በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ለሚከሰቱ ግጭቶችና የሰላም እጦት ችግሮች ሙስና ዋነኛው መንስኤ መሆኑን ትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ አስታወቀ። ባለፈው ዓመት በተካሄደው ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በሙስና ከዓለም 87ኛ ደረጃ ላይ እንደነበረች ተጠቁሟል። የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ሙስና በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶችና የሰላም እጦቶች ዋነኛ መንስኤ ነው። ኢትዮጵያ የተለያዩ የጸረ ሙስና ስምምነቶችን ብታደርግም፤ የጸረ ሙስና ትግሉን የሚያጠናክሩ ተቋማት አለመኖራቸው ውጤታማ ስራ እንዳይሰራ ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ። በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችና የሰላም እጦቶች በአንድም ሆነ በሌላ ከሙስና ጋር የተያያዙ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ሳሙኤል፤ ሙስናና ብልሹ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ