• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በመዝገበ ቃላት የችጋር መጠሪያ የነበረችው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ወደ ውጭ ላከች

February 13, 2023 03:28 am by Editor Leave a Comment

እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015ዓም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የስንዴ ምርት ወደ ውጭ የመላክ መርሃግብር በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አስጀመሩ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረቱን በሰላም፣ ልማትና ብልፅግና ላይ በማድረግ የበለፀገችና ለሌሎች የምትተርፍ ሀገር ለማየት እንዲተጋም ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባሌ ላይ ያየነው ስንዴን ኤክስፖርት የማድረግ ሂደት ለኢትዮጵያ ማድረግ ከሚገባን ትንሹ ስኬት ነው ብለዋል።

የምናደርገውንና የምናቅደውን በተግባር በአረንጓዴ አሻራና በህዳሴ ግድብ እያሳየን መጥተናል፤ አሁን ደግሞ ስንዴን ከውጭ ከማስገባት ከማቆም ባለፈ ወደ ውጭ በመላክ ያሰብነውን በተግባር ፈፅመን ለኢትዮጵያዊያንና ለዓለም አሳይተናል ነው ያሉት።

በዚህም ኢትዮጵያ ከስንዴ እርዳታ መላቀቅና ወደ ውጭ መላክ አትችሉም ያሉንን ችለን በማሳየታችን ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል።

ለዚህ ስኬት የኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ ሌሎች ክልሎችም በክረምት፣ በበልግና የበጋ መስኖ ልማት ጉልህ አበርክቶ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

በተለይም የኦሮሚያ፣ የሶማሌ እና የአማራ ክልሎች ሰፊ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ላይ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ250 ሚሊዮን በላይ እርዳታ ፈላጊዎች መኖራቸውን በመጥቀስ “ኢትዮጵያን ኤይድ” በሚል ስንዴ ለመለገስ ተግተን እንሰራለን ነው ያሉት።

በዓለም ላይ የተፈጠረውን የስንዴ ገበያ ችግር ለማቃለልም ኢትዮጵያ የበኩሏን እንደምትወጣ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረቱን በሰላም፣ ልማትና ብልፅግና ላይ በማድረግ የበለፀገችና ለሌሎች የምትተርፍ ሀገርን ለማየት እንዲተጋም ጥሪ አቅርበዋል።

የሚያጋጥሙ ችግሮችን በስሜት ሳይሆን በምክክርና በማስተዋል እየፈታን ለሀገር መስራት አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግስት ህዝቡን ከድህነት ለማላቀቅ ከሚሰራው ስራ ባሻገር ለዘመናት ተከማችቶ የቆየውን የእዳ ጫና የማቃለል ትልቅ ህልም ይዞ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያን የስንዴና ሌሎች የኤክስፖርት ምርቶች በማሳለጥ ልማቷን በማፋጠን ጠንካራና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን ብለዋል።

“ኢትዮጵያ ያሰበችውን ከማሳካት ሊያቆማት የሚችል እንደሌለ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በወንድማማችነት፣ እየተመካከርን፣ እየተደማመጥን በጋራ የሀገራችንን ህልም ማሳካት አለብን ነው ያሉት።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሺመልስ አብዲሳ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰነቁት ሀሳብ መሠረት በስንዴ ምርት እራስን ከመቻል እስከ ኤክስፖርት ማድረግ ታቅዶ በመሰራቱ ሰፊ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው ዓመት 10 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ ዝግጁ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በክረምት ይለማ ከነበረው 800 ሺህ ሄክታር መሬት በአሁኑ ወቅት 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መድረሱን በመጥቀስ በ7 ሺህ ሄክታር መሬት የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በዘንድሮው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር ለማልማት ወደ ሥራ መገባቱን ገልፀዋል።

የክልሉ ህዝብ ስንዴን ኤክስፖርት በማድረግ ታሪክ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ፤ የኢትዮጵያ ስንዴ ኤክስፖርት የማድረግ ህልም በህይወት እያሉ በመሳካቱ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

ሀገራዊ ለወጡን ተከትሎ መንግስት ስንዴን በስፋት በማምረት በአጭር ጊዜ ከውጭ የሚገባ ስንዴን በሀገር ውስጥ ምርት መተካቱን ጥቀሰዋል።

የስንዴ ምርት እና የምግብ ፍጆታ ሚዛን ታይቶ ከሀገሪቱ ፍጆታ የሚተርፍ 32 ሚሊዮን ኩንታል ትርፍ እንደሚኖር በመረጋገጡ በዚህ ዓመት ስንዴን ወደ ውጭ የመላክ ስራ በይፋ ተጀምሯል ብለዋል።

ለዚህም ዘንድሮ ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ስንዴ የመግዛት ፍላጎት ያላቸው ስድስት አገራት ጋር የ3 ሚሊዮን ኩንታል የውል ስምምነት ተፈርሟል ነው ያሉት። (ኢዜአ)

በኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት “ችጋር” ለሚለው ቃል ኢትዮጵያን እንደ ምሳሌ መጥቀሱ በርካታዎችን ያሳዘነና አንገት ያስደፋ ነበር። ታሪክ ተቀይሮ ከችጋር መጠሪያነት ወደ ስንዴ ላኪነት የተቀየረችው ኢትዮጵያ በጸረ ኮሎኒያሊዝም ትግል ፋና ወጊ እንደነበረችው በዚህም መስክ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ምሳሌ እንደምትሆን ይጠበቃል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: Ethiopian Wheat Export, famine, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule