የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያን አስመልክቶ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ኢትዮጵያ በትናንትናው ዕለት መንግሥት አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አስመልክቶ የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻሉን ያስታውቃል። ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውስው ይህ ማሻሻያ ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ ወደሆነና በገበያ ላይ ወደተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት እንደሚያሸጋግራትና በኢኮኖሚ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተንሰራፍቶ የቆየውን የማክሮ ኢኮኖሚ አለመረጋጋትና መዛባት እንደሚያሻሽል ይታመናል። የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያው በአዲሱ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሠረት የሚተገበር ይሆናል። ይህ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ላይ የተመሠረተና … [Read more...] about የዘመናት ማነቆዎችን የበጣጠሰውና ተስፋን የሰነቀው የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ማሻሻያ