ከአራት ሰዎች አንድ ሰው የችግሩ ሰለባ እንደሚሆን ተመላክቷል
በኢትዮጽያ የዜጎች ከፍተኛ የጤና ጠንቅ ከሆኑ መካከል የአእምሮ ጤና እክል መሆኑ ተመላክቷል። የሕመሙ ተጠቂዎችን በቅርበት የሚረዳቸው በማጣት እና ተገቢ የሆነ የሕክምና ክትትል ባለማግኘት ለከፋ ችግር እንደሚዳረጉ ተጠቁሟል፡፡
በአማኑኤል ስቼሻላይዝድ ሆስፒታል የተመላላሽ ሕክምና ክፍል ኃላፊ እና የተቀናጀ የአዕምሮ ሕመም ሕክምና ከፍተኛ ባለሙያው ሳሙኤል ቶሎሳ፤ በማሕበረሰቡ ዘንድ ለአእምሮ ጤና ያለው አመለካከት ዝቅተኛ መሆኑን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
የሕመሙ ተጠቂዎች እራሳቸውን መቆጣጠር በማይችሉበት ደረጃ የደረሰን የጤና እክል ብቻ ልክ እንደ አእምሮ ሕመም በመቁጠራቸው ሳቢያ በዝቅተኛ የአእምሮ ጤና እክል ውስጥ የሚያልፉ ዜጎች መኖራቸው እንደሚዘነጋም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 27 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ከዝቅተኛ አንስቶ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ለሚደርስ የአእምሮ ጤና እክል የተዳረጉ ናቸው ያሉት ሃላፊው፤ ከአራት ሰዎች አንድ ሰው የችግሩ ሰለባ እንደሚሆንም አመላክተዋል፡፡
ብዙሃኑ የማሕበረሰብ ክፍል ለአእምሮ ጤና እክል ከሚያስቀምጠው መመዘኛ ያልደረሱ ግን ደግሞ በጊዜ ሂደት ሥር የሚሰዱ የአአምሮ ጠንቆች ተጋላጭ የሚሆኑ ዜጎችን ቀርቦ መረዳት እና በጊዜ እገዛ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ ሳሙኤል ቶሎሳ ጨምረው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡ (የአዲስ ማለዳ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
FESEHA KEBEDE says
yes specially after government change 1983 Eth-calendar some case are deliberately done
i am in diredawa i cant to support my son he is Victimae by addiction n0w he is 24 years old
FESEHA KEBEDE says
let aim volunteer to participate with physically on their treatment