እኅቴ ወ/ሮ ሚሊ ተስፋዬ እንደምን አለሽ በዚህ ዘመን የሚሠሩት የሀገራችን ፊልሞችና ድራማዎች (ምትርኢቶችና ትውንተ-ድርሰቶች) ከሞላ ጎደል ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ደርዝ፣ ጭብጥ፣ ትልም ያላቸው አይደሉምና፤ ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ከሀገር ጥቅም አንጻር በጥልቀትና በብስለት የሚዳሰስባቸው አይደሉምና ተከታታይ አይደለሁም፡፡ በመሆኑም በዚህ ኢንደስትሪ (ምግንባብ) ባለሽና በነበረሽ ሚና አላውቅሽም ነበር፡፡
በእንጨዋወት የኢ.ቢ.ኤስ የቴሌቪዥን (የምርዓዬ ኩነት) ትዕይንተ-ወግ (ቶክ ሾው) ዝግጅት ላይ እንግዳ ሆነሽ ቀርበሽ ያደረግሽውን ወግ ስመለከት ሃይማኖትሽን ስለ መቀየርሽ ስታወሪ “ክርስቲያን ሆንኩኝ፤ ክርስቲያን ከሆንኩ በኋላ…” እያልሽ የገለጽሽው አገላለጽ በጣም ስለገረመኝና የሠራሽው ስሕተት ከብዶ ቢታየኝ ነው ይህችን መልእክት ልጽፍ የተገደድኩት፡፡
እኅቴ በእርግጥ ይህ የተሳሳተ አገላለጽ ያንቺ ብቻ ሳይሆን በየ ብዙኃን መገናኛው ሃይማኖትን የቀየሩ ዜጎቻችን ሃይማኖታቸውን መቀየራቸውን ሲገልጹ ሆን ብለው የሚጠቀሙት ቃል ወይም አገላለጽ ነው፡፡ አንቺ የነበርሽበት ሃይማኖት (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ) ውስጥ ያለን ምእመናን ሁሉ ክርስቲያኖች እንደሆንን እናውቃለን፡፡ አንቺ ግን እኛ ክርስቲያን እንዳልሆንንና አንቺም ክርስቲያን እንዳልነበርሽ ሁሉ ሃይማኖትሽን መቀየርሽን “ክርስቲያን ሆንኩ” በሚል ቃል ገለጽሽ፡፡ ሌሎችም እንዳንችው በሥነ-ኪን ዘርፍ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን ጥጋብና ዝና የሚሠሩትን ሲያሳጣቸው ለዚያ ባበቃቸው ሕዝብ ላይ ሲወረግጡ ምኑንም ሳያውቁት ሃይማኖታቸውን ይቀይሩና በብዙኃን መገናኛ ቀርበው አስቀድሞ በነበሩበት ሃይማኖት ያለን ክርስቲያኖች ጌታን እንዳልተቀበልን ሁሉ “ጌታን ተቀበልኩ” ሲሉ ይገልጻሉ፡፡
እነዚህ አገላለጾች ሳይታሰብባቸው በአጋጣሚ የሚባሉ ቃላቶች አይደሉም፡፡ ሆን ተብሎ ለማጥቃት የሚሰነዘሩ እኩይና አጥቂ ቃላቶች ናቸው እንጂ፡፡ እነዚህ ሰዎች ማንንም ማጥቃት ሳያስፈልጋቸው ፕሮቴስታንት (ተቃዋሚ) ሆንኩ በማለት ያላቸውን ለውጥ መግለጥ የሚችሉበት ዕድል ነበር፡፡ በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር የብዙኃን መገናኛዎቹ ለእነዚህ ሰዎች እንዴት ይሄንን ጥቃት ለመፈጸሚያ መገልገያ መጠቀሚያ ለመሆን እንደሚፈቅዱና ጥቃቱን እንደሚያስተናግዱ ነው፡፡ በእርግጥ አንዳንዴም ወያኔ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ባለው ጥላቻና ጠላትነት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የጥቃት ሴራ እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ምናልባት ሳይስተዋል ስሕተቱን የሚፈጽሙ ወገኖች ካሉ ስሕተቱ በተደጋጋሚ ለረጅም ጊዜ ሲፈጸም የኖረ ጉዳይ በመሆኑ በዚሁ ሊቀጥል ይችላል ከሚል ሥጋትም አንጻር ያለውን እውነት ፍርጥርጥ ባለ መልኩ ዳስሸ ለማስረዳት፣ ግንዛቤውን በመስጠት ስሕተቱ እንዳይደገም ከማድረግ አንጻርም ነው ጽሑፏን መጻፌ፡፡
ወ/ሮ ሚሊ ሃይማኖትሽን ከመለወጥሽ በፊት ሕይዎትሽ ዓለማዊ (ኃጢአት የበዛበት) እንደነበር ነግረሽናል፡፡ ታዲያ ከዚህ ሕይዎት ለመውጣት ያንን ጥሩ ያልሆነ ሕይዎትሽን ለመቀየር መቀየር የነበረብሽ ራስሽን እንጂ ሃይማኖትሽን እኮ አልነበረም መቀየር የነበረብሽ፡፡ ምክንያቱም የነበርሽባት ሃይማኖት ዓለማዊነትን አትሰብክምና ኃጢአተኞች ሁኑ ብላ አትሰብክም አታስተምርምና፡፡
ወ/ሮ ሚሊ ያንች ምትርኢት (ፊልም) ምንም እንኳን ያየሁት ባይሆንም ካወራቹህት እንደተረዳሁት ከሆነ ሊኖረው ከሚችለው ማኅበራዊ ፋይዳ አንጻር ስመዝነው በጣም ጠቃሚና ጥሩ ነው ማለት እችላለሁ፡፡ ለሕዝባችን ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጤና ተጨንቀሽ ይሄንን ምትርኢት በማቅረብሽም ስለ እውነት በጣም አደንቅሻለሁ፡፡ ይሄ ድካምሽ ከንቱ ሆኖ ሊቀር ከመቻሉ አንጻር ካለኝ ሥጋት አኳያም እጅግ አዝኘልሻለሁ፡፡ በሃይማኖት ውስጥ ሆነሽ ይሄንን ግሩም ሥራ ሠርተሽ ቢሆን ኖሮ ከጌታ ዘንድ ምን ያህል ዋጋ ባሰጠሸ ነበር፡፡ ምን ማለቴ መሰለሽ በወጋቹህ ወቅት ምትርኢትሽን ከመሥራትሽ በፊት ጥናት እንዳደረግሽ ነግረሽናል፡፡ ከጥናትሽ እስከአሁንም ልብ ያላልሽውን አንድ ቁም ነገር እንዳገኘሽ አምናለሁ፡፡ ጥናት ስታደርጊ ልሳን ተገለጸልን ብለው በየ አዳራሹ ምንነቱን የማያውቁትን የሚያዥጎደጉዱትን የዛር መንፈስ ቋንቋ እንደ ፓስተሮቹ ሁሉ በየጠንቋዩ በየቃልቻው ቤት በቃልቾቹ ወይም በጠንቋዮቹ አንደበት ሲባል ሲዥጎደጎድ ሰማሽ አይደል? እንዴትና ለምንስ ሊሆን እንደቻለ የምታውቂው ነገር አለ እኅት ወ/ሮ ሚሊ? የሚሠራባቸው መንፈስ አንድ ስለሆነ ነው ሌላ አይደለም፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሐዋርያት ልሳናት(ቋንቋዎች) ተገልጸውላቸው ነበር፡፡ የሐዋ. ሥራ 2፤4-13 እነዚያ ለሐዋርያቱ የተገለጹላቸው ልሳናት ወይም ቋንቋዎች ታዲያ ከተለያዩ ሀገራት መተው በዚያ ተሰብስበው የነበሩ የተለያዩ ሀገራት ሰዎች ቋንቋዎች በመሆናቸው በዚያ የነበሩ የተለያዩ ሀገራት ሰዎች ሐዋርያት ቋንቋዎቻቸውን በመናገራቸው “እነዚህ ዕብራዊያን ሲሆኑ እንዴት በየቋንቋችን ሊናገሩን ቻሉ?” በማለት ተደነቁ እንጂ ልሳን ተገለጸልን ብለው ምንነቱ የማይታወቅ የቃላት እሩምታ እንደሚያዥጎደጉዱት ፓስተሮች ማንም የማያዳምጠውንና የማያውቀውን አይደለም የተናገሩት፡፡ ታዲያ እኅቴ አዳራሽ ውስጥ በአገልጋዮችሽ አንደበት ስትሰሚው የነበረውን የክፉ መንፈስ ቋንቋ ጠንቋይ ቤትም መስማትሽ ምንም የጫረብሽ ጥያቄ አልነበረም?
ይሄውልሽ እኅቴ ወ/ሮ ሚሊ የዋህ አትሁኝ ሃይማኖት አንዲት ናት ከዚህች አንዲት ሃይማኖት ውጪ እንድንበት እንጓዝበት እንኖርበት ዘንድ የተሰጠ ሌላ ሃይማኖት የለም፡፡ ይሄንን ያልኩት እኔ አይደለሁም የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፡፡ “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ. 4፤5 ይህች አንዲት ሃይማኖት ከአዳም ጀምሮ ነበረች እስከ ዓለም ፍጻሜም ትኖራለች፡፡ ክርስትናና ይሁዲነት (ሐዲስ ኪዳንና ብሉይ ኪዳን) ወይም ሐዲስና ኦሪት በአንዲቷ ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ኪዳናት ናቸው እንጂ ሃይማኖቶች አይደሉም፡፡
የኢየሱስን ስም ስለጠሩ እውነት እንዳይመስልሽ የትኛውን ኢየሱስ እንደሚጠሩ አላወቅሽም፡፡ አውሬውን ጨምሮ ብዙ ሐሰተኞች ኢየሱሶች አሉና፡፡ ይህ እንደሚሆን እራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ኢየሱስ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ ሲቃረብ ብዙዎች ሐሰተኞች መምህራን በየ እልፍኙ የሚሰብኩላቸው ሐሰተኞች ኢየሱሶች ሐሰተኞች ክርስቶሶች ይመጡ ዘንድ እንዳላቸውና ከእነሱም እንድንጠበቅ አስጠንቅቆናል፡፡ ማቴ. 24፤1-28
ቅዱስ ጳውሎስም “ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯቹህን ዋኖቻቹህን አስቡ የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታቹህ በእምነት ምሰሏቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘለዓለምም ያው ነው ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፡፡ ልባቹህ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና ” ዕብ. 13፤7-9 እናም እኅቴ የትንቢት መፈጸሚያ አትሁኝ አዲስ ኢየሱስ የለም ካለም ሐሰተኛው አውሬው ነውና ልብ አድርጊ፡፡ እኅቴ ወ/ሮ ሚሊ ዛሬ የክርስቲያን ሃይማኖት ነኝ የሚሉት ብቻ 33000 ደርሰዋል፡፡ እያንዳንዳቸው ስለ ኢየሱስ ማንነት የሚናገሩት አንዱ ከሌላው የተራራቀ የተለያየ ነው፡፡ አንደኛው ኢየሱስ እንደኛ ሰው ነው በመልካም አገልግሎቱ ተሾመ ሲለው ሌላኛው አማላጅ ነው፣ ሌላው ሚካኤል ነው ሲለው ሌላኛው አንድ ገጽ ነው፣ አንዱ ሁለት ባሕሪ ነው ሲለው ሌላኛው በመንፈስ እንጂ በአካል አልተነሣም ሲል እንዲህ እንዲህ እያሉ ሐሰተኞችን ኢየሱሶች ክርስቶሶች ይሰብካሉ፡፡ ቃሉ እንዳለው ከነዚህ ውስጥ አንዱ ብቻ ከሆነ ትክክሉ 32999ኙ ሐሰተኞችና የጥፋት የሞት መንገዶች ናቸው ማለት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ስለ እነዚህ ሐሰተኞች ሲናገረን “ ነገር ግን ወንድሞች ሆይ እናንተ የተማራቹህትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና መሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንዳትመለከቱ እለምናቹሀለሁ፡፡ ከእነሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ እንደነዚህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ያታልላሉ” ሮሜ 16፤15-23 “እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና፡፡ ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅ አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፡፡ ፍጻሜያቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል፡፡ 2ኛ ቆሮ. 11፤13 እያለ ስለማንነታቸው ቁልጭ አድርጎ በግልጽ ጽፎባቸዋል፡፡
እኅቴ ወ/ሮ ሚሊ እባክሽን ንቂ አትታለይ “ መንፈስ ግን በግልጥ በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንት ትምህርት እያዳመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ” ብሏል 1ኛ ጢሞ. 4፤1-2 በእርግጥ አንች ቃሉ እንዳለው አስመሳዮች በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግር ሲደልሉሽ እውነት መስሎሽ ይሆናል መናፍቅ የሆንሽው፡፡ ያለው እውነታ ግን ይሄው ነው፡፡ ሃይማኖት ዛሬ በኔና በአንቺ ዘመን የመጣ የተፈጠረ እንዳልሆነ ብታስተውይ ብቻ፤ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት ባይኖርሽ እንኳን ለመንቃት ላለመታለል በቻልሽና ዛሬ በኛ ዘመን በየቀኑ ማንም ቀባዣሪ ሐሰተኛ በድፍረት ለራሱ እንደሚመቸው አድርጎ አጣሞ እየተረጎመ የምንትስ ቤተክርስቲያን እያለ በየ አዳራሹ እየለጠፈ የሚለፈልፈው ሁሉ አዳዲስ በመሆናቸው ብቻ ከላይ እንደጠቀስኩልሽ የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ በኋለኛው ዘመን ይመጣሉ ተጠንቀቁ እያል የገለጻቸው የአውሬው አገልጋዮች ሐሰተኞች መምህራንና ሐሰተኞች ነቢያት መሆናቸውን ማወቅ መረዳት በቻልሽ ነበር፡፡
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም መንገድ ወዴት እንደሆነች ዕወቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች ዕወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳቹህም ዕረፍትን ታገኛላቹህ እነሱ ግን አንሄድባትም አሉ” ኤር. 6፤16 “የመጀመሪያዋን እምነት እስከመጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና” ዕብ. 3፤14 ይላል ቃሉ እኅቴ ወ/ሮ ሚሊ እውነት መዳን ከፈለግሽ ወደ መጀመሪያዪቱ ወደ ቀዳሚዋ ወደ ጥንታዊቷ ክርስቶስም በደሙ ወደ ዋጃት ወደ እውነተኛዋ ሃይማኖት ነይ፡፡ የኢየሱስ ምስክር ያለንና የመዳን ተስፋ የተሰጠን እኛ የቅድስት ብጽዕት ድንግል ማርያም ልጆች ነን “ ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘሯ የቀሩትን ሊዋጋ ሔደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ” ራዕ. ዮሐ. 12፤17
እኅቴ መዳን ከፈለግሽ ብቸኛው የመዳኛ መንገድ ይሄው ነው የዮሐ. ወንጌል 19፤26-27 ላይ እንደተገለጸልን የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ በመከራ ላይ ሆኖ እየቃተተ በሚወደው ሐዋርያ በዮሐንስ ወንጌላዊ አማካኝነት የተሰጠችንን እናትነቷንና ልጆቿ ተደርገን የመቆጠር የአምላክ ስጦታ ወደሽ አምነሽ አክብረሽ ተቀብለሽ ከዘሯ ተቆጠሪ ከዚህ ውጪ መዳን የምትችይበት መንገድ የለም፡፡
እኅቴ ሚሊ ምንም እንኳ ስለ ክርስቶስ ፍቅር መቀኘቱ አስፈላጊ ቢሆንም እንዲህ ፍቅሩ ካለሽ ልታደርጊው የሚገባሽን ነግሮሻል “ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሰክሞ ይከተለኝ ” ማቴ. 16፤24 ለዚህም ነው ሐዋርያት “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” ያሉት የሐዋ. ሥራ 14፤22 ስለዚህም በምቾትና በድሎት በመሽሞንሞን በመቀማጠል አይደለም ራስሽን ጣዪ መስቀሉን (መከራውን መራብ መጠማቱን በድካም በእንግልት ስለ ስሙ ስለ ክብሩ ስለ ፍቅሩ መሰቃየቱን ወዘተ.) በመሸከም በመፈጸም ነው የክርስቶስ የሚኮነው እሺ? መንፈሳዊነት ማለትም ይሄ ነው እንጂ የሥጋን ምኞትና ምቾት መጠበቅ መከተል አይደለም ዓለማዊነት ማለት እሱ ነው፡፡ አንቺ የምታመልኪበት ድርጅት ይሄንን የክርስቶስ ቃል በመቃወም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ በሆነ መንገድ ስለ ክርስቶስ ስለ ፍቅሩ ስለ ክብሩ መከራ መቀበልን አይቀበሉም፡፡
ሐዋርያው ያዕቆብ ስለ እነዚህ ሲናገር “ ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?….ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው ” ያዕ. 2፤ ብሎሻልና ልብ በይ ሃይማኖት እንዲህ ፌዝ አይደለምና ተጠንቀቂ፡፡ ጾምን በመጥላት ብቻ መናፍቅ የሆነ ሰው አውቃለሁ፡፡ መናፍቅ በመሆን ጾም ጸሎት ስግደትና የተለያዩ መንፈሳዊ ተግባራትን ማድረግ ሳያስፈል ባቋራጭ መጽደቅ የሚቻል ስለ ሚመስላቸው፡፡ “ሙሽራው ከእነሱ የሚወሰድብት ወራት ይመጣል በዚያ ጊዜም ይጾማሉ” ማቴ. 9፤15 “ይህ ዓይነት ክፉ መንፈስ ግን ከጸሎትና ከጾም በስተቀር አይወጣም” ማቴ. 17፤14-21
“በጠበበው ደጅ ግቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጁ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ወደ ሕይዎት የሚወስደው ደጁ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው” ማቴ. 7፤13-14 እርግጠኛ ነኝ እንደብዙዎቹ የአንቺ እምነት ተከታዮች ሁሉ የሥጋ ፈቃድሽን የሥጋ ምኞትሽን ለመጠበቅ ማለትም ላለመጾም ላለመጸለይ ላለመስገድ በስሙ መከራ ላለመቀበልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ መንገድ አንድ ጊዜ በጸጋው ድኛለሁ አያስፈልግም እያሉ እራሳቸውን በማታለል ከእነኝህ ግዴታ ከሆኑ መንፈሳዊ ሥራዎች ለመራቅ ብለሽ ላለ መፈጸም ላለመገዛት ብለሽ ካልሆነና በየዋህነት መስሎሽ ተታለሽ ከሆነ መናፍቅ የሆንሽው እውነቱን ተረድተሸ ለመመለስ እስካሁን የነገርኩሽ ቃል በጣም ከበቂ በላይ ነው፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር በጾም በጸሎት በስግደት ላለመገዛት፣ ጌታን በእነዚህ ላለማክበር፣ ጾም ጸሎት ስግደትን በመጥላት ሆድሽን ወደሽ ሳትጾሚ ለመኖር፣ ላለመጸለይ፣ ላለመስገድ፣ ስለ ፍቅሩ ስለ ስሙ ስለ ክብሩ ወደሽና ፈቅደሽ ፈልገሽ የተለያዩ መከራዎችን መቀበልን (መስቀሉን መሸከምን) ሥጋን የማድከም መንፈሳዊ ሕይዎትን ጠልተሽ የሥጋ ፈቃድሽን የሥጋ ምኞትሽን የሥጋ ምቾትሽን ለመጠበቅና ዓለማዊ ለመሆን፣ ጹሚ ጸልዪ ስገጂ የተለያዩ መንፈሳዊ ተግባራትን እያደረግሽ ስለ ክርስቶስ መከራ ተቀበዪ የሚልሽ ሳይኖር “አንድ ጊዜ በጸጋው ድኛለሁ” እያልሽ እራስሽን በማጃጃል እንደፈለግሽ ሆነሽ ልጓም እንደሌለው ፈረስ እየፋነንሽ ለመኖር ከሆነ የሄድሽው እኔ አይደለሁም እሱ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ወርዶ ቢነግርሽ እንደማትሰሚው እርግጠና ነኝ ፈልገሽ የሄድሽው እሱን አይደለምና፡፡
እኅቴ እንዲያው ሌላው ሁሉ ይቅር እነዚህ ሃይማኖት ነን ባይ ድርጅቶች እኮ በሚገባ እንምታውቂው ሁሉ ግብረሰዶምን ተቀብለው ሥርዓት እየፈጸሙ ወንድን ከወንድ ሴትን ከሴት የሚያጋቡ እርኩሶች ናቸው፡፡ የሃይማኖት መሪዎቻቸውም ይሄንን ጸያፍ እርኩሰት የሚፈጸሙ መሆናቸውን በግልጽ በአደባባይ ይናገራሉ፡፡ ሀገር ውስጥ ያሉት የእነዚህ እርኩሶች ቅርንጫፎች መሆናቸውንና ያቋቋሟቸው ወይም የመሠረቷቸውም እነዚሁ እንደሆኑ ታውቂያለሽ፡፡ ስም መጥቀስ ሳያስፈልገኝ ከዐሥር ዓመታት በፊት አንድ የእናንተ የእምነት ድርጅት መሪ “ግብረ ሰዶማዊ የሆነ ሰው የእኛ አባል መሆን ይችላል” ብለው መግለጫ ሰጥተው ከሀገራችን ባሕልና ሕግ የሚጻረር አቋም በመሆኑ ውዝግብ ተነሥቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ እንግዲህ ይሄንን ሁሉ ጉድ እያየሽ እንዴት ሃይማኖት ነው እድንበታለሁ ብለሽ ልትኖሪበት ቻልሽ? ይሄ ሁሉ ጉድ የሚሠራባቸው መንፈስ የዲያብሎስ መንፈስ እንደሆነ አያመለክትሽም? እንዳታስተውዪ ያደረገሽ የክፉ መንፈስ አዚም ነውና ክርስቶስ ይስበርልሽ፡፡
አብሶ ደግሞ ሰው ኢትዮጵያዊ ሆኖ መናፍቅ ሲሆን እጅግ የሚገርም ነገር ነው እኛ እኮ ልጆቹ ሕዝቡ እንደሆንን በቃሉ በአንደበቱ የመሰከረልን ክቡር ሕዝብ ነን “የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላቹህምን ይላል እግዚአብሔር” ትን. አሞ.9፤7 ከእግዚአብሔር ልጅነት ነው የኮበለልሽው ተመለሽ ተመለሽ ተመለሽ “በፊቱ ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ ጠላቶቹም አፈርን ይልሳሉ” መዝ.71፤9 ተብሎ እግዚአብሔርን አምላኪነታችን የተጻፈልን የተመሰከረልን ሕዝብ ነን፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ኪዳናት አስቀድሞም በሕገ ልቡና እግዚአብሔርን ያመለክን በዓለም ብቸኛ ሕዝብ እንደሆንን ታውቂ ይሆን? ታዲያ እኛ ነን ለሌላው መመስከር ያለብን ወይስ ሌላው ለእኛ? ማንም ከእግዚአብሔር ጋራ ምንም ዓይነት ትውውቅ ያልነበረው አረማዊ ሁሉ ያውም ለእኛ ምንም የማለት ሞራላዊም ሆነ መንፈሳዊ ብቃት አለው ብለሽ ታምኛለሽ? ሲጀመር የእነዚህ ሰዎች ዓላማ ሰውን ሃይማኖተኛ ማድረግ አይደለም፡፡
ታሪክን ታውቂ እንደሆን ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ገብተው ለቅኝ ግዛት መሰለልና ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር በማሳጣት፣ ማንነታቸውን በማስካድ ለቅኝ ግዛት ማመቻቸት ነበር፡፡ አንጋፋው የኬንያ መሪ ጆሞ ኬንያታ ያሉትን አልሰማሽም “ ሃይማኖትን እንስበክላቹህ ብለው መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው ገቡና ሰበኩን ስትጸልዩም አንገታቹህን ደፍታቹህ ዐይናቹህን ጨፍኑ አሉን እኛም እንደዚያው አደረግን ዐይናችንን ገልጠን ቀና ስንል ግን መሬታችንን ሁለ ነገራችንን ወስደውት በእጃችንም ላይ ካቴና ገብቶ የእነሱ ባሪያ ሆነን እራሳችንን አገኘነው” ብለው ነበር፡፡
ዛሬም ቢሆን ቅኝ ግዛት መልኩን ቀየረ እንጅ አልቀረምና እናንተ ላይ ሲንጸባረቅ እንደምናየው ሁሉ ዓላማቸውና ተግባራቸው ይሄው ነው፡፡ ከእነሱ ጋራ ስትተባበሪ ለሀገርሽ ለታሪክሽ ለሕዝብሽና ለማንነትሽ ጠላት እየሆንሽ እንደሆነ ተረጂ፡፡ ከእነዚህ ወገኖች ጋራ ኖረሽ ዐይተሽ እንደተረዳሽው ያላቸው አቋምና ስሜታቸው ሁሉ ፀረ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የሀገር ፍቅር ስሜት የሚባል ነገር ጨርሶ የላቸውም፡፡ እንዲህ ሆናቹህ ለመቀረጻቹህ የእነዚያ ባዕዳን ሰባኪዎቻቹህ ሚና ሙሉ ድርሻ አለው፡፡ ለባሕላችን ለማንነታችን ለቅርሶቻችን ለእሴቶቻችን ሁሉ ዴንታ የላቹህም ብቻ ሳይሆን ለማጥፋትም ታጥቃቹህ ትሠራላቹህ፡፡ እንደዜጋ እንደ ኢትዮጵያዊ የራሳቹህ እንደሆነ አይሰማቹህም፡፡ ይሄ ባንዳነት ነው ከዚህ የከፋ ባንዳነት የለም፡፡ እናም ከሁለቱም በኩል በሃይማኖቱም በፖለቲካውም ፋይዳና ትክክለኝነት መሠረት የሌላቹህ የጥፋትና የክህደት ማዕከላት ናቹህ፡፡ ለአንድ ዜጋ ከዚህ በላይ ሞት አለው ብየ አላስብም፡፡
እኅቴ ወ/ሮ ሚሊ ኢትዮጵያዊነትሽን ማንነትሽን ስርሽን የምትወጅው የምታከብሪውና የምትኮሪበትም ከሆነ ውጪ ከእነሱ ተለዪ ራቂ ወደማንነትሽ ተመለሺ፡፡ በምንም መመዘኛ ባንዳነት ክህደት፣ ውርደት፣ ሞት እንጅ ኩራት ክብር አይደለምና፡፡ በእውነት እንዲህ በመሆንሽ ልታፍሪ ይገባል እራስሽን ነው ያዋረድሽው፡፡ ለራስሽ ያለሽን ዝቅተኛ ግምት ነው ያሳየሽው፡፡ ይሄ ሁሉ ጉድ እያለ ማስተዋል ተስኖሽ በዚህ ውስጥ መቆየትሽ መቀጠልሽም ያለሽን ደካማ የብስለትና የማስተዋል የንቃት ደረጃና ብቃት ያሳያል፡፡ ያንችን ብቻ ሳይሆን እዚያ ካምፕ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንንም ሁሉ ነው፡፡ በዚህ ያላፈርሽ በሌላ በምንም ነገር ልታፍሪ አትችይም፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩልሽ (ትን. አሞጽ 9፤7) ኢትዮጵያዊነት ማለት የእግዚአብሔር ልጅነት ማለት ነው፡፡ ወደ እግዚአብሔር ልጅነትሽ ተመለሽ፡፡ ኢትዮጵያዊነትሽን ጠብቀሽ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንሽ ጸንቶ የመኖር እናት አባቶቻችን የጣሉብሽን አደራ መጠበቅ መወጣት ይኖርብሻል፡፡ ተመለሺ ተመለሺ ተመለሺ፡፡
እኅቴ ይህቺ ሃይማኖት ብቸኛዋ የእውነት መንገድ እንደመሆኗ መጠን ሰይጣን እጅግ ይፈታተናታል፡፡ ከዚህ የተነሣ ምናልባት አንዳንድ ደስ የማያሰኝ ነገር ብታዪ ቢያጋጥምሽ ወደ እግዚአብሔር እያመለከቱ ያንን ጠንክሮ መዋጋት ነው እንጅ መጥፋቱ መውጣቱ መፍትሔ አይደለም፡፡ እባክሽን እኅቴ ይሄ የሞትና የሕይዎት የጽድቅና የኩነኔ ጉዳይ ነውና እንደቀላል እንደዋዛ እንደ ቀልድ አትይው፡፡ ከዚህ በላይ ሊያሳስብሽ የሚገባ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ከሕይዎት በላይ ምን ሊያሳስብ የሚገባ ነገር ሊኖር ይችላል?
ለማንኛውም እኅቴ እውነቱ ይሄው ነው ከእነዚህ ሰዎች ጋራ እንደመኖርሽ የታዘብሽው ብዙ ሌሎች ነገሮች ይኖራሉ ብየ አምናለሁ፡፡ እስኪ ልብ ብለሽ ተመልከቻቸው ጤነኞች ናቸው? የሥነ ልቡና ችግር ያለባቸው ንኮች አይደሉም? የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ልቡናሽን ያብራልሽ እውነትን ይግለጥልሽ ከሞት ከጨለማ ከአውሬው እጅ ይታደግሽ፡፡ አሜን! አሜን! አሜን!
amsalugkidan@gmail.com
Tamirat fikadu says
እዉነትህ ነዉ ወዳጀ እዉነት በሆድ ይዘዉ ለገንዘብ ሲሉ ሀሰትን ከሚሰብኩ አዉሬዎች የቅድስት ድንግል ማሪያም ልጅ መደሀኒት አለም ይጠብቀን አሜን!!!
Abel H/mariam says
ትምክህት 101… ደሞ ሀይማኖት መስበክ ጀመራችሁልኝ… kikiki
Easak atlaw says
Tkkl blehal bzu sewoch emnetachewn yemikeyrut lebr new
Maru says
Betam rikashi kalatin bemetekemih mamenetih tawukol
Bini says
Seali amesalu, TSEHUFEHEN anebebkut. ye mejemeriyaw 5 anqtseoch(paragrpahs) betam arif neberu. enem bante esmamalehugn. ye lelawun sew haymanot meneqef ene becha tekekele negn, be leleoch beyahmanot west yalu sewoch behatiyat new yeminorut be hatiyat new malet alemebsel new. Haymanot science aydelem. ye emenet guday new ke lib gar becha yemigenagn. leleawun mefred ayegebam. lezih new i agree only in the first 5 pargraphs yalkeh. keza behuala yetsafekew gin, ante yewekeskat setyo yaderegechewen new antem ayderkew. tadiya yanet ena yesua liyunet mindenew. esua orthodox haymanoten ankuasheshech, ante degmo ke orthodx wechi yaluten hulu ankuasheshek. RESPECT!
Kas Kebede says
Well said… thanks bro. It is a must read .. those of you who are wasting your time through the bad spirit spread by wealth seeker pastors, take your time to read and return to the truth. God bless all.
gashaw says
very impressive!! God bless
yegeta negn says
e/r yimarik !besimet sayhon beslet maletim bewinet lay yetemeserete neger bintsif tiru new lemanignawim bible anbib lemetechet sayhon lemedan.
Misgana says
Nothing spritual in your post. Though, you qoute from the Bible not in its full context. You used Bible verses only for your hatred politics. You are hatred filled politician not the disciple of Jesus who preached love in word and did. The way to salivation is not religion but Jesus who proclaimed Himself so. ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም
ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
Jhon 14: 6
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት
እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር
አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ
ወዶአልና። Jhon 3:16
You are only accuser which is Devils’ behavior according to the Bible. You are hattred filled that is typical to Satan. Your objective is purely politics as I can see. Protestant christians are protesters against those are contrary to Gods’ Word. We love our country and our fellow brothers regaedless of their differences in religion, race etc. Don’t you know in Ethiopia, there are protestants who are beaten even killed for holding Truth and siding public in the former regime. Come out of darkness and be man of peace. Don’t accuse people for their religious prefferences.
God is Love!
Amsalu G/kidan Argaw says
You do not understand @ Misgana, those all proverbs (quotations) are not mine, the proverbs are God’s word. So you are not blaming me, you are blaming God. Please read again and again until you got understand please? I am not the one who said them false prophet, gluttons, devils, disciples of devil, dead faith etc.
Do you believe in bible? If you say yes, so how you reject the word “one Jesus, one Faith, one Baptism” Eph.4:5 and the other quotations I quoted in the article? Please, read attentively forget your early thinking and wrong understanding about the Lord Jesus and Faith (Religion) .
Yes indeed God is love, but you haven’t the real God. Because what you believe about God and his identity is wrong. I never hate any one, but I hate their bad works and habits as the Lord Jesus Christ expect me to do. So I condemn the Heresies acts (preaching homosexuality and others) and I avoid them as I should be as a Christian. The word of God ordered me to do so. Is that hatred? You do not understand this is not about ethical case this is about religion, this is about Jesus Christ not about something another. You are protesting the one Lord (Jesus) …. Ok? you have no unity even among your selves (protestant) about many things not only about Jesus, you create new new Jesus every day. This is ridiculous. Do not try denying the truth, do not make yourself the accomplishment of prophecy, do not cheat yourself, wake up brother?
“I am the way, the truth, and the life. No one comes to the Father except through Me.” Yes that is undeniable. I never said there is another way of salvation. What I have been wrote is about the Way, the Faith, the Religion that makes us to find the real Jesus Christ OK? And now I need to quote this Lord Jesus word “He who receives you (his holy disciples) receives Me, and He who receives Me receives Him who sent Me. He who receives a prophet in the name of a prophet shall receive a prophet’s reward. And He who receives a righteous man in the name of a righteous man shall receive a righteous man reward. And who ever gives one of those little ones only a cup of cold water in the name of a disciple, assuredly , I say to you, He shall by no means lose his reward” Matt. 10:40-42 this means He who do not receives them (his holy disciples) do not receives Him. Haven’t you heard that Lord’s word before? I doubt it, you have nothing in your hands.
“ remember those who rule over you, who have spoken the word of God to you, whose faith follow, considering the out com of their conduct. Jesus Christ is the same yesterday, today, and forever. Don’t be carried about with various and strange doctrines. For it is good that heart be established by grace, not with foods which have not profited those who have been occupied with them.” Heb. 13:7 you are protesting that word of God.
one Jesus Christ!
Amsalu
abebe says
“(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)” መቀየር የሚያስፈልገው ራስን ወይስ ሃይማኖትን? በማለት ላቀረብከው ሃሳብ ነው ምላሽ የሰጠሁህ
የሠዓሊነት ማዕረጉ ከስነመለኮት ትንተና ጋር ያለው ግንኙነት አልታይ ቢለኝም ማስታወቂያ ካልሆነ ማለቴ ነው ለማስተካከል የተፈለገውን ሃሳብ በሌላ ጠብአጫሪ ቃላቶች ማስተካከል መፈለግ አስገራሚ አድርጎብኛል..ለምሳሌ “…ሆን ተብሎ ለማጥቃት የሚሰነዘሩ እኩይና አጥቂ ቃላቶች ናቸው እንጂ፡፡ እነዚህ ሰዎች ማንንም ማጥቃት ሳያስፈልጋቸው ፕሮቴስታንት (ተቃዋሚ) ሆንኩ በማለት ያላቸውን ለውጥ መግለጥ የሚችሉበት ዕድል ነበር፡፡ በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር የብዙኃን መገናኛዎቹ ለእነዚህ ሰዎች እንዴት ይሄንን ጥቃት ለመፈጸሚያ መገልገያ መጠቀሚያ ለመሆን እንደሚፈቅዱና ጥቃቱን እንደሚያስተናግዱ ነው፡፡…” መገናኛ ብዙሃን ማለት የትኛውን ሃሳብ ብቻ ማስተናገድ አለባቸው…ፕሮቴስታንት የሚለውን ስያሜ እራሳቸው የሚጠሩበት ነው ወይስ አንተን መሰሎች የሚጠሩበት ነው?ማወቅ ከፈለክ ግን ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች ብለው ነው ራሳቸውን የሚጠሩበት፡፡
መቼም አቃቤ እምነት ለመሆን ስለምትጥር .መቼም ምኞትህ ጥሩ ቢሆንም .ያለ በቂ መፍጻሃፍ ቅዱሳዊ አውድና ሹመት ያው እንደገለጽከው በሰዓሊነት..መጽሓፍ ቅዱስ ስዕል አይደለም.. በቂ ጥናት የሚፈልግ ሲሆን ይህ የመደዴ ዘመን አይደለም እና አንዳንድ ጉዳዮች ላስታውስህ፡፡
….ይሄንን ያልኩት እኔ አይደለሁም የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፡፡ “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ. 4፤5 ይህች አንዲት ሃይማኖት ከአዳም ጀምሮ ነበረች እስከ ዓለም ፍጻሜም ትኖራለች፡፡ ክርስትናና ይሁዲነት (ሐዲስ ኪዳንና ብሉይ ኪዳን) ወይም ሐዲስና ኦሪት በአንዲቷ ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ኪዳናት ናቸው እንጂ ሃይማኖቶች አይደሉም፡፡
ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም… ማን ነው ታዲያ…አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…የኤፌሶን ጸሓፊ አንዲት ነበረች አንዲት ትናራለች ነው ያለው? ይህ መጽሓፍ ቅዱስን ሳይማሩ ለማስተማር የሚሞክሩ ደፋሮች አተረጓገጎም ነው፡፡ ባንተ አተረጓገጎም ይህን ጽሁፍ በተጻፈበት ጊዜ የነበረችው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስለነበረች የሮም ማለቴ ነው እኔ ባለቤቱ ነኝ ትለው ነበርና ያቺ አንዱዋ እኔ የምላት ነች ለማለት ትጠቀምበት ነበር ግን ሊሆነ አይችልም፡፡ አሁን አንደ.ይሁንና ..አንዲት እምነት ያለው አንድነትን ለመጠበቅ ትጉ ኑሮአችሁና ትምህርታችሁ ይመሳሰል ለማለት እንጂ ያኛው ልክና ያህኛው ልክ አይደለም ለማለት የተቀመጠ አይደለም፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ሓዋሪያው ጳውሎስ ክርስትናና ይሁዲነት አንድ ናቸው አይልም፡፡ ክርስትናና ይሁዲነት ፈጽሞ ሊታረቁ የማይችሉ እውነታዎች ናቸው ኢየሡስ አምላክ ነው እና ኢየሡስ አታላይ ነው ብሎ በማመን ያህል ያለ ልዩነት ነው ያለው የሰቀሉትም ለዚህ ነው፡፡ ብሉይና አዲስ ኪዳንም የአካልና የጥላ መካከል ያለ ልዩነት ስለሆነ አንድም አይደሉም፡፡ በአሮጌና በአዲስ መካከል ያሉ ልዩነቶች ናቸው፡፡ ኦሪት ያረጀና ወደሱም ሲዞሩ ኦሪት የሚያደርግ ሲሆን ወደ አዲስ ኪዳን ሲዞር ግን መንፈስና ጌታን ወደሆነው ወደ ክርስቶስ የሚታይበት የተባረከ መገለጥና ብርሃን የሚበራበት ማእከል መመልከት ነው፡፡
ሰዓሊውና ፈሪሳዊው ወንድሜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አሁን አንተ ልትሙዋገትላት እንደምትፈልገው አይነት ቤተክርስቲያን አይደለችም፡፡ እንዳንተ አይነት ሳይማሩ ለማስተማር ፓለቲካውን ከእግዚአብሔር ቃል ቀላቅለው..ፓለቲካ መልካም አስተዳደርን ለማምጣት ቢነካኩት ምንም አይደለም ሰውን ለማጥቃት ለመዝረፍ ለመሳደብና ለመግደል ሰይጣናዊ ስራን ለመስራት ምሽግ የሚያደርጉበት አይደለም፡፡ ነገር ግን እውነትን በፍቅር ለመግለጽ እድሜውም ብቃትም እውቀትም ስላላት ከኦርቶዶክስ ቤተእምነት ውጪ ያለን ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች ብንሆንም ደግሞ በአክብሮት የምንሰማት ስለሆነች ባንተ ያልተገራ ንግግር ቤተክርስቲያኑዋን አንመዝንም፡፡ እጅግ የተከበሩ እውነትን የሚያውቁ ያወቁትን የሚኖሩ የበዙባት ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ያ ማለት ግን ክርስቶስን ሳያውቁ በውስጥዋ የሚኖሩ የሉም ማለት አይቻልም አንተ ወንድማችን በከፍተኛ ወኔ ባገኘከው እድል ያሻህን ለማለት መፈለግህን ስለምታሳየን ኢየሱስ እንዳልገባህ ቃላቶችህ ምስክር ናቸው፡፡
……ከእነዚህ ወገኖች ጋራ ኖረሽ ዐይተሽ እንደተረዳሽው ያላቸው አቋምና ስሜታቸው ሁሉ ፀረ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የሀገር ፍቅር ስሜት የሚባል ነገር ጨርሶ የላቸውም፡፡”
ደፋሩ ፈሪሳዊው ወንድማችን የራሱን ስሜት እንኩዋን በቅጡ የማያውቀው ቢያንስ 16 ሚሊዮን የሚሆንን ቁጥር ያለው ህዝብ ሲጨረግድ ያው ያለፍርሃትና ያለሃፍረት በመሆኑ እገረምበታለሁ፡፡ የምድር ባለቤት እግዚአብሔር እስከሆነ ድረስ የማንም ስሜት የማንንም ስሜት ሊለካ ስለማይችል አሜሪካ ቁጭ ብሎ ኢትዮጵያዊ ማነው የሚል ትንታኔ ለመስጠት የበለጠ ኢትዮጵያዊ እኔነኝ ለማለት ማሰብ ያስገርማል ፡፡ ሓዋሪያት ስራ 17፤26 እያንዳንዱ የሚኖርበትን ዳርቻና የሚኖርቡትን ልክ ወሰነላቸው ስለሚል አንተ ከዳርቻው ውጪ ስለሆንክ ኢትዮጵያዊ ነኝ ልትል አትችልም ኢትዮጵያዊ ሆነህ ከእግዚአብሔር የተሰጠህን ትእዛዝ ለመፈጸም ተልከህ ካልሆነ..ያረከውን አርገህ ፈርጥጠህ ተከባብሮና ተቀባብሎ የሚኖርን ህዝብ ለመሸንሸን ማንነት ይጎድልሃል፡፡ ሰዓሊው ..በንግግር ደረጃ እራስን ከሾመው ሰአሊው መናገር ቢያስፈልግ ኢትዮጵያዊ አለመሆንህን ልነግር እችል ነበር ቢያንስ አሁን እኔ የምኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ ስሆን ደስታዋን መከራዋን ስቃዩዋን አብሬ የእለት ከእለት ትንፋሹዋን የምምጋት ደግሞም ሓገር ማለት መሬቱ ሳይሆን ሃገር ማለት እኔ ነበርኩ! ቢያስፈልግ ኢትዮጵያዊነት መመዘኛ ነጽብ እኔ መሆኔን እገልጽልሃለሁ፡፡
ለማንኛውም መዘላበድህን ትተህ ቁጭ ብለህ አንዱን ያዘው ዘመኑ የፐሮፌሺናሊዝም ዘመን ነው፡፡
ይታደግሽ፡፡ አሜን! አሜን! አሜን!…
አሜን እግዚብሔር ማለትና አሜን ይሁን ማለት ነው፡፡ ሰው እራሱ ተነግሮ እርሱው ንግግሩ ይሁን የሚል ከሆነ ድግምት ወይም አስማት ነው ፡፡ አሜን የሚለው ቃል ስራ ላይ የሚውለው እንደእግዚአብሔር ቃል ስንናገርና …ቀጥሎም ጥያቄአችንን በራሱ በተሰጠን መመሪያ መሰረት ይሁንልን ብለን ስንጠይቅ ነው፡፡ በስሜ የምትጠይቁትን እኔ አደርገዋለሁ ሲል ጌታችን ኢየሡስ ክርስቶስ ስለተናገረ.. በኢየሠሱስ ክርስቶስ ስም ይሁንልን ማለት ነው፡፡ሸ ስለዚህ እባክህ ቁጭ ብለህ ሓገር ያቆሙ ዘመን ያሻገሩ የተከበሩና ያስከበሩ አባቶች ስላሉ ከነርሱ ተማር፡፡
አበበ ነኝ ኢትዮጵያ
Amsalu G/kidan Argaw says
አቶ አበበ በጣም ትገርማለህ እኔን ያለሞያህ በማታውቀው ነገር ዘባረክ እያልክ አንተ ብሰህ መገኘትህ ገርሞኛል፡፡ ነው ወይስ አንተ የሥነ-መለኮት ሊቅ ነህ? አዎ እንዳትለኝና ጉድ እንዳታሰኘኝ፡፡ ነገሩ ደፋሮች አይደላቹህ ትላለህ እኮ አታፍርም፡፡ ሲጀመር እኔ የሥነ-መለኮት ሊቅ ነኝ አላልኩም ቃሉ “በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋቹህ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃቹህ ሁኑ” 1ኛ ጴጥ. 3፤15 ይላልና ቃሉ አማኝ ሆኘ በሃይማኖት ውስጥ ስኖር ስለ አምላኬ ላውቀው የሚገባኝንና ያወኩትን ነው ለመመስከር የሞከርኩት፡፡ ይሄንን ለማድረግ የሥነ መለኮት ሊቅ መባል የግድ አይጠበቅብኝም ክርስቲያን መሆኔ በቂ ነው እሽ? በክርስቲያንነቴ ግዴታ አለብኝ፡፡
“ጳውሎስ አንድነትን ለመጠበቅ ትጉ ኑሯቹህ ትምህርታቹህ ይመሳሰል ለማለት እንጅ ይሄኛው ልክ ነው ያኛው ልክ አይደለም ለማለት አይደለም” ነበር ያልከው? የምትለው የጨነቀህ ትመስላለህ፤ እውነት አስጨንቅሀለች፤ እንዳታምን ማመን አትፈልግም ዝም እንዳትል ደግሞ የሕሊናህ ጩኸት እረፍት ነሳህ እሱን ያስታገስክ መስሎህ ምን ይሉኛል ብለህ ሳትጨነቅ ጨርሶ የማይመስልን ነገር ቀበጣጥረህ አረፍከው፡፡ ይገርማል በቃ ይህችን ታክል ናት እውቀትህ? አዎ በእርግጥ ስለማታውቅማ ነው የሳትከው ስለዚህ ለዚህ ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ለሆነው ምላሽህ መደነቅ የለብኝም፡፡ ነገር ግን እንዲህ ግልጽ ሆኖ የተጻፈን ነገር መረዳት ባለመቻልህ እጅግ መደነቄን ሳልነግርህ አላልፍም፡፡ ለነገሩ መረዳት ባለመቻልህ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ቃሉ እንዳለው ሆድህን ወደህ እውነትን በሆድ ለውጠሀትም ሊሆን ይችላል፡፡
ጥሩ “የመጀመሪያዋን እምነት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና” ዕብ. 3፤14 ይሄስ ምን ማለት ነው? ከመጀመሪያዋ በስተቀር በኋለኛው ዘመን የሚመጡት በሐሳዊያኑ ሆዳቸው አምላካቸው ክብራቸው በነውራቸው በሆኑት የተመሠረቱት ድርጅቶች ትክክል ናቸው ማለት ነው አይደል? አየ አንተ! እስኪ ጆሮህክ ክፍት አድርግና አዳምጥ? ይሄውልህ ሲጀመር እነዚህ ከ33,000 በላይ የሆኑ የክርስትና ሃይማኖት ነን የሚሉ ድርጅቶች የተለያየ የሚለያዩበት አስተምህሮ ባይኖራቸው ኖሮ ባልተለያዩም ነበር፡፡ ነገር ግን የሚያለያያቸው ነገር ስላለ ተለያዩ ቁጥራቸውም እዚህ ሊደርስ ቻለ፡፡ አቶ አበበ አንተ ስታስበው ሁሉም ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚያወሩት የሚያምኑት የተለያየ ሆኖ እያለ እንዴት ሁሉም ልክ ሊሆኑ ይችላሉ? ቃሉን ተወው አሌ ብለኸዋልና ነገር ግን እንዲያው በአመክንዮ (በሎጂክ) ዐይን ስታየው ሁሉም የሚያወሩት የተለያየ ሆኖ እያለ እንዴት ሁሉም ልክ ሊሆኑ ይችላሉ? ዐየህ ምን ያህል እንደደነቆርክ? ይሄ ጥያቄ እኮ ገና አፉን የፈታ ሕፃን ሳይቀር በቀላሉ ሊመልሰው የሚችለው ጥያቄ ነው፡፡ ችግርህ ገብቶኛል ሳታውቀው ቀርተህም ላይሆን ይችላል ከላይ እንዳልኩት ሆድህን መውደድህ ነው እንዳታስተውል ወይም ለምታውቀው ነገር ግን ለማትኖረው እውነት እንዳትገዛ ያደረገህ፡፡
ለማንኛውም ቃሉ በጣም ግልጽ ነው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ.4፤5 ይሄ ማለት አንዱ ብቻ ነው ልክ ሌላኛው አይደለም ማለት አይደለም ስትል ጌታም አንድ አይደለም ብዙ ነው ጥምቀትም አንዲት አይደለችም ብዙ ናት ማለትህ እንደሆነ ገብቶሀል? ጌታንም ሐዋርያው ጳውሎስንም ውሸታም እያልክ እንደሆነስ ገብቶሀል? “በዚያ ጊዜ ማንም እነሆ ክርስቶስ እዚያ አለ ወይም እዚህ አለ ቢላቹህ አትመኑ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉና ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ፡፡ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳቹህ” ማቴ. 24፤23-25 ይሄ የጌታ ቃልና ጽሑፉ ላይ የጠቀስኳቸው ቅዱስ ጳውሎስ የአጋንንትን ስብከት እያዳመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ እያለ የተናገራቸው ቅዱስ ያዕቆብ ሥራ የተለረው እምነት የሞተ ነው እያለ የገለጸው እነኝህ ሁሉ ውሸት ናቸው ማለት ነዋ! እውነት ከሆኑ ደግሞ ከአንዱ በስተቀር 33,999 ኙ ሃይማኖት ነኝ ባይ አወናባጅ የአውሬው ድርጅት ሁሉ ሐሰተኛና የጥፋት መሆናቸው ግድ ነው፡፡ እነዚህ ከጊዜ በኋላ የተፈጠሩትና አሁንም በየቀኑ የየሚፈጠሩት አዳዲሶቹም ካልሆኑ ሌላ ማን ሊሆን ይችላል? ምስጋና ለእሱ ይሁንና ቃሎቹስ ውሸት አይደሉም እውነት ናቸው የአምላክ ቃል ናቸውና ይሄው በእናንተ ላይ ተፈጽሞም እያየን ነው፡፡ ጌታ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳቹህ ያለባቹህ፣ ቅዱስ ጳውሎስ እያለቀስኩ እላቹሀለሁ ከእነሱ እራቁ ያለባቹህ እናንተ ናቹህ፡፡ ወዮ ለእናንተ ከእውነት ይልቅ ሆዳቹህ ለበለጠባቹህ ዲያብሎስን ለምታገለግሉና ለምታመልኩም፤ ጌታ በፊቱ እሳት እየነደደ ለመፍረድ ሲመጣ በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ በማይጠቅም ለቅሶና ዋይታ በግራው ለፍርድ ትቆማላቹህና፡፡ ከግብር አባታቹህ ከዲያብሎስና ከሠራዊቱም ጋራ ወደ ዘለዓለም እሳት ትጣላላቹህ፡፡ በእርግጥ አንተም እንደ የጥፋት መልእክተኛነትህ ቃሉን እውነት ነው እንድትል አይጠበቅብህም፡፡
“ይህ ጥቅስ በተጻፈበት ወቅት የነበረችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስለነበረች ካቶሊኮች ለእኛ የተነገረ ነው ይሉ ነበር” ነው ያልከው? እንዲያው ግን አታፍርም? አእላፋት በሚያዩት በሚያነቡት መካነ ድር ላይ ዝም ብለህ ጨርሶ የማታውቀውን ነገር በግምት ትቀባጥራለህ? ካቶሊኮችም ከቤተክርስቲያን በመነጠል ካቶሊክነትን ከማወጃቸው በፊት ቤተክርስቲያን አንድ እያለች የሐዋርያት አለቃ የሆነው ጌታም የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ ቁልፍ የሰጠው ጴጥሮስ መንበሩ ከእኛ ነውና እኛ የበላይ ነን ይሉ ነበር እንጅ ይሄንን አንተ ያልከውን እንደማይሉ መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን በገጠማት አጋንንታዊ ፈተና ምዕራቦቹ አዲስ አስተምህሮ በማብጣታቸው በምሥራቅና በምዕራብ ተከፍላ የተለዩት የወጡት ምዕራባዊያኑ ካቶሊክ (የሁሉም) ነባሩ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (ነባር፣ ቀጥተኛ) ተብሎ ስም የወጣላቸው 451ዓ.ም. በኬልቄዶኑ ጉባኤ ነው እሽ? እስከዚያ ዘመን ድረስ የዚህ የዚህ የሚባል ቅጽል ስም አልነበረም፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ብቸኛዋ ትክክለኛ ሃይማኖት ናት ብየ ስል ይሄ ስሟ ኤርሚያስ በ6፤16 ላይ ጳውሎስ በኤፌ. 4፤5 ላይና ዕብ. 3፤14 ላይ ስለ እሷ በተናገሩበት ዘመን ነበረ እያልኩ አይደለም፡፡ አታስተውልም እንጂ እዛው ላይ ገልጨዋለሁ በዚህች ሃይማኖት ውስጥ ሁለቱም ኪዳናት ጊዜያቸውን ጠብቀው ተፈጽመዋል ብያለሁ፡፡ ስለዚህ ይህች ሃይማኖት አሁን የተሰጣት ክርስቲያናዊ ሥያሜ በብሉይ ዘመንና በሐዲስም እስከ አምስተኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ አልነበረም ማለት ነው፡፡ ነግር ግን በየ ኪዳናቱ ዘመን በወቅቱ ያለውን ኪዳን በሚያመለክት መልኩ ስሞች ነበሯት፡፡ እነዚያም ስሞች ሁለቴ ተቀያይረዋል፡፡ ሥሟ ይቀያየር እንጅ እሷ ግን ያችው እሷ ናት አልተለወጠችም፡፡ ይህች ትክክለኛ ሃይማኖት ያለችው በአምስቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት (oriental Churches) ሀገራት ነው፡፡ እነሱም በኢትዮጵያ፣ በግብጽ፣ በሶሪያ፣ በአርመንና በሕንድ፡፡ በዚህ በዘመኑ ፍጻሜ ግን ከአውሬው ውጊያ ብርታት የተነሣ በአንዳንዶቹ አስተምህሯቸውን የሚለውጥ ችግር እየተፈጠረባቸው ነው፡፡
“ጳውሎስ አይሁድነትና ክርስትና አንድ ናቸው አላለም” ነበር ያልከው? እንጭጭ የሆነን ሰው ማስረዳት እንዴት አስቸጋሪ ነው ባካቹህ? እሽ ጳውሎስ የት ቦታ ላይ ነው አንድ አይደሉም ሁለቱ የማይጣጣሙ የሚቃረኑ ናቸው ያለው? ወንድሜ በኦሪት ውስጥ ሐዲስ እንደነበረች ያለ ኦሪት ሐዲስ እንደማትኖር አታውቅም? ሐዲስ ጊዜዋ ሲደርስ ለመወለድ በእናቷ በኦሪት ማሕጸን ነበረች፡፡ ኦሪትና ነቢያት ስለ መሲሑ ስለ ክርስቶስ ትንቢት መናገራቸውን፣ ሱባኤ መቁጠራቸውን፣ በተስፋ መጠበቃቸውን አታውቅም? ይሁዲነት(ኦሪት) የማን ነው? ማንስ ነው የመሠረተው? ነቢያቱ የማን ናቸው? ሕግጋቱስ የማን ናቸው? የእግዚአብሔር አይደሉምን? ሲባል ሰምተሀል፤ በእርግጥ ሙሴ በመሥፍንነቱ ለአሥተዳደር እንዲያመቸው የደነገጋቸው ሕጎች አዎ ተሽረዋል፡፡ የኃጢአት ማሥተስረያው የበግና የእርግብ ወሥዋዕትም ተሸሮ በአማናዊው በግ በኢየሱስ ክርስቶስ ተተክተዋል፡፡ አሮጌው እርሾ ማለት እነኝህ የተሻሩት ናቸው እንጅ ኦሪትና ነቢያት አይደሉም ምክንያቱም በዚያ ዘመን ለነቢያቱ ለዘለዓለም ለዘለዓለም እያለ የገባቸው ቃልኪዳኖች እንዳለው ሁሉ የዘለዓለምና የማይሻሩ ናቸውና፤ እግዚአብሔር ቃሉን የሚያጥፍ ወይም ውሸታም አይደለምና፡፡ ስለ ኦሪትና ነቢያትማ ክርስቶስ እንዳረጋገጠው “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር አልመጣሁም ልፈጽም እንጅ ለመሻር አልመጣሁም፡፡ እውነት አላቹሀለሁ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም ሁሉ እስኪያልፍ ድረስ” ማቴ. 5፤17- 18 “ነገር ግን ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ያቀላል” ሉቃ. 16፤17 ነው ያለላቸው፡፡
አንተ ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ከአጋንንት በተማርከው ትምህርት “ክርስትናና ይሁዲነት ፈጽሞ ሊታረቁ የማይችሉ እውነታዎች ናቸው” ስትል ዘባረክ፡፡ “ኢየሱስ አምላክ ነው ማለትና ኢየሱስ አታላይ ነው ብሎ የማመን ያህል ልዩነት ነው ያለው የሰቀሉትም ለዚህ ነው” አልክ ለመሆኑ ይሁዲነት ወይም ኦሪት የት ቦታ ላይ ነው ኢየሱስ አምላክ አይደለም አታላይ ነው ያሉት? ይልቁንም አምላክ መሲህ እንደሚወለድና እንደሆነ የአመጻ ልጆች ግን አምላክ መሲሕ አይደለም ብለው እንደሚሰቅሉት በሞቱም አርነት እንደሚያወጣን እንደሚቤዠን ተናገሩ ተነበዩ እንጅ፡፡ ኢሳ.7፤14 ኢሳ. 53፤1-12 ኢሳ. 9፤6 መዝ. 21(22) 12-18 መዝ. 47(48)፤5 መዝ. 34(35)፤ 1-28 ወዘተ. ያንተ ችግር አታውቅም የሚገርመው ያለምንም ሐፍረት ዝም ብለህ በግምት ትዘባርቃለህ፡፡ የቀያፋና የሐና ጉባኤ ማለት ይሁዲነት ወይም ኦሪት ማለት አይደለም እሽ? ስለ አንተ እኔ አፈርኩልህ፡፡ ወይ አልገባኝም አላውቅም ብሎ መጠየቅ አንድ ነገር ነው፡፡ ዐውቃለሁ ብሎ ግን ጨርሶ የማያውቁትን ነገር መዘባረቅ ነውር ነው ያዋርዳልም፡፡
አቶ አበበ ፕሮቴስታንት(ተቃዋሚ) የሚለውን ስም አንተ ነህ ወይ የሰጠኸን ነው ያልከኝ? በጣም የሚገርም ነው፡፡ ባይሆን ስማችን ማንነታችንን ግብራችንን ሥራችንን እያሳበቀብን ስለሆነ ቀይረነዋል በለኝ እንጅ በመላው ዓለም መጠሪያ ስማቹህ እንደሆነ ጭራሽ እኔ ልንገርህ? ይሄ የታወቀ ነገር አይደለም እንዴ? አቶ አበበ እባክህን የምታስተባብለውን ነገር እንኳን ለይተህ ዕወቅ? ያለብህ የክህደት አባዜ ሁሉም የሚያውቀውን ነገር ለመካድ ለማስተባበል ሲያስደፍርህ በግልጽ ትታያለህ፡፡ እባክህ ሰው ምን ይለኛል በል?
አቶ አበበ አሜሪካ ተሁኖ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ስለ ኢትዮጵያ መቆጨት መቆርቆር በፍቅሯ መቃጠል እንዴት ሆኖ ነው የማይቻለው? ወያኔ ነህ እንዴ? በተሰደዱ ወገኖቻችን ላይ ከባድ ጥላቻ ይታይብሀል፡፡ እንዴት ነው የምታስበው? በስንቱስ ጥሬ ሆነህ ትዘልቀዋለህ? አሜሪካ እንደምኖር እንዴት እርግጠኛ ሆነህ ለማውራት እንደደፈርክ ገርሞኛል፡፡ ይሄን ግምትህን እውነት እያስመሰልክ ማውራትህን አትተውም? ለማንኛውም እኔ የምኖረው እዚሁ ሀገሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ለምንም ነገር ብትፈልጉኝ አለሁ፡፡
አዎ ለኢትዮጵያ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ታሪክ፣ ማንነት፣ መለያ ለእሴቶቻችን ሁሉ ፍቅር ተቆርቋሪነት የላቹህም ብያለሁ፡፡ የማናውቅ መሰለህ እንዴ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የምትነጥቋቸውን በጎች ምንም ነገር ለማስተማር ከመሞከራቹህ በፊት የመጀመሪያ እርምጃቹህ የነበራቹህባትን ሃይማኖት፣ የነበራቹህን ማንነት በሙሉ እንዲህ እያላቹህ እርገሙ እያላቹህ ማስረገም አይደለም እንዴ? ባንዳ ብየ ስል ዝም ብየ ከምንም ተነሥቸ ወይም በጥላቻ ይመስልሀል? ነው ወይስ ይሄንን አያውቁም ብለህ ነው? አንተን ሲያስክዱህ እንዴት አደርገው ነው ያስካዱህ? ከመናፍቃን ወላጆች ተወልደህ መናፍቅነትን ከእነሱ ወርሰህ ከሆነ ይሄ እጣ አያጋጥምህም፡፡ ከአንዲቷ ሃይማኖት ወጥተህ ተነጥለህ ጠፍተህ ተጠልፈህ ከሆነ ግን የተቀላቀልካቸው ይሄ አይቀርልህም፡፡ 16 ሚልዮን (አእላፋት) ሆነናል ነው ያለከኝ? ይሄ ሁሉ በግ ተበልቷል? ለቅድስት ቤተክርስቲያን ከዚህ የከበደ ኃዘን አለ? ወዮ ይሄንን ያህል መንጋ ላስበሉት እረኞች! ምንም እንኳን አባት ያልተከለው ተክል መነቀሉ የማይቀር ቢሆንም ክርስቶስ ከሐሰት ከጥፋት ወደ እውነት፣ ከሞት ወደ ሕይዎት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዲመልሳቹህ መጸለይ ግን ግዴታየ ነውና እጸልያለሁ፡፡
አምሳሉ
Amsalu G/kidan Argaw says
የእናት ሀገር የድረሱልኝ ጥሪ ???…
ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡
ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ላይ ፋሽትት ጣሊያን ለሰበው የቅኝ ግዛት ይዞታ ዘለቄታ ሲል በነበረው ስልት (Strategy) ተአማኒነት እንዲኖረው በእውነተኛው ታሪካችን ላይ ሆን ብሎ በክፋት የፈጠረውን ፈጠራ በርዞ የሕዝባችንን አንድነት፣ ሰላም፣ ጥምረት፣ ወንድማማችነት (እኅትማማችነት)፣ መተማመን ለመፈረካከስና ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲጠቀምበት የነበረውን ድርሰት ወያኔ ሐሰት እንደሆነ እያወቀ ነገር ግን ላለው ተመሳሳይ የጥፋት ዓላማ ከወደቀበት በማንሣት የፈጠራ ሠማዕታትን የሚዘክር የመታሰቢያ ሐውልት አስገንብቶ አስመርቋል፡፡ እንደሚታወቀው ፋሺስት ጣሊያን አስቀድሞ የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ክፍል በኋላም መላውን ኢትዮጵያን ይዞ በነበረበት ወቅት ሕዝቡን አዳክሞ ቅኝ አገዛዙን ለማጽናት እንዲያስችለው በፋሺስታዊና የቅኝ አገዛዝ ስልት (Strategy) ሕዝቡን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በሞያ ወይም በሥራ ዓይነቶች ሳይቀር ከፋፍሎ ያናቁር ለማፋጀትና ለማባላት ይጥር እንደነበር ታሪክ ዘግቧል፡፡ ፋሺት ጣሊያን ይህ እኩይ ሴራው ያሰበውን ያህል ሳይሠምርለት ቀርቶ በጀግኖች አርበኞቻችን ድል ተመትቶ ተባረረ፡፡ ነገር ግን ሰላዮቹ ሚሲዮኖችና ሀገር አሳሾቹ ሀገራችንን ለመበቀል ሰላምና አንድነት እንዳይኖራት ለማድረግ ብዙ እኩይ ፈጠራዎቻቸውን እውነት አስመስለው በመጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ዛሬ አሸባሪዎቹ ወያኔ ኦነግና ሻቢያ የኦሮሞን ሕዝብ በሔጦሳና በጨለንቆ ተፈጽሞብሀል የሚሉትን በጅምላ ጡት እጅና ብልት የመቁረጥ ቅጣት ወይም ግፍ ተፈጽሟል ብሎ የጻፈ ሚሲዮን ወይም አሳሽ አንድ እንኳን የለም፡፡ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች እከሌ እከሌ የተባለ ታሪክ ጸሐፊ እንደዚህ በሚለው መጽሐፍ እነደጻፈው እያሉ የጠቀሷቸውን መጻሕፍትም ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቻችንን ሳይቀር አስቸግረን መጻሕፍቱ አሉበት በተባሉ ቦታዎች አፈላልገን ስናነብም በሚገርም ሁኔታ ከሚሉት ጋራ ጨርሶ የማይገናኝና የሌለ ፈጠራ ሆኗል፡፡ ይሄ ምንን ያመለክታል ወገን?
ይሄን ብለው የሚያወሩ ወገኖች ዐፄ ምኒልክ ሀገርን መልሶ አንድ ለማድረግ በዘመቱበት ወቅት ከጦር አበጋዞቻቸው ዋናዋናዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች እንደነበሩ አያውቁም፡፡ ለምሳሌ የጦሩ አበጋዝ (ዋና ሹም ወይም ኃላፊ) ራስ ጎበና ዳጬ ነበሩ፡፡
ጥቂት የማንባል ዜጎች በየሕሊናችን “ወያኔ ይሄንን ሐውልት የሠራው እውን ከማስተዋል ማነስ ብቻ ነው ወይስ ከጀርባው እንዳች ነገር አለው?” የሚለው ጥያቄ እየፈራነውም ልናስበው ሳንፈልገውም ገፍቶ ይመጣብናል፡፡ ገፍቶ ከመጣም በኋላ ልንተወው ወይ ልንመልሰው ለማንፈልገው ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመመለስ ስንሞክር የሆነ አስጨናቂ ስሜት ይጫጫነናል፡፡ የምናውቀውን እውነታም ላለማመን ከራሳችን ጋር ከባድና የማያዋጣ ሙግት እንገጥማለን፡፡ ሳንቋጨውም ባለበት መተውን እንመርጣለን፡፡ አደጋው እንግዲህ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ እንዲህ ያለው አደገኛ ነገር በእንጭጩ መታረም መቀጨት ካልቻለና ጊዜ እያገኘ በሄደ ቁጥር ስር እየሰደደ፣ እየከበደ፣ እየጠነከረ የሚሔድ መሆኑና ካደገ፣ ከከበደ፣ ስር ከሰደደ፣ ከጠነከረና ከአደጋ ቀለበት ውስጥ ከከተተን በኋላ የጠነሰሰውን አደጋ ከመጋት ውጭ ለማረም ለማስተካከል የማንችል መሆኑ፡፡ ከዚህ የሔጦሳና የጨለንቆ የፈጠራ ሠማዕታት የመታሰቢያ ሐውልቶች ከማንም በላይ የደነገጡ ግራ የተጋቡና ያዘኑት በተቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ ታዋቂ የኦሮሞ ልኂቃን ናቸው፡፡ ተፈጽሟል የተባለው ድርጊት እንዲሁ ከመወራቱ ውጪ ለመፈጸሙ አንድም መረጃ እንደሌላ በመግለጽ ጭምር፡፡
ወያኔ ይሄንን የጥፋት ሥራ ከመሥራቱ በፊት ከዚህ ሥራ መቅደም የነበረበትን ሥራ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ያለ እንዳች ማሰለስ ሥራዬ ብሎ በሚገባ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የነበረውን በዘርና በጎጥ ያልተገደበ ያልታጠረ የአንድን ሕዝብና የአንዲት ሀገር አስተሳሰቡን በማፈራረስ ዜጎችን “ወደ ክልልህ” እየተባሉ እስከ መፈናቀልና መሰደድ የደረሰ በዘርና “ክልል” ብሎ በጠራው የሀገር ቅርጫ አጥብቦ ከፋፈለው፡፡ ኢትዮጵያዊነት የመጥፋት ያህል ደበዘዘ፣ ብሔርተኝነት ነገሠ፣ በኢትዮጵያዊነት መለያና ቀለም ቦታ ዘርና ብሔርተኝነት ተተካ፣ ዜግነት በብሔር ተተካ፡፡ በውጤቱም ሀገራዊ (ብሔራዊ) ስሜት ጠፋ ሕዝቡ ተፈራቀቀ ተራራቀ፡፡ ወያኔ ይሄንን እኩይ ሥራ በአጥጋቢ ውጤት እንደሠራ ካመነ በኋላ የእኩይ ዓላማውን ቀጣይ ምዕራፍ በቅርቡ ተግብሯል፡፡ ሦስተኛውንና የዚህን እኩይ ድርጊት የመጨረሻ ምዕራፍ በያዘለት የጊዜ ቀጠሮ ለመከወን ያስባል፡፡
ይህ ዓይነት ዘውጋዊ የእምነተ-አሥተዳደር (የፖለቲካ) አስተሳሰብ ሀገራትን ለምን ዓይነት ችግር እንደዳረገ የዓለም ታሪክ በሚገባ ያስረዳናል፡፡ ሩቅ ሳንሔድ ሩዋንዳን የወሰድን እንደሆነ ለምን ዓይነት አደጋና እልቂት እንደዳረጋት ሁሉም የሚየውቀው የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡ ሩዋንዳዊያን ጣሊያን በእኛ ላይ እንዳደረገው ሁሉ ቅኝ ገዥዎቻቸው በሠሩት የመከፋፈልና የማባላት ሴራ ከደረሰባቸው ከዚያ አሳዛኝና ዘግናኝ የእርስ በእርስ እልቂት በኋላ ዛሬ ላይ ሩዋንዳ ውስጥ እኔ ሁቱ ነኝ እኔ ቱትሲ ነኝ እኔ ትዋ ነኝ በማለት ማንነትን በዘር ለመግለጽ መሞከር የተወገዘና በሕግ የተከለከለ ሆኗል፡፡ አንድ ሩዋንዳዊ ራሱን ማንነቱን ለመግለጽ በፈለገ ጊዜ እኔ ሩዋንዳዊ ነኝ በማለት ነው እራሱን የሚገልጸው፡፡
እኛ ታዲያ ዘርን መሠረት ካደረገው የዘውግ እምነተ-አስተዳደር (ፖለቲካ) አስተሳሰብ ለመውጣትና እኔ ትግሬ ነኝ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፣ እኔ ጉራጌ ነኝ፣ እኔ አማራ ወዘተ. እያልን ማንነታችንን ከኢትዮጵያዊነት አጥበን በዘራችን በመግለጽና አንድነታችንን ከሚከፋፍል የዘውግ ፖለቲካን ለመተው ለመጣል የግድ እንደ ሩዋንዳ ያለ የዘር ፍጅት ውስጥ ማለፍ ይኖርብናል ወይ? ብልጥ ከሌላ ይማራል ነበር ብሂላችን፡፡ ይህ እንዲሆን ካልተፈለገ በስተቀር ይሄንን መረዳት ይሳናቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ ሂደቱም ቁልጭ አድርጎ እያሳየን ያለው ይሄንን እውነት ነው፡፡ የእኛ መሪዎች አቶ መለስን ጨምሮ ሩዋንዳ በየጊዜው የዚህን የዘር ፍጅት ለማሰብ በዓል ባዘጋጀች ቁጥር ይሄዳሉ ሥነ ሥርዓቱንም ተካፍለው ይመጣሉ፡፡ እጅግ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር እያደረጉት ካለው አደገኛና እጅግ ኃላፊነት የጎደለው ሥራቸው መረዳት እንደሚቻለው ሩዋንዳ የሚመላለሱት የዘር ፍጅትን እንዴት ማነሣሣት እንደሚቻልና ከሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ወንጀል ድክመት ጥንካሬውን ተምረው በተሻለ አፈጻጸም እንዴት መከወን እንደሚችሉ ለማጥናት ይመስላል፡፡ አንድነት የነበረውን ሕዝብ እስኪበቃቸው ድረስ እየሰበኩ በዘር በሃይማኖት ከለያዩና ካራራቁ በኋላ ሐሰተኛ ወሬ በመንዛት ቂምና በቀልን በመፍጠር የዘር ፍጅት ለመፍጠር አንዱን ሕዝብ በሌላው ላይ ያነሣሣሉ ይቀሰቅሳሉና፡፡
ይህ እኩይና ሳይጣናዊ ዓላማ ባይኖራቸው ኖሮ ከአንድ መንግሥት በሚጠበቅ ኃላፊነት፤ እንኳን ጠላት ለጥፋት ዓላማው የፈጠረውን ፈጠራ አንሥተው ሊቀሰቅሱ ሊያነሣሱ ይቅርና በትክክል የተፈጸመ የተደረገ ጉዳይ ቢሆንም እንኳ ጉዳዩ ሊፈጥር ከሚችለው የማይፈልግ አደገኛ አሉታዊ ውጤት አንጻር አሁን እያደረጉት ካለው ድርጊት ሁሉ በተቆጠቡ ነበር፡፡ እያደረጉት ያሉት ግን ከዚህ ፍጹም የተቃረነውን ነው፡፡ በሔጦሳና በጨለንቆ ያስገነቧቸውን ሐውልቶች ብናይ እኔ ምን ዓይነት የሞራል (የግብረ ገብ) ደረጃና ሰብእና ቢኖራቸው እንደዚያ ያለ የሚያየውን ሁሉ የሚሰቀጥጥ የሚያስደነግጥና የሚዘገንን ቅርጽና ገጽታ ያለው ሐውልት ለምን ሊያቆሙ እንደቻሉና እንደፈለጉ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የዚያ ድርጊት ሰለባ ናቸው ለሚሏቸው ወገኖች የሕሊናና የሥነ ልቡና ጤና እና ደኅንነት እንኳን አልተጠነቀቁም አልተጨነቁም፡፡ የእነዚያ የተሠው የተባሉ ወገኖች ወገን ነኝ የሚል ሁሉ ይሄንን ሰቅጣጭ አስደንጋጭ ሐውልት ባየ ቁጥር ሕሊናው ይቆስላል ይደማል ይህ ስሜትም ወዲያውኑ የበቀል ስሜትን ይወልዳል፡፡ የሐውልቶቹ ቅርጽና ገጽታ እንዲህ ዓይነት ስሜት ሊፈጥር በሚችል መልኩ የተቀረጹት ሆን ተብሎ እንደሆነ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡
ከዚህ ይልቅ ይሄንን ያስገነቡ ወገኖቻች ቀና ቢያስቡ ኖሮ እንኳንና ድርጊቱ አለመፈጸሙን እያወቁ ድርጊቱ ተፈጽሟል ብለው የሚያምኑ ቢሆኑም እንኳ በሆስፒታል (ዐቢይ የህክምና ማዕከል) እና መሰል የአገልግሎት መስጫ የልማት ግንባታዎች ተገልጾ ቢሆን ኖሮ ኅብረተሰቡ በአገልግሎቱ ከመቀጠሙም ባሻገር ከእንደዚያ ያለ ሐውልቱን በመመልከት ከሚፈጠር የሥነ-ልቡናና የሕሊና ሁከት ቁስለትና ጉዳት በተገላገሉ በተረፉ ነበር፡፡
በተለይ ከነዚህ ሐውልቶች መገንባት በኋላ በየአካባቢው ያሉ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚደርስባቸው ጥቃት በዓይነትና በመጠን ጨምሯል ተባብሷል፡፡ “እንናንተ የሚኒልክ ዘሮች ናቹህ” የምትባል ቃል በመጠቀም ብቻ ከፍተኛ የሆነ የሥነ ልቡና ጥቃት እያደረሱባቸው ለከባድ ሰቀቀን ጭንቀት እና ሥጋት እየዳረጓቸው ይገኛሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ወገኖቻችንን ዛቻ ማስፈራሪያውን በመፍራት ወልደው የከበዱበትንና ሀገራቸውን ጥለው ለቀው ለመውጣት ተገደዋል፡፡ በብዙኃን መገኛኛዎች እንደተሰማውም በተለያዩ አካባቢዎች እዚህ ከቅርብ ስሉልታ ሳይቀር ልቀቁ እየተባልን አደጋም እየተጣለብን ነው፡፡
ወያኔ ከትናንት እስከ ዛሬ የሕዝብ (የመንግሥት) የብዙኃን መገናኛዎችን በመጠቀም ኢንተርሀምዌዮቹ ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ የተለያዩ መንገዶቹን በመጠቀም ያነጣጠሩበትን ብሔረሰብ ለማስመታት በአቶ ጥልማሞት ትእዛዝ ተደርሶ በሬዲዮ ፋና (Radio Mille Collines) ይተላለፍ ከነበረው እጅግ አረመኔያዊ ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሣሣ ረጅም የማፋጃ ድርሰትን ጨምሮ እስከ ትናንትናው የባህርዳሩ የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ውድድር እስከ ተደረገው ሴራ ድረስ የሕዝብ (የመንግሥት) የብዙኃን መገናኛዎችን በመጠቀም ለማጫረስ ለማፋጀት ያልተጣረ ጥረት የለም፡፡ በባህር ዳሩ የስፖርት ዝግጅት ላይ ወያኔ የኦሮሞ ብሔረሰብን የሚዘልፉ የሚሰድቡ ምንደኞችን አዘጋጅቶ እያስጨፈረ በማሰደብ ያንኑ ድርጊትም በኦሮሚያ ቴሌቪዥኑ (RTLMC, Radio Television Libre des Mille Collines) የቀጥታ ሥርጭት ለኦሮሞ ሕዝብ ያሳይ ነበር፡፡ የወያኔ ቅጥረኞች ይሄንን ሲያደርጉ ሥራው የወያኔ ነበርና የፌዴራል ፖሊስ አጠገባቸው ሆኖ አንዳችም ዓይነት ፍርሐትና መጨነቅ አይታይባቸውም ነበር፡፡ ፌዴራሎቹም በእነሱ ላይ አንዳችም ዓይነት የእርምት እርምጃ አልወሰዱም ነበር፡፡
እንደ የፖለቲካ ፓርቲ የገባው ንቁና ኃላፊነት የሚሰማው የፖለቲካ ፓርቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ከምንም ነገር በላይ በታላቅ ንቃት እልህና ቁጭት ማስተዋልና ቁርጠኝነት ይሄንን የራሱን የተቀናበረ ሸረኛና እኩይ ሒደት ጠብቆ ዛሬ ላይ ሐውልት ግንባታ ድረስ የደረሰውን የማፋጃ፣ የማባያ፣ የማስተላላቂያ እንቅስቃሴ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍን ጨምሬ የተለያዩ የመቃወሚያ መንገዶችን በመጠቀም አሸባሪዎቹ ወያኔና አጋሮቹ ኦነግና ሻቢያ እየመረዙት ያለውን ሕዝብ ትክክለኛውን መረጃ እንዲደርሰው በማድረግ ሀገርንና ሕዝብን መቀመቅ ለመክተት ከሚጠነጠነው ሴራ እራሱን እንዲያርቅ እንዲጠብቅ ተባባሪ እንዳይሆን ማድረግ ማስቻልና ለዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብም እየተሠራብን ያለውን የኢንተርሀምዌዮች እንቅስቃሴ ሴራ ማጋለጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄንን በማድረግ ችግሩ ቢረፍድብንም ሳይመሽብን ከወዲሁ ሊቀረፉ እንዲችሉና የየዋህነት ይሁን የምን ምንነቱ በቅጡ ባልታወቀው ዝምታችን ድነገት ነገ ከተፍ ከሚልብን ከአስፈሪው አደጋ ሕዝብንና ሀገርን ይታደጉ፡፡ የተጣለባቸውን ሀገራዊና ሕዝባዊ አደራ ሳይመሽ ይወጡ፡፡ እኩዩን ሰይጣናዊ ሴራ ያክሽፉ፡፡ ይህ ኃላፊነት የእነዚህ አካላት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋም ጭምር ነው፡፡
ከዚህ ሁሉ ዓመታትም በኋላ በፖለቲካ ፓርቲ (በእምነተ-አሥተዳደር ቡድን) ደረጃ ተመሥርተው ወያኔ በግላጭ በዓይናቸው ሥር እየሠራው ያለውን እኩይና ሰይጣናዊ ሴራ ማወቅ፣ መረዳት፣ መገንዘብ፣ የሚያስከትለውን አደጋ ከርቀት ማየት፣ ማሽተት ካልቻሉና እንደፖለቲካ ፓርቲ መውሰድ ያለባቸውን ተገቢና ወቅታዊ እርምጃ በሰዓቱ መውሰድ ካልቻሉ ጨርሶ ምኑም አልገባቸውምና፣ አልበሰሉምና አልነቁምና አልበቁምና ፓርቲዎቻቸውን አፈራርሰው እየቤታቸው ይቀመጡ፡፡
ወያኔ ለማንም የሀገር ልጅ በማይገባና ሊገባም በማይችል የጥፋት ዓላማ ሀገርንና ሕዝብን መርዞ ለዚህ አድርሶናል፡፡ በእርግጥ ምንጊዜም ቢሆን በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ምንም ቢደረጉ ቢመከሩ ቢዘከሩም የማይሰሙና የማይገባቸው ፈጽሞ ኃላፊነት የማይሰማቸው ፀረ-ማኅበረሰባዊ ሰብእና (Anti-social personality) ያላቸው ዜጎች ይኖራሉ፡፡ ይህ ሰብእና ያለባቸው ግለሰቦች “መቸም ቢጤ ከቢጤው ጋር” ነውና የሚወዳጀው አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ተሳስበው በአንድ የመቧደን ዕድል ያገኛሉ፡፡ ይህ ሰብእና ያለባቸው ቡድኖች የጠላት መጠቀሚያ ለመሆን እጅግ የተመቹ ናቸው፡፡ በሀገራችን ከዐሥርት ዓመታት ወዲህ እንዲህ ዓይነት ሰብእና ያላቸው ዜጎች የመንግሥትን ሥልጣን የመጨበጥ ዕድሉን አግኝተው ብዙ ነገሮችን እያበላሹ እያጠፉ እንዳሉ ዐይተናል እያየንም ነው፡፡ ከተበላሹትና ከጠፉት እሴት ሀብቶቻችን ብዙዎች በሚያሳዝን ሁኔታ ድጋሚ ላናገኛቸው ያጣናቸውና የምናጣቸውም ናቸው፡፡ በይነ ሕዝባዊ (ዴሞክራሲያዊ) ሥርዓት በሌለበት ሀገር እንዲህ ዓይነት ሰብእና ያላቸው ዜጎች ሥልጣን ለመጨበጥ ሰፊ ዕድል አላቸው፡፡
አንድ ሕዝብ በእነዚህ ዓይነት እኩያን ቡድኖች ላይ ነቅቶ መከላከል ካልቻለና ድርጊቶቻቸውን በዝምታ ለመመልከት ከመረጠ ሕልውናውን እስከማጣት ድረስ የሚያደርሰውን ዋጋ መክፈሉ የማይቀር ይሆናል፡፡ ይህ ችግር በሀገራችን እንደመኖሩ እኛንም ዝምታችን ከባባድ ዋጋ አስከፍሎናል እያስከፈለንም ይገኛል፡፡ ዓለም እንደ አንድ መንደር መጥበቧ ታላቅ እንቅፋት ሆነባቸው እንጂ እንደ ጥንቱ እንደድሮው በአንድ ቦታ የተደረገውን በሌላው ያለው የማያውቅበት የማይሰማበት ዘመን ላይ ብንሆን ኖሮ ወያኔ በተለይም አማራን ከምድረገጽ ሳያጠፋ እንድ ምሽት ማሳለፍ ባልመረጠ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በዘመነ ሉላዊነትም (Golobalization) ቢሆን ዓለም የደረሰበት ዘመናዊ አስተሳሰብ ሳያግዳቸው ለ 23 ዓመታት ጥፋት እያሴሩ ሲዳዳቸው እንዳየናቸው ዝንባሌያቸው ይሄንን ማድረግ ነው፡፡ ከዓለም ዕይታ ውጪ ሆኖ እንዴት ለማድረግ እንደሚቻል ቸገራቸው እንጂ፡፡ በጅምላ ማለቴ ነው እንጅ በተናጠል ወይም በጥቂት በጥቂቱ መመንጠሩንማ ከተያያዙት ይሄው 23ዓመታት ሆኗቸዋል፡፡
የአንድ ሀገር ሕዝብ መሆናችንና አንድ የጋራ ሀገር ያለን ወንድማማች (እኅትማማች) መሆናችን ተዘንግቶ “አንተ አማራ ነህ ውጣ ልቀቅ” ከተባለ ቆንጨራ አለመጨመሩ ነው እንጅ ከሩዋንዳው የኢንተርሀምዌ ፍጅት በምን ተለየ? ለነገሩማ ቆንጨራን ከሩዋንዳ ቀድመው በበደኖ፣ በአቦምሳ፣ በአርባጉጉ፣ በወለጋ ወዘተ. የፈጁበት የእኞቹ አልነበሩም? በሩዋንዳ ያ ዘግናኝ የዘር ፍጅት ከመከሰቱ በፊት የነበረው እንቅስቃሴ ይሄው ነበር፡፡ አንድን ዘር ነጥሎ በጥላቻ በመመልከት “ሀገራችንን ልቀቁ” የሚል፡፡ ያ እልቂት በሩዋንዳ በድንገት ከመከሰቱ በፊት ለሁለት ዐሥርት ዓመታት ያህል የጥላቻ ፖለቲካ ሲነዛ ከርሞ ነበር፡፡ ያሰቡትን ጥቃት ጥቃቱ የታሰበባቸውን ዘሮች ብቻ ነጥሎ ለማጥቃት እንዲያስችላቸውም መታወቂያቸው ላይ ብሔረሰባቸው እንዲሰፍር ተደርጎ ነበር፡፡ እኛንም እኮ ለዚህ ሲያመቻቹን ነው መታወቂያችን ላይ ብሔረሰባችን ከየት እንደሆነ እንዲሰፍር ማድረጋቸው፡፡ አሸባሪዎቹ ወያኔና አጋሮቹ ኦነግና ሻቢያ የቤት ሥራዎቻቸውን እንደማጠናቀቃቸው መጠን ክርስቶስ ይታደገን እንጂ ከፊታችን ባሉ ጊዜያት ቆንጨራ ላለመጨመሩ ምን ማረጋገጫ አለን?
አቶ መለስ ይሄንን ማለትም ሕዝብን በዘሩ ምክንያት እያፈናቀሉ “ውጡልን ልቀቁልን” ስለሚለው ጉዳይ ተጠይቀው ሲመልሱ “የክልሉ መንግሥት መብት ነው እንደመሰለው ማድረግ ይችላል” ብለው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቶ መለስ አልገባቸውም እንጂ ይሄንን ሲሉ “በእርግጥ እኔ ተብሏል የሚል እምነት የለኝም ሐሰተኛ ውንጀላ ነው” ነገር ግን ወያኔ ተብሏል እያለ እንደለፈፈው ሁሉ በምርጫ 97ዓ.ም ዋዜማ ተቃዋሚዎች “እቃ ወደ ቀበሌ ትግሬ ወደ መቀሌ” ብለዋል እያለ ይከስ የነበረውን ክስ ጥፋት አይደለም ትክክለኛ አባባል ነው ብለው እያረጋገጡ ነው፡፡
ሐሰተኛ የፋሺስት ሴራ መሆኑ እየታወቀ ከግብር አባታቸው ፋሺስት ይሄንን እኩይ ሴራ በመውረስ “እንዲህ አድርገውህ ነበር” እያሉ መቀስቀስ አጸፋውን እንዲመልስ መገፋፋት ማነሣሣት የቆንጨራን መተላለቅ ለመጋበዝ ካልሆነ ፍቅርን መተሳሰብን እንድነትን ለማምጣት ለመመሥረት እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ እመኑኝ እነዚህ ወገኖች እንዲህ ዓይነት እኩይ ሰይጣናዊ ሐሳብ ባይኖራቸው ኖሮ እንኳን እውነት ያልሆነውን እውነት ቢሆን ኖሮም እንኳ እያደረጉት ያለውን ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው አድራጎት በፍጹም በፍጹም ባልሞከሩት ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሴራ እንደ አያጅባጅቦ ሁሉ አመሃኝቶ ለመብላት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡
መጨረሻ የሚሉት ሰዓት ሲደርስ ወይም ለእነሱ አስቸጋሪ ሆኖ የታያቸው ሰዓት ሲመጣባቸው ምንም ነገር ሳያሳስባቸው ልክ የተቀበረን ፈንጂ አንዲት ቁልፍ በመጫን ማፈንዳት እንደሚቻል ሁሉ መቀመጫችን ላይ የቀበሩብንን ዘርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ የጥላቻ ፈንጅ ስስ ብልቱ የት እንደሆነ በሚገባ እንደማወቃቸው መጠን የሆነ ቦታ አንዲት ነገር በማድረግ ብቻ አፈንድተው ሊያባሉን ሊያፋጁን ሊያጫርሱን በሚችሉበት ሁኔታ አመቻችተው አስቀምጠውናል፡፡ ወገን ሆይ! እባክህ ይሄንን የተሸረበብህን የተተበተበብህን የተጠነሰሰብህን የተቆመረብህን የእልቂት ሴራ ጠንቅቀህ ዐውቀህ የትም ቦታ፣ መችም ቢሆን፣ ምንም ቢፈጠር የሕዝብ ደም የተጠሙ አጋንንትን ነቅቸብሀለሁ “እንቢ” በማለት ተፋቅረህ ተዋደህ ተከባብረህ ጠላትህን አሳፍር፡፡ ከተደገሰልህ እልቂት፣ ሞት፣ ጥፋት አምልጥ ዳን፣ ሀገርን ከመፍረስ ታደግ፡፡ አምላክ ይርዳህ፡፡
ወያኔ ይሄንን ሐሰተኛ የጥፋት የፈጠራ ታሪክ አዲስ በቀረጸው የኢትዮጵያ ታሪክ የትምህርት ዓይነት እንዳካተተው ይነገራል፡፡ እርግጡን ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የምንረዳው ይሆናል፡፡ አገዛዙ ካለውና ከምናውቀው እኩይ ዓላማው እንጻር ስናየው ግን ይሄን አይደለም ከዚህም የከፋ ሊያደርግ እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡
ሌላው አበክሬ ማስገንዘብ የምሻው ነገር ቢኖር የምዕራቡ ዓለም መንግሥታትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች “ከሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ጀርባ ማን ነበረ” የሚለውን ለጊዜው እንተወውና በሰው ልጆች ታሪክ “እጅግ ዘግናኙና ተወዳዳሪ የሌለው የዘር ማጥፋት” በመባል የሚታወቀውን የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት እንዳይከሰት ማድረግ እየቻሉ በመዘናጋታቸው ይህ በመሆኑ እየተጸጸቱ ያ የዘር ፍጅት በየዓመቱ በታሰበ ቁጥር በሚያወጧቸው መግለጫዎች ያረጋግጣሉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ ወንጀልና የወንጀል ሰለባዎች (victims) ያላቸው የያገባኛል መንፈስ (concern) ይሄንን ያህል ከሆነ ወያኔ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ምን ለማድረግ ምን እየሠራ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉና ያለፈው ስሕተታቸው እንዳይደገም ምን እያደረጉ ነው? የወያኔን እኩይ ሴራ ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም፡፡ አይደለምና ይሄንን ያህል ግዙፍ ጉዳይ የዕለት ተዕለት ጥቃቅን ጉዳዮቻችን እንኳን ከእኛ ቀድመው በወቅቱ በሰዓቱ ዐውቀው ለእኛም ሳይቀር የሚያሳውቁን እነሱው ናቸውና፡፡ ታዲያ ነገሩ እንዲህ ከሆነ ዝምታው ለምንና ምንስ እስኪሆን ድረስ ነው? በዚህ ኃላፊነት የጎደለው ዝምታና ዳተኝነት በሚፈጠር ችግር ዳግም እንደገና “በመዘናጋታችን እንዳይከሰት ልናደርግ እንችል የነበረው ችግር በመከሰቱ እናዝናለን እንጸጸታለንም” እያላቹህ የአዞ እንባ በማንባት እንድታላዝኑልን ከቶውንም አንሻም፡፡ ኃላፊነታቹህንና ግዴታቹህን መወጣት ካለባቹህ በቋፍ ካለ አደጋ ላይ ነንና ነገ ሳይሆን ዛሬ ከዛሬም አሁን ድረሱልን፡፡ ታሪክና አጋጣሚ የጣለባቹህን ኃላፊነት ሳትወጡ ቀርታቹህ በምትደጉሙትና በምትረዱት በምትደግፉት “መንግሥት” ለሚፈጠረውና ለሚፈጸምብን አደጋና ችግር ሁሉ ሙሉ ኃላፊነትን ትወስዳላቹህ፡፡ በውጪ የምትኖሩ ዜጎቻችን ሁሉ ሳትዘገዩ ይሄንን ጉዳይ በሰላማዊ ሰልፎችና በተለያዩ መንገዶች ለሚመለከተው ሁሉ እንድታስገነዝቡ አበክሬ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ይህ የታፈነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው፡፡
Amsalu G/kidan Argaw says
ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል፡፡
ባለፈው ሰሞን አንድ ከ “ሰማእታት” የመታሰቢያ ሐውልቶች ጋር በተያያዘ ታሪክ ቀመስ ጽሑፍ መጻፌ ይታወሳል “አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” እንዲሉ ይህ ጽሑፍ ለንባብ ከበቃ በኋላ በፊት ለምን እንደሆነ በቅጡ የማይገቡኝ የነበሩ እጅግ የሚገርሙ ነገሮች ለምን ይደረጉ እንደነበር ከተለያየ አቅጣጫ በአካልና በመልእክት ካገኘኋቸው ግብረ መልሶች ተረዳሁ፡፡ በዚያ ጽሑፍ ላይ ኦሮሞና ትግሬ ነን የሚሉ ካድሬዎች በተለየ ሁኔታ ትኩረታቸው ተስቦ ነበር፡፡ አንዳንዶችም አነጋግረውኝ ነበር፡፡ በንግግራችን ውስጥ ከዚህ በፊት ያልተረዳኋቸው ነገሮች ግልጽ ሆኑልኝ፡፡ ለነገሩ ያልተረዳኋቸው ማለት ይከብዳል ነገሩ እጅግ የማገርምና ለማመንም የሚቸግር በመሆኑ ሁል ጊዜ እንግዳ ሰለሚሆንብኝና ለጉዳዩ ሁሌም አዲስ እንግዳ ስለሚያደርገኝ ነው፡፡ ባይሆን ስጠረጥራቸው የነበሩ ብል ይሻል ይመስለኛል፡፡ እናም እጅግ ገረመኝ በእርግጠኝነት እንደኔ ሁሉ ብዙው ሰው የሚደረጉ ነገሮች ዓላማቸው የገባው አይመስለኝም፡፡ ወያኔ ለካ አማራን እንዳያንሠራራ አድርጌ ሠብሬዋለሁ እንዳይነሣ አድርጌ አድክሜዋለሁ ብሎ ያምን ኖሯል፡፡ መቸም ሥራቸውን ያውቃሉና ነው እንዲህ ሊያስቡ የቻሉት፡፡ ለካ እንዲያው ሳናውቀው ገለውናል ጃል! ታዲያ እላቹህ እንዲህ ብለው እያሰቡ እያመኑ እያለ ይህ ጽሑፍ በዚያ ቅኝትና ይዘት መጻፉ አማራን በተመለከተ የነበራቸው ግምትና እምነት እንዳሰቡት ሳይሆን ቀርቶ ከ 20ዓመታት ቅጥቀጣና ድቆሳ በኋላ እንደነሱ አባባል እንደዚህ ዓይነት ጽሑፍ በእኔም ብቻ ሳይሆን ከእኔም በኋላ በሌሎች ወገኖችም በአጋጣሚ ተከታትሎ በአንድ ሰሞን በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች መንጻባረቁና በአንባቢያን መወደዱ ለመግለጽ እጅግ በሚያስቸግር የመደነቅ ድባብ ውስጥ ከቷቸው ነበር፡፡ ይሄን ሁሉ ጉድ የማላውቀው የዋሁ የእግዚአብሔር በግ እኔ ደግሞ መደነቅ መገረማቸውን ሳይ እንዴ ይሄም ኖሯል ለካ ብዬ ሁኔታቸውና አስተሳሰባቸው ሁሉ እኔንም በተራዬ ከከባድ ድንጋጤ ጋር እጅግ እጅግ እጅግ አስደነቀኝ አስገረመኝ አዘንኩም፡፡ እንዲያው ሰው በተለያየ ምክንያት ዝም ሲል ጊዜ እጅ ሰጥቶ ተንበርክኮ መሰላቸውና ጭራሽም እንደሞተ ያህል ቆጥረውት ቁጭ አሉ፡፡ ወያኔ አማራን በተመለከተ አይቅበሩት እንጅ እንደሞተ እንዳበቃለት አድርገው ማሰባቸው ስሕተት እንደነበረ ከመጸጸት ጋር ይቆጩ ይዘዋል፡፡ እነሱ ዘመትንበት አጥፍተነዋል ያሉት ይህ ለሀገር፣ ለቅርስ፣ ለታሪክ፣ ለመለያ፣ ለማንነት፣ ለሃይማኖት ተቆርቋሪ የመሆንን ስሜት ወዴት ተደብቆ እንደተረፈ በአንከሮ እያጠኑት ይገኛሉ፡፡ በተለያዩ የብዙኀን መገናኛች ለመረዳት እንደቻላቹህት ማኅበረቅዱሳን አንዱ መደበቂያ መሸሸጊያ ነው ብለው በማመናቸው ማኅበሩን ለማፍረስ ለመዝጋት ሴራ እየጠነሰሱ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ማኅበር ከዚህ ቀደምም ቢሆን በወያኔ የዓይነ ቁራኛ የቅርብ ክትትል ስር የነበረ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩን አቅጣጫውን ለማሳትና ወደ ሚፈልጉት መንገድ ለመውሰድ በርካታ ጥረቶችን ሲየደርጉ ቆይተዋል፡፡ በየዓመቱ ከየዩኒቨርሲቲው (መካነ-ትምህርት)ተመርቀው የሚወጡትን የማኅበረ ቅዱሳንን የግቢ ጉባኤ አባላት እንደ ማንኛውም ተመራቂ ሁሉ ወያኔ የድርጅቱ አባል አድርጎ እያወጣ ማኅበረ ቅዱሳንን በአባላቱ ጠቅጥቆ ቢሞላውም ማኅበሩ ሃይማኖታዊ ማኅበር ከመሆኑ አኳያ እነኝህ የወያኔ አባላቶችም ከሃይማኖታቸው ይልቅ ወያኔ በሚፈልገው መጠን ለመርሑ ታማኝ ሆነው ባለመገኘታቸውና ምቹ ሁኔታ ስላላገኙ ወያኔ የሚፈልገውን ውጤት በሚፈልገው ፍጥነት ማስመዝገብ አልቻሉም፡፡ ከዚህ ሙከራ ክሽፈት በኋላ ወያኔ ማኅበሩን በአክራነትና በአሸባሪነት ከሶ ያለ ማፍረስ የተሻለ አማራጭ እንደሌለ ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ከወጡ መረጃዎች መረዳት ተችሏል፡፡ እንግዲህ ወያኔ ይሄንን ሳይጣናዊ ምኞትና ሐሳብ ለማሳካት በአዲስ ጉልበትና ስልት (strategy) ሊዘምትብን እንደሆነ ግልጽ ሆኗል ማለት ነው፡፡
እንዳስተዋላችሁት ወያኔ ታሪካዊ ለሆነ ቀደምት የሀገራችን እሴቶች ጨርሶ ትኩረት አይሰጥም፡፡ የመንግሥት (የሕዝብ) የብዙኃን መገናኛዎች ከመጀመሪያው ጀምሮ በዚሁ ቅኝት እንዲሠሩ ተደርጓል፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በየዩኒቨርስቲው የአማራ አሻራ ይጎላበታል ያሏቸውን ቋንቋን ታሪክን ባሕልን ሥነ-ኪንን የተመለከቱ ዲፓርትመንቶችን (ከፍለ ጥናቶችን) አከታትለው ዘግተዋቸዋል፡፡ እነኝህ እኩይ እርምጃዎች የተወሰዱት በአጋጣሚ ወይም ከተራ ጥላቻ የተነሣ አልነበረም፡፡ እኔ እንደዛ ይመስለኝ ነበር እኔ ብቻም አይመስለኝም ብዙው ሰው እንደዚህ ይመስለዋል ብዬ እገምታለው፡፡ ነገሩ ለካ ከዚያም የከበደ ጫን ያለ ኖሯል፡፡ ለካ እነኝህ ስንት የተደከመባቸው ስንት መሥዋዕትነት የተከፈልንባቸው የሀገራችን እሴቶች ከነአካቴውም የእሱ ሀብት ነው እሴቱ ነው ከሚሉት ብሔረሰብ አባላት ልብ ዘንድም ሳይቀር እንዲደመሰስ፣ እንዲጠፋ፣ እንዲረሳ ይፈልግ ኖሯል ለካ! ይሀንንም የጥፋት ዓላማ ለማሳካት ኖሯል ለካ ከትምህርት ሥርዓቱ እስከ ባሕላዊ ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን አትኩረው በሚሠሩ ተቋማትም ዘንድ ምክንያቱ ሳይገለጽልን ቦታ እንዲያጡ እንዲገለሉ እንዲወገዱ የተደረገው፡፡ ወያኔ ይሄንን የጥፋት ውጤት ለማስመዝገብ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ እሴቶቻችን በመጥፋታቸው ከሚደርስብን የጀርባ አጥንት ሥብራት ጉዳት በተጨማሪ በዘመኑ ሁሉ ይሄንን ለማድረግ ምን ያህል እንደደከመ፣ ምን ያህል አቅሙን እንዳባከነ፣ ምን ያህል የመንግሥትን ወይም የሕዝብን የገንዘብ የጊዜ የጉልበት ወዘተ. ሀብቶችን እንዳባከነ እንዳከሰረና ያን ሁሉ ዘመን በዚህ እኩይ ሥራ ተጠምዶ ይሄን ሁሉ ጉዳት ኪሳራ ለማስመዝገብ ባባከነው ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ጥረት፣ ወዘተ. ሀገርንና ሕዝብን ለሚጠቅም፣ ለሚያንጽ፣ ለሚገነባ ጉዳይ አውሎት ቢሆን ኖሮ የት ልንደርስ እንችል አንደነበረ ሳስበው ውስጤ እንደ እሳት በሚገርፉ ቁጭት ይቃጠላል፡፡
ከዚህ በላይ የእግር እሳት ሌላ ምን አለ ወገኔ? “ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል” አለ የሀገሬ ሰው፡፡ ተበድሮ ሲበላ ከርሞ መኸር ደረሶ ሰብሉን አጭዶ ከመረና ሲያልፍ ሲያገድም ከርቀት በኩራት ጉም ብላ ትታየዋለች ያኔ እየተበደረ ሲበላው የከረመው እህል ታወሰውና ክምሩን “አየ አንች ክምሬ ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል” ሲል በኃዘን ተናገረ፡፡ ለካ የአማራ ሕዝብና እሴቱ ያለ ይመስለናል እንጅ አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ለካ 23 ዓመታት ሙሉ ጉዱን አያውቅ እሱ የሚጠፋበት መንገድ ተቀይሶ እላዩ ላይ የጥፋት ሥራ ሲሠራበት ነበር የባጀው? ” ጉድ ሳይሰማ አሉ” እኮ በል ተጠየቅ ወያኔ የእፉኝት መንጋ ለምን? እኮ ለምን? ይሄ ነው እንዴ በይነ ሕዝብ? (ዴሞክራሲ?) ይሄ ነው እንዴ የብሔር ብሔረሰቦች መብት? ለካ እነዚህ ድንጋጌዎችህ ማጃጃያዎችህ ኖረዋል ለካ? ጭራሽም ልታጠፋን ትጥራለሃ ለካ? “የጊዮርጊስን ግብር የበላ ለፍልፍ ለፍልፍ ይለዋል ምን ነውሳ እኔን አያስለፈልፈኝ” አለ አሉ አንዱ እየለፈለፈ መሆኑን ሳያውቅ፡፡ ለካ በብዙኃን መገናኛዎች ሳይቀር አማራንና ኦርቶዶክስን አዳከምነው ተብሎ መፎከሩ ለዚህ ነው? በጣም የሚገርመው ቤተክርስቲያንንም የነፍጠኛ ሃይማኖት ብሎ በመፈረጅ የጥቃቱ ሰለባ አድርጓት መቆየቱ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአንድ ጽሑፍ ላይ እንዳነሣሁት ወያኔ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የአማራ የህልውና መዋቅር አድርጎ ነው የሚቆጥራት ጥርሱን ነክሶ ለማዳከም ብሎም ለማጥፋት ሲሠራ የኖረውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ አባ ጳውሎስ የተባሉ ሰው አስቀምጠው ከአንድ አረማዊ እንኳን በማይጠበቅ ድፍረትና ጭካኔ የቤተክርስቲያኗን ሥር ሲቆርጥ መኖሩ የሚታወስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ታላቅና ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ነው፡፡ የእኒህን ሰው እርኩሰት አስከናቸው ባረፈበት ቦታ ሳይቀር በሚያሳየው ተአምር እየገለጸ ነው፡፡
ይሄንን ታውቁ ኖሯል ወገኖቸ? ለካ “የአንድ ብሔረሰብን ባሕል፣ ማንነት፣ ሃይማኖት፣ እሴት አስተሳሰብ በሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ለመጫን ነው ገዥዎች ሲጥሩ የኖሩት” እየተባለ በቁጭት ሲነገረን የኖረው ሠም ለበስ አነጋገር ኖሯል? ወርቁ ለካ የዚህን ብሔረሰብ ባሕል፣ ማነነት፣ አስተሳሰብ ወዘተ. ከዚህ በኋላ ማየት አንፈልግም የሚል ኖሯል ለካ? ለካ ለዚህ ነው ካድሬዎቹ ከዚህ በኋላ አማራዊት ኢትዮጵያ አትኖርም እያሉ የሚፎክሩት? እጅግ ደግሞ የሚገርመኝ ብአዴን ተብሎ በአማራ ብሔረሰብ ማኅበር ስም ለአማራ ሕዝብና እሴት ሊሠራ በተደራጀው የኢሕአዴግ አጋር ድርጅት ተቋቋመ ተብሎ በውስጡ ያሉ የአማራ ተወላጅ ነን ባዮች ይሄንን ናዚያዊ አስተሳሰብ እምነውበት የገዛ ሕዝባቸውን የገዛ ወገናቸውን እና እሴቱን እንዲያጠፋ እንዲደመስሱ ወያኔ ብዙ የሚጠብቅባቸው ከአማራ የወጡ መሆናቸው ነው፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ናቸው? እንደኛ ይናገራሉ? እንደ ሰው እጅና እግር ዓይንና ጆሮ ያላቸው የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ናቸው? እውን ከአማራ ሕዝብ የተገኙ የወጡ ናቸው? አይገረማቹህም አይደንቃቹህም? ከዚህ የተነሣ ነው ለካ አማራነታቸውን (ከሆኑ) ጨርሰው እረስተውት “አማራ” እያሉ ጨርሶ የማይገባውን ዘለፋ በአደባባይ ሲዘልፉት ሲያዋርዱት ቅንጣት ታክል የማይሰማቸው፡፡ አሁን እነዚህ ሰለ እውነት ሰዎች ናቸው? የሰው ጭንቅለት አላቸው? ለማይሞላው በቃኝን ለማያውቀው ሆድ ብለው? እንደ እንስሳ? ሰው እንዴት የገዛ ራሱን ልዩና ባዕዳንን ሁሉ በእጅጉ የሚያስቀና ማንነቱን እሴቱን ሀብቱን እንደሰው ለምን እንዴት ብሎ ሳይጠይቅ በገዛ አንደበታቸው የሚናገሩትን ገደብ የለሽ የብሔር ብሔረሰብ መብት ተላልፈው፣ እራሳቸውን ከሰውነት ወደ ውሻነት አውርደው ቻዝ እንደተባለ ውሻ እንዴት ያለ አግባብ በገዛ ማንነታቸውና ሕዝባቸው ላይ የጥፋት ሰይፋቸውን መዘው ይዘምታሉ? አሁን እነዚህ ሰዎች ናቸው? አሁን እነዚህ የሰው ጭንቅላት አላቸው? አፈር ያስበላችሁ በሉልኝ በቁማቹህ የሞታቹህ ናቹህ፣ በቁማቹህ የበከታቹህ በክቶች ናቹህ፣ በቁማቹህ የበሰናቹህ ብስብሶች ናቹህ እንስሳ የሚጥለውን እዳሪ እበት ፋንድያ ቁረን በጠጥን የሚያህልን እንኳን ዋጋ እርባና የሌላቹህ በድኖች ናቹህ በሉልኝ፡፡ ከእናንተ የተወለዱት ልጆቻችሁ ከእናንተ የተለዩ ሊሆኑ የሚችሉበት ተአምራዊ ዕድል ይኖር ይሆን? ለነገሩ እበት እዳሪ አዛባ ትልን እንጅ ምን ይወልድና፡፡ እውነት ይሄ ሁሉ ጉድ በእውን አይደለም በሕልም እንኳን ይሆናል ተብሎ ይታሰባል? ጭራሽ እኔ ይደንቀኝ የነበረው ወያኔዎች እንዴት ግን ኢትዮጵያዊያን ሆነው ሳለ የጠላት ቅጥረኛ ሆነው በገዛ ሀገራቸው እሴት ላይ ጠላት ሊሆኑ ቻሉ? እያልኩ እድሜ ልኬን ሲገርመኝ የፈጣሪ ነገር ጭራሽ የባሱ አሉልህ ብሎ ይሄንን ያሳየኝ? ይሄንን ያሰማኝ?
“የአማራ ህዝብ ባሕል፣ አስተሳሰብ፣ ማንነት፣ ሥልጣኔ ወዘተ. በተቀረው ሕዝብ ላይ እንዲጫን አንፈልግም ” ነው ያላቹህት? እኮ ለምን? ሲጀመር “የኢትዮጵያ” ተብሎ የሚጠራው የሚታሰበው ባሕል፣ አስተሳሰብ፣ ማንነት፣ እሴት የአማራ ህዝብ ብቻ ነው ወይ? በራሱ ሂደት ከሌሎቹም ብሔረሰቦችም መልካም መልካም የተሻለ የተሻለውን ተሞክሯቸውን መርጦ፣ እራሱን የቀረጸ የገነባ አይደለም ወይ? ደናቁርት ሆይ! ደዳብት ሆይ! ምንም ነገርን ከማንም ሳይወስድ የራሱን ብቻ ባሕል በሉት አስተሳሰብ ቋንቋ ባሉት ምን ይዞ እንደ ደሴት እራሱን ነጥሎ ብቻውን የኖረና የሚኖር ብሔረሰብ ከኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ከመላው ዓለም አንድ ብሔረሰብ በሉት ጎሳ አንድ ብቻ እንኳን ልትጠቅሱልኝ ትችላላችሁ? አማራ የመሪነትን ሚና እንደመጫወቱ ከሌሎቹ ወገኖቹ ኋላ ቀር አስተሳሰቦችን እንዲተውና የተሻውን፣ የበለጠውን፣ የላቀውን አስተሳሰብ እንዲጨብጡ ማድረጉ፣ መጣሩ፣ ማሠልጠኑ ኩነኔው፣ ኃጢአቱ፣ ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው? ሥልጣኔ እንዴት ሆኖ የተስፋፋ ነው የሚመስላቹህ? ጠቃሚና የተሻሉ አስተሳሰቦችን፣ ተሞክሮዎችን ልምዶችን አንዱ ከሌላው በመውሰድ ያንንም ሥራ ላይ በማዋል አይደለም ወይ? አየ መለስ ነፍስህን አይማረው የደንቆሮ መጨረሻ፡፡ እንኳን እዚህ ለዚህ ወገን ለወገን ቀርቶ ስንት ኢትዮጵያዊ እሴት ነው ከእኛ ወጥቶ ለሌላው ዓለም የተረፈው? ሌሎቹ ብልጦቹ ከእኛ ወስደው የተጠቀሙ ስንት እግዳሉ ይታወቅ አይደለም ወይ? ይህች ሀገር የአማራ እሴቶች ያላቹህትን ሁሉ አጥታ ምን ይቀራታል? ታዲያ እነኝህ እሴቶች ጠቃሚ መሆናቸው ከታወቀ ከተመሰከረ እኮ በምን ምክንያት ነው የአማራ ስለሆኑ ብቻ ይጥፉ ይወገዱ የሚባለው? ይሄ ምን ማለት ነው? አማራ ከዚህ በኋላ ለሀገሩ ለወገኑ መሥራት አይችልም አይኖርበትም ማለት ነው? ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን ሥልጣን ኃላፊነት መያዝ አይችልም ማለት ነው? አዎ ይሄንን ማለታቹህ እንደሆነ በምትሠሩት ሥራ ሁሉ አረጋገጣቹህ፡፡ ግን በ 21ኛው መቶ ክ/ዘመን እንዲህ ዓይነት የድንጋይ ዘመን የአረማውያን አስተሳሰብን ሥራ ላይ ለማዋል መሞከር የለየለት እብደት አይደለም ወይ? ይቻላል ወይ? እስከ አሁን እንደቻላቹህ ነገም የምትችሉ ይመስላቹሀል ወይ? እኔ ወያኔ የፈለገውን ያህል ሲጠብ ሲደነቁር ቢኖር የዚህን ያህል ይጠባል ይደነቁራል ብዬ ለማሰብ እጅግ ይቸግረኛል፡፡ እጅግ ያሳዝናል እውነታው ይሄው ነው፡፡ የሚጠቅም ሆኖ እስከተገኘ ጊዜ ድረስ እምየ ኢትዮጵያና ሕዝቧ አይደለም ከአማራ ባሕር ተሻግራም ከአቦርጁኖችም ቢሆን ትወስዳለች ልትወስድም ይገባታል፡፡ የሠለጠነ የበሰለ አስተሳሰብ ማለት ይሄ ነው፡፡ ወይ ወያኔ የአረማዊነት ማጥ ውስጥ ሰምጠሽ ዐረፍሽው?
መልካም ሥራ የሠራ የዚህች ሀገር ምኑንም ነገሩን ሳይሰስት የመጨረሻ መሥዋዕትነት እየከፈል ሀገሪቱን በነጻነቷ የኮራች የደመቀች ባለታሪክና የሥልጣኔ መሠረት እንድትሆን ማድረግ የቻለ ሊደነቅ ሊከበር ጎሽ ሊባል ሊመሰገን ይገባል እንጅ እኮ በምን ሒሳብ ነው ስንት የሆነላትን ሀገር ታሪክ ገደል ከቶ በመቶ ዓመት ገድቦ፣ ከንቱ አመድ አፋሽ አድርጎ በገዛ ወገኖቹ እንደጠላት በክፉ ዐይን ሊታይ የሚገባው? ዛሬ ወያኔ በሠራው የክፋት ሥራ አማራነትና እሴቱን ተገላይ አላስፈላጊ የሚጠላና የማያሳፍርም ማድረግ የቻሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በርካታ ብሔረሰቦች ባሉበት ሀገር የአንድ ብሔረሰብ የበላይነት (Domination) የማይቀር ተፈጥሯአዊና የታሪክ ሀቅ ነው፡፡ የትም ዓለም ያለው ተሞክሮ ከዚህ የተየ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም የተለየች ልትሆን የምትችልበት ተአምር የለም፡፡ በእርግጥ ግፍንና በደልን በተመለከተ ተመሳሳይ የአሥተዳደር ሥርዓት ከነበራቸው ሀገራት እንጻር ሀገራችን ስትታይ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ምስክርነት ከጥንት ጀምሮ ሕዝቧ እግዚአብሐርን አምላኪ ሕዝብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሌሎቹ ሀገራት ሲፈጸሙ የነበሩ ዘርን መሠረት ያደረጉ ግፎችና ኢሰብአዊ ድርጊቶች ፈጽሞ አልነበሩም አልተፈጸሙም፡፡ እያወራሁ ያለሁት እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ ላይ በርካታ ብሔረሰቦች እናሳም ሆኑ ምን ሠፍረው ያሉበት ቦታ ለምና አረንጓዴ ሆኖ የምናገኘው፡፡ ፋሽስት ጣሊያን ይሄንን እሴትና ቅርስ በማጥፋት ሀገሪቱንና ሕዝቧን ለመከፋፈል ብሔረሰብን፣ ሃይማኖትን፣ ሞያን ሳይቀር መሠረት ያደረጉ ያልፈጠረው የሀሰት ስም ማጥፋት ያላደረገው ጥረት አለነበረም፡፡ ብዙዎቹ ፈጠራዎቹ ዛሬ ላይ እንደ እውነት ተወስደው ወያኔ ኦነግን ሻቢያና ኦብነግን የመሳሰሉ ድርጅቶች ከራሳቸው ዓላማ ጋር ተጣጥሞላቸው ሕዝባችንን እያሳሳቱበት ይገኛል፡፡
በሉ እንግዲህ አንተ መከረኛ ወገኔ ምን ላድረግህ ወዴት አባቴ ልሸሽግህ ባትወደውም እውነቱ ይሄው ነው ረ ተው በቃ በል? እንደ በግ እየተነዳህ ወደ መቃብርህ ትተምለታለህ እንዴ? ምን እሚሉት መደንዘዝ ነው እንዴት ያለ ፍዘት ነው? ምን እሚሉት ፍርሐት ነው ከሞት በኋላ ሌላ ሞት ያለ ይመስለሀል እንዴ? ምኑን ነው የምትፈራው? ምን አድርገ ልቀስቅስህ ምን አድርገ ላንቃህ ምን አድርገ ልታደግህ ኸረ እኔስ ጨነቀኝ፡፡ ምን አባቴ ልሁን? በአዋጅ አማራ ይጥፋ ተብሎ እስኪታወጅ ነው የምትጠብቅ? ገና ዛሬ ተጃጃልክ፡፡ ለነገሩ እሱም ቢሆን አልቀረም በይፋ በአደባባይ አማራን ኦርቶዶክስን አዳከምን ብለው ፎከሩ እኮ! ዓላማቸው ማዳከም ብቻ ይመስልሀልን? አንተን ለማጥፋት ስንት ነገር እንደተደረገና እየተደረገም እንዳለ እረሳኸው እንዴ? ዝምታህ እስከቸ ነው ነው? ወይስ አንተም እንደ ብአዴን ካድሬዎች አማራነትህን ማንነትህን መለያህን ክደህ አስደምስሰህ አስረሽነህ ማንዘራሽ ምናምንቴ ሆነህ ለመኖር ፈለክ? ይሄ ነው ፍላጎትህ አታደርገውም! ፈጣሪዬ ይሄንን ሳታሰማ ጥራኝ፡፡ ታዲያ ምን ነው መናቁ መገፋቱ መጨቆኑ መረገጡ አልሰማህ አለ? አላስቆጣህ አለ? የታለ አሳየኛ? ከየት አመጣኸው ይሄንን ፍርሐት አማራነት እኮ እንዲህ አልነበረም፡፡ አማራነት እኮ ከራሱ አልፎ ተርፎ ለአፍሪካዊያን ወንድሞቹ የነጻነት ትግል ከሙግት እስከ መሥዋዕትነት በተግባር አሳይቶ እንዳረጋገጠው ስለ ሌሎች ነጻነት የሚገደው የሚቆጨው የሚያንገበግበው ዕረፍት የሚነሳው የነጻነት የፍትሕ የእኩልነት ጠበቃ እኮ ማለት ነው፡፡ ይሄንን አኩሪ እሴትህን ቅርስህን ሀብትህን ማንነትህን የት ጣልከው ? ወዴት አደረስከው ምን በላብህ ምንድን ነው ፍላጎትህ ምንድን ነው ዓላማህ?
ኢትዮጵያ ከማንነቷ ከታሪኳ ከቅርሶቿ ከሃይማኖቷ ጋር ለዘላዓለም ትኑር፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
Amsalu G/kidan Argaw says
ምርጫ 97ና ትውስታዬ
የምርጫ ነገር ሲታሰብ ሲነሣ በሁላችንም ልቡና የሚታሰበን ከፊታችን ድንቅ የሚልብን ምርጫ 97ዓ.ም. ነው፡፡ በምርጫ 97ቱ ወቅት መቸም የማይረሱን ጉልህ ጉልህ ጉዳዮች አሉ፡- ያ ምርጫ የወያኔ “ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ አላደለንም” የሚለው የምጸት ጸሎቱ ተሰምቶለት ተአምር ሊባል በሚችል መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወያኔ የመቋቋም አቅም በላይ መልስ ያገኘበት፣ በዓለም ውስጥ ከታዩት ጥቂት ታላላቅ የሕዝብ ማዕበል ከታየባቸው ሰላማዊ ሰልፎች አንዱ የተደረገበት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከየትኛውም ሀገር ሕዝብ በላቀ መልኩ (ይሄንን ስል በድፍረት ነው) ያለውን የበሰለ ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) አስተሳሰብና አስደናቂ ሥነ-ሥርዓት (ዲሲፒሊን) ያሳየበት፣ የወያኔን ሲጀመር ጀምሮ ይዞት የነበረውን የውሸት የማስመሰል ዲሞክራሲ (በይነ ሕዝብ) ካባ አስወልቆ እርቃሉን በማስቀረት ትክክለኛ አንባገነናዊ ማንነቱት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያጋለጠበት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ሁሉ ያለውን ጠንካራ አንድነት ያሳየበት፣ ተጨባጭ የኢትዮጵያ ተስፋ ለአፍታም ቢሆን የታየበት፣ በሕዝቡ ልቡና ውስጥ ሀገርን ከወደቀችበት ለማንሣት ያለውን የጋለ የተነቃቃ ስሜትና ቁርጠኛ ፍላጎት ያየንበት፣ ወዲያው ተመትቶ ወደቀ እንጅ የንባብ ባሕል የተቀጣጠለበት (እናቶች ሳይቀሩ ጋዜጣ ገዝተው “እባካቹህ አንብቡልኝ?” እስከማሰኘት የደረሰ)፣ ከረጅም ጊዜ ጨፍጋጋና ኃዘን የተሞላ ገጽታ በኋላ በሕዝቡ ገጽታ ላይ ተስፋን የሰነቀ የሞቀ ስሜትና ፈገግታ ደምቆ የታየበት ወዘተ.
እኔ ደግሞ በግሌ አንድ ልዩ ትዝታ አለኝ በዚያ አይረሴ የምርጫ ሂደት ውስጥ ጎልቶ ይታይ የነበረው በየ የምረጡኝ የምርጫ ቅስቀሳና የክርክር መድረኮች ላይ ይገለጽ የነበረው የየፓርቲው መሪ ቃል (slogan) ነበር፡፡ ከእነዚህ መሪ ቃሎች ውስጥ የቅንጅትና የኢሕአዴግ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛዎች ሳይቀር ልዩነታቸውን በማንሣትም ጭምር ተደጋጋሚ ሽፋን ተሰጥቶት ነበር፡፡ እነዚህ መሪ ቃሎች የየፓርቲውን የብስለት፣ የአስተሳሰብ፣ የንቃተ ሕሊና ልዩነቶች አጉልተው ያሳዩ ነበሩ፡፡ የቅንጅትንና የኢሕአዴግን ብናይ የነበራቸው ልዩነት የኋላ ቀርና የዘመናዊ (የአናሎግና የዲጂታል) የዛሬና የነገ፣ የገጠርና የከተማ ያልሠለጠነና የሠለጠነ ያህል ዓይነት ነበር፡፡ የኢሕአዴግ የምርጫ ቅስቀሳ መሪቃል “ ንብን ይምረጡ! ንብ ታታሪ ሠራተኛ ናት፤ ንብ ማር ትሰጣለች ንብን ይምረጡ!” የሚል ነበር የቅንጅት ደግሞ “ ቅንጅትን አለመምረጥ መብት ነው፤ ግን የሀገርን የስቃይ የመከራ የችጋር የፈተና ዘመንን ማራዘም ነው ” የሚል ነበር፡፡ ይሄንን በሚገባ የተረዳው የኢትዮጵያ ሕዝብም በምርጫ ካርዱ ንቃቱን፣ ብስለቱን፣ ፍላጎቱን፣ ምኞቱን፣ ማንነቱን፣ አቋሙን ባረጋገጠ መልኩ ተናገረ ጮኸ አሰማ አስደመጠ፡፡ በሚያሳዝን መልኩ ወያኔም ይሁን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በእሱ የንቃተ ሕሊናና የብስለት ደረጃ ያሉ ስላልነበሩ ምላሻቸው የሚያሳዝን ሆነ፡፡
“ ቅንጅትን አለመምረጥ መብት ነው፤ ግን የሀገርን የስቃይ፣ የመከራ፣ የችጋር፣ የፈተና ዘመንን ማራዘም ነው ” ይህ መሪ ቃል የእኔ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
Amsalu G/kidan Argaw says
ሰላም ወንድሞቸ ይሄንንና ስትራግል የሚለውን የምትለጥፉት ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው አደራ
በዘመነ ወያኔ ዐባይ ቢገደብ የነዳጅ ዘይት ቢገኝ ለሀገራችን በረከት ወይስ መርገም?
ከምርጫ 97ዓ.ም. በኋላ በሀገራችን በርካታ የልማት ሥራዎች ተሠርቷል እየተሠራም ይገኛል፡፡ በአስተውሎት ለማያይ ሰው እነኝህ የልማት ሥራዎች አስደሳችና አጥገቢ ናቸው፡፡ ላንተስ የሚለኝ ቢኖር እውነት ለመናገር እነኝህ የልማት ሥራዎች ለእኔ እያንዳንዳቸው በእየራሳቸው የልማት ሥራ ሳይሆኑ የጥፋት ሥራዎች ናቸው፡፡ ሁለቱን በምሳሌነት ላንሣ፡- ዛሬ ላይ በጥራት ችግር ምክንያት አገልግሎቱን ለደንበኞቹ በቅጡ መከወን አቅቶት ከፍተኛ ችግር ላይ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ደረጃውን ባልጠበቀ የመሣሪያ የጥራት ችግር ምክንያት ለዚህ ዓይነት ችግር እንደሚዳረግ የተረዳ አንድ ኃላፊነት የሚሰማው በዚያው መሥሪያ ቤት በኃላፊነት ደረጃ የነበረ የድርጅቱ ሠራተኛ ተረድቶ በቢልዮኖች(ብልፍ) ዶላሮች ልብ በሉ በሚልዮኖች(አእላፋት) ሳይሆን በቢልዮኖች(በብልፎች) ዶላር በጀት ሥራው እየተሠራ እያለ በሞያውና በኃላፊነቱ ከቻይና መጥተው ሊገጠሙ ያሉ መሣሪያዎች ከተመደበላቸው ወጪ እጅግ የወረደ ጥራት ያላቸውና ከደረጃ በታች በመሆናቸው ችግራቸውን በመግለጥ ለአገልግሎት ሊውሉ ስለማይችሉ ፊርማውን ላለማሥፈር በመቁረጡና በእንቢተኝነቱ በመጽናቱ ለአሳዛኝ ውክቢያ ተዳርጎ በመጨረሻም በገዛ ሀገሩና ሕዝቡ ፊት በቻይኖቹ በጩቤ ተወግቶ መጣሉ ከሥራም መሰናበቱ ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምሥጢር የነበረ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በወቅቱ በኅትመት የብዙኃን መገናኛዎች መዘገቡና የዜጎችን ልብ እጅግ ያሳዘነ ተግባር ነበር፡፡
ይህ ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ጥራታቸው ከደረጃ በታች ነው ልንሠራባቸው አንችልም ያላቸው ዕቃዎች ተገጥመው አገልግሎት እንዲሰጡ ሲደረግ በቴሌ አገልግሎት ላይ ምን ዓይነት የተወሳሰበ ችግርና እጅግ አስቂኝና አስገራሚ እንዲህ ነው ተብሎ ሊገለጽ የማይችል የሞተ አገልግሎት እንደፈጠሩ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ ልብ በሉ ለዚህ እርባና ለሌሉ አገልግሎት ግን በትውልደ ትውልድ ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ሀገር ተዘፍቃለች፡፡ በዚህ ስም የተበደርነው ገንዘብ መበላቱ ብቻ አይደለም ተበልቶም በተረፈው እርባና ያለው ሥራ ቢሠራበት ምንኛ እድለኞች በሆንን ነበር፡፡
ሌላው በመንገዶች ሥራ ላይ ያለው ጉድ ነው፡፡ በአጋጣሚ የተዋወኩት ሰው ነው በመንግሥት የተመደበ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (supervisor) ሆኖ ይሠራ የነበረ ነው፡፡ ከሥራ የተፈናቀለበትን ምክንያት ሲነግረኝ በሥራ ላይ እያለ ቻይኖቹ ቀኑ አይበቃንም ሌሊትም መሥራት እንፈልጋለንና ይፈቀድልን ብለው ጠይቀው ይፈቀድልቸውና ሌሊትም መሥራት ጀመሩ፡፡ እሱ ግን የሚከፈለው በመደበኛ የሥራ ሰዓት በመሆኑ ሌሊት ተገኝቶ ሥራውን ሊሠራ አልቻለም ነበር፡፡ ሥራቸውን መሥራት እንደቀጠሉ አንድ ቀን የቀን ሠራተኞቹ ለዚህ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ አንድ ጥብቅ ጉዳይ ሹክ ይሉታል “ይሄውልህ ቻይኖቹ ቀን ያሠርነውን የአርማታ ብረት ሌሊት ሌሊት ግማሹን አስፈትተውን ካወጡት በኋላ ነው የኮንክሪት ሙሊቱን የሚሞሉት” ብለው ይነግሩታል፡፡ አጅሬ ምንም ነገር የሰማ ሳይመስል ጸጥ ብሎ ይቆያል፡፡ ቻይኖቹ ሥራውን እየሠሩ በሠሩት መጠን ሒሳብ እንዲለቀቅላቸው የሚያደርግ አሠራር ስላለ ሒሳባቸውን ለማስለቀቅ በተገቢው መንገድ ለመሠራቱ የተቆጣጣሪው መሐንዲስ ፊርማ አስፈላጊ ነበርና እንዲፈርም ተጠየቀ፡፡ አጅሬው ሲጠብቀው የነበረው ጊዜ ይሄ ነበርና ተቋራጮቹን ይዟቸው ሄደና ከድልድዩ መሐል ቆመ፡፡ ጥሩ ፊርማዬን ነው የምትፈልጉት አይደል? ምንም ችግር የለም ብቻ እዚች ላይ ቴስት ማድረግ (መፈተሽ) እፈልገለሁና ከልሎ እያሳየ በዚህ ስፋት እዚህ ላይ ቆፍሩልኝ አላቸው ቻይኖቹ ደነገጡ፣ ተሸበሩ እንደጉንዳን ወረሩት ለመደራደር ሞከሩ 200,000ብር መደለያ አቀረቡለት አጅሬ ወይ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ አለ፡፡ ቻይኖቹም አይ እንግዲያውስ ምንም አታመጣም የት እንደምትደርስ ምን እንደምታደርግ እናይሀለን አሉት፡፡ ያልሄደበት ይመለከተዋል መፍትሔ ይሰጠዋል ብሎ የገመተው የከፍተኛ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት አልነበረም፡፡ አርፎ ካልተቀመጠ በሕይወቱ እንደፈረደ እንዲቆጥረው ዛቻና ማስፈራሪያ ከየአቅጣጫው ይመጣበት ጀመር፡፡ ጭራሽም ከሥራው አውጥተው ጣሉት፡፡ የምላቹህ በትክክል እየገባቹህ ነው? በሙስና ምክንያት መንገዶቹ እየተሠሩ ያሉት ደረጃውን ባልጠበቀ ግብአትና አሠራር ነው እየተሠሩ ያሉት፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ይሄ ከዚህ ሳይባል መንገዶቹ ጭራሽም ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ከመሆናቸው በፊት ውኃ ውስጥ እንደገባ ካርቶን ፍርክስክሳቸው የሚወጣው፣ የሚቀበሩት ቱቦዎች ለከፍተኛ መንገድ አይደለም ለመንደር ውስጥ መንገዶች እንኳን በማይበቃ ስፋት ተሠርተው የሚቀበሩትና የክረምቱን ጎርፍ የማሳለፍ አቅም አጥተው ጐርፉ አስፋልቱን አጥለቅልቆ የሚፈሰው፡፡ እነኝህን ብላሽ መንገዶች ለማሠራት ግን ሀገሪቱ በትውልደ ትውልድ ተከፍሎ ሊያልቅ ከማይችል የዕዳ ማጥ ውስጥ እንደተዘፈቀች ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡
የልማት ሥራ እየተባሉ በከፍተኛ ወጪ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ባለባቸው የተወሳሰቡና በርካታ የጥራት ችግሮች ምክንያት ችግር ሲያጋጥም ያለባቸው ችግር ይቀረፍና እንደገና በጥራት ይሠሩ ቢባል መጀመሪያ ለአጠቃላይ ግንባታ ከጠየቁት ወጪ እጥፍ እንደሚጠይቁና ከብዙ አቅጣጫ ቀድሞውኑ አለመሠራታቸው ይመረጥ እንደነበር ባለሙያዎች አበክረው ይናገራሉ፡፡ በእነዚህ ብላሽ ሥራዎች ሀገርና ሕዝብ ምን ያህል እንደሚጎዱ ለመግለጽ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ከኪሳራው በተጨማሪ አስከትለውት የሚመጡት የችግር ዓይነት ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ እንግዲህ የዚህ ሁሉ መንስኤው ኃላፊነት የማይሰማው ሀገሬ ሕዝቤ የሚል ቁጭትና ሐሳብ እውስጣቸው በሌለ ቡድን የሚሠራ ሥራ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ቡድን ከዚህ የዘለለ ነገር መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ ይሄ ይሄ ችግር ነው የተሠሩትን ሥራዎች የልማት ሳይሆኑ የትፋት የሚያደርጋቸው፡፡
በመብራት ኃይል መሥሪያ ቤት ዙሪያም ያለው ጉዳይ ከዚህ የከፋ እንጅ የተሻለ አይደለም፡፡ ለማሳያ ያህል እነዚህን ሁለት ባለሙያዎች አነሣን እንጂ በተመሳሳይ ሁኔታ በየ መሥሪያ ቤቱ ችግር ላይ የወደቁና ዜጎችና የተፈጸሙ ችግሮች ቁጥር የትየለሌ ናቸው፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በምን ምክንያት የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ኃላፊን አቶ ምሕረት ደበበን፣ በምን ምክንያት ከኃላፊነታቸው አንሥቶ ምን ሥራ እንደተሠራና የዚያ ውጤትም መብራት ኃይል አገልግሎቱን በብቃት ማቅረብ ሳይችል ቀርቶ በምን ዓይነት የኃይል መቆረረጥ ችግር ከቶን እንደከረመና በእነዚያ በሙስናው በተገዙት ከደረጃ በታች የሆኑ መሣሪያዎች ወደፊትም ላሳለፍነው ዓይነት ችግር እንደሚዳርጉን፤ በዚህ መሀል ሀገርና ሕዝብ ለከፍተኛ ኪሳራና ችግር እንደተዳረጉና እንደሚዳረጉም በተለይ በአሁኑ ሰዓት የአደባባይ ምሥጢር ነውና ይሄንን መዘርዘር አይጠበቅብኝም፡፡
ወያኔ ዐባይን ለመገደብ የተነሣባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፡-
1. የሕዝብን የምርጫ ድምፅ ለመንጠቅ፡- ይሄን የምለው ወያኔ ይሄንን ሥራ የጀመረው በእርግጥም የሕዝብ አቅም ይህን ፕሮጀክት (የሥራ ዐቅድ) ለመፈጸም የሚያስችል መሆኑን አውቆና አምኖ ከሆነና እውነታውም እንደዚያ ከሆነ ነው “ገንዘባችሁ ባለበት በዚያ ልባቹህ አለ” እንዲል መጽሐፍ አቶ መለስ ቦንድ ግዙ እያልኩ የእያንዳንዱን ገንዘብ ከያዝኩበት ለእኔ ሲል ሳይሆን ለራሱ ሲል “ገንዘቤን ይዞብኛል” ሲል፣ ቀልጦ እንዳይቀርበት ሲፈራ፣ የግዱን የእኔን መኖር በሥልጣን መቆየት ይፈልጋል፡፡ በዚህም ዘዴ ቢያንስ ግድቡ ካለቀም በኋላ ገንዘቡ እስኪመለስለት ድረስ ለዐሥርት ዓመታት መቆየት የሚያስችለኝን ዋስትና መጨበጥ እችላለሁ ገንዘቡ ጥሩ መያዣ ይሆንልኛል፡፡ ምርጫን ማጭበርበር ሳያስፈልገኝ በቀላሉ ማሸነፍ ያስችለኛል ሳይወድ በግዱ እኔን ይመርጣል፡፡ በሚል ብልጣብልጥ መሰል አስተሳሰብ የሥልጣን ዕድሜን ለማራዘም የተፈጠረች ዘዴ ናት፡፡
2. እጥረት ወይም ችግር በመፍጠር አመጽን ለመቆጣጠር ከሚል የአንባገነኖች ስልት፡- ወያኔ በግድቡ ግንባታ ሰበብ የየወር ደሞዙን በመቆንደድና ሕዝቡን ለችግር በመዳረግ ሀሳቡንና ትኩረቱን በጓዳው ችግር ብቻ እንዲወሰን እንዲጠመድ በማድረግ እሱን(አገዛዙን) እንዲረሳ እንዳያስብ ማድረግ እንደሚቻል በጽኑ ያምናል፡፡ ዋነኛ የአገዛዝ ስልቱም ነው፡፡ ደስ የማይለው አዝማሚያው የማያምረው አንቅስቃሴ በተፈጠረ ቁጥር እጥረት በሌለበት ሁኔታ መብራትና ውኃን ጨምሮ ሰው ሠራሽ እጥረት በመፍጠር መሠረታዊ ፍጆታዎች እንዳይኖሩ እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ የፈራውንም ነገር በቀላሉ ይቆጣጠራል፡፡ ይህ አሠራሩ እስከ አሁን ቢይዝለትም እስከመቼ እንደሚያዘልቀው ግን አላውቅም፡፡ ለማንኛውም ለዐባይ ግድብ እያለ አንደኛ ዙር ሁለተኛ ዙር ሦስተኛ ዙር ገናም ይቀጥላል፡፡ ከሕዝቡ የሚነጥቀው ገንዘብም በዚህ ረገድ እንዳሰበው አድርጎለታል ህዝቡን በየጓዳው ችግር ለመጥመድ ስላስቻለው ባሰበው መንገድ ለመቆጣጠር አብቅቶታል፡፡
3. አሥጊ ወቅታዊ የሕዝብ ትኩረትን ለማስቀየስ፡- እንደሚታወሰው የዐባይ ግድብ ፕሮጀክት በድንገት ታውጆ ሥራው በተጀመረበት ወቅት በተለያዩ ሀገራት ሕዝባዊ አመፆች እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለና ኢትዮጵያንም እንደሚያሠጋት ይወራ የነበረበት ወቅት እንደሆኑ መጠን የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየስና ሕዝብን በመደለል ለአመፅ እንዳይነሣሣ ለማድረግ ድንገት የተፈጠረ ፕሮጀክት ነው፡፡ ለዚህም ነው ይሄንን ለሚያክል ግንባታ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት ሊከወኑ የሚገባቸው መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ሂደቶችና ዝግጅቶች ሁሉ ሳይፈጸሙለት፤ ለምሳሌ አግባብነት ባለው አካሄድ ግልጽ ጨረታ፣ በእጅ ያለ በጀት፣ ሌላው ቀርቶ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ሥራ ከተጀመረ በኋላም እንኳን ይሄንን የሚያህል ፕሮጀክት በአንዲት መለስተኛ የመቆፈሪያ ማሳልጥ (Excavator Machine) ብቻ ሥራው ከወር በላይ ሲሠራ የነበረው፡፡
4. ጠያቂን አካል በማስመታት ከተጠያቂነት የማምለጫ መንገድ የመፈለግ ሸር፡- ወያኔ የዐባይን ግድብ ኘሮጀክት (የልማት ሥራ) ይፋ ሲያደርግ ግድቡን ለመሥራት አስቦ አልነበረም፡፡ በነገራችን ላይ ይህ የግድብ ሥራ ይፋ ሲደረግ የደነገጥኩትን ድንጋጤ እኔና እግዚአብሔር ነን የምናውቀው መቀመጫቹህ ላይ ፈንጅ ቀበርኩባቹህ የተባለ ነው የመሰለኝ፡፡ ሀገራችንን ጥቅልል አድርጎ ወደ ገደል የወረወራት ነው መስሎ የተሰማኝ፣ ያለ የሌላትን በዚህ ሰበብ ጠራርገው ሲበሉት ቀልጦ መና ሆኖ ሲቀር ነው የታየኝ፡፡ ከጀርባው ሊኖሩ የሚችሉ ነገሮች ወዲያው ነበር ይታዩኝ የጀመሩት “አይ በቃ ወያኔ ሰለቸ ታከተ ማለት ነው፣ የሚገላግለውን ነገር ፈለገ ማለት ነው” ነበር ያልኩት፡፡ ምክንያቱም ዐባይን በተመለከተ የሚሰሙ ምንም ዓይነት ሹክሹክታዎችን ግብጽ እንደማትታገስ አቶ መለስ ስለሚያውቁ በጠባብነት ታንቀው በሚዘውሩት አገዛዛቸው ቢሉት ቢሉት አልሆን ስላላቸው፣ ደላላ (ሎቢ) እየገዙ የሚያሥወሩት የውሸት እድገት የትም እንደማያደርሳቸው ስላወቁና ተስፋም ስለቆረጡ የሌለን ነገር ያለ ለማስመሰል የቻሉትን ሁሉ ቢያደርጉም ገሀዳዊው እውነታ ድንገት ተገልጦ መዋጣቸው አይቀሬ መሆኑን ስለተረዱና በሌላ አማራጭ ሥልጣን ከለቀቁም የሚከተላቸውን የሚያጋጥማቸውን ያውቃሉና ይሄንን አስልተው ከዚህ ሁሉ ጣጣ ሊድኑ የሚችሉበትን ዕድል ሲያፈላልጉ የተከሰተላቸው መላ ነበር፡፡ በእኔ እምነት የዐባይን ግድብ ግንባታ የወለደው ይሄ “የእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” አስተሳሰብ ነው እንጅ ወያኔ ብሔራዊ ሐሳብ ማሰብ ችሎ የተተለመ ትልም አይደለም፡፡ ሰብእናውና ተሞክሮው ይሄን አያሳይምና አያረጋግጥምና፡፡ ነገር ግን የሚያሳዝነው ነገር በአጋጣሚ ሆኖ ግብጽ በራሷ ችግር ተመሰቃቅላ ከመጠመዷ ጋር ተያይዞ አቶ መለስ በግልጽ ግብጾችን በዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛ “ወንድ ከሆናቹህ ኑ እንዋጋ” እያሉ የጦርነት ግብዣ ቢያቀርቡም ግብጽ ልታርገው አልቻለችም፡፡ መቶ መለስ ጉዳቸው ፈላ ተጋለጡ፡፡ ያሰቡት ቀርቶ ያላሰቡት ሆነ “አይ እግዚአብሔር ደጉ!” አቶ መለስ ባላሰቡት ሥራ እንደተጠመዱ አለፉ ግንባታው እስከ አሁን ባለው ሂደት በገንዘብ እጥርት ምክንያት በጣም ተጓቷል፡፡ በዚህ ወቅት 60% ያህሉ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡ የተጠናቀቀው ግን መጠናቀቅ ከነበረበት ከግማሹ የሚበልጥ አይደለም፡፡ ቀጣዩ ወቅት ትኩረት የሚስብና ልብ አንጠልጣይ ነው፡፡ ከመንግሥት ካዝና የለም የተባለው ገንዘብ ከየት እንደሚመጣ እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ ብድር አልተገኘም አስቀድሞም ይገኛል ተብሎ ተስፋ አልተደረገም፡፡ በጃንሆይና በደርግ የነበረው እንቅፋት ዛሬም አለና፡፡ እስከ አሁን በሕዳሴው ግድብ ሦስተኛ ዓመት ክብረ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ መሠረት 34% ቢሊዮን ብር ማለትም ለግንባታው ያስፈልጋል ከተባለው ወደ ግማሽ የሚጠጋ ወጪ እንደተደረገ እየተናገሩ ነው፡፡ አንድ ሦስተኛ ለማይሞላ ክንውን ይህንን ያህል ወጣ ማለት ግድቡን ለመጨረስ ለማጠናቀቅ ከ 113 ቢልዬን (ብልፍ) ብር በላይ የግድ ያስፈልጋል፡፡ ግድቡን ለማጠናቀቅም አሁን በያዙት ፍጥነት ከቀጠለ 10 ዓመታት ይወስዳል ማለት ነው፡፡ እሱም ገንዘቡ ከተገኘ ነው፡፡ ሳያስቡት የተጠመዱበትን ነገር ከመፈጸም ውጭ አማራጭ የለም ብለው ከተመዘበረው ገንዘብ ጥቂቷን አምጥተው ለመፈጸም ካሰቡ ምናልባት ግድቡ ይፈጸም ይሆናል፡፡ ይህ ዕድል ከሌለ ግን ኳሷን ወደ ሕዝቡ እግር በመምታት ማስተባበርና በግድም በውድም ከጎናቸው ማሰለፍ የቻሉት የሕዝብ አቅም የታየውን ያህል እንደሆነና የማያወላዳ አለመሆኑን እያውቁ ሕዝቡን “ግድቡ ማለቅ ካለበት አውጡ አናወጣም የለንም አንችልም ካላቹህ ግን ሥራው መቆሙ ነው” ውሳኔው የናንተ ነው በማለት ኃላፊነቱን ከራሳቸው ለማውረድ እንደሚሞክሩ እገምታለሁ፡፡ አቶ ኃይለማርያም ባላቸው መረጃ ደግሞ ለእስካሁኑ ክንውን 27 ቢሊዬን (ብልፍ) ያህል ብር ወጪ ሆኗል፡፡ በዚህም መሠረት ለማጠናቀቅ ከ90 ቢሊዬን(ብልፍ) ብር በላይ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡
የዐባይ ግድብ በሕወሓት ኢሕአዴግ መገደቡ ተገቢ አለመሆኑን ወይም አደገኛ መሆኑን የሚያረጋግጡ ነጥቦች፡- ጠላት ካልሆነ በስተቀር ጤነኛ አእምሮ ያለው ዜጋ ሁሉ የዐባይን መገደብ የማይፈልግ ይኖራል ብዬ አልገምትም አይኖርምም፡፡ እንዲያውም ዐባይ መገደብ ከነበረበት ዘመን በጣም ዘግይቷል፡፡ ግብጽ የምትፈጥረው እንቅፋት እየተሳካላት ቀደማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዐባይን ለመገደብ የሚያስችል ብድር አጥተው ዐባይን የመገደብ ሕልማቸው ሳይሳካ ቀረ፡፡ በደርግም ዘመን እንዲሁ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ሰላም እጦት ወይም የእርስ በእርስ ጦርነት እንቅፋት ሆኖበት ደርግም ሳያሳካው ቀረ፡፡ በዚህ የእርስ በእርስ ጦርነት ጀርባ የግብጽና የሱዳን ሙሉ እጅ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ የግብጽንና የሱዳንን ድጋፍ ያገኘ በነበረው በሕወሓት ኢሕአዴግ ዘመን ግን እንኳን ዐባይን ስለመገደብ ሊያስብ ይቅርና ደርግ ከፍተኛ ወጪ መድቦለት ሥራው ተጀምሮ በመቀጠል ላይ የነበረውን የጣና በለስን ፕሮጀክት እንዲዘጋ አድርጎት ነበር፡፡ ወያኔ ይህ አድራጎቱ ስሕተት እንደሆነ ለመረዳት የአንድ ታዳጊ ወጣት እድሜ አስፈልጎት ነበር፡፡ የደርግ መውደቅንና የወያኔን ሥልጣን መያዘ ተከትሎ በደርግ ዘመን በእንግሊዝ ሐሳብ አቅራቢነት የላይኞቹ የዐባይ ተፋሰስ ሀገራት የውኃ ድርሻ እንዲኖራቸው ያቀረበችው ሓሳብ ግብጽ ያለው የውኃ መጠን ሳይታወቅ እይሆንም ብላ በመቃወሟ ይሄንን ጉዳይ የሚያጠና ቡድን ተቋቁሞ እየተደረገ የነበረው ጥናትና ድርድር ሳይቋጭ ደርግ በመውደቁ ተቋርጦ ወያኔም ቅጥረኛነቱና አገልጋይነቱ ገና አፍላ ነበርና ይህ ድርድር እንዲቀጥል ፍላጎት ስላለነበረው እንደተቋረጠ ቀይቶ ነበር፡፡
ከጃንሆይ ጀምሮ እስከ ደርግ ሲጠና ሲከለስ ሲጠና ሲከለስ የቆየውና በደርግ ዘመን ተነቃቅተው የነበሩት ዐባይን መሠረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችም (የሥራ ዐቅዶች) ውኃ ተቸልሶባቸው ተዳፍነው ለመቆየት ግድ ሆኖ ነበር፡፡ ይህ ወቅት ለግብጽና ሱዳን የእፎይታ ዘመን ነበር፡፡ ወደ ኋላ ላይ አዲስ አበባ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብሰባ ሲመጡ በግብጹ መሪ ሆስኒ ሙባረክ የግድያ ሙከራ በመደረጉ ሳቢያ የሦስቱ ሀገራት ግንኙነት መሻከሩን ተከትሎ ወያኔ እንደ ማስፈራሪያ አድርጎት አዳፍኖት የነበረውን ዐባይን መሠረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችን በብዙኃን መገናኛ በአለፍ ገደም ማሳየትና ማሰማት ጀመረ፡፡ በተጨማሪም አንገብጋቢ እየሆነ የመጣው የሀገሪቱ የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ማሟላቱ ግዴታ ሲሆን የተቀያየሙት ወዳጆቹ ስለነሱ ሲል በዐባይ ላይ ምንም ዐይነት ፕሮጀክት ላለማሰብ ቃል ገብቶ የነበረውን ለማጠፍ ቅያሜው ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮለት በደርግ ተጀምሮ የነበረውንና ሽሮት የነበረውን የጣና በለስን ፕሮጀክት ካዳፈነበት በመቀስቀስ ሥራው ተጠናቆ ከ 4ዓመታት በፊት ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ይህም ጉዳይ በግብጽና በሱዳን ቅሬታ አሳድሮ የተግባቡት ቃል እንዲፈርስ ጥሩ ተጨማሪ ሰበብ ሆነ፡፡ አሁን እንደምናየውም ከ 50 ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲታሰብ የነበረው የዐባይን ግድብ እውነት የሚገነባ መስሎ እራሱ ለሚያውቀው ዓላማ ማለትም ለመገላገያ አስቦ የጀመረው እስከአሁን እንደምናየው ከሆነ እየሆነ ያለው ያሰበው ሳይሆን ያላሰበው ነው፡፡ የዚህ ግድብ እውንነት በጃንሆይ ዘመን እንደታቀደው ተከውኖ ቢሆን ኖሮ የሀገራችንና የሕዝባችን ገጽታ ምንኛ የተቀየረ በሆነ ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድም መታወቂያችን የሆነው የ1977ቱ ዓ.ም ድርቅና ረሀብም ባልተከሰተ ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ ለዚህ አሳፋሪ አዋራጅና ቅስም ሰባሪ ድህነት ባልተጋለጥን ነበር፡፡ በመሆኑም የዚህ ግድብ የመገደቢያ ትክክለኛ ሰዓት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዐባይን ለመገደብ ያቀዱበት ያ ጊዜ ነበር፡፡ አልሆነም አልተሳካም፡፡ ይህ የዐባይ ግድብ በሕወሓት ኢሕአዴግ ዘመንና በዚህ ወቅት መገደቡ ተገቢ ጠቃሚ የማያደርጉት ስድስት ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ቀደም ሲል መግቢያዬ ላይ ካየናቸው ባለ ቢሊዮን(ብልፍ) ዶላር በጀት የወያኔ የልማት ሥራዎች ተሞክሮ እንዳየነው አሳሳቢና አደገኛ የጥራት ችግር ነው፡- ይሄንን ይሄንን የሚያካክል የግንባታ ሥራ በወያኔ የነቀዘ ትከሻና ክንድ የተመረዘ ጭንቅላት በጥራት ይሠራል ብሎ ማሰብ የህልም እንጀራ ነው፡፡ የቀደመው ተሞክሮው በሙሉ የሚያሳየው ይሄንን ነውና፡፡ እምነት እንድንጥልበት የሚያደርጉ አይደሉምና የለብ ለብ እና የማታለል የዚያችው የዕለቷን ምስጋናን ማግኘት ብቻ ታሳቢ ያደረጉ ብላሽ ሥራዎች ናቸው፡፡ ወያኔ ሁሌም ሲያስብ ዛሬን እንደምንም ብሎ ማለፉን ነው እንጂ ስለ ነገ አይጨነቅም በዚህ ምክንያት ነው ምክንያት ነው ሥራዎቹ ከባባድና ከፍተኛ የጥራት ችግሮችን እንዲያስተናግዱ የተገደዱት፡፡ እሱም አባይ ውሸታም አጭበርባሪ የሆነው፡፡ ውሸቱ እብለቱ እንደ ውሸትነቱ እንደ እብለትነቱ ሁሉ በተጋለጠ ጊዜ ያኔ ምን ይውጠኛል ብሎ ፈጽሞ አያስብም አይጨነቅም፡፡ “አይነጋ መስሏት ከቆጡ ላይ ምን አለች” የሚለው ብሂላችን ወያኔን አንድም ቀን ገብቶት አያውቅም፡፡ እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ (mentality) ባለው ግለሰብም በሉት ቡድን ጥራት ከነ አካቴው ቦታ አይሰጠውም፡፡ ስለሆነም የጥራት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ስለሆነ፡፡
2. አቶ መለስ እንዳስታወቁት ይህ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ በሕዝቡ አቅም ይገነባል በማለታቸውና የሕዝቡ አቅም የምናየውን ያህል መሆኑ፡፡ በነገራችን ላይ ሕዝቡ ይህ የልማት ሥራ ግብዣ የቀረበለት በማያምነውና በክፉ ነገር ሁሉ በቁጥር አንድ በሚጠረጥረው በወያኔ በመሆኑ እንጅ ኢትዮጵያዊ በሆነና የሕዝብ ፍቅር ባለው መንግሥት ቢቀርብለት ኖሮ ይሄንን አይደለም ሌላም ቢጨመር በስኬት ለመደምደም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና ከሀገር ውጭ ያሉ ልጆቹ አቅም ብቻ ከበቂ በላይ በሆነ ነበር፡፡ የሀገሪቱ ካዝናም ቢሆን እዚህ ድረስ ባላሳበቀ ባላሳጣ ነበር፡፡ እናም ሀገርም ሕዝብም አቅም አልባ የሆኑት መሐንዲሱ ታማኙ ተወዳጁ ተፈቃሪው ወያኔ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ ሕዝቡ እንደምታውቁት ይሄንን ያህል ወገቡ ተሠብሮ አዋጥቶም ከሚፈለገው ዐሥር በመቶ እንኳን አልተገኘም፡፡ ይህ ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት ሕዝቡ ለወያኔ ያለው መነሣሣትና እምነት ይታወቅ ስለነበረ ጊዜው አለመሆኑን መረዳት ከባድ አልነበረም፡-
3. ሙስና፡- ሙስናን ወያኔ አንዱና ዋናው የአሥተዳደር ሥርዓቱ ስልት (strategy) አድርጎ የሚጠቀም ምናልባትም የዓለማችን ብቸኛ “መንግሥት” ነው፡፡ እያልኩ ያለሁት ሙስና የሚፈጽም አይደለም፡፡ አይፈጽምም ማለቴ አይደለም ሀገራችን ዐይታው የማታውቀው ሙሰኛ መንግሥት እንደሆነ ይታወቃልና፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት ወያኔ ዜጎችን የዘለዓለሙ ባሪያው አገልጋዮቹ እንዲሆኑ ተሽቆጥቁጠው እንዲገዙለት ሲያስብ ሲፈልግ ሆን ብሎ ሙስና ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡ ከዚያ በኋላ ያችን ይይዝና በማስፈራሪያነት እየተጠቀመ ያንን ዜጋ እንደፈለገ አድርጎ የሕሊና ጥያቄ እንዳያነሣ የታዘዘውን ብቻ እንዲሠራ አድርጎ ይገዛዋል፡፡ ለወያኔ እንደ ሙስና ዋና ጠቃሚ መሣሪያ የለም፡፡ እንዲህ ዓይነት የወደቀ የዘቀጠ አስተሳሰብ አመለካከት የያዘ ቡድን እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ የልማት ሥራ በጥራትና በብቃት መሥራት አይደለም ማሰብም እንኳን ከቶውንም አይችልም፡፡ በዚህ ግድብ ዙሪያ የሚነሡ በርካታ የሙስና ጉዳዮች አሉ፡፡ የግድቡ ሥራ ግልጽ ጨረታ አልወጣበትም፣ የግብአት አቅራቢ ድርጅቶችን በተመለከተ ግልጽና የተለያዩ የሙስና መገለጫ ገጽታዎች በሰፊው እየታየበት ይገኛል፡፡ በመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ መሠረት በወያኔ ዘመን 25 ቢሊዮን ዶላር ከሀገሪቱ እንደተመዘበረ ተነግሯል፡፡ ይህ ገንዘብ አንድ ብቻ አይደለም ከ10 በላይ የዐባይ ግድብ ሊገነባ የሚችል የሕዝብ የሀገር ሀብት ነው፡፡ እናም ሙሰኝነቱም ሌላው ዋነኛ ችግር ነው፡፡
4. የወያኔ ወያኔያዊ ባሕርይ ፡- ማለትም “ጠባብነት” ወያኔ በተፈጥሮው ጠባብ ነው ጎጠኛ ነው ብሔራዊ (ሀገር አቀፍ) አስተሳሰብን ሽታውንም አያውቀው፡፡ ኃላፊነት የማይሰማው ሀገሬ ሕዝቤ የሚል ሥዕል ከጭንቅላታቸው ውስጥ በሌለ ቡድን ጭንቅላት ውስጥ ከጎጥ አጥር ውስጥ ወጥቶ ከልብ (genuinely) ሀገርንና ሕዝብን ታሳቢ አድርጎ ብሔራዊ የልማት ሥራ ሊታሰብ ስለማይችል፡፡ በመሆኑም ወያኔ እንዲህ ዓይነት ግዙፍ የልማት ሥራ (mega project) አቅዶ በብቃት የመሥራት የሞራል (የቅስም) ብቃት አይኖረውም፡፡ ቅስምን ያህል ኃያል አቅም ሳይይዝ የሚሠሩ ሥራዎች ሁሉ እንደ እንቧይ ካብ ናቸው፡፡ ወያኔ የማይድን በሽታ አለበት “የጎጠኝነት ነቀርሳ” ይህ በሽታው ከጎሳው በላይ የሆነ ሐሳብ ሊያሳስበው አይችልም፡፡ ለዚህም ነው ዛሬም ከ23ዓመታት በኋላ ይሄ በሽታው ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከአፋር ሌላ ተጨማሪ መሬቶችን ወደትግራይ እንዲከልል ያደረገውና እያደረገው ያለው፡፡ ለምን ይምስላቹሀል? ምንስ እያሰበ? ያለ ዓላማ እንዲህ የሚያደርግ ይመስላቹሀል? ታዲያ በእንደዚህ ዓይነት ጠባብና ጎጠኛ ጭንቅላት ላይ ነው ኢትዮጵያ እንደ ኢትየጵያነቷ ታስባ እሷንና ሐዝቧን ተጠቃሚ የሚያደርግ በብቃትና በጥራት ግዙፍ የልማት ሥራ የሚታለመው? በሽታው በየት በኩል አሳልፎት? በነገራችን ላይ ከዚህ ከጠባብነት በሽታው ሳልወጣ ወያኔ ለትግራይም ሕዝብ ቢሆን አሳቢ ተቆርቋሪ እንዳልሆነ ታውቃላቹህ? ጠቀምኩ ብሎ የሚያደርገው የሚሠራው ሥራ ሁሉ ከወያኔ “መንግሥት” ህልፈት በኋላ የትግራይን ሕዝብ ከተለያዬ አቅጣጫ ለችግር ለፈተና የሚዳርጉ ናቸውና፡፡ ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ አሳቢ ነው ተቆርቋሪ ነው ልለው እችል የነበረው ወያኔ ኖረም አልኖረ መቸም ጊዜ ቢሆን የትግራይ ሕዝብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በፍቅር በሰላም በመተሳሰብ መኖር የሚችልበትን ሁኔታ ቢፈጥር ኖሮ ነበር፡፡ አስተዋይነት ብልህነት አርቆ ማሰብ መሪነት ማለት ይሄ ነው፡፡ ወያኔ ግን እየኖረ ያለው በ 21ኛው መቶ ክ/ዘ ይሁን እንጅ ሥራውና አስተሳሰቡ ግን ገና የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለሆነም ወያኔ ለማን እንደሚሠራና ምን እንደሚሠራ እንኳን የማያውቅ ፍጥረት ነው፡፡ “መንግሥት” ከሆነ በኋላ ኃላፊነቱ ለሁሉም እኩል መሆኑን መቀበል ተቸግሮ ሕዝቡን እየለየ ይሄ ሕዝቤ ይሄ ጠላቴ እያለ አንድን ብሔረሰብ በጠላትነት የፈረጀ በተቻለውም መጠን ለማጥፋት የሚጥር፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘርና በሐይማኖት ከፋፍሎ ለማባላት ለማፋጀት ለማስተላለቅ የሚጥር መሠሪና ክፉ አገዛዝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚያስችልን ሥራ ሊሠራ አይችልም፡፡ አቶ መለስ ምን ሲሉ እንደነበር አታስታውሱም? “አንዲት ግራም ጉልበት እስክትቀረኝ ድረስ ድርጅቴን አገለግላለሁ” ልብ በሉ ሀገሬን አይደለም ያሉት “ድርጅቴን” ነበር ያሉት፡፡ ለነገሩማ በትክክልም ያገለግሉና ያስጠብቁት የነበሩት ሀገርንና የሕዝብን ጥቅም ሳይሆን ድርጅታቸውንና የድርጅታቸውን ጥቅም በመሆኑ ሀገሬን አለማለታቸው ትክክል ነው፡፡ በዚህ መርሐቸው ሳቢያ የቱንም ያህል ለሀገር የሚጠቅምነ የሚበጅ ነገር ግን ለድርጅታቸው የማይበጅና የማይጠቅም ጉዳይ ቢኖር ጥንቅር ይላል እንጂ አይ የሀገር ጥቅም ይበልጣል ይቀድማል ብለው ለሀገር ከበጀ ይሁን አይሉም፡፡ የአስተሳሰባቸው መሠረት “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዳለችው እንስሳ ነውና፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ሀገርን የማይጠቅምና የሚጎዳ ነገር ግን ድርጅቱን የሚጠቅም ቢሆን ሀገርን ሽ ጊዜ ይጉዳ እንጅ የድርጅቱ ጥቅም ቅንጣት ታክል እንኳ እንድትቀር አይፈለጉም፡፡ በዚህ ምክንያት ሀገረችን ቢዘረዘሩ የማያልቁ ብዙ አጥታ ብዙ ተጎድታለች አንዳንዶቹ ለመቸውም መልሰን ልናገኛቸው የማንችላቸው ናቸው፡፡
5. የጦር ኃይል አቅም ውስንነት፡- ግብጽ አሁን ለጊዜው ኃይል መጠቀም አልፈለገችም ማለት በቃ ትታለች ማለት አይመስለኝም፡፡ ጦር ልታነሣ የምትችልበት ሥጋት ሰፊ ነው፡፡ ጦር የምታነሣበት አጋጣሚ ቢፈጠር ከወታደራዊ ትጥቋ አንጻር መመከት የሚያስችለን ተመጣጣኝ የትጥቅ ዝግጅት ሊኖረን የግድ የተገባ መሆን ነበረበት፡፡ ይሄንን የቤት ሥራ ማጠናቀቅ የቻለ መንግሥት ሲኖረን ግብጽም ራሷ ትንፍሽ ሳትል ግንባታችንን መፈጸም የምንችልበትን ሁኔታ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ይህ ጉዳይ ለኔ ምሥጢር ሊሆን ይችላል፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ቅርብ ለሆኑ ተቋማት ግን አይመስለኝም፡፡ በቅርቡ V.O.A. “ግሎባል ፋየር ፓወር” የተባለን መካነ ድር ጠቅሶ እንደገለተው ግብጽ ባላት ትጥቅና ወታደራዊ ዝግጅት ከዓለም 13ኛ ስትሆን ሀገራችንን ደግሞ 40ኛ ናት ብሏታል፡፡ እንደነሱ ትንታኔ የግብጽና የእኛ ወታደራዊ ትጥቅ አቅም ጨርሶ የማይመጣጠን እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ጥቃት ቢሰነዘርብን በብቃት ልንወጣው በማንችልበት ሁኔታ ዐባይን ለመገደብ መሞከር አስቀድሜ እንደገለጽኩት ተፈልጎ ካልሆነ በስተቀር ፍጹም ተገቢ ያልሆነና ያልበሰለ ውሳኔ ነው፡፡ “ስለሆነም ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከንቢያው ቁጢጥ” በመሆኑ ወይም “ከፈረሱ ጋሪው” በመቅደሙ፡፡
6. ይህ ግድብ እንዲያው ብሎለት ከእነኝህ አሳሳቢ ችግሮቹ ጋር በዚያም በዚህም ተብሎ ቢጠናቀቅና እየተናገሩ እንዳሉት ሁሉ የሚመነጨውን ኃይል ለሀገር ውስጥ ለገበሬው ሳይሆን ለውጭ ገበያ አቅርበው “መቼም አሁን ለጅቡቲና ለሱዳን እየተሸጠ ያለው ከእኛ ተርፎ ነው የሚለኝ እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ” እንኳን መብራት የሌላቸው አከባቢዎች መብራት ሊያገኙ ይቅርና አዲስ አበባን ጨምሮ የከተሞችን መብራት በማጥፋት ጭምር እንደሆነ ሁሉ እየተሸጠ ያለው ከዐባይ ግደብ የሚገኘው ኃይልም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ይውላል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ከወዲሁም ውል እየፈጸሙ ቸብችበውታል፡፡ እናም ከዚህ ግድብ የሚመነጨውንም ኃይል ለውጭ ገበያ በማዋል ጠቀም ያለ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ቢሆን የሚጠቅመው የሚያፈረጥመው የወያኔን ጡንቻ እንጅ ሀገርን ባለመሆኑ ፡- ከዚህም ጋር በተያያዘ ለምሳሌ የነዳጅ ዘይት በሀገራችን ቢገኝና ወያኔ ፔትሮ ዶላር ማፈስ ቢችል ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስባቹሁታል? “ሰብአዊ መብት ካላከበርክ” ከሚል ሊሰማው ከማይፈልገው ቅድመ ሁኔታ ጋር በሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ ይሄንን ያህል መፈናፈኛ መላወሻ አሳጥቶ የደቆሰን፣ የረገጠን፣ ያሰቃየን፣ የጨቆነን በአፍጢማችን ሲደፋን የተቃረበ አገዛዝ ማንም የማያዝበትን ቅድመ ሁኔታ የሌለበትን ለዚህ ለዚህ ብቻ ሳይባል እንደፈለገ የሚያደርገውን የራሱን የካበተ ገቢ ያገኘ ጊዜ ምን ሊያደርገን እንደሚችል አስባቹህታል? እስከዛሬም እኮ የጭካኔውን የሐሳቡን የምኞቱን ያህል ሊያደርግብን ያልቻለው አቅም ገድቦት ነው፡፡ አቅም ሲያገኝስ? ያኔማ እነሱን አያርገኝ ነዋ የሚለው! የነዳጅ ዘይት ለናይጄሪያ ምስኪን ሕዝብ ምን የተከረለት ነገር አለ? በድህነት ከመማቀቅ ፈቀቅ አደረገው ወይ? ጄኔራሎቹን ከማድለብ በስተቀር፡፡ ወያኔ ደግሞ ከናይጄሪያ መንግሥት ምን ያህል የከፋና መሠሪ እኩይ እርጉም እንደሆነ አታውቁም እንዴ? እነ ኤፈርትንና እራሳቸውን ነበር የሚያደልቡበት፡፡ እንጅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ጠብ የሚልለት እንዲት ነገር አይኖርም፡፡ እናም ነዳጅ በወያኔ ዘመን አንዲገኝ የምትፈልጉ የምትመኙ የምትሳሉ ወገኖች ካላቹህ የዮፍታሔን ስእለት (መጽሐፈ መሳፍ. 11፤30-40) እየተሳላችሁ ነውና ወዮ ለራሳቹህ፡፡ ኢትዮጵያዊ የሆነ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ያማከለ የሕዝብ ፍቅር ያለው፣ ተጠያቂነት ግልጽነት ያለው መንግሥት ሲኖረን ቢወጣ ግን የእያንዳንዷ የዘይት ነጠብጣብ ዋጋ በእያንዳንዱ ደሀ ገበሬ ታርፋለችና በጅቦች ተበልቶ እምጥ ይግባ እስምጥ ሳይታወቅ ከሚቀር፣ ለእኛም መሰቃያ መሣሪያ ከሚሆን የተባረከ መንግሥት በቶሎ ለመፍጠር ተነሥተናልና የተቀደሰ ሐሳባችንን ታሳካልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁንና ይሄንን ቶሎ እስክታስፈጽመን ድረስ እንደሠወርከው አቆይልን የሚለው የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡
እንግዲህ በእነዚህ ስድስት ዋና ዋና ፈተናዎች ችግሮች ምክንያት በዚህ ወቅትና በወያኔ እጅ የዐባይ ግድብ መሠራቱ ለሀገርና ለሕዝብ ሊሰጠው የሚችለው ጥቅም ሳይሆን ጉዳት ነው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ግንባታ የችግሮች ቋት በሆነው በሕወሓት ኢሕአዴግ እንዲገነባ መፍቀድ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው፡፡ እና መች ነው ጊዜው ካላቹሁኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጎኑ ማሰለፍ የሚችል፣ የሚታመን፣ ጠባብ ያልሆነ፣ ከጎጥ ተሻግሮ ማሰብ ማየት የሚችል፣ ኃላፊነቱን በቅጡ የተረዳና የሚሰማው፣ የበቃ የኢትዮጵያ መንግሥት ሲኖር መሆኑን እናንተም ለገማቹህ ፈራቹህ ትዕግሥቱን አለቅጥ አበዛቹህት እንጂ ታውቁታላቹህ፡፡ ወያኔን የምናውቀው የሀገሪቱን ጥቅምና ሉዓላዊነት አሳልፎ በስጠቱ ለጠላቶቻችን ቅጥረኛ ሆኖ ሲሠራላቸው እንጅ ለሀገራችን ሲሠራ አይደለም፡፡ እያልኩ ያለሁትን ነገር እየተረዳቹህ ነው? ኃላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ እንዴት ታዩታላቹህ? ምን ይሰማቹሀል? አስኩ አሰላስሉ፡፡ ሕወሓት ኢሕአዴግ እራሱን እንደገና መፍጠርና ኢትዮጵያዊ መሆን ካልቻለ በስተቀር እንዲህ መሆኑንም በማያሻማ ሁኔታ ሊያረጋግጥልን ካልቻለ በስተቀር ምንም ተስፋ አታድርጉ የዐባይ ግድብም ሆነ የነዳጅ ዘይት መገኘቱ ለሀገሪቱ መርገም እንጅ በረከት አይሆኑም፡፡ ወያኔ አሁን ባለበት ማንነቱ የሚሠራ ሥራ ሁሉ ለትውልደ ትውልድ የሚተላለፍ ድርብ ድርብርብ ኪሳራ እንጂ ኪሳራ ብቻ አይደለም የሚያተርፍልን፡፡ ጭፍን ሆኜ አይለም ማሳያዎቸን መከራከሪያዎቸን ይዠ ነጥብ በነጥብ የጠቀስኩ በመሆኑ፡፡ ጨለምተኛም ሆኘ አይደለም ያልኩት ሁሉ ውሸት በሆነና እኔ ጨለምተኛ ሆኜ በዚህ አስተሳሰብ የማፍር የምዋረድ ብሆን ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ጨለምታኛ (pessimist) ላለመባል ብሎ በዲያብሎስ እጅ መሆንን ወዶ ፈቅዶ እያለ አንድ ሰው ሽ ጊዜ ተስፈኛ (optimist) ቢሆን ምን ይጠቅመዋል? ምን ጠብ ይልለታል? ጨለምተኛ ማለት ተስፋ እያለ ተስፋ ለማድረግ አለመቻል ማለት እንጅ ተስፋ በሌለበት ተስፋ አለማድረግ ማለት አይደለም፡፡
የመንግሥት ሠራተኛ የሆነና የእንጀራ ምጣዱ ከመንግሥት ጋር የተገናኘ ነጻነቱን አሳልፎ ሰጥቷልና በእጁ ለማድረግን ሲንቀሳቀስ አይታይምና “ሴትዮዋ ናት አሉ የፍል ውኃ ጠበል ለመጸበል ወደ ጸበሉ ስትገባ ፍል ጸበል ነውና ለምጥጧታል ያኔ ዋይ ብላ ጮኸች ጸበልተኛው •ረ ተይ! እንደሱ አይባልም! እሰይ እሰይ ነው የሚባለው ብለዋታል:: የኔ ሴትዮዋ “የግድ እሰይ የግድ እሰይ” እያለች ተጸበለች አሉ” አሁንም የመንግሥት ሠራተኛ ሆኖ ከዚህ የተለየ አቋም ለማንፀባረቅ ሠራተኛው ሊፈጥረው የቻለው ወይም የተተወለት ዕዳልና መብት የለምና “የግድ እሰይ” ነው ነገሩ፡፡ ደግሞ ሌሎች አሉ ዳቦው የራሳቸው ሆኖ እያለ አሳልፈው ሰተው ሲያበቁ ፍርፋሪ የሚለቃቅሙ፣ ፍርፋሪ ለመለቃቀም ተስፋ አድርገው ደጅ የሚጠኑ እነዚህ ሁሉ ይሄ ያልኩት ሁሉ በሚገባ ቢገባቸውም ፈጽሞ የገባቸው መምሰል አይፈልጉም “ልማት” እያሉ ብቻ በአጫፋሪነት አብሮ የሚያጨበጭብ ነው፡፡ ለፍርፋሪ ብቻም ሳይሆን ያለመብሰልና ደካማ ሰብእናም ነው ጥቅምና ጉዳትን ትርፍንና ኪሳራን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ደምሮ ቀንሶ አካፍሎ የማስላትና የመረዳት አቅም ከማጣትም ነው፡፡ እነዚህ እነዚህ ናቸው እንግዲህ የወያኔ አገዛዝ እስትንፋስ፡፡ እንደነዚህ ዓይነቱ ዜጋ ባይበዛ ኖሮ ወያኔ 23 ዓመታት አይደለም 23 ቀናትም እንኳን የመቆየት ዕድል ባለገኘ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ከተወዳጅ ሕዝቧ ጋር ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው