በዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው፤ እንዲያውም ከልመና ውጭ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኑሮ የለም ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ ስለዚህም ልመና ባህላዊ ጥበብ ሆኖአል፤ አንዳንድ አላዋቂዎች፣ አንዳንድ አዋቂዎችም አንዳንዴ እየተሳሳቱ ልመናን እንደነውር ይገልጹታል፤ ልመና ነውር አይደለም፤ ለጨዋ ልጆችማ አንዳንድ አጥንትን የሚያበላሽ ሥራ ከመሥራት ለምኖ መብላት ክብር ነው፤ ይህ ባህላዊ ጥበብ ያልገባቸው የድሬ ዳዋ ለማኞች ብቻ ናቸው፤ እጃቸውን እየዘረጉ ‹‹እስቲ አሥር ብር ስጠኝ!›› ይላሉ! በጫት ሞቅ ሲላቸው መቶ ብር ይጠይቃሉ፤ የድሬ ዳዋ ልመና መሆኑ ነው!
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቄሶቹ ምንም ይስበኩ በተግባር እንደሚታየው ጽድቅ የሚገኘው በልመና ነው እንጂ በሥራ አይደለም፤ ሥራኮ ለአበሻ ከእርግማን የመጣ ነው፤ አበሻ አልተረገመ፤ ታዲያ ለምን ብሎ ይሥራ! አሁን እንደሚሰማውና እንደሚመስለኝ አገዛዙም እንደተቀበለው የቻይና ሰዎችም እንደመሰከሩለት ከሥራ ጋር ጠብ አለው፤ ደግሞስ ለምን ይሥራ! ለአንድ እንጀራ? ለተራበ አብልተው ለመጽደቅ የሚፈልጉ ስንትና ስንት ሰዎች አሉ፤ ስለዚህም ደግ ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ ለመጽደቅም መለመን ያስፈልጋል፤ ጸሎት ልመና መሆኑን አትርሱ፤ ስለዚህም ዋናውና ከፍተኛው ልመና ወደእግዚአብሔር ነው፤ ብልጦቹ እግዚአብሔርን የሚለምኑት ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ነው፤ አንድ ቀን ተነሥተው እግዚአብሔር ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት እንደሰጣቸው ያውጃሉ፤ አውጀውም በሕዝብ ራስ ላይ ይወጣሉ፤ በራሱ ላይ ወጥተውም ይጨፍራሉ፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው መለየት ይሳናቸዋል፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው ያጣላሉ፤ እግዚአብሔር ለእናንተ ብቻ እንዴት ሰጣችሁ? እግዚአብሔር እኛን ለምን ነፈገን? ብሎ የሚጠይቃቸውን እየደበደቡና እያቃጠሉ፣ እየገረፉና እያራቆቱ በዝምታ እንዲገዛ ያደርጉታል፤ አልበቃው ካለም አካሉን ለውሻ ሰጥተው ነፍሱን ወደእግዚአብሔር ይወረውራሉ፤ እግዚአብሔር እየቆጠረ የማይመዘግብ ይመስላቸዋል፤ የጠጠረ ጉልበታቸው ዓይኖቻቸውን አውሮ፣ ኅሊናቸውን አፍኖ እግዚአብሔር በዕዳ እንደሚይዛቸውና በጥጋባቸው ያደሉትን መከራና ስቃይ፣ የወረደውን እንባና ደም ከነወለዱ እንደሚያስከፍላቸው መገንዘብ ያቅታቸዋል።
እግዚአብሔር ፍርዱን እስቲሰጥ ድረስ ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ተረክበናል የሚሉት የተለያዩ ስሞችን እየለጠፉ በተዋረድ የለማኞችን ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ሕዝብ ሁሉ ከነዚህ የለማኞች ሠራዊት በአንዱ ውስጥ ለመግባት በፉክክር ይተላለቃል፤ ሠራዊቱ ውስጥ በመግባት የሚገኘው ጉርሻ ልጆቻቸውን እንኳን ከረሀብ የማያድን መሆኑን ሳይገነዘቡ መብታቸውን እያስረገጡ የሌሎችን መብት ለመርገጥ መሣሪያ ይሆናሉ፤ እነዚህ እንግዲህ ልመናን በማኅበረሰቡ ውስጥ ተክለው እየኮተኮቱ የሚያስፋፉት ናቸው፤ ልመናን ባህል የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው፤ ልመናን ታሪካችን ያደረጉት እነዚህና ከነሱ የቀደሙት ገዢዎቻችን ናቸው።
በእኛ ባህል የራበውን በማብላት ጽድቅ ይገኛል፤ ስለዚህም ለምኖ መብላት ይቻላል፤ ስለዚህም ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ እንግዲህ ለምነው እየበሉ መኖር ከተቻለና እግዚአብሔርን በመለመን ጽድቅ ከተገኘ፣ የመሬቱንና የሰማዩን ጣጣ በልመና መገላገል ከተቻለ ታዲያ ሥራ ለምን ያስፈልጋል! ለነገሩስ ሥራ በእርግማን የመጣ ነው፤ ስለዚህ የተረገሙት ሲሠሩ ያልተረገሙ የሚመስላቸው ይለምኑ፤ ለሌላው ዓለም ልመና የችግር ምልክት ነው፤ ለአበሻ ግን ልመና የጽድቅ ምልክት ነው፤ የጨዋ ልጅ፣ ማለት በልመና በሰዎች ላይ ሥልጣንን ከአግዚአብሔር አግኝቻለሁ ብሎ የሚያምን፣ አይሠራም፤ ቀን ቢጥለውም የጨዋ ልጅ በእጁ ሠርቶ ከሚበላ ለምኖ ቢበላ ይሻለዋል፤ ሆድ የተፈጥሮ ነው፤ ረሀብም የዕለት ከዕለት የተፈጥሮ ግዳጅ ነው፤ ስለዚህም ለአበሻ የተፈጥሮን ሆድና የተፈጥሮን ረሀብ በልመና መወጣት የተፈጥሮን ሥርዓት መከተል መስሎ ይታየዋል።
ሌላ ቀርቶ ተማሪ ለምኖ ካልበላ ትምህርት አይገባውም፤ ለተማሪ ሲሆን ልመና አይባልም፤ ቀፈፋ ነው፤ አበሻ በልመና ምን ይህል እንደተራቀቀ የሚያመለክተው ለተለያዩ ልመናዎች የተለያዩ ስሞች ማውጣቱ ነው፤ እንደተባለው ተማሪ ሲለምን ቀፈፋ ነው፤ በዘመናዊ ቋንቋ የትምህርት ታክስ ነው፤ ምግብ የሚቀርብበትን ሰዓት እየጠበቀ ከተፍ የሚለው ቀላዋጭ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ለቀላዋጭ ቀላል ሰበብ የሚሆነው ቀላውጦ የሚያገኘው ወሬ ነው፤ ሌላም የልመና ዓይነት አለ፤ እርጥባን ይባላል፤ — ደርቄአለሁና አርጥቡኝ ማለት ነው! ‹ላሊበላዎች› የሚባሉት ለምነን ካልበላን እንቆመጣለን በማለት ልመናን የኑሮ መሠረት አድርገውታል፤ ሌላም የልመና ዘር አለ፤ ደጅ መጥናት ይባላል፤ ደጅ መጥናት ማለት ብርዱን ችሎና እንቅልፉን አቋርጦ በሌሊት እየተነሡ በመኳንንቱና በመሳፍንቱ፣ በንጉሡ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ደጃፍ ላይ አጥር ወይም ዛፍ እየተደገፉ የተፈለገውም ሰው ብቅ ሲል በመሬት ላይ በመነጠፍ እጅ በመንሣት ፊት ለማስወጋት ለመታወቅና ለሹመት ለመታጨት የሚጠቅም የልመና ዘዴ ነው፡፡ በአበሻ አገር ሁሉም ነገር በልመና ነው፤ ምግብ በልመና፣ ትምህርት በልመና፣ መሬት በልመና፣ … በልመና፣ ግብር የሚከፈለው በልመና ነው፤ ሥልጣን የሚገኘው በልመና ነው፤ ንጉሥነትም የሚገኘው በልመና ነው፤ ባጭሩ ኑሮ ማለት ልመና ነው፤ ልመና ማለት ኑሮ ነው ።
ezra says
አዬ ፕሮፌሰር መስፍን! ሁሌ መቼም ኢትዮጵያዊ ውርደትን እንደ “ጨዋ” ተግባር አድረገው በማቅረብ ወዳጆቻችው የሆኑትን ነጭችን በጹፋቸው ያስፈንድቃሉ። ነገ ደግሞ ስርቆትንና የቡደን ዝርፊያን ፕሮፌሰር መሥፍን ባማዳነቅ አቦ ሲዘርፉ እንዴት ያስደንቃሉ ብለው …? ” ኖቬል” የሚያሸልም የ “አበሻ ጀብዱ” ብለው ይጽፉልናል። እሳቸው መቼም ዉርደትን በተቃራኒው ነው አሳመረው በጽሁፋቸው የሚያቀርቡት ። አሁን ማን ይሙት በዉነቱ ሥራ እንጅ “ልመና”፡ ያስክበራልን? ፕሮፌሰሩ “አጥንት ከሚሰብር ስራ” ልመና ይሻላል ብለው ወጣቱን አደራጅቶ ማታገሉ ሲያቅታቸው የለም “ለምኖ መኖርን የመሠለ የለም”፡ብለው አገር ተረካቢዉን ወጣት እንዲለምን ያበረታታሉ። ምን ይደረግ ነፍሱ አይማርና ልመናንን እንደ ትልቅ ክብር አደርጎ መለሠ ዜናዊ ለጌቶች የአውሮፓና አሜሪካ መንግስታት እንገዲህ ደረቅ በአገሪቱ እየገባ ነው ይኽው ነገሪያችኋለሁ፡፤ እኔ ኃላፊነት የለብኝም ባስችኳይ እርዳታ እንዳታደርጉልን ብሎ ጌቶቹን(ነጮችን) ሲማፀንና ሲለምን ልመናዉን እንደ ክበር ቆጥሮት ነበር የእነርሱ እዳ አድርጎት ። WHAT A SHAME! ፕሮፌሰር መሥፈን ወልደማርያም በዚህ እድሜያቸው ልመናን ኣድንቀው መፃፋቸው በጣም አሳፍሪ ብቻ ሳይሆን የሚያስገምታቸዉም ነውና- እባክዎን እድሜዎን ለመጥፎ ነገር አይጠቀሙበት።
mindpeace says
@ezra: I think you did not understand the message of this article. This article is written to discourage the culture of begging in Ethiopia. It further emphasized that begging/dependency is deep rooted in the culture, norms and history of Ethiopia. This article intended for the readers that they should understand the magnitude of of begging/dependency problem and to incite the readers fight against it. In conclusion, the way this article is written is known in Amharic as “Silak” that is the reverse is true.
me says
እኛ ሃበሾች ስንባል እውነቱን የሚያወራውን ሳይሆን የሚያባብለንን እናምናለን ለማኞች ነን አዎ ግጥም አርገን ለማኞች ነን ከንቱዎች ነን። ግን ብንሆንስ!!!
Demeke Yeneayhu says
@Ezera
I wonder about your reading level. Stupid, the least!
yekefaw says
This so called professor is really out of realty. It is shame to hear such kind of categorization of Ethiopians. I believe this so called professor leaved for his stomach through out the past governments. I haven’t seen any Ethiopian who is begging in the western world. We Ethiopians are known for sharing during hard times and celebrating together when we have. My fellow Ethiopians, please watch out these kind of professors. They don’t have respect to themselves nor to their people. So don’t take every thing at face value because the professor said so. Long live Ethiopia and its people.
Nathyson says
I was so surprised to have read such demeaning article from one of the best professors in Ethiopia. This is really an insult to the hardworking Ethiopians who have a longstanding bondage to one another. How on earth could one advocate begging as something
that the Ethiopian People could live without? I wouldn’t consider the professor’s intent is to discourage begging as such.. With all due respect to the Professor, this is excruciatingly painful piece of article I can possibly imagine. Thanks to Dagnachew’s thoughtful response to the Professor on Ethio-Media (in Amharic) where he clearly showed us how the Professor dropped the ball regardless of his age, knowledge and authority on Ethiopian history and culture.
Chuchu says
I see nothing wrong in this article,this is prevailing reality that we can’t deny.We don’t like when our weak sides are told this way forward.Tell the people their weak side so that they can learn from it.Don’t glorify with empty words and put them in a position they don’t suppose to be.Good article professor!!!
ezra says
የሚገርም ነው የነ Demeke ኣስተያየት! ፕሮፈሰሩ ኣይሳሳቱም ፣ ከተሳሳቱም እንደተሳሳቱ አደርጎ መመልከት ወይም መተርጎም “ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሕገ-መንግስታዊነትን” እንደመንካት አስቆጥሮ ያስቀጥፋል ዓይነት መሰለኝ የነ DemeKe Yeneayehu አስተያየት። ይቅር ይበለህ Demeke
Thomas Ayalkebet says
God Bless Professor Mesfin. He is the mirror that shows us who we are indeed… He uses his brain well and honors his GOD; take your time to really really really understand the message … make sure you all use your brains very well before you attack Professor Mesfin… How dare any logical person ? To really change, we need to openly talk about who we really are? Understanding our “Hodam” nature is like going 50% of our way to the solutions …for our country’s future.
You know even the significant majority of our priests, pastors and Imams are hodam first ( just like our so called politicians) and worship their GOD last and their congregations are consistently fooled…
GOD NEVER SAID DO NOT USE YOUR THINKINGKING ABILITIES. NEVER …
May we all use our brains and HONOR OUR GOD and live in a free world where we could all think and ask questions of our so called religious leaders and so called politicians…We know God does not appreciate Hodams and people that do not use the brains HE Gave them… Peace!!!
Joo says
Thank you Prof. You have showed us who we are.
Sabure says
Professor Mesfin
Abesha yemilew tshufwo meleekt rswonm slemichemir ene bizu alkefagnm. Yih yedeberewot yelmena bahel abebo endigomera kekotekotut sewoch mekakel erso be ginbar kedem yitekesalu. Yelmena eset meseretu saytal lemenad ewuketum hone gize fekdolwot neber. Ende edel hono yanen aladeregum. Begulbet yaladereguten beshibet binteketek ena bejimla bisadebu men waga alew. Degmo wushaw mindenew? woi reesun ABESHA ENA WUSHA YIBELUT. Ayyee… kareju aybeju ale yagere sew
weldemeskel says
abet profeser seyasaznu endih aynet erkash ena tera sidib kerso ayitebekim. Lenegeru eraswon new yesedebut. betam yasafral yastemaruwachew betam yaznubotal erswo yethafut mehonunem yiterateralu. Tadia ene erswon bihon tolo biye mastebabeya eset neber alebelezia betesebocho saykeru yafrubotal. asafari astesaseb newna.
dereje says
Beggis is really a part of our culture weather we admit or not. It is something that we inherited from the feudalist Ethiopia of the past. To identify , admit , get over it and try to change a percieved bad calture is not something to be ashamed of. I have heard many criticizing the proffesor for not magnifying the goodness of Ethiopian culture as something a static being that never go under any reform or a change. Self decieving is the worst kind of spiritual poverty.
Bewunetu says
It is sad that most of commentators didn’t want to hear the truth, that among Ethiopian population, Habasha is known by it’s culture of begging. Even proud of it by saying “bileminim Amhara negne” to reflect false history about Amhara’s hierarchy over other peoples of Ethiopia. It is not secret that the sources of beggary and prostitution in Ethiopia is Abasha people. It is a time to accept the reality and try to eliminate for the future. Denying doesn’t change the history of these bad culture; instead, it is necessary to focus and work on to change once and for all than criticizing those who speak out the truth. Please don’t jump to insult eye witnesses of history who lived in it, but try to learn from them.
PROFESSOR, THANK YOU AND GOOD LUCK!