ከአራት ሰዎች አንድ ሰው የችግሩ ሰለባ እንደሚሆን ተመላክቷል በኢትዮጽያ የዜጎች ከፍተኛ የጤና ጠንቅ ከሆኑ መካከል የአእምሮ ጤና እክል መሆኑ ተመላክቷል። የሕመሙ ተጠቂዎችን በቅርበት የሚረዳቸው በማጣት እና ተገቢ የሆነ የሕክምና ክትትል ባለማግኘት ለከፋ ችግር እንደሚዳረጉ ተጠቁሟል፡፡ በአማኑኤል ስቼሻላይዝድ ሆስፒታል የተመላላሽ ሕክምና ክፍል ኃላፊ እና የተቀናጀ የአዕምሮ ሕመም ሕክምና ከፍተኛ ባለሙያው ሳሙኤል ቶሎሳ፤ በማሕበረሰቡ ዘንድ ለአእምሮ ጤና ያለው አመለካከት ዝቅተኛ መሆኑን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ የሕመሙ ተጠቂዎች እራሳቸውን መቆጣጠር በማይችሉበት ደረጃ የደረሰን የጤና እክል ብቻ ልክ እንደ አእምሮ ሕመም በመቁጠራቸው ሳቢያ በዝቅተኛ የአእምሮ ጤና እክል ውስጥ የሚያልፉ ዜጎች መኖራቸው እንደሚዘነጋም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 27 … [Read more...] about በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ