
አፈቀላጤ ሬድዋን “ጥቂት” በማለት የጠሯቸው ነገር ግን በዓለምአቀፍ ሚዲያ በብዙ ሺህ ተብሎ የተዘገበው የተቃውሞ ትዕይንት ከቪዲዮ ምስሎች ላይ ያውጣጣነው ፎቶ በዚህ መልኩ አቅርበነዋል፡፡ ቀላጤ ሬድዋን 7ፖሊሶች መደብደባቸውን ሲናገሩ ፖሊሶቹ ስላሸበሩት ሕዝብ ግን ምንም አለማለታቸው “እንዳያስገመግማቸው” ያስፈራል፡፡ ከ“ምርጫው” በኋላ የሚመጣውን የፈሩ ይመስላል ቀላጤ ሬድዋን ኅያዋንን ብቻ ሳይሆን ሰማዕታትንም ዜግነት በመንፈግ ትጋታቸውን ጨምረዋል፡፡ ስለዚህ ደብዳቢ ፖሊሶቹ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ያጣሩልን” እንላለን፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
“የተቀሉት ግን በእምነታቸው የጸኑ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው እኛም አውቀናል የዓለም ሕዝብ አረጋግጧል!”
——————————————————————————-
*************************
አይ የእኛ ነገር በቋንቋ ብሔር ንትርክ
ትልቁን ዓለም ትተን በክልል መቸክ
የተሰዋው ሠው ነው ኢያሱ ይኵኖአምላክ
መች ዳነ ተማረ በብሔሩ ባልቻ በለጠ
ሊያልፍኝ ብሎ ሲንከራተት ከአውሬ አላመለጠ
በካቴና ተጠፍሮ ተጨምድዶ እንዳይሸሽ
በቋንቋው ሳይሆን በእምነቱ ታረደ ዳንኤል ሐዱሽ
ለለውጥ ለሠላም በበረሃ ሊያልፍለት ሲባክን
ደሙን ጠጣው አውሬ ቡሩክ ካሳሁንን
ተው ስማኝ ሕዝቤ ወገኔ ጆሮ አልባው ወያኔ
በሀገሩ ክብር ተስፋ ቆርጦ ነው ኤልያስ ተጫኔ
በዱር በገደል በበረሃ በሰው ሀገር ሊማቅቅ
ቢከፋው ነው ቢያዝን ቢዋረድ በቀለ ታጠቅ
ያላየ ባልደርሰው ዕድገት ሌት ተቀን ጆሮው ቢደማ
እንቢኝ አለ የበይ ተመልካች በቀለ አርሰማ
እኩልነት በወሬ ዲሞክራሲ በጭፈራ ሲያደርጉ
ልዩነት ውበት አደለም አንድንት አለ ዳዊት ሐድጉ
ቢያልፍልኝ ልሰደድ አለ ሰው ብሆን ላቤን አፍስሼ
ከበይ ተመልካችነት ስደት መርጦ መንግሥቱ ጋሼ
እያስታወሰ የጥንቱን የእስላም ክርስቲያን አብሮነቱን
ከባልጀራው አብሮ ተሰዋ በሜንጫ ጀማል ራህማን
የሃይማኖት ጽናት ቁርጠኝነት ወርሷልና ከቤተሰቦቹ
አልበጥስም አለ የቅድስና ማተቡን አወቀ ገመቹ
*****
ደማችሁ የፈሰሰ በውለታ ቢስ እርጉም
በሰይጣን..ጭራቅ..እጅ ብትወድቁም
ሞት አንድ የእግዝሐብሔር በር ሠፊ ነው
ጽንፈኝነት አክራሪነት ነፍስ ማጥፋት ጠባብነት ነው!
ስማችሁም ላልተወሳ ጌታ ብል በማይበላው ይጻፈው!
ነፍስ ይማር የሰው ልጅ ሁሉ ክቡር ፍጥሩ ነው በለው!!
***************************************