በኢህአዴግ የተሰየሙት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ በሰኔ ወር መገባደጃ አካባቢ ወደ አሜሪካ ጉዞ እንደሚያደርጉ ታወቀ። በቆይታቸው ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ በተለይ በሰላማዊ መንገድ ትግል ከሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን ጋር በግልና በቡድን በመገናኘት ሊነጋገሩ እንደሚችሉ ተነግሯል። በህወሓት/ኢህአዴግ ስያሜ የጠቅላዩን መንበር የተቆናጠጡት ዓቢይ አህመድ ላለፉት በርካታ ሳምንታት በአገር ውስጥ እና በአጎራባች አገራት ጉብኝቶችን ሲደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቀጣይ የተያዘው መርሃግብር ወደ አውሮጳና አሜሪካ ጉዞ ማድረግ እንደሚሆን መረጃዎች ሲወጡ ነበር። ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ የጠቅላይ ሚ/ሩ የአሜሪካ ጉብኝት መረጃ ቀደም ብሎ የደረሰው ቢሆንም በወቅቱ የተባለው በሰኔ ወር መገባደጃ ወይም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላይ ንግግር ለማድረግ በመስከረም አካባቢ … [Read more...] about ጠ/ሚ/ሩ በአሜሪካ ከወሳኝ ኢትዮጵያውያን ጋር ሊነጋገሩ ነው