እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015ዓም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የስንዴ ምርት ወደ ውጭ የመላክ መርሃግብር በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አስጀመሩ። የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረቱን በሰላም፣ ልማትና ብልፅግና ላይ በማድረግ የበለፀገችና ለሌሎች የምትተርፍ ሀገር ለማየት እንዲተጋም ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባሌ ላይ ያየነው ስንዴን ኤክስፖርት የማድረግ ሂደት ለኢትዮጵያ ማድረግ ከሚገባን ትንሹ ስኬት ነው ብለዋል። የምናደርገውንና የምናቅደውን በተግባር በአረንጓዴ አሻራና በህዳሴ ግድብ እያሳየን መጥተናል፤ አሁን ደግሞ ስንዴን ከውጭ ከማስገባት ከማቆም ባለፈ ወደ ውጭ በመላክ ያሰብነውን በተግባር ፈፅመን ለኢትዮጵያዊያንና ለዓለም አሳይተናል ነው ያሉት። በዚህም ኢትዮጵያ ከስንዴ እርዳታ መላቀቅና ወደ ውጭ መላክ አትችሉም … [Read more...] about በመዝገበ ቃላት የችጋር መጠሪያ የነበረችው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ወደ ውጭ ላከች