የሚዲያው ዝምታ ለምን ይሆን?
የኮሮና ቫይረስ በቻይና ከመከሰቱ በፊት በአሜሪካ በቫይረሱ ተጠቅተው የሞቱ መኖራቸው ተረጋገጠ። ይህንን ያረጋገጡት የአሜሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል (CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሬድፊልድ ናቸው። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ይህ የታወቀው በኢንፍሉዌንዛ በሞቱ ሰዎች ላይ በድጋሚ በተደረገ ምርመራ ነው።
በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ሲነገር እንደቆየው የኮሮና ቫይረስ የተጀመረው በቻይና ዉሃን ከተማ እንደሆነ ነበር። ለበሽታው መነሻም የተለያዩ መላምቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። አንዱ መላምት ከእንስሳት ወደ ሰው ነው የተላለፈው የሚል ነው።
ለዚህም እንደ ማስረጃነት የሚቀርበው ቻይናውያኑ የሚበሉት፣ “እርጥብ ገበያ” (wet market) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከባህር የሚገኙ ማንኛውም የአሣ ዝርያ እስከ የሌሊት ወፍ፣ እባብ፣ ውሻ፣ ሸለምጥማጥ፣ የዱር ድመት፣ ዓይጠመጎጥ፣ ወዘተ እየታረዱና እየተከተፉ የሚሸጡበት በደም፣ በፈርስና በመሳሰሉ የአራዊቱ ፍሳሾች የተበከለ በመሆኑና በሽታው የተነሳው እነዚህን እንስሳት ከመብላት ነው የሚል ነው።
ሌላኛው መላምት ደግሞ በቻይና ዉሃን ከተማ ድብቅ የባዮሎጂካል መሣሪያ ማምረቻ ጋር የተያያዝ ነው። መላምቱ፣ በፋብሪካው የኮሮና ቫይረስ ለማምረት ሙከራ ሲደረግ ስለነበር ቫይረሱ ከዚያ አፈትልኮ የወጣ ነው የሚል ነው። ይህም በሽታው የተዛመተው ከእንስሳት ወደ ሰው ሳይሆን፣ በቅድሚያ ሰዎች ተይዘው ነው ወደ እንስሳቱ የተዛመተው ለሚለው መከራከሪያ እንደ ማስረጃ ይቀርባል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የተለያዩ መላምቶች የሚቀርቡ ሲሆን በሚዲያ ብዙም ትኩረት ሳያገኝ የታለፈው ጉዳይ ግን በሽታው በቻይና ከመከሰቱ በፊት በአሜሪካ የኢንፍሉዌንዛ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የሞቱ ሰዎች እንዳሉ መገለጹ ነው።
ይህ የሚዲያ አውታሮች በሚገባው መጠን ጆሮ የከለከሉት ወይም እንደ ጉዳዩ ግዝፈት ሰፊ ሽፋንና ትኩረት ያልሰጡት ጉዳይ ይፋ የሆነው የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ማርች ፲፩ በተወካዮች ምክርቤት ለውይይት ተጠርተው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነበር።
የምክርቤቱ ኦቨርሳይት ኮሚቴ (Oversight Committee) የማዕከሉን (CDC) ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሬድፊልድን ጠርቶ ባወያየበት ወቅት ጥያቄዎችን አቅርቦላቸው ነበር። በውይይቱ ወቅት ሃርሊ ሮውዳ የተባሉ የካሊፎርኒያ እንደራሴ ባለፉት ወራት አንዳንድ ኢንፍሉዌንዛ ወይም ፍሉ በሽተኞች በርግጥ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እንደነበሩና ምናልባትም በትክክል ሳይመረመሩ እንደቀሩ ለዳይሬክተሩ ጥያቄ ያቀርባሉ።
ዳይሬክተሩ ሲመልሱም “ባለው መደበኛ አሠራር የመጀመሪያው ምርመራ የኢንፍሉዌንዛ ምርመራ ማድረግ ነው፤ በኢንፍሉዌንዛ ከተያዙ ፖዘቲቭ ይሆናሉ (ወይም ኢንፍሉዌንዛ ይዟቸዋል ይባላል)” ብለዋል።
እንደራሴው በመቀጠልም ባለፉት ወራት ኮሮና ይፋ ከመሆኑ በፊት በኢንፍሉዌንዛ የሞቱትን አሁን ከሞቱ በኋላ ኮሮና እንደነበረባቸው ምርመራ ስለመደረጉ ይጠይቃሉ።
ዳይሬክተሩ ሲመልሱም “በሁሉም ከተማ፤ በሁሉም ጠቅላይ ግዛት እና በሁሉም ሆስፒታል ባይተገበርም ማዕከላችን በሳምባ ምች የሞቱ ሰዎችን የሚከታተልበት ስልት አለው” ይላሉ።
ይህንን ምላሽ ተከትለው እንደራሴው እንዲህ በማለት ሌላ ጥያቄ ያቀርባሉ፤ “ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች በአሜሪካ በኢንፍሉዌንዛ የሞቱ ናቸው ያልናቸው እንደተባለው ሳይሆን በርግጥም የሞቱት በኮሮና ቫይረስ ነው ሊባል ይችላል” በማለት ጥያቄያቸውን አጠናክረው ያቀርባሉ።
ዳይሬክተሩ ሲመልሱም፤ “አንዳንድ ኬዞች በርግጥ በዚያ መልኩ በአሜሪካ ለመከሰታቸው በምርመራ ታውቋል” ብለዋል።
በአሜሪካ የኢንፍሉዌንዛ (የፍሉ) ወቅት የሚባለው የሚጀምረው በኦክቶበር (ጥቅምት) አካባቢ እንደሆነና ዲሴምበር (ታህሣሥ) ላይ ከፍ እያለ መጥቶ እስከ ማርች (መጋቢት) ድረስ አንዳንዴም እስከ ሜይ (ግንቦት) እንደሚዘልቅ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከሉ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ከሴፕቴምበር ፳፱ ጀምሮ እስከ ፌብሩዋሪ ፲፱ ባለው ጊዜ ውስጥ 250,000 አሜሪካውያን ከፍሉ ጋር በተያያዘ ሆስፒታል ገብተው እንደነበርና ከእነዚህም 14,000 በዚህ የኢንፍሉዌንዛ ወቅት መሞታቸውን የኢንፌክሽንና የአለርጂ በሽታዎች ብሔራዊ ማዕከል አስታውቆ ነበር። ከሞቱት ቁጥር ውስጥ ስንቱ በኮሮና ቫይረስ እንደሞቱ በውል አልታወቀም።
እንደራሴው አጥብቀው ላቀረቡት ጥያቄ የማዕከሉ ዳይሬክተር የሰጡት ምላሽም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው። ዳይሬክተሩ ያሉት በመደበኛ ኢንፍሉዌንዛ ሞቱ ከተባሉት ውስጥ ከሞት በኋላ (posthumous) በተደረገ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ታውቋል የሚለውን ነው ያረጋገጡት።
ጉዳዩ ይህ ከሆነ በቻይና ዉሃን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ከመሞታቸው በፊት አሜሪካ ውስጥ ሞተዋል የሚለውን የሚያረጋግጥ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ በሽታው አስቀድሞ አሜሪካ ተከስቶ ነበር ወደሚለው ድምዳሜ ይወስዳል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በቻይና እና ጃፓን የሚገኙ የሚዲያ ውጤቶች እያነሱ ያለው ጥያቄ በአሜሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ተጠቂ የሞተው መቼ ነው? እስካሁን ስንት ሞተዋል? በሽታው በአሜሪካ የጀመረው መቼ ነው? ወዘተ የሚሉ ሆነዋል። እነሱ ይህንን ቢሉም ራሳቸው የአሜሪካን ሚዲያ አውታሮች ግን ይህንን ታላቅ ጉዳይ ዝም ማለታቸው ለምን ይሆን የሚለው ግን ከቫይረሱ የመከላከያ ክትባት ባልተናነሰ ምክንያቱ የመታወቁ ጉዳይ ልዩ ምርምር ያሻዋል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
AA says
Hallo dear Goolgule colleagues,
I am writing this to you because I appreciate what you are doing and I hope that you remain as you are now. I strongly suggest that you stay away from posting the kind of information that you did on this Covid-19. Remember the issue is so scientific, too technical and very new even to the world of scientists. Your piece of writing is not something that is substantiated. It is not verified and it has some kind of twisting interpretations. Stay on things that you are sure of.
Thank you.
Editor says
Dear AA,
Many thanks for your comments and suggestions.
As we have linked the article with the source that we found, it is very substantiated and supported by evidence. Dr. Redfield of the CDC said that at the House Oversight Committee discussion. He admitted that in the United States people have actually been diagnosed with and died of Covid-19 while it was thought that it is influenza. This was a posthumous diagnosis and it was confirmed by the good doctor himself.
In case you have overlooked the link here it is – https://edition.cnn.com/world/live-news/coronavirus-outbreak-03-11-20-intl-hnk/h_1319f66f92245a2fe4ec63fe91ab66c9
It was reported by the CNN and here is what was reported:
3:46 p.m. ET, March 11, 2020
CDC director says some coronavirus-related deaths have been found posthumously
During the House Oversight Committee discussion on the novel coronavirus response, the director of the US Centers for Disease Control and Prevention said some deaths from coronavirus have been discovered posthumously.
Rep. Harley Rouda asked CDC director Dr. Robert Redfield if it’s possible that some flu patients may have been misdiagnosed and actually had coronavirus.
“The standard practice is the first thing you do is test for influenza, so if they had influenza they would be positive,” Redfield said.
Rouda then asked Redfield if they are doing posthumous testing.
Redfield said there has been “a surveillance system of deaths from pneumonia, that the CDC has; it’s not in every city, every state, every hospital.”
Rouda followed up and asked, “So we could have some people in the United States dying for what appears to be influenza when in fact it could be the coronavirus?”
The doctor replied that “some cases have actually been diagnosed that way in the United States today.”
Thanks for your engagement.
Editor
Tesfa says
ሃሳቡ የቀረበው በአማርኛ በመሆኑ ያለኝን ሃሳብ በዚሁ ቋንቋ ባካፍል የሚሻል ይመስለኛል። ዓለማችን ከእንስሳት ወደ ሰው ከሰው ወደ እንስሳ በሚተላለፉ በሽታዎች መታመስ የጀመረችው አሁን አይደለም። እውቁ ቫይሮሎጂስት Stephen S. Morse የበሽታን ትልልፍ አስመልክቶ እንዲህ ይለናል። Viruses have no locomotion. ማለት የፈለገው በሌላው ላይ ተንጠላጥለው ነው በየዓለማቱ ሁሉ የሚዳረሱት ነው። ቻይና ነገሮችን በማፈንና በመደበቅ የምትታወቅ ሃገር ናት። ለዚህም መረጃው በኮሮና ቫይረስ ሟች ዶክተሯ የበሽታውን ምልክት እንዳገኘ ሲነግራቸው የወሰድት ፓሊስ ጣቢያ ነው። ውሸት ነው ብለህ ፈርም ተብሎ በመፈረም ከተለቀቀ በህዋላ ያው እንደ ሰደድ እሳት የቫይረሱ ስርጭት በቻይና ሲቀጣጠል እርሱም የዚሁ ሰለባ ሆኗል በማለት የቻይና መንግሥት አሳውቆናል። ታዲያ መንግሥታት የውሸት ቋቶች ለመሆናቸው ምስራቅ ምእራብ ማየት አያስፈልግም። የማይዋሽ መንግስት የለም። ወደ በሽታው ቀድሞ መከሰት ጉዳይ ስንገባ የሚታመን ወሬ የለም። CNN እና Fox News ጎራ ለይተው የሚፋለሙ የውሸት ቱልቱላዎች ናቸው። ራሱ ዜናው ሁሉ በውሸት የተሞላ ነው። በዚያ ላይ ሶሻል ሚዲያን እና ሌሎችንም የፈሪ ድላዎች ስታክልበት እውነት መቀበሯን በቀላሉ ተረዳለህ። ዋናው ነገር በሽታው የዓለም ችግር መሆኑ ነው። ይህ ጉዳይ በቅርብ እልባት ካላገኘ አዕላፍ ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ። በመሆኑም ምንጩ የት ሃገር እንደሆነ መከራከሩ ጠቃሚነት የለውም። ዝም ብሎ በመከራ ዝናብ መካከል ድንጋይ መወራወሩም ለማንም አይበጅም። በመሰረቱ ብዙ ነገሮች ስም የሚሰጣቸው በመነጩበት (በተገኙበት) ሥፍራ ነው። ግን የአሁኑ ጂኦ ፓለቲካ አትንኩኝ የሚል በመሆኑ ቻይናም ከእኔ አልመጣም ማለቷ አታድርስ ነው። አሜሪካም ቢሆን በሌሎች ላይ ነገርን ማላከኳ ዛሬ የተጀመረ አይደለም።
የዚህ ድህረ ገጽ ዝግጅት ክፍልም የሁለቱን መንግስታት አተካራም ሆነ የአሜሪካው የወሬ አውታር ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ቃለ ምልልስ ዋቢ አርጎ ያቀረበውም መጣጥፍ እንደ መረጃ ማቅረቡ ጠቃሚነት የለውም። ይልቁንስ ለህዝባችን ምክር ነገር ሃሳብ በሙያው ከተሰማሩ ሰዎች አጠናቅሮ ቢያቀርብ መልካም ነበር እላለሁ።
Editor says
ተስፋ
ለአስተያየቱ እናመሰግናለን፤ ሆኖም ዜናው ሲኤንኤን እንደ ዜና ከዋናው ስብሰባ ቀንጭቦ አቀረበው እንጂ በርግጥም በምክርቤቱ ውይይት የተደረገበት ነው። እንጂ የሃሰት ዜና አይደለም። ሙሉውን እዚህ ላይ ማዳመጥ ይቻላል። https://oversight.house.gov/legislation/hearings/coronavirus-preparedness-and-response
እርስዎ በጠቀሱዋቸው የዜና አውታሮች መካከል ያለውን ጉዳይ እኛም ሳናውቀው ቀርተን አይደለም። ሆኖም ዋናው ነገር ዜናው በምክርቤት ደረጃ የቀረበ መሆኑን ለማሳወቅ ነው።
በየጊዜው ስለሚሰጡት አስተያየቶች ምስጋና እናቀርባለን።
የጎልጉል አርታኢ
Alex says
I prefer better to think about our problems doesn’t matter where it’s already done we have to think how to stop the virus inside our country if all of the continent think the same way coronavirus I don’t think it’ll get space on the planet but talking about a thing even not sure exactly what it is, how stop that I don’t think will be solution when a news posted about must be you are responsible for it don’t bring a news from other social media how sure even that news taken from other same do. Every news must be take responsible for that should be taken by you attended.
Ayele says
ከሞት በኋላ (posthumous) በተደረገ ምርመራ ??? mean postmortem?
Editor says
The title of the news reads:
CDC director says some coronavirus-related deaths have been found posthumously
Both would work. Thanks for the comment, though.
Editor