• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው

February 3, 2023 05:17 pm by Editor Leave a Comment

ክርስቲያኗ ክስ መመሥረቷም ተሰምቷል

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ውስጥ የተፈጠረውን መከፋፍለ ተከትሎ አንደኛውን ወገን ለማውገዝ ተጠርቶ ከነበረው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መካከል የባህር ዳሩ መሰረዙ ተገለጸ።

“ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንዲቀርብ” ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ነው “ጥር 28 በባሕር ዳር ከተማ እሑድ ጥር 28 ፡ 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ሊደረግ የነበረው “ኦርቶዶክሳዊ” የተባለው ሰልፍ እና የምህላ ፀሎት መራዘሙ በመግለጫ የተገለጸው።

“ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላልፏል። ስለሆነም በቀጣይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚቀርብልን አቅጣጫ ተከትለን የተጀመሩ ስራዎች ሳይቋረጡ ለጊዜው ለጥር 28 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል” ሲል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የባሕርዳር ሀገረ ስብከት አመልክቷል።

ቀደም ሲል “ሼር! ፖስት ይሁን!” በሚል “ባሕርዳር ኦርቶዶክሳዊ ሰልፍና ጸሎተ ምህላ ጥሪ አድርጋለች። የፊታችን እሑድ ሁሉም ምእመን ከአጥቢያው በኅብረት ተነሥቶ 1:30 ባሕር ዳር መስቀል አደባባይ እንዲደርስ ጥሪ ተደርጓል። በዚህ አጋጣሚ በኮሚቴው ከተዘጋጁ ባነሮች ውጭና ያልተፈቀዱ መልእክቶችን ይዞ መምጣትና ማስተላለፍ የተከለከለ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዐርማ ውጭም ምንም ነገር መያዝ አይፈቀድም ተብሏል” ታውጆ ነበር።

በተመሳሳይ ዜና ችግሩ በመነጋገር ብቻ እንደሚፈታ የመስማማት ፍንጭ መታየቱን ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ ገልጸውልናል። ዝርዝሩን ወደፊት እንደሚናገሩ ያስታወቁ “ኦርቶዶክስ በፖለቲካ ቁማርተኞችና ካድሬዎች ሴራ ከገጠማት ችግር በቅርቡ እንደምትፈውስ እምነት አለን” ሲሉ ተናግረዋል። 

“ሁሉም ወገን ጋር እውነት፣ ሁለቱም ወገኖች ጋር ስህተት አለ” ያሉት ክፍሎች፣ እንደ እምነት አባት ንስሃ ገብተው ችግራቸውን መፍታት ሲገባቸው ጉዳዩን ለተመሪው ምዕመን አቀብሎ ለውዝግብ በር መክፈት ትክክል እንዳልሆነ የተቀበሉ አሉ። ከሁለቱም ወገን ስህተታቸውን ለማረም የተዘጋጁ መኖራቸው አንድ እርምጃ እንደሆነ ገልጸው “ታላቁ መስዋዕትነት ይቅርታ ማድረግና ይቅርታን መቀበል ነው። ይህን የማያደርጉ ክርስትና አልገባቸውም” በሚል መወቀሳቸውንም አመልክተዋል። ህዝበ ክርስቲያኑ ለዕምነቱ ስለሚቀና ከስሜትና ድፍን ጥሪ መታቀብ እንደሚገባ በመታመኑ መላዘብ እንደተጀመረ ታዉቋል።

ይህን ችግር በመጥለፍ የፖለቲካ አላማና የቆየ ጥላቻቸውን ለማቀጣጠል “የማይቀረው ህዝባዊ አብዮት” በሚል ሰሞኑንን ጉዳዩ ላይ ነዳጅ ሲያርከፈክፉ የነበሩ በዜናው መበሳጨታቸው ታውቋል። (Ethio12)

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመንግስት የተለያዩ ተቋማትና በተወገዙት የቀድሞ ሶስት ጳጳሳትና የተሾሙት 25 ጳጳሳት ላይ ክስ መመሥረቷም ተሰምቷል።

የክሱ ዝርዝር ዋና ዋናዎቹ የቤትክርስቲያንን ክብርና ስም በመንካት፤ በህይወት የመኖር፣ የመዘዋወር እና የማምለክ መብትን በመንካት፤ መንግስት ሁሉን ሰው በእኩል ህጋዊ ጥበቃ እና በእኩልነት የማየት ህገመንግስታዊ ሀላፊነትን ባለመወጣት፤ የቤተክህነት ንብረት ሲዘረፍ እርምጃ ባለመውሰድ፤ ጳጳሳትን እና የቤተክህነት ህጋዊ መዋቅር ውስጥ ያሉትን በማፈን፣ በማሰርና በማስፈራራት፤ የመንግስት ሚዲያ በህዝብ ሀብት እየተዳደረ የቤተክርስቲያኗን መግለጫ እና የደረሰባትን የህግ ጥሰት ባለመዘገብ ህገመንግስታዊ ሀላፊነትን ባለመወጣት፤ አቶ ሀይለሚካኤል ታደሰ የተባሉ የህገወጦቹ ቃል አቀባይ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ፀብ አጫሪ ቅስቀሳ በማድረጋቸው ተከሰዋል።

ክሱ ሰኞ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት በስምንት ሰዓት ይሰማል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለያየ አገረ ስብከቶች የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳተ አሁንም አየታሰሩ እንደሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ የዜና ምንጮች ይጠቁማሉ። ይህንን አፈና፣ ማዋከብና እስር በተመለከተ ከመንግሥትም ሆነ በአብዛኛው ችግሩ ከሚከሰትበት ኦሮሚያ ክልላዊ መሥተዳድር የተባለ ነገር የለም።

ከተወገዘው ሲኖዶስ ጋር አብረው የነበሩት እና በኋላም በንሰሐና ይቅርታ የተመለሱት ከጥቂት ቀናት በፊት ታሰርሁ ብለው መልዕክት ከላኩ በኋላ በዚያው ስልካቸው ተለቅቄአለሁ ብለው ለወዳጃቸው መላካቸው ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ የጣለ ተግባር ሆኖ አልፏል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Right Column, Social Tagged With: Ethiopian Orthodox Church, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule