በድሬደዋ የፀጥታ አካላት በጋራ ባካሄዱት የክትትልና ቁጥጥር ስራ በህገ -ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የሀገርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች መያዛቸው ተገለፀ።ገንዘቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ትላንት መስከረም 6/2013 ዓ/ም ሲሆን ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ መሰረት ባደረገ ክትልል መሆኑን ድሬ ፖሊስ አስታውቋል።ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ መታየት መጀመሩም ተገልፃል።በቁጥጥር ስር ከዋሉት የብር ኖቶች ውስጥ በዋነኝነት፦ ዘጠኝ መቶ አርባ አርት ሺ አንድ መቶ አስር (944,110) የኢትዮጽያ ብርአንድ ሺ ሁለት መቶ ሀምሳ (1250) የአሜሪካን ዶላርአንድ መቶ ስልሳ አምስት (165) የሳውዲ ሪያልሰባት መቶ አርባ አምስት (745) ዩሮ ሲሆኑ ከእነዚህ ጋር አብሮም ከዘጠኝ በላይ የሚሆኑ … [Read more...] about በድሬዳዋ፤ ደቡብ ኦሞና ጌዴኦ ሃሰተኛና ሕገወጥ የብር ኖቶች ተያዙ
illegal money
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሀመድ እንደገለጹት፣ በክልሉ በሚገኙ 4 የተለያዩ ኬላዎች በተደረገ ፍተሻ 2,370,000 ብር በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ በክልሉ ኩርሙክ ወረዳ ሱዳን ድንበር አካባቢ በግለሰብ ሲዘዋወር የነበረ 600 ሺህ ብር የሚሆን ገንዘብ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተናግረዋል፡፡ ግለሰቡ 600 ሺህ ብር በሞተር ብስክሌት ጭኖ ሲጓዝ የጸጥታ ኃይሎች ባደረጉት ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል። በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪው ለፖሊስ በሰጠው ቃል ገንዘቡን ለወርቅ ግዥ እያንቀሳቀስኩ ነው ማለቱን ተናግረዋል። በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ማንኩሽ ኬላ 300 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን … [Read more...] about በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር ዋለ