* የመለስ ፋውንዴሽን 100 ሺ ዶላር ወስዷል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ሥልጣን በያዙ ማግስት የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ካዝና ክፉኛ ተመዝብሮ ባዶ እንደነበር ተናግረው ነበር። እርሳቸውም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ከብሔራዊ ባንክ ደንብና መመሪያ ውጭ ሲባክን እንደ ነበር ሸገር ያገኘው አንድ ሰነድ ያስረዳል። ከለውጡ ወዲህ ባሉ ጊዜያትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውጭ ለማይፈቀድላቸው እንደሰጠ ሸገር ካገኘው ሰነድ ተረድቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአቶ በቃሉ ዘለቀ ይመራ በነበረበት በ2010 ዓመት ከግንቦት እስከ ነሐሴ ከባንኩ በትንሹ ከ69 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ (የውጭ ምንዛሪ) ከመመሪያ ውጪ ለተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች እንደተሰጡ ከሰነዱ አንብበናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ … [Read more...] about ከ69 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከመመሪያ ውጪ ከኢትዮጵያ ባንክ መባከኑ በሰነድ ተረጋገጠ