ምርጫው አዲስ “ጠቅላይ ሚ/ር” አግኝቷል

“የተለቀቁት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እናጣራለን?” ኢህአዴግ

በሊቢያ ታፍነው የነበሩ ወደ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል ነጻ አውጪነት መለቀቃቸውን የግብጽ መንግሥት አስታወቀ፡፡ የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲ የተለቀቁትን ኢትዮጵያውያን አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመገኘት አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ ኢህአዴግ እንደተለመደው “የተለቀቁት ኢትዮጵውያን መሆናቸውን አጣራለሁ” እንደማይል ተገምቷል፡፡ “ተይዘን የነበረው በሊቢያ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ነበር” ከተለቀቁት አንዱ ኢትዮጵያዊ፡፡

በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን ሐሙስ በተሰራጨው የዜና መረጃ መሠረት በሊቢያ ደርና እና ምስራታ በተባሉ ከተሞች ታፍነው የነበሩ 30 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል እና በሊቢያ ድጋፍ ነጻ መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፡

ዜናውን ከካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ የግብጽ የዜና አውታሮች በቀጥታ ለአገራቸውና ለዓለም ሕዝብ እንዲሰራጭ አድርገውታል፡፡ ኢትዮጵያውያኑን የጫነው የምስር (አልምስሪያ) አውሮፕላን መሬት ሲነካ ከፓይለቱ ክፍል አካባቢ የግብጽ ሰንደቅ ሲውለበለብ ተመልክቷል፡፡ ቀጥሎም የተለቀቁት ከአውሮፕላኑ ከመውጣታቸው በፊት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ እስኪመጡ እንዲጠብቁ ተደረገ፡፡ እርሳቸውም እንደደረሱ ኢትዮጵያውያኑ የግብጽን ሰንደቅ እያውለበለቡ ሲወጡ ፕሬዚዳንቱ እያንዳንዳቸውን “እንኳን ለምስር አፈር አበቃችሁ” በሚል ፈገግታ እየጨበጡ ተቀብለዋቸዋል፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያን በግፍ ከታረዱ በኋላ በዚያ ስለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ሁኔታ ግብጽ በጥልቀት ስታስብ ነበር፤ ለዚህም ነው እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ወደቤታቸው እንዲመለሱ በጣም ጥረት ስናደርግ የነበረው” በማለት የቀድሞው የጦር ጄኔራል አልሲሲ እዚያው አየር ማረፊያው የተለቀቁትን ኢትዮጵያውያን ከኋላቸው አድርገው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ይኸው ከሳምንታት በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ግድያ እጅግ ያሳመማቸው መሆኑን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ እነዚህን ኢትዮጵያውያን በህይወት አስለቅቆ ወደ ግብጽ ለማምጣት የተፈለገው ጥረት ሁሉ መደረጉን በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡ “የግብጽ (የጦር ሠራዊትና የደኅንነት) አገልግሎቶች በዚህ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን በመከላከል፣ በማዳንና በማስለቀቅ ተግባር ተሳትፈዋል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ “በሊቢያ የሚከሰተው ነገር ሁላችንንም ይመለከተናል” ብለዋል፡፡

ዜናው እንደተሰማ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንዳሉት “ከመጪው ምርጫ አኳያ ይህ የግብጽ ተግባር እና የፕሬዚዳንቱ ቁርጠኝነት እንዲሁም ደመላሽነት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በመጪው ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ቢሆኑ ሳይሻል የሚቀር አይመስለኝም” በማለት ከአዲስ አበባ አካባቢ በላኩት ዋዛ አዘል መልዕክት አስታውቀዋል፡፡

የወገኖቻችን አሰቃቂ ግድያ እንደተሰማ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራን ነው” በማለት ሲያላግጥ የነበረው ኢህአዴግ ሦስት ቀን “ብሔራዊ ሃዘን” በማለት ቢያውጅም ከአንድ ቀን በላይ መቀጠል አለመቻሉ ብዙዎችን ያጠያየቀ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ከዚህም ሌላ ደርግን “በጦርነትና በጀግንነት” አሸንፈን “ነጻ አወጣን”፣ “ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ነን የሚለው ህወሃት “ካስፈለገም ጦርነትን እንሰራለን” ሲል እንዳልኖረ ሁሉ 30ኢትዮጵያውያን በግፍ ከታረዱ በኋላ ምንም ዓይነት የጀግንነት፣ የአርበኝነት ወይም የጦረኝነት ምላሽ ቢያንስ እንኳን ለማሳየት አለመቻሉ ከመጀመሪያውኑ ባዶ ጀግንነት የተሸከመ በምዕራባውያን ድጋፍ የራሱን ወገን በመሸጥ ሥልጣን ላይ የተቀመጠ፤ ኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ ኩራትና ወኔ የሌለው በከንቱ ጀብዱ የተሞላ ባዶውን የቀረ ቀፎ ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል፤ ለዚህም ነው ለሃዘን የወጣው ሰልፈኛ “ያገር አንበሳ የውጭ ሬሳ” ብሎ የፈከረው በማለት ብዙዎች ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ከርመዋል፡፡

ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የግብጽ ሚዲያ ኢትዮጵያውያኑ ከታፈኑበት ተለቀቁ ቢልም ከተፈቱት መካከል አስተያየቱን የሰጠ አንድ ኢትዮጵያዊ እንደተናገረው ተይዘው የነበረው በሊቢያ የጸረ ሕገወጥ ኢሚግሬሽን አካል እንደነበረና የግብጽ መንግሥት መጥቶ እንዳስለቀቃቸው ተናግሯል፡፡

ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ጽ/ቤት የተለቀቀው መረጃ እንደጠቆመው ፕሬዚዳንት ሲሲ “የመጀመሪያውን ዙር ከሊቢያ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ወንድሞችን” መቀበላቸውንና ይህም በቀጣይነት የሚካሄድ ዘመቻ መሆኑን አመላክቷል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Comments

 1. Ewunetegna yehagerna yewegen fikr yalew zega yinur.
  ENE KEMOTKU SERDO AYBKEL SEWOCH BEIHADIG MERIWOCH lay silemitay

 2. >>> የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲ በሊቢያ ታፍነው የነበሩ ወደ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል ነጻ አውጪነት በመለቀቃቸው የተለቀቁትን ኢትዮጵያውያን አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመገኘት “እንኳን ለምስር አፈር አበቃችሁ” በማለት በፈገግታ እየጨበጡ አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ያስለቀቁት የግብፅ ወታደሮችና የግብፁ ፕ/ት አብድል ፈታህ አልሲስ ግብፅም እራሷ ቀድሞውንም ኢትዮጵያ እንደነበሩ እናጣራለን!? እንግዲህ የሊቢያ ኢምግሬሽን ይሁን የኢህአዴግ ደላላ ወይንም እራሳቸው ግብፆች ያገቷቸውና ለፖለቲካ ድምቀት የሰሩትም ትዕይንት ከሆነም ይጣራል!።
  *****
  “ደርግን “በጦርነትና በጀግንነት” አሸንፈን “ነጻ አወጣን”፣ “ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ነን የሚለው ህወሃት “ካስፈለገም ጦርነትን እንሰራለን” ሲል እንዳልኖረ ሁሉ 30ኢትዮጵያውያን በግፍ ከታረዱ በኋላ ምንም ዓይነት የጀግንነት፣ የአርበኝነት ወይም የጦረኝነት ምላሽ ቢያንስ እንኳን ለማሳየት አለመቻሉ ከመጀመሪያውኑ ባዶ ጀግንነት የተሸከመ በምዕራባውያን ድጋፍ የራሱን ወገን በመሸጥ ሥልጣን ላይ የተቀመጠ፤ ኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ ኩራትና ወኔ የሌለው በከንቱ ጀብዱ የተሞላ ባዶውን የቀረ ቀፎ ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል፤” ይልቁንም የሕዝብን አመፅና ብሶት ‘እንደ ትኩስ ድንች’ ሲፈጀው ሕጋዊ ደላሎች አነማን? ምን እደሰሩ? ለፓርቲው የሰጡትን የገንአብ መጠን ሳይናገር “በሕገወጥ ደላላና ሰማያዊ ተፎካካሪ ፓርቲ ላይ ጣለው …
  *******
  ** በመሠረቱ ህወአት/ወያኔ.ኢህአዴግ ልመታዊ አትረፊ ደርጅት ነው…የድሃ ልጅ ይገላል እንጂ ያለትርፍ አይሞትም ከሱማልያና ደቡብ ሱዳን የባሪያ አሳዳሪዎቻቸውን የግል ጥቅም ለማስከበር ኢንቨስትመንታቸውን ለመንከባከብ ግን የወሰደና ያስበላው የድሃ ገበሬ ልጅ ቁጥር አይታወቅም! አይነገርም! አይጠቅም!..ሻእቢያ የቀጠናው አታራማሽ ሲሆን ህወአት የቀጠናው ሰላም አስከባሪ ሆኖ ኢህንን ነጭ.. በነጭ ወሬ..በቢጫ ጋዜጠኛና ልማታዊ አርቲስት ዳንኪራ ታጅቦ ሞኖፓሊያቸውን በማስፋፋት ይቦጠቡጣሉ። ለዚህም ሥልጣን አስከባሪዎች የጋራ ድርሻቸውን(ኮሚሽናቸውን) በታላቁ ባለሀብት(ሺክ አላሙዲን) ሥም በእጅአዙር ይቀበላሉ፡ ኢህአዴግና ቤተሰቦቻቸው ያለባቸውን ብድር ከፍለው እስኪያገባድዱ የሀገሪቱን ግማሽ የልማት ቦታ ለሃያ ዓመት አጥረው በመያዣ ያስቀምጣሉ..አብዮታዊ(ፖለቲካ) ልማታዊ(ገንዘብ) ዴሞክራሲያዊ (ወሬ) ታጅቦ አጀይብ ያሰኘ ወሮ በላ ቡድን!!!

Speak Your Mind

*