• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

December 9, 2012 10:03 am by Editor Leave a Comment

የጉራ ፈርዳ አማሮች መሬታቸው በሃራጅ ተሸጠ

ቪኦኤ ሰለባዎችን በማነጋገር እንደዘገበው የጉራ ፈርዳ ነዋሪ አማሮች መሬታቸውን እንዳያርሱ ከተከለከሉ በኋላ መሬታቸው በሃራጅ እየተሸጠባቸው እንደሆነ ይፋ አድርጓል። መሬታቸውን በህጋዊ መንገድ የግላቸው እንዳደረጉና ግብር እየከፈሉ የሚኖሩት ተበዳዮች ርምጃው የተወሰደባቸው ቅንጅትን በመምረጣቸውና ለመኢአድ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል እንደሆነ ተናግረዋል።

በተደጋጋሚ መታሰራቸውንና በከሰሳቸውን የተናገሩት የጉራ ፈርዳ ነዋሪ ከእስር ከተፈቱ በኋላ “መሬታችሁን የያዛችሁት በህጋዊ መንገድ ነው” በማለት ለመኢአድ መረጃ መስጠታቸው እንደ ጥፋት እንደተወሰደባቸው አመልክተዋል። በ1997 ምርጫ ወቅት በምስጢር የድምጽ መስጫ ክፍል ውስጥ የጤና ባለሙያዎችን በማስቀመጥ ማንን እንደመረጡ መሰለላቸውንም አመልክተዋል። የሚሸጠውን መሬት የወረዳ፣ የቀበሌ፣ የባለስልጣናትና የፖሊስ አባላት በሚስቶቻቸውና በዘመዶቻቸው ሚስት እንደሚገዙት ተናግረዋል። መንግስትም ሆነ የአካባቢው ሃላፊዎች አስተያየት ለመስጠት አልተገኙም። ቀደም ሲል ሰባ ሺህ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ መደረጉ አይዘነጋም።

ሙስሊሞች የህገመንግስት ያለህ እያሉ ነው

መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት  ሙስሊሞች፣ ሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር አበክረዉ እያሳሰቡ ነዉ። የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዓርብ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በተለይ የሐይማኖት ነፃነት የተደነገገበት  አንቀፅ ሃያ-ሰባት መጣሱን ቁጥሩን በማሳየት ጭምር አዉግዘዋል።

“ሕገ-መንግሥት የማስከበሩ ሃላፊነት ከአገሪቱ መንግሥት ይልቅ የመብት፣ የነፃነት ተሟጋቾችና ሃላፊነት የሚሰማቸዉ ወጣቶች የመሆኑ እንቆቅልሽ ገሐድ እየወጣ ነዉ” ሲል የዘገበው የጀርመን ሬዲዮ፣ ዞን-ዘጠኝ በሚል መጠሪያ የተደራጁ የድረ-ገፅ ወጣቶች ታዳሚዎች ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበትን አስራ-ስምተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ «ሕገ-መንግሥቱ ይከበር» የሚል ዘመቻ ትናንት ከዓርብ የጸሎት ስነስርዓት በኋላ መጀመራቸውን አስታውቋል። የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተቃውሞውን እየገለጸ ያለበት አግባብ ሰላማዊና ከመሆኑ አኳያ ስለ ሰላማዊ ትግልና ‹‹በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል አይሰራም›› ለሚሉና ለሌሎች ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

“ጣጣ የለውም” ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

ከካው ቦይ ባርኔጣቸው ጋር ምስላቸውና ዜናቸው ሰሞኑን የተሰማው ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ ከቪኦኤ የአማርኛ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አነጋጋሪ ምላሽ ሰጥተዋል። በስደት አሜሪካ የሚገኙትን የኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ ከነሙሉ መንበራቸው አገር ቤት እንዲገቡ የሚፈቅድ ደብዳቤ መላካቸውን ተከትሎ አዲሱ አበበ ማረጋገጫ ሲጠይቃቸው አለ ምንም ማቅማማት ነበር ደብዳቤውን እሳቸው እንደጻፉት የተናገሩት፡፡

ደብዳቤው መበተኑን ተከትሎ የእምነቱ ተከታዮች ምርቃትና ምስጋና ውሎ ሳያድር አዲሱ አበበ ተጨማሪ ዘገባውን በድምጽ ጥራት አሳቦ አስከተለ። ይህኔ ነበር “ውሳኔው የግሌ ነው። የመንግስት አይደለም። አንስቼዋለሁ” በማለት እንደ አራዳ ልጆች “ጣጣ የለውም” አይነት ምላሽ ነው የሰጡት። መቶ አለቃ ግርማ ተጠባባቂው አቡነ ህዝቅኤል እንደተቆጧቸው ገልጸው ሃሳባቸውን መቀየራቸውን ሲያስታውቁ በስህተት “እገሌ ነው የተቆጣው” አለማለታቸው ድምጻቸው ከመቆራረጡ በስተቀር የሶፍትዌር ችግር እንደሌለባቸው ያረጋገጠ ሆኗል። ፕሬዚዳንት ግርማ ሃሳባቸውን ለመቀየራቸው በተደጋጋሚ ሲጠየቁ አቃለውና ተረጋግተው “ሃሳቤን ትቼዋለሁ፣ የመንግስት ውሳኔ አይደለም፣ በችኮላ የተደረገ ነው፣ የሄዱት ቢመለሱ ምንም አይደለም ከሚል ነው። አቡነ ናትናኤል ጣልቃ አትገባ አሉኝ፣ እኔ እንደዚህ ከኋላው ጣጣ ያለው አልመሰለኝም” በማለት ሌላ የፖለቲካ ዝርዝር ሳይቀላቅሉ ጨርሰዋል።

የመለስ ውርስ (ሌጋሲ)፡ ወደብ አልባነታችን!!

በጅቡቲ ወደብ ላይ ያለውን ክምችት በመቀነስ የኪራይ ወጪ ለመቀነስ ታስቦ የተገነባው የሰመራ ደረቅ ወደብ ግንባታ በርቀቱ ሳቢያ ተጠቃሚ ማጣቱ ተሰምቷል።ስራውን ከሚመራው ክፍል ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ሸገር ኤፍ ኤም እንደዘገበው የሰመራ ወደብ የተቋቋመለትን ዓላማ አላሳክም። ዘገባው ዳር ዳር ቢልም የሰማራ ደረቅ ወደብ ሙሉ በሙሉ ለተዋለለት ውሎ ለጅቡቲ የሚከፈለውን ወጪ መቀነስ አላስቻለም።

በ650 ሚሊዮን ብር ወጪ፣ በ14 ሄክታር ሞጆ ላይ የሚገነባው ደረቅ ወደብ ግንባታ ከቅርበቱ አንጻር ባስቸኳይ ለማጠናቀቅና ለወደብ ኪራይ የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ ትኩረት መሰጠቱን የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ለሸገር ተናግረዋል። የሞጆ ደረቅ ወደብ ግንባታ ከተጀመረ አራት ዓመት አስቆጥሯል። ወደቧን አስረክባ በየበረሃው የምትዳክረዋ አገራችን ለዚህ ችግር የተዳረገችው በራስዋ መሪዎች መሆኑ ከችግሩ በላይ የሚያቃጥል የታሪክና የዘመን ሁሉ በሽታዋ መሆኑ ነው። ምስጋና ለህወሓትና መለስ!!

ብሄራዊ ባንክ በወርቅ ስም ተጭበረበረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሚያካሂደው የወርቅ ግብይት ከአንድ የወርቅ አቅራቢ ወርቅ ነው ተብሎ ቁርጥራጭ ብረቶችና እንጨቶች በሳጥን እየታሸጉ ይደርሱታል፡፡ለራሱ ከፍያለው ኡመታ የሚል ሀሰተኛ ስም፣ መታወቂያና የንግድ ፈቃድ በማወጣት ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ ፥ ከባንኩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በነበረው የጥቅም ግንኙነት 29 ጊዜ ወርቅ ነው እያለ ይህን ባእድ ነገር ሲያቀርብ ቆይቷል። በባንኩ የስራ ሃላፊዎች የሻኪሶ ቅርንጫፍ ጥፍጥፍ ወርቅ ተረክበናል የሚል ማረጋገጫ ተሰጥቶት ክፍያው እንዲፈጸም ተደርጎ ፥ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ በመቀበል ለግል ጥቅሙ ማዋሉን የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ነው።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በዚህ ተከሳሽ ላይ ከዚህ ቀደም የጥፋተኝነት ብይን ያሳለፈ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት በዋለው ችሎት ደግሞ ፥ በወቅቱ የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበሩትን አቶ ሰይፈ ደስታን ጨምሮ በ5 የባንኩ ሀላፊዎች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ቢሰጥም ፣ፍርድ ቤቱ 3ኛ ተከሳሽ የነበሩትን አቶ ዋሱ አደም አሊን የቀረበባቸውን ክስ በሚገባ ተከላክለዋል በማለት በነጻ አሰናበቷቸዋል፡፡ ለመጨረሻ ውሳኔም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ወርቅ ገዛሁ እያለ ባዕድ ነገር በመግዛት በተደጋጋሚ ከፍተኛ ገንዘብ መጭበርበሩ የሚታወስ ነው።

አላሙዲ የተለመደው ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው

የሚድሮክ እህት ኩባንያ የሆነው ሁዳ ሪል ስቴት ከ15 ዓመታት በፊት መሀል ፒያሳ ላይ ወስዶ ያጠረውን መሬት ግንባታ የማይጀምርበትና በፍጥነት ገንብቶ የማያጠናቅቅ ከሆነ እንደሚነጠቁ አስጠነቀቀ። ቦታውን ወስዶ ለሌላ ልማት እንደሚያውለው ሪፖርተር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አምባዬ  እንዳስታወቁት፣ ሁዳ ሪል ስቴት ፒያሳ ላይ አጥሮ ያስቀመጠው መሬት ላይ ጅምር ሥራዎች አሉ፡፡ በሚፈለገው መንገድና ፍጥነት ግን አልሄደም፡፡ እስካሁን ለመዘግየቱ የራሱ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡ ምክንያቶቹ እንደተጠበቁ ሆነው መዘግየቱ ሁሉንም ያስማማል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ግንባታ መግባት አለበት፡፡ ካልሆነ መሬቱን እንደሚረከቡ አስጠንቅቀዋል። አስተዳደሩ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት ከማስጠንቀቅ የዘለለ ርምጃ መውሰድ አለመቻሉ ትዝብት ላይ ጥሎታል። ሼኽ መሀመድ አላሙዲ ቦታውን የተረከቡት ከሊዝ ክፍያ ነጻ መሆኑ የሚታወቅ ነው። (በተዛማጅ ጉዳይ ላይ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ሰሞኑን አጠር ያለ ዘገባ ያቀርባል)

ዘራፊዎቹ ፖሊሶች ተፈረደባቸው

የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል የሆኑ ሶስት ታጣቂዎች በመሳሪያ በማስፈረራት ወንጀል የሌለበትን ሰው ቦሌ ካራማራ ሆቴል አጠገብ በማስቆም በህግ እንደሚፈለግ ከገለጹ በኋላ ካቴና በማውጣት እጁን ያስሩታል። ተከሳሽ ኮንስታብል አዲስ ደሳለኝ እና እንደሻው መላኩ ወንጀሉን ካልተያዘው ተባባሪያቸው አቶ ገመችስ ጋር በመሆን ያከናወኑት ጥቅምት 15, 2005 ዓ.ም ረፋድ ላይ ነው። ሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ እንዳስታወቀው ተበዳይ አቶ መሃመድ ዑመርን የሰራኸው ህገ ወጥ ስራ ስላለ ለጥያቄ እንፈልግሃለን ብለው በማስፈራራት በዕለቱ 20 ሺህ ብር ካላመጣ እንደሚገሉት ያስፈራሩታል። ለጊዜው የያዘውን 8100 ብር እና የኪስ ቦርሳውን ይረከቡታል።

የቀረውን ብር ለማግኘትም ለጓደኛው እንዲደውል በማስገደድና በማስደወል 10 ሺህ ብር ተጨማሪ ይወስዳሉ። የተረፈውን ብር ከ2 ቀን በኋላ ለመቀበል ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ይቀጣጠሩና ስፍራው ይደርሳሉ። በውላቸው መሰረት ሃያ ሺህ ለመሙላት የጎደለውን 1900 ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው የክስ ሂደቱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ የወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ፥  እያንዳንዳቸው በ4 አመት ጽኑ እስራትና 7 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተደርጓል። በባንክ የተገኘው አስራ አራት ሺህ ብር ለተበዳይ እንዲመለስ ተደርጓል። ገመቺስ የተባለው ተጠርጣሪ ፖሊስ አልተያዘም። ቅጣቱም ተመጣጣኝ አይደለም ከመባል አልፎ በአገሪቱ ውስጥ ሕግ ማስከበር የሚገባቸው ሥልጣናቸውን ከለላ በማድረግ የሚያካሂዱትን ግልጽ ዘረፋ በጨረፍታ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm
  • “ሙሽራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ February 15, 2023 03:13 pm
  • በመዝገበ ቃላት የችጋር መጠሪያ የነበረችው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ወደ ውጭ ላከች February 13, 2023 03:28 am
  • ውዝግቡን በሐዋሪያት መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል February 10, 2023 09:06 am
  • የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው ቄሮ” መሪ ዘመድኩን በቀለ! February 10, 2023 12:48 am
  • በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር February 9, 2023 01:25 pm
  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule