመሆኑ ምን ያህል መንግስት በጭካኔ ስራው ሊቀጥል እንደ ወሰነ ያሳያል። በመሆኑም የነዚህ ወገኖች መታሰር፣ የፖለቲካው ምህዳር ምን ያህል እየጠበበ መምጣቱን፣ መንግስት ለህዝቡ ያለው ንቀት ጫፍ መርገጡን ያሳያል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በብሄርና በሃይማኖት ሳይከፋፈል የኦሮሞ ወገኖቻችንን ወቅታዊ ጥያቄና የጋዜጠኖቹን እስር ጉዳይ ወደ ኣጠቃላይ ፍትህና ዴሞክራሲ ጥያቄ ከፍ ኣርገን በያለንበት እንነሳ :: ዴሞክራሲና ፍትህ ሲሰፍን ጥያቄዎቻችን ሊፈቱ ይችላሉና ኢትዮጵያዊያን በጋራ ለለውጥ እንድንነሳ ወገናዊና ወንድማዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

የማትከፋፈል ኢትዮጵያን ለትውልድ እናሳልፋለን!

በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድምጽ

smne banner

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule