• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሕግ አምላክ የሞተባት አገር፤ በሕገ መንግሥት ሳይሆን በወያኔ የጫካ ሕግ ለሃያ ዓመታት

May 1, 2014 06:37 am by Editor Leave a Comment

ለከት ያጣው የወያኔ ጭካኔ እና የማይነጥፈው የሕዝብ ትእግስት ኢትዮጵያን ወዴት እየወሰዷት እንደሆነ አገሪቱ ዛሬ ያለችበት ውጥንቅጥ ሁኔታ በግላጭ ያሳያል። በመግደል አባዜ የተለከፉት የወያኔ ተጋዳላዮች ዛሬም መግደላቸውን ቀጥለዋል። ለይስሙላ በወረቀት ላይ የሰፈረው ሕገ-መንግስት እና በውስጥ የያዛቸው መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች ለወያኔ ተጋዳላዮች ምናቸውም እንዳልሆነ በተደጋጋሚ እያሳዩን ነው። በአገሪቱ ውስጥ ያለው የሕግ ማእቀፍ (አንዳንዶቹ ሕጎች በራሳቸው የማፈኛ መሳሪያ ተደርገው የተቀረጹ መሆኑ ሳይረሳ) ለወያኔ ተጋዳላዮችና ተራ ካድሬዎች ሳይቀር ምናቸውም አይደለም። ሲሻቸው ይገድላሉ፣ ያፍናሉ፣ ይሰውራሉ፣ ባደባባይ ይደበድባሉ፣ ሺዎችን በየማጎሪያው ያሰቃያሉ፣ ያዋርዳሉ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ ይሞስናሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ያስፈራራሉ፣ ሴቶችን ይደፍራሉ፣ ህዝብን ያሸብራሉ፣ ምኑ ቅጡ።

እንግዲህ የሕግ አምላኩ ሲሞት ሥርዓት አልበኝነት ይነግሳል፤ ዘራፊዎች ይበራከታሉ፣ ገዳዮች ባደባባይ ገድል ይጥላሉ፣ ሙሰኞች አገርን እና ሕዝብ ይቆጣጠራሉ፣ የአገር ሃብት ያሸሻሉ፣ በድሆች ጉሮሮ ላይ ቆመው በሃብት ይጨማለቃሉ። በዚህ ላይ ጎጠኝነት ሲታከልበት መላ ቅጡ ይጠፋል። ብዙዎቹ እየከሰሙ ያሉ አገሮች (failed states) እየተባሉ በየጊዜው የሚጠቀሱ አገሮች በእነዚህ ችግሮች ውስጥ የሚማቅቁ ናቸው። ወያኔም ለኢትዮጵያ የዋለላት አንዱ ትልቁ ነገር ከእነዚህ አገሮች ተርታ እንድትሰለፍ ማድረጉ ነው። እንደ ታላቅ ስኬት የሚቦተለክለት የዛሬዋ የኢትዮጵያ ልማት ውስጡ ሲገባ ላዩ አሮ ውስጡ ሊጥ እንደሆነ ዳቦ ስለመሆኑ ምንም ጥናትና የተለየ ምርምር ሳይጠይቅ 95% የሚሆነውን የአገሪቷን ሕዝብ ኑሮ ማየት በቂ ነው። አንጻራዊ በሆነ መልኩ በወያኔ ዘመን የመጀመሪያዎቹ አሥር አመት ውስጥ እንኳን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያገኛቸው የነበሩትን እንደ መብራት፣ ውኃ፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ዛሬ ተነፍጓል።

የደብል ዲጂት ልማታዊነት ነጠላ ዜማዎች በወያኔ እና ባጫፋሪዎቹ የአለም አቀፍ ‘የልማት’ ተቋማት ጆሮዋችን እሲደነቁር በሚዘፈንበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስከፊ በሆነ የኑሮ ዋስትና ማጣት ውስጥ ሆኖ የመከራ እንቆቆውን እየተጋተ ይገኛል። የእነዚህ የመሰረታዊ አቅርቦቶች በዚህ ደረጃ ላይ አቆልቁሎ መገኘት አንኳን የቀለም አብዮት፤ ሌላም መገለጫ የሌላቸው አመጾችንና እልቂትን ቢወልድና በአገሪቱን ወደ ከፋ ብጥብጥ ቢከት የሚገርም አይደለም። ይሁንና እንደ ወያኔ ያለ ክፉ፣ መረን የማያውቅ እና ጨካኝ ሥርዓት እድለኛ ሆኖ ሆደ ሰፊ፣ የማይቻለውን ሁሉ የሚችል፣ ጨዋና ታጋሽ ሕዝብ ሲጋጥመው ጭካኔውን እያበረታ፣ የአፈና ሰንሰለቱን እያጠበቀ፣ አባላቱን በአሃብት እያሞሰንነና እያጎለበተ ይንሰራፋል። የአገር መፍረስ ወይም አደጋ ላይ መወደቅ የራሳቸውን ጥቅም አደጋ ላይ እስካልጣለ ድርስ ግድ የማይሰጣቸው ጎጠኛ ፖለቲከኞችም በደሃው ሕዝብ ላይ ይሰለጥኑበታል፤ ይሰይጥኑበታልም።

ሰሞኑን በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለው የፖለቲካ ድባብ ወያኔ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ አገሪቱን የሚዘውርበት መሪ ከቁጥጥሩ ውጭ እንዳይወጣ እየተውተረተረ ያለ መሆኑን ነው። ለዚህም ይመስላል ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ባንዲራና መፈክር ይዘው በተንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፤ በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን አስሮ እያሰቃየ ያለው። ለዚህም ነው በማኅበራዊ ድኅረ ገጾች በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን እያጫሩ ሕዝቡ እንዲወያይ ይጋብዙ የነበሩ የዞን 9 አባላትን ለቃቅሞ አጉሮ እያሰቃያቸው የሚገኘው። ይህም አልበቃ ብሎ ባለፉት ሦስት እና አራት ቀናት ውስጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ (ጥያቄያቸው ምንም ይሁን ምን) እያቀረቡ ያሉ የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ ዩንቨርሲቲ ተማሪች ላይ የተለመደውን የጭካኔ እርምጃ እየወሰደ ያለው። ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው ከሆነ በርካታ ተማሪዎች በታጠቁ ሃይሎች የጭካኔ እርምጃ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል። በተለይም በአንቦ ከተማ ተማሪዎች በግፍ ተገድለዋል። የወያኔ መንግሥት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በተማሪዎች ላይ ተደጋጋሚ የጭካኔ እርምጃዎችን ወስዷል። በመላ አገሪቷ በወያኔ እርምጃዎች ከተጠቁት ተማሪዎች ውስጥ ግን ትልቁን ግፍ የተቀበሉት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ስለመሆናቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚመለከቱ ሪፖርቶች ይመሰክራሉ። በሥራዬ አጋጣሚ እኔም ይህን አረጋግጫለሁ።

ዛሬ ላለንበት ጠቅላላ አገራዊ ክሽፈት፣ ውርደት እና የመከራ ሕይወት ከላይ እንደጠቀስኩት ለከት ያጣው የወያኔ ጭካኔ እና አፈና፤ እንዲሁም የአለማችን ተጭባጭ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን  የማይነጥፈው የሕዝብ ትእግስት እና ዝምታም ትልቁን አስተዋጾ አድርጓል። በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ተማሪዎች ላይ፣ በጋዜጠኞች ላይ፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች ላይ፤ እንዲሁም በኃይማኖት መሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል በጋራ ልናወግዘው እና ልንታገለውም ይገባል። በፍትሕ እና በኢ-ፍትሐዊነት፣ በጭቆና እና በነፃነት  መካከል ገለልተኛ ሆነው የሚንጠለጠሉበት ገመድ ወይም የሚቆዩበት ደሴት የለም። ፍትሕ ሲጓደል እያዩ እንዳላዩ መሆን በራሱ ኢ-ፍትሐዊነት ነው። መብት ሲጣስ እያዩ እንዳላዩ መምሰል በራሱ የጣሹ ግራ እጅ መሆን ነው። ንጹሃን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ፣ ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩ እና በሃሰት ክስ እየተፈረደባቸው በእስር ሲማቅቁ እያዩ ገለልተኛ መሆን አይቻልም። የፖለቲካ ገለልተኝነትን እና ለፍትሕ፣ ነጻነት እና ለህሊና መቆምን ባናምታታቸው ጥሩ ነው።

ለፍትህና ለነፃነት በመቆም የሰውነትም፤ የዜግነትም ግዴታችንን እንወጣ!

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ፣ ቤልጂየም

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule