የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ አምስት የቀበሌ መታወቂያ እና 25 የተለያዩ የባንክ ደብተሮች ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ግለሰቡ በያዛቸው የባንክ ደብተሮች ውስጥ 2 ሚሊየን 966 ሺህ 189 ብር እንደተገኘበት ኮሚሽኑ አስታውቋል።
አቶ መሃሪ ተከስተ ገብረኪዳን የተባለው ግለሰብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ናሆም አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ የፀጥታና ህግ-ማስከበር የቀጠና 1 ሻለቃ 2 ኃይል 1 አዛዥ ኢንስፔክተር አዲሱ ተሾመ ገልፀዋል።
አሁን ያለውን ወቅታዊ የፀጥታ ችግር የአሸባሪው ህወሓት ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ለመፈፀም የተለያዩ ሰዎችን እየተጠቀመ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከዚህ አንጻርም የሽብር ቡድኑን ተግባር ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ስላሉ የፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጠንካራ ፍተሻ እያደረገ እንደሚገኝ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply