በማኅበራዊ ሚዲያ የትህነግን ጉይ እየተከታተለ መረጃ የሚያጋራው አስፋው አብርሃ በትግራይ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ካጋራው መረጃ ጥቂቱ እንዲህ ይነበባል፤
በትግራይ ልጁን ለወያኔ ያልሰጠ ወላጅ እየታሰረ ነው። አሁን ይኼ ውጪ አገር የሚኖር ልጅ ነው። በአንድ ወቅት “ወያኔ ቅዱስ ነው ” ብሎ FB ላይ ለጥፎ ነበር። አሁን “ወላጅ እናቴ ታስራለች። በሽተኞችን ሳይቀር እየተሸከሙ ያስሯቸዋል” ይላል የባይቶናው ክብሮም በርሄ። (“ልጆቻችሁን ደብቃችኋል ፤አምጡ” እየተባሉ ነው የሚታሰሩት..)
የትግራይ ወጣቶች የሚመዘኑበት መስፈርት “ታግሏል ወይስ አልታገለም” የሚል ብቻ ሆኗል። ልጁን ለወያኔው ትግል አሳልፎ ያልሰጠ የትግራይ ወላጅ ደግሞ ለእስር የሚዳረግበት ትልቅ ወንጀል ሆኗል።
ይሄ ፅሑፍ ገራሚ ነው።
ፅሑፉ ልጃቸውን አምጡ ተብለው ስለታሰሩ አንድ አባት የሚያትት ነው። የሰውዬው ልጅ ግን የወያኔ ታጣቂ ሆኖ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ሲዋጋ ሞቷል። ሰውየው አሁን ፈረስማይ ውስጥ ታስረዋል። የወረዳዋ አስተዳዳሪ ነጋሲ ገረንችኤል ነው። ሰውዬው ልጃቸው ሲዋጋ መሞቱን ቢናገሩም አስተዳዳሪው ግን “ልጁን ደብቃችሁታል። እንኳንስ ሊሞት ጭራሽ አልታገለም” ብሎ እንዳሰራቸው ፀሐፊው አዝኖ ይገልፃል ።
ከጥቂት ቀናት በፊት የትህነግ ፅ/ቤት ኃላፊ ዓለም ገብረዋህድ ይህንን ብሎ ነበር፤ “ከግምባር የተመለሱትም (ቁስለኛውም፤ የሸሸውም) ቢሆን 10 ቀን ሰልጥነው በድጋሚ መዝመት አለባቸው። አሃዱ (ጓድ) የነበረው ቀድሞ ወደ ነበረበት አሃዱ (ጓድ) ይመደባል። አሃዱ የሌለው ወደ አዲስ አሃዱ ይመደባል። እነሱን መልሰን እንዲዘምቱ ካላደረግን አዳዲስ ልጆችን እንዲዘምቱ ማድረግ አንችልም። አንድ ሰው መቅረት የለበትም። ይሄን የማያደርግ አመራር ካለ እንዳናየው፤ ከፊታችን ዞር ይበል”።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply