ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያን እንዲያስተዳድሩ ከተሰየሙበት ቀን ጀምሮ መነጋገሪያ ሆነዋል። “ራሳቸውን ችለው መስራት አይችሉም” ከሚለው ድፍን አስተያየት ጀምሮ አቶ ኃይለማርያምን “ለወቅቱ አስፈላጊና ብቃት ያላቸው” በማለት የሚመሰክሩላቸው አልታጡም። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት አቶ ኃይለማርያም “ህዝብን የምጨቁን ሰው አይደለሁም” በማለት በሚያመልኩት አምላካቸውና በእግዚአብሔር ህዝብ ፊት አስቀድመው ቃል መግባታቸውንና የተፈጥሮ ባህሪያቸውን በማመሳከር ይከራከራሉ። በሌላ ወገን ደግሞ “አቶ ኃይለማርያም የቀድሞው ስብዕናቸው ፈርሶ በአዲስ ተሰርቷል። አቶ መለስ በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ፍልስፍና አጥምቀዋቸዋል። ከእርሳቸው ምንም አይጠበቅም” በሚል የሚያጣጥሏቸውም አሉ። አቶ ኃይለማርያምን ያሳደገችው የኢትዮጵያ ሐዋሪያት ቤተ ክርስቲያን አባሎች ከዛሬ ሶስት ዓመት … [Read more...] about “ሕዝብን የምጨቁን ሰው አይደለሁም”
የኔ ውብ ከተማ
የኔ ውብ ከተማ ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር? የኔ ውብ ከተማ ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ ሕንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ? የሰውን ልብ ነው፡፡ ምን ቢነድ ከተማው ተንቦግቡጎ ቢጦፍ ቢሞላ መንገዱ በሺ ብርሃን ኩሬ በሺ ብርሃን ጎርፍ ምን ያደርጋል? ምን ያሳያል? ካለሰው ልብ ብርሃን ያ ዘላለማዊ ነበልባል ያ ተስፋ ሻማ ጨለማ ነው ሁሉም ጨለማ፡፡ በዓሉ ግርማ … [Read more...] about የኔ ውብ ከተማ
A call from Center for Rights of Ethiopian Women (CREW)
For Immediate Release September 6, 2012 A CALL FOR PEACE AND RECONCILIATIONS IN ETHIOPIA The death of Ethiopia’s long-time ruler, Prime Minister Meles Zenawi, has created uncertainty in the country. The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW), a peace and human rights organization created to promote the rights of Ethiopian women worldwide, expresses its concern about the current situations in Ethiopia. We would like to encourage all concerned parties to use this crucial juncture in … [Read more...] about A call from Center for Rights of Ethiopian Women (CREW)
“ሰለባው” ማን ነው?
አቶ መለስ መሞታቸውን መንግስት አላምንም ማለቱ ጉጉት ፈጠረ። መለስ ታመዋል የሚለው ወሬ ሹክ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ የሁሉም ጆሮ በመለስ እስትንፋስ ማለፍና አለማለፍ ዙሪያ የሚሰጡትን መግለጫዎችና ዜናዎች ማሳደድ ላይ ተጠመዱ። እስካሁን ለንባብ ባይበቃም አቶ መለስ ረጅም ሰዓት የፈጀ የአእምሮ ቀዶ ጥገና ካደረጉ በኋላ መንቃት በሚገባቸው ሰዓት ውስጥ ባለመንቃታቸውና ምንም ዓይነት የመንቃት ምልክት ማሳየት ባለመቻላቸው ሃኪማቸው “clinically dead” በማለት በህክምናው ረገድ ማረፋቸውን ተናግረው ነበር፡፡ ግን ህይወታቸው አላለፈችም የሚል ሪፖርት ማቅረባቸውን የቅርብ ምንጮች ከነገሩኝ ቆይቷል። ሃኪማቸው እጃቸውን አጥብቆ ሲይዝ ምንም ምላሽ ባለመስጠታቸው በሙያው ቋንቋ የተስፋ መቁረጥ ሪፖርት ያቀረቡት ሃኪማቸው ከቀናት በኋላ በተመሳሳይ እጃቸውን ሲጨብጥ መለስም ያዝ በማድረግ ምላሽ … [Read more...] about “ሰለባው” ማን ነው?
The Death of Meles Zenawi and the Challenges of Establishing Strong Democratic Institutions in Ethiopia
The passing away of the late Prime Minister Meles Zenawi has once again brought the absence of strong institutions in Ethiopia to the spotlight. Though Meles Zenaw is responsible for masterminding a very radical ideology that has made the Ethiopian political market murky and unpredictable, his sudden departure has gripped the nation causing credible concern including to his detractors. This is mainly due to the fact that the country has not departed from its totalitarian past and political power … [Read more...] about The Death of Meles Zenawi and the Challenges of Establishing Strong Democratic Institutions in Ethiopia
ህወሓት ለዳግም ሥልጣን እየሮጠ ነው
ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ለመተካት የሚደረገው የውስጥ ለውስጥ ሽኩቻ ኢህአዴግ እንደሚለው “በቀላል ሽግግር” የሚቋጭ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ነው። መለስን በወኪሏ ወ/ሮ ሱዛን ራይስ አማካይነት በአስከሬን ሽኝቱ ወቅት ያቆለጳጰሰችው አሜሪካ የስልጣን ሽግግሩ ላይ ያላትን የማያወላዳ አቋም ትዕዛዙን ባለመቀበል ከሚመጣው መዘዝ ጋር ማስታወቋም ተሰምቷል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጮች ከኢህአዴግ ከፍተኛ ደጋፊዎችና የቅርብ ባለሃብቶች እንዳገኙት ገልጸው በላኩት መረጃ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲተኩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን በቅድሚያ እጩነት መያዛቸውን አመልክተዋል። መረጃ አቀባዮቻችን ደብረጽዮን ለሹመቱ የታጩበትን ምክንያት ሲያስረዱ መነሻ ያደረጉት በህወሓት ክፍፍል ወቅት የነበራቸውን … [Read more...] about ህወሓት ለዳግም ሥልጣን እየሮጠ ነው