• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ

March 9, 2020 08:09 am by Editor 7 Comments

በአሜሪካ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክትል ሊቀ መንበር ተደርጎ የተሾመው የቀድሞው የህወሃት ካድሬና የበረከት ስምዖን ታማኝ ኤርሚያስ ለገሰ መሰናበቱ ተሰማ። እስክንድር ነጋን የጠቀሱ የጎልጉል እማኞች እንዳሉት ኤርሚያስ መባረሩን አያውቅም። በዚህ ሳቢያ 360 እንደ ስሙ ዘመቻውን ያዞራል ተብሎ ይጠበቃል።

የእስክንድር ነጋን የአሜሪካ ጉዞ ተከትሎ በሰርግና ምላሽ የባለ አደራው ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ኤርሚያስ ሹመቱን አስመልክቶ ስለ ቀጣዩ የትግል አቅጣጫ፣ የትግሉ ግብና አደረጃጀት እንዲሁም ኔትዎርክ ማብራሪያ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ተያዘውም ወደ ተፈለገው ዓላማ እንደሚደርሱ ምሎ ነበር።

ለድርጅቱ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ቅርብ የሆኑና ይህ ውይይት ሲደረግ የነበሩ ኤርሚያስ ለገሰ በቅርቡ ከሃላፊነት መነሳቱ ይነገረዋል “የእሱ መሰናበት ያለቀ ነው። መጀመሪያም ትክክል አልነበረም” ሲል እስክንድር የተናገረውን ቃል በቃል የሰሙትን የጎልጉል እማኞች ተናግረዋል። ይህ ሲሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይስቅ ነበር።

ይህንኑ ዜና ተከትሎ ማየት የተሳነው የወያኔ መልዕከተኛ ቴዎድሮስ ጸጋዬ የሚመራው ርዕዮትና 360 የተሰኘው የዩቲዩብ የ”ዛሬ ምን አለ?” መድርክ በእስክንድር ነጋ ላይ ፊታቸውን እንደሚያዞሩ ይጠበቃል።

በህጋዊ የብሮድካስት ፈቃድና አገር ቤት ተመዝግቦ በሚሰራ አንድ ሚዲያ ባለቤት በስውር የሚደጎመው 360 የኤርሚያስን መሰናበት፣ ስንበቱ እሱ ሳያወቀው መደረጉን፣ እንዲሁም በሚስጢር መያዙን ሲሰማ “ዛሬ ምን አለ?” በሚለው የ360 የድራማ  ክፍለ ጊዜ ላይ ምን ዓይነት ትንተና እንደሚሰጥ ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል።

እስክንድር እግረ መንገዱንም ስንታየሁ ቸኮልን ጨመሮ ሹም ሽር እንደሚሚደረግ ፍንጭ ሰጥቷል።

በቅርቡ የአሜሪካ ዜግነት የተቀበለው ኤርሚያስ ለገሠ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ወደ ምርጫ ውድድር የገባው ባለአደራ ምክትል ሆኖ እንዴት ሊሠራ እንደሚችል ጥያቄ የፈጠረ ጉዳይ ነበር። ኤርሚያስ ግን፤ የአሜሪካንን ዜግነት የተቀበልኩት ፕሬዚዳንት ትራምፕን ታግዬ ከሥልጣን ለማባረር ነው፤ በማለት በዚሁ የ360 ዩትዩብ ማስተላለፊያ ሲናገር ተደምጧል።

ድህረ ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ለውጥ ሲመጣ ኤርሚያስ ወደ አገር ገብቶ በሹመት ለመሥራት መፈለጉን በመግለጽ ለጠ/ሚ/ር ዐቢይም በወቅቱ የአማራ ክልል መሥተዳድር ለነበሩት ገዱ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር፤ “የድሮው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ሚስጥራዊ ዶክመንቶች፣ ቪዲዮዎች ወዘተ በእጁ እንደሚገኙ፤ እነዚህን ለጠ/ሚው አሳልፎ መስጠት” ፍላጎቱ እንደሆነ፤ “ይህንን የሚያደርገው ጥሩ ሹመት፣ ቤት እና መኪና እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ሲሟሉለት እንደሆነ” በላከው ማስታወሻ መላኩ የሚታወስ ነው። ይህ ጥያቄው ተቀባይነት ካጣ በኋላ ምክንያት ዐልባ ጭፍን ተቃዋሚ ጎራ ራሱን እንዳስገባ “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ርዕስ የታተመው ጽሁፍ ያስረዳል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Filed Under: Middle Column, News, Slider Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    March 9, 2020 10:54 pm at 10:54 pm

    የጎልጉል ድህረ-ገጽ በኤርምያስ ለገሰ ላይ ተደጋጋሚ ውግዘትና ውሸት የምታስተጋባው ለምን ይሆን ? ጎልጉል ድህረ-አብይ መሆንዋን በግልጽ እያየን ነው ማንኛውም ድህረ-ገጽም ይሁን ጋዜጣ ወይም መጽሔት ከገዥዎች ጋር ከወገነ መቆሸሹንና ርካሽ መሆኑን በግልጽ ያመለክታል ፥ እናንተም ከገዥው የኦሆዲድ -ኦነግ ጋር ተለጥፋችሁ የሰዎችን ስም በከንቱ የምታጠፉ ርካሾች ናችሁ ፥ ኤርምያስ ለገሰን ከምትወንጅሉ ይልቅ ከእናንተው ጋር ሀገሪቱን የሚመራው የኦሆዲዱ ሊ/መ ግራኝ አህመድ አሊ በፋሽስቱ ህወሃት ሥርዓት ቀንደኛ አገልጋይና የኦሮሞንና የአማራን ወጣቶች ሲያስገድልና ሲያሳስር የነበረ ሴረኛና ሻጥረኛ ግለሰብ ለምን አንድ አትሉሉም ? ሌላው የብልግናችሁ ጥግ ጋዜጠኛ ቲዎድሮስን “ማየት የተሳነው” ስትሉ በፍጹም ከአንድ ለሕዝብ ከሚቀርብ ጋዜጣ ዝግጅት የማይምጥን ዜሮ (0) መሆናችሁን አሳይታችሁዋል ፥ እርሱ ማየት ተሳነው እናንተ ግን ልባችሁ ከእርሱ ዓይን በበለጠ ታውሮዋል ፥ እኔ የቴዎድሮስም ሆነ የኤርምያስ ለገሰ ደጋፊም ሆነ የቅርብ ሰው አይደለሁም ፥ ሁለቱንም በቲቪ መስኮት በሚያስተላልፉት ታላቅ ቁም ነገር እከታተላለሁ ፥ ጎልጉል ሙጀሌ ይጎልጉል እንጂ ቁም ነገር የለውም ፥ የሀገሬ ሰው ሲናገር ” ማሽላው ሞረት ማማው ቅንብቢት” ይላል ፥ እናንተም ከኤርምያስ ጋር በምንም ዓይነት የማይገናኝ ትርኪ ምርኪ እየቃረማችሁ ትለጥፋላችሁ ፥ በእኔ እይታ ኤርምያስ ለገሰ ከባልደራስ ቢባረር ምን ይመጣል ? ድሮስ እርሱ የተሾመው የውጭውን ዲያስፖራ እንዲያስተባብር እንጂ አ/አ ሄዶ ሥልጣን ለመጋራት አይደለም ፥ ድሮም ኤርምያስ ፈልጎ ሳይሆን ራሱ እስክንድር ነጋ መርጦ ሾመው እንጂ ኤርምያስ በምልጃ ያገኘው ሹመት አይደለም ፥ እባካችሁ ከምታደርጉት ግለሰባዊ እይታ ወደ ዘርፈ ብዙው የሀገራችን ችግሮች ላይ ምልክታችሁ አድርጉ ፥ አሉባልታ የትም አያደርስም ፥ ራስን ያቀላል እንጂ !

    Reply
  2. Ashebir says

    March 11, 2020 09:34 am at 9:34 am

    ጎልጉል ባትሳሳት ደስ ይለኛል። “ኤርምያስ ለገሰ ተባረረ” የተባለው ስህተት ነው። ኤርምያስ ገና ስክንድር ነጋ ከሲቪክ ድርጅትነት ወደ ፖለቲክ ድርጅትነት ለመለወጥ ሲያስብ ውዲያውኑ ቀድሞ ባልደራሱ ወደ ፖለቲክ ድርጅትነት ከትለወጠ፤ ሃላፊነቴት እለቃለሁ ሲል በ360 ሲናገር ስምቸዋለሁ። ስለዚህ በፈቃዱ ለቀቀ ቢባል ትክክል ይሆናል። ከአክብሮት ጋር

    Reply
  3. አለም says

    March 11, 2020 09:42 pm at 9:42 pm

    ኤርምያስን እስክንድር ሾሞ ከሻረው፣ እስክንድርም መባረሩ አይቀርም። ኤርምያስም በሄደበት ሳይቆይ በተደጋጋሚ እየተባረረ ነው። ለምን ይሆን?

    Reply
  4. mar says

    March 12, 2020 04:06 pm at 4:06 pm

    ይሄ ውሸት ግን የእውነቱ ወጥቶ ጎልጉል የተባለ የመረጃ መረብ ለማመን ይከብዳል

    Reply
  5. Selma Haile says

    March 15, 2020 01:16 pm at 1:16 pm

    You are simply attacking some one because you have other agenda.The whole article a collection of gossips not a single fact in it.Now we know who you are !

    Reply
  6. mas says

    March 16, 2020 12:12 am at 12:12 am

    Kotone said Kaffa.

    Reply
  7. TD says

    April 14, 2020 03:27 am at 3:27 am

    Ermias ahun mekawem yefelgew yasebew altesakaletm Ethiopia chigr bifeter men endemitekem alawkem esu lemidia yemihon aydelem betkikel mebarer new yemigebaw

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule