• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጎልጉል ቅምሻ

December 10, 2012 01:44 pm by Editor Leave a Comment

ብልቴን ሰረቁት

በምስራቅ ቻይና የዢያንግ አውራጃ የኒቂያዖ ፖሊስ የደረሰው ክስ ግራ የሚጋባ ሆኗል፡፡ የ41ዓመቱ ፌ ሊን “ተኝቼ ሳለ ሌቦች ክፍሌ በርግደው በመግባት ብልቴን ሰረቁት” በማለት ነበር ወንጀሉን ያብራራው፡፡ ሲቀጥልም ሌቦቹ ቤቱ እንደገቡ ጭንቅላቱ ላይ የሆነ ነገር አድርገው ሱሪውን ወደታች ካወረዱ በኋላ ሮጠው እንደጠፉ አስረድቷል፡፡ “በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ምንም የተሰማኝ ነገር አልነበረም፤ በኋላ ግን እየደማሁ መሆኔን ሳስተውል ብልቴ ተበጥሶ መሄዱን አስተዋልኩ” ብሏል፡፡

ፖሊስ እንደሚለው ሌቦቹ ሊን በሚያዘወትራቸው በርካታ ሴቶች የቀኑ አፍቃሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምት በመስጠት ፍለጋውን ቀጥሏል፡፡ ሊን ግን ይህንን የፖሊስ መላምት ካለመቀበል በተጨማሪ የትም ሂያጅ ሳይሆን ታማኝ እንደሆነ ለራሱ ይመሰክራል፡፡ በስርቆቱ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም በርካታዎች ግን “የት አስቀምጦት ነው ሊሰረቅ የቻለው” በማለት የመከራከሪያ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡

ከፊልም ሙያ ወደ ምክርቤት

ታዋቂዋ የፊልም ተዋናይ አሽሊ ጀድ የዴሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል ለአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) ልትወዳደር እንደምትችል በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡ የባራክ ኦባማ ደጋፊ የሆነችው አሽሊ የምትወዳደረው ከኬንታኪ ጠቅላይ ግዛት ሲሆን ተፎካካሪዋም በመወሰኛው ም/ቤት የሪፓብሊካኑ ንዑሳን መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ናቸው፡፡

አብዛኛውን የፊልም ኢንዱስትሪና ታዋቂነትን ይዛ ወደ ዘመቻ የምትገባው አሽሊ ውሳኔዋን አሳውቃ ለውድድር የምትቀርብ ከሆነ እጅግ በርካታ ደጋፊዎቿ ከሌሎች ጠቅላይግዛቶች በመምጣት ለምርጫ ዘመቻ በፈቃደኝነት እንደሚያገለግሉ ቃል እየገቡ ይገኛል፡፡

ከቶ አይቀር ሞቱ ምንም ቢረዝሙ

የዓለማችን ረጅሟ ሴት ቻይናዊቷ ያዖ ደፈን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ የ39ዓመቷ ረጅም የዛሬ ሁለት ዓመት በዓለም የድንቆች መዝገብ የዓለማችን ረጅም ሴት በመባል ተመዝግባ ነበር፡፡ 7ጫማ ከ7ኢንች (2ሜትር ከ33ሴ.ሜ.) የምትረዝመው ያዖ የሞተችበትን ምክንያት የቻይና ዜና ባያስታውቅም የረጅምነት በሽታ (ጃይጋንቲዝም) እና ሌሎች ስትሰቃይ ቆይታለች፡፡

ወጣት ሳለች የቅርጫት ኳስ ትጫወት የነበረችው ያዖ በ15ዓመቷ 6ጫማ ከ7ኢንች (ሁለት ሜትር) ትረዝም ነበር፡፡ በበሽታ ትሰቃይ ከነበረችበት አልጋ ሆና “በፍጹም ደስተኛ አይደለሁም፤ ለምን ይህንን ያህል ረጅም ሆንኩ? ይህንን ያህል ባልረዝም ኖሮ ሰዎች እንደዚህ አይመለከቱኝም” በማለት የዛሬ ሦስት ዓመት ሃዘኗን መግለጽዋ ተዘግቧል፡፡

“አላሁ አክበር” በቤተክርስቲያን

የሙስሊም ሕዝብ ጉዳዮች ምክርቤት (MPAC) ለመጀመሪያ ጊዜ ዓመታዊውን ስብሰባ በቤተክርስቲያን ሊያደርግ ነው፡፡ በፓሳዴና ካሊፎርኒያ በሚገኘው የሁሉም ቅዱሳን ኤጲስቆጶሳዊ ቤ/ክ (All Saints Episcopal Church) እንደሚካሄድ የተነገረለት ይኸው የሙስሊሞች ስብሰባ እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ይገኛል፡፡

“በመቻቻል ስም ኢስላሚስቶች ጅል በሆኑ ክርስቲያኖች እየተጠቀሙ ነው”፤ “የአገራችንን (የአሜሪካንን) ሕገመንግሥት ለማፍረስና የሻሪያ ሕግ ለማስፈን ከሚሰራ ድርጅት ጋር በማበር የአገሬንና የልጅ ልጆቼን መጻኢ ዕድል አደጋ ላይ በመጣላችሁ ተጠያቂዎች ናችሁ” የሚሉ ጠንካራ መልዕክቶች የደረሷቸው መሆኑን የገለጹት የቤክኑ አስተዳዳሪዎች ስብሰባው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የደኅንነትና የፖሊስን ድጋፍ እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡ የምክርቤቱ ፕሬዚዳንት ሳላም አልማራያቲ “እንደቀድሞው ሁሉ ስብሰባውን በሆቴል ወይም በስብሰባ አዳራሽ ማድረግ እንችል ነበር፤ ሆኖም ቤ/ክ ውስጥ ማድረጋችን ም/ቤታችን ለሰላም እና ፍትሕ የቆመ ለመሆኑ ማሳያ እንዲሆን በመፈለጋችን እና ለሙስሊሞችም እርስበርሳቸው እየተነጋገሩ ችግራቸውን ይዘው ከሚኖሩ ለአብዛኛው የአሜሪካ ሕዝብ መልዕክታቸውን እንዲያደርሱ ታስቦ የተደረገ ነው” ይላሉ፡፡ አክራሪ የክርስቲያን ተቋማት መሪዎች የሙስሊሙን ም/ቤት በእጅ አዙር ለአሸባሪዎች ዕርዳታ የሚሰጥ ራሱ አሸባሪ የሆነ ድርጅት ነው በማለት ይከስሳሉ፡፡ የመንግሥትና ሃይማኖትን ጥምረት የሚቃወሙም እንዲህ ዓይነቱን የመንግሥት ድጋፍ የሚሰጠው ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ አጥብቀው ያወግዛሉ፡፡

ከ6ሴቶች 9ልጆች

በአሜሪካ የዊስኮንሲን ጠቅላይግዛት ነዋሪ የሆነው ኮሪ ከርቲስ ከስድስት የተለያዩ ሴቶች ዘጠኝ ልጆችን በመውለዱ ቤተሰቡን በሚገባ ማስተዳደር እስከሚችል ድረስ “መራባት እንዲያቆም” ፍርድቤት ወስኖበታል፡፡

ወደ 90ሺህ ዶላር ያልተከፈለ የልጆች ማሳደጊያ ድጎማ ዕዳ ያለበት የ44 ዓመቱ ዕዳውን ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ 10ኛ ልጅ መጨመር እንደማይችል ዳኛው ማስጠንቀቂያ ሰጥተውታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በኬንታኪ ጠቅላይ ግዛት ከ11ሴቶች 12ልጆችን የወለደውን “አቶ ዘረብዙ” 13ኛ ልጅ እንዳይጨምር መራባት እንዲያቆም የወሰኑበት ዳኛ በአመክሮ በሚቆይበት ከ1 እስከ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከወሲብ እንዲታቀብ ትዕዛዝ ሰጥተውታል፡፡ የሁለቱም ፍርድቤት ውሳኔዎች አፈጻጸም ግን በውል አልታወቀም፡፡

ፕሬዚዳንት ሂላሪ ክሊንተን?

የዛሬ አራት ዓመት ለፕሬዚዳንትነት ፓርቲያቸውን ወክለው በመወዳደር በባራክ ኦባማ የተሸነፉት ሂላሪ ሮድሃም ክሊንተን በ2016 ዳግም ለፕሬዚዳንትነት ይወዳደራሉ የሚል ወሬ በስፋት እየተናፈሰ ነው፡፡ በቅርቡ በተጠናቀቀው ምርጫ የተሸነፉ የፓርቲያቸውን እጩዎች የሚያበረታታ በራሳቸው እጅ የተፈረመ ደብዳቤ መላካቸው በተንታኞች ዘንድ በቀላሉ አልታየም፡፡ ምዕራብ ኒውዮርክን በመወከል ለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድረው በጠባብ ውጤት ለተሸነፉት ኔት ሺናጋዋ በላኩት ደብዳቤ ላይ በአሁኑ ምርጫ ቢሸነፉም በቀጣይ ዓመታት በህዝባዊ መድረኮች ላይ የእርሳቸውን ድምጽ እንደሚሹ ሂላሪ ክሊንተን ጠቁመዋል፡፡

ባራክ ኦባማ በዚህኛው የምርጫ ዘመቻቸው መሪቃል ወደፊት (Forward) የሚል እንደነበር ሁሉ ሂላሪ ክሊንተን በደብዳቤያቸው ላይ “Onward” በማለት የጠቀሷት ቃል ምናልባት የምርጫ ዘመቻቸው የመፈክር ቃል ትሆን የጎልጉል ግምት ነው፡፡ መቆየት ደጉ ብዙ ያሰማናል፡፡

ባለሦስት እግሩ በራሪ

የሥራ ሰዓት ሲረፍድ፤ ታክሲ ሲጠፋ ወይም መንገዱ በትራፊክ ሲጨናነቅ፤ ሰዓቱ ሲበር በሰማይ መብረር ያሰኛል፡፡ በእርግጥ መብረር ይቻላል፡፡

መፍትሔው 75ሺህ ዶላርና የፓይለት መንጃፈቃድ ማውጣት ብቻ ነው፡፡ ከዚያ አንዴ ነዳጅ ሞልቶ ለ5ሰዓታት መብረር ነው – በበራሪው ባለሦስት እግር፡፡

ሳቅ በሳቅ LOL

ለሦስት ዓመታ በከንፈር ወዳጅነት ከቆዩ በኋላ ከሦስት ወር በፊት ሲለያዩ ለወንድየው ቀላል የሆነው መለያየት ልጅቷን አእምሮዋን በማሳት ወደ ወንጀል መርቷታል፡፡ በቴክሳስ ጠቅላይግዛት ነዋሪ የሆነችው ኤልሳቤጥ ማክሌይን ከወንድ ጓደኛዋ ከተለያየች በኋላ ህይወቱን ቀውጢ በማድረግ በቀን እስከ መቶ ጊዜ ስልክ ትደውልለት ነበር፡፡ ጉዳዩ ያሳሰበው ወጣትም ለፖሊስ ያመለክታል፡፡

እርሷም ከተለያዩ ስልኮች መደወሏንና ማስፈራራቷን ቀጠለች፡፡ በቀን እስከ 750 ጊዜ ድረስ በመወደልና በአንድ ጊዜ እስከ 126 አጭር ፈጣን መልዕክት (ቴክስት) በመላክ ህይወቱን መቅኖ ቢስ አደረገችው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ግን የልጁን እናት በመኪና በመግጨት ወደ መንገድ ከጎተተቻት በኋላ በሞትና ህይወት መካከል ጥላት ለቀድሞው የከንፈር ወዳጇ “ህይወት እንዴት ነው ሳቅ በሳቅ (LOL)” በማለት አጭር መልዕክት ትልካለች፡፡ እናትየው በርካታ የአጥንት ስብራትና ጉዳት ደርሶባት በህክምና የእየተረዳች ሲሆን ኤልሣቤጥ በወንጀል ተከስሳ የ65ሺህ ዶላር የገንዘብ ዋስ ተበይኖባታል፡፡

የሳምንቱ ምርጥ ፎቶ

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሚጓጓዙበት ካዲላክ ባለአራት እግር ታንክ ቢባል የተጋነነ አይደለም፡፡ ከ300ሺህ ዶላር በላይ ወጪ የፈሰሰበትና የአርፒጂ ጥይት የማይበሳው ይህ መኪና አሠራሩና ውስጡ ያካተተው ቁስና መከላከያ እጅግ የሚያስደንቅ ነው፡፡ ለዚህ ሳምንት መርጠነዋል፡፡

ለማንኛውንም የባዮኬሚካል ጥቃት እንዳይጋለጥ ልዩ መከላከያ ይለብሳል፡፡

 

ቀጥተኛ ጥቃት ቢደርስበት እንኳን እንዳይፈነዳ የነዳጅ ማጠራቀሚያው ልዩ ስፖንጅ ለብሷል፡፡
አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የፕሬዚዳንቱን ዓይነት ደም በተጨማሪ ይቀመጣል፡፡
ከፊትለፊት በምሽት ማየት የሚያስችልና አስለቃሽ ጋዝ ተደምደውበታል፡፡
ጎማው በቀላሉ በስለትና ሹል ነገሮች መበሳት እንዳይል የተደረገ ሲሆን ባጋጣሚ ጎማው ቢተነፍስ ቸርኬው ያለችግር መሽከርከር ይችላል፡፡
ከውስጥና ከውጭ የለበሰውና የተሰራበት እንደ አሉሚኒየም፣ ቲታኒየም፣ … ያሉት መኪናውን በእርግጥም ተንቀሳቃሽ ምሽግ የሚያስብለው ነው፡፡
በሮቹ እንደ ቦይንግ 757 የፓይለቶች በር ጋር ይመሳሰላል ቢባልም ከውስጡ ያለው መከላከያ እጅግ የተቀቀ ነው፡፡
ስለ መስታወቱ ብዙ ማለት ባይቻልም በርካታ ርብራብ ያለውና ጥይቶችን በቀላሉ እንደ ቤዝቦል ጓንቲ አፍኖ የሚያስቀር ነው፡፡
ዋጋው ብቻ ሳይሆን ሁሉ ነገሩ ውድነው፤ በሰዓት 60ማይል ብቻ የሚሄድ ሲሆን በአንድ ጋሎን (3.7ሊትር) 8 ማይል (wd 13ኪሎሜትር) ብቻ ነው የሚጓዘው::
ምስሉ ላይ በመጫን ዝርዝር መረጃውን አጉልቶ ማየት ይቻላል::

ዘገባውን ለማጠናቀር በየጽሁፉ ከጠቀስናቸው ምንጮች በተጨማሪ ሌሎችንም የሚዲያ ውጤቶች መጠቀማችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ከዜናዎቹ ማነስ አኳያ በየጸሁፉ ለመግለጽ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule