ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ አደጋ ላይ ነች። ይኼን ሁላችንም እናውቀዋለን። የትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውና በማድረስ ላይ ያለው ልክ የለሽ በደል፤ ተጽፎም ሆነ ተነግሮ አላበቃም። ገና ብዙ ይጻፋል። ገና ብዙ ይተረካል። ለነገሩ መቼ ይኼ ጉደኛ የወንበዴዎች ድርጅት በደሉን አበቃና! የመጨረሻው ለመቃረቡ ግን፤ የመውደቂያ ደወሉን ራሱ አስምቶናል። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መውደቁ አይቀሬ ነው፤ ቀን ከመቁጠር ባሻገር። ይኼ ሲከሰት ግን ምን ይከተላል የሚለው ጥያቄ እንደተንጠለጠለ ነው። ያልተመለሱ ብዙ ጥያቄዎች ዙሪያችንን አጥረውናል። ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ዘር፣ ጎሳ፣ ሀገር፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ኅብረተሰብ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ የነፃ አውጪ ድርጅት፣ ግንባሮች፣ ጥምረቶች፣ ትብብሮች፣ ደጋፊዎች፣ ተደጋፊዎች፣ . . . እነዚህ ሁሉ ፅንሰ ሃሳቦች … [Read more...] about ስጋቴን ልግለፅላችሁ
በ2005 እንዲህ ብለን ነበር!
በአዲሱ ዓመት የተመሰረትንበትን አንደኛ ዓመታችንን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ወቅቶች ለንባብ ካበቃናቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል መርጠን ለትውስታ አቅርበናል። ካቀረብናቸውም ሆነ በድረገጹ ላይ ያሉትን ጽሁፎች በመምረጥና በማሰራጨት ልደታችንን ታከብሩልን ዘንድ ግብዣችን ነው። በሌላ በኩል የዝግጅት ክፍላችን ኤዲሪቶሪያል ቦርድ አንባቢዎች በነጻነት አስተያየት እንዲሰጡ፣ አስተያየታቸውም ያለ አንዳች ገደብ እንዲታተም ወስኗል። በመሆኑም ጎልጉልን አስመልክቶም ሆነ በርዕሰ አንቀጽ ላይ ባስቀመጥነው ሃሳብ ላይ በመንተራስ አስተያየት ለምትልኩ "ከስድብና ከዘለፋ" ውጪ በደስታ የሚስተናገድ እንደሆነ አስቀድመን እንገልጻለን። የዓመቱ ምርጥ በማለት "መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ" እና "ጥቁሩ ሰው ይናገራል" የሚሉትን ቃለ ምልለስሶች በስጦታ አቅርበናል። መልካም አዲስ ዓመት፣ ለኛም መልካም አንደኛ … [Read more...] about በ2005 እንዲህ ብለን ነበር!
አዲስ ዓመት – በነተበ ሥርዓት
ጊዚያቶች ክንፍ አውጥተው የሚበሩ ይመስላሉ። 2005 አምና ለመሆን በቅቷል። የተፈጥሮን ህግጋት ጠብቆ በዳመና የጠቆረው ዳመና እየገለጠ፣ አበቦች እየፈኩ ምድሪቷ የመስከረም ወር መጥባቱን ብታበስርም፤ በክፉ የወያኔ አገዛዝ ቀንበር ስር ለሚማቅቀው የአገሪትዋ ህዝብ ዛሬም እንጉርጉሮው የሀዘን ነው። የኑሮ ውድነቱ፣ የሰብአዊ መብት ጥስቱ፣ ፍትህ ማጣት እና በመሳሰሉ ስር በሰደዱ ችግሮች እግር ተወርች ተቀፍድዶ ነገን በተስፋ ተሞልቶ አዲስ ዓመት ይጠብቃል ማለት ዘበት ነው። ይልቁንም አዲስ ዓመት ይዞት በሚመጣው የኑሮ ጣጣ የሚቆዝመው ህዝብ ቁጥር እልፍ ነው። ‹‹ትራንስፎርሜሽን›› የሚባል የወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያ የተዘጋጀው እቅድ እንደተወራለት በአምስት ዓመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ህዝብን የሚያሰልፍ አለመሆኑን ሁሉም ተገንዝቦታል። ይልቁንም የህውሃት ግዙፉ ድርጅት … [Read more...] about አዲስ ዓመት – በነተበ ሥርዓት
‹‹ጀርባ የሚልጡ›› ትናንቶች
ለቅሶ ቤት ቁጭ ብለው የሚጨዋወቱ ሰዎች በእጃቸው ካለው የመጫወቻ ካርድ (ካርታ) እኩል ትኩረት ያደረጉበት ርዕሰ ጉዳይ የአዲሱ ዓመት በዓል ገበያ ነበር፡፡ ሽንኩርት በኪሎ 15 ብር መግባቱ የሚገርማቸው ብቻ አልነበሩም፤ ከአገር የጠፋው በሽተኛው ቲማቲም 25 ብር ላይ መተኮሱ ጭምር ለባለካርታዎቹ መነጋገርያቸው ነበር፡፡ ‹‹ለነገሩ አንድ ኪሎ የቲማቲም ዘር ሁለት ሺሕ ብር በገባበት በዚህ ወቅት፣ ገበሬ በስንት ብር ሊሸጥ እንደሚችል መገመት ይቻላል፤›› በማለት የፀረ አረም ኬሚካሎችንና የአትክልት ዘሮችን የምታከፋፍለው ወጣት፣ የዕድምተኛውን ልብ መለስ አደረገች፡፡ ቲማቲም በበሽታ መመታቱ ብቻ ሳይሆን ለዘርም ለዘሪም መጥፋቱ ዋጋውን ሰማይ አድርሶታል ብለን ብንስማማም፣ የበዓሉን እግር ተከትለው የናሩ ምርቶች ግን የሚጋረፉ ናቸው፡፡ ‹‹የሐበሻ›› እንቁላል አንዷ ያውም የቄብ የምታህለው፣ … [Read more...] about ‹‹ጀርባ የሚልጡ›› ትናንቶች
የዛሬዎቹ ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› እና ‹‹ሆያሆዬ››
ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ በዓሎቻቸውን ስለየበዓላቱ ትርጉም ባላቸው ዝማሬዎችና ጭፈራዎች ያደምቁታል፡፡ ከእነዚህ አንዱ የሆነው የዘመን መለወጫንም ‹‹እንቁጣጣሽ››ን በ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› ያደምቁታል፡፡ እንቁጣጣሽ ሲመጣ ልጃገረዶች ከበሯቸውን ይዘው በየቤቱ እየዞሩ ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› እያሉ ሲጨፍሩ፣ ድምፃዊቷ ዘሪቱ ጌታነህም በየራዲዮ ጣቢያው ‹‹እንቁጣጣሽ እንኳን መጣሽ…›› እያለች በቀጭኑ ድምጿ የምታቀነቅነው ዘፈን ሲሰማ በዓሉን ለመቀበል ያለውን ስሜት ሞቅ ሞቅ ያደርጋል፡፡ ቀደም ሲል ልጃገረዶች ‹‹አበባ አየሽ ሆይን›› ለመጨፈር ተቧድነው እንግጫ ይዘው፣ ከበሯቸውን እየመቱ ከዋዜማ እስከ በዓሉ ዕለት ይጨፍራሉ፡፡ ያኔ የነበረው ጭፈራ የግጥምና የዜማ መፋለስ ችግር አልነበረበትም፡፡ ጨፋሪዎቹም ለዓይን ሞላ ያሉ ነበር፡፡ ጨፍረው ሲያበቁም በዋናነት የሚሸለሙት ቤት ያፈራውን ስለነበር … [Read more...] about የዛሬዎቹ ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› እና ‹‹ሆያሆዬ››
አምላክ ሆይ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው!
አንድየ ሆይ! ያላንተ እዚህ መድረስ አይታሰብምና ከሁሉ አስቀድሜ ለከበረው ስምህ ፣ ለማይደፈር ለማይገሰሰው ሰማያዊ ክብርህ ፣ ለቸርነት ፣ ምህረት ይቅርታህ ምስጋና ይድረሰው ! አባታችን አዳም ትዕዛዝክህ ተላልፎ ታላቁን ስህተት ፈጸመ ፣ ከገነትም ተባረረ ! አባት ሆይ ! አዳም አጠፋ ብለህ አልተውከንም ! የምህረት አምላክ ነህና መንግስትህን እንወርስ ዘንድ በህግ ትዕዛዛትህ እንድንመራ አዘዝከን! ዳሩ ግን ትዕዛዛት ህግ ቀኖናህን ስንጥስ ኖርን ... ይህ ሆነ ብለህም አልተውከንም ... ያለባላ በዘረጋህው ሰማይ ፣ ያለመሰረት ባነጠፍከው ምድር ፣ በእጹብ ስራህ የምድር መቀነት አድርገህ ባንሰራፋህው ውቅያኖስ እና ወንዝ ደምቀን ስታኖረን የምንበላው የምንጠጣውን የምንለብስ የምንጠለልበት በመለኮታዊ ስልጣን ከቸርነት እና ከምህረትህ ጋር ያልተውከን አንተው ብቻ ነህ ! እናም እናመሰግንሃለን … [Read more...] about አምላክ ሆይ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው!
መርዓዊና መንታ መንገዳቸው!
“መልካም መሥራትን ተማሩ፤ ፍርድን ፈልጉ፤ የተገፋውን አድኑ፤ ለድሃ አደጉ ፍረዱለት፤ ስለመበለቲቱም ተሟገቱ። ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር ፤ ኃጢያታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነፃዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ። እሽ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችሁዋለች፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና።`` ትንቢተ ኢሳይያስ 1፣17-20 ውድ አንባብያን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። 2006 ዓ.ም በአገራችን ሰላም ፍቅርና አንድነት የሚሰፍንበት እንዲሆን ስመኝ ባለፉት ዓመታት የነበሩ ግድፈቶች በዓለማዊውም ይሁን በመንፈሳዊው ቤት ተነቅሰው የሚወገዱበትን መንገድ ማመቻቸትን ግን ግድ እንደሚለን በመጠቆም ነው። የእምነቱ ተከታዮች ስለሆንን ያየነውን እኛም ከመናገር ዝም ስለማንል ይህን ለማለት … [Read more...] about መርዓዊና መንታ መንገዳቸው!
የ2005 ዋና ዋና ፖለቲካዊ ክንዉኖች
የመለስ ዜናዊ አስተሳሰብና ምግባር ሕዝብን በተለይም ፖለቲከኞችን በተራራቀ ተቃራኒ ጫፍ እንዳቆሙ መሞታቸዉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበጎ ወይም በመጥፎ፥ ወይም በሁለቱም መሐል-ክፉኛ መንካቱ እንደማይቀር ያኔ ተብሎ ነበር። አሁንም አልቀረም። የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትር ተሸኙ። ሁለት ሺሕ አራትም ተሰናበተ። እና አዲስ ዓመት። ሁለት ሺሕ አምስት። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃና ጳጳሳት እና፥ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ማግስት የባተዉ ሁለት ሺሕ አምስት ካዲስ መሪ፥ ካዲስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሹመት ጋር አዲስ ተስፋ አጭሮም ነበር። ዓመቱ ዛሬ-አርጅቶ ሊሰናበት ሁለት ቀን ቀረዉ። የዓመቱን የኢትዮጵያ አበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች እየጠቃቀስን፥ ተስፋዉ መጠዉለግ-መፅደቁን፥ ላፍታ እንቃኛለን። አብራችሁኝ ቆዩ። መለስ በተቀበሩ በሳምቱ ሁለት ሺሕ አምስት እንደ አዲስ ዓመት ሲብት ሁለት … [Read more...] about የ2005 ዋና ዋና ፖለቲካዊ ክንዉኖች
ዓረና ትግራይ ፓርቲ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠ
ከጳጉሜን 2 እስከ 3 ቀን 2005 ዓ.ም. ሦስተኛ ጉባዔውን በመቐለ ከተማ ያካሄደው ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት (ዓረና ትግራይ) ፓርቲ በቀድሞው የትግራይ ፕሬዚዳንት አቶ ገብሩ አስራት ምትክ፣ የፓርቲውን የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ በርሄን ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ፡፡ የሕወሓት መሥራች አቶ አስገደ ገብረ ሥላሴ በፈቃዳቸው ከፓርቲው አመራር መልቀቃቸው ታውቋል፡፡ በአቶ ገብሩ አስራት የቀረበው የፓርቲው የሦስት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት የተገመገመ ሲሆን፣ በክልልም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ የማያሠራ ቢሆንም በዚሁ ሳይደናቀፍ ዓላማውን እያሳካ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በክልሉ ውስጥ በበርካታ ከተሞች በሕገወጥ መንገድ ቤቶች መፍረሳቸውን የተመለከተው ፓርቲው፣ ሕዝቡ በመልካም አስተዳደርና በፖለቲካ ነፃነት ችግር ውስጥ እንደሚገኝ መገምገሙን … [Read more...] about ዓረና ትግራይ ፓርቲ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠ
How the black lions of Ethiopia transformed from palookas to fearsome net bangers.
“We want to go back to the drawing board and make very tangible plans that will help us in our preparations ahead of very important matches that will decide our destiny and determine if our dream of qualifying for the world cup is fulfilled.” Coach Sewnet Bishaw of Ethiopia speaking to super sport.com. “Today is indeed special for me since it was an important match and that goal I scored gave me a lot of motivation especially knowing my friend Getaneh Kebede was out injured. We have always … [Read more...] about How the black lions of Ethiopia transformed from palookas to fearsome net bangers.