• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Editor

ባለቤቱን ከአልናቁ . . .

December 29, 2013 10:41 am by Editor Leave a Comment

ባለቤቱን ከአልናቁ . . .

መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ያወጣውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ባለቤቱን ከአልናቁ . . .

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

በከፊቾ ዞን የጽላት ዝርፊያና ቀበኞቹ

December 27, 2013 08:52 pm by Editor 4 Comments

በከፊቾ ዞን የጽላት ዝርፊያና ቀበኞቹ

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በከፊቾ ዞን በጥንታዊ አድባራት ጽላት መዘረፉን እናውቃለን ያሉ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ገለጹ። የዜናው ምንጮች የዞኑ አገረ ስብከት በዞኑ በሚገኙ አድባራት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቀዋል። ዝርፊያውን የሚያካሂዱት "ባለሃብቶች" መቀመጫቸውን አዲስ አበባና ጅማ ከተማ ያደረጉ የክልሉ ተወላጆች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ነዋሪነታቸው ቦንጋና ጊምቦ እንደሆነ የሚገልጹት የዜናው ምንጮች "ቀበኞች" በማለት የሚጠሯቸውን የጽላት ዘራፊዎች የዝርፊያ ስልት ተናግረዋል። በመጀመሪያ እድሜ ጠገብ የሆኑትን አድባራት ይለያሉ። በቃፊሮቻቸው አማካይነት መረባቸውን ዘርግተው ሰዎችን ያጠምዳሉ። ህዝበ ክርስቲያን በሚሰበሰብበት ወቅትና ዓመታዊ የበዓላትን ቀን መርጠው በርዳታና በእድሳት ስም ውዳሴ ይቀበላሉ። በዞኑ የሚገኙት አቢያተ ክርስቲያናት እድሜ ጠገብ በመሆናቸው በርካታ … [Read more...] about በከፊቾ ዞን የጽላት ዝርፊያና ቀበኞቹ

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ረቡዕ ምሽት በመንፉሃ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ!

December 26, 2013 11:03 am by Editor Leave a Comment

ረቡዕ ምሽት በመንፉሃ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ!

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጀመረውን ፍተሻ በማረጋገጥ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች በሰላማዊ መንገድ በአስቸኳይ ለጸጥታ አስከባሪዎች እጅ በመስጠት ወደ መጠለያ በመግባት ወደ ሃገር እንዲገቡ ማምሻውን ባወጣው ማስታወቂያ አሳስቧል። ካለፉት ሳምንታት ወዲህ በሪያድ መንፉሃ በኤምባሲውና በሃገር ሽማግሌዎች የተቋቋሙ የመረጋጋት ኮሚቴ አባላት ወደ መንፉሃና ኢትዮጵያውያን በሚበዙባቸው መንደሮች በመንቀሳቀስ ዜጎች ያለ ምንም ጉዳት እጃቸውን ሰጥተው ወደ ሃገር ለመግባት እንዲዘጋጁ የመከረ ቢሆንም ጥረቱ አልተሳካም ነበር ።  የሪያድ ኤምባሲ የሽማግሌዎች ኮሚቴ አባላት ባደረጉት ቅስቀሳ ወደ ሃገር ለመግባት ባልተጨበጠ ተስፋ የተዘናጉ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ያልያዙ ወደ ሃገር በመግባቱ ላይ እንዳያቅማሙ መምከራቸው ይጠቀሳል! አሁን በተጀመረው የመንፉሃ ፍተሻ ማዋከብ የለበትም። ህጋዊ መኖርያ ፍቃድ … [Read more...] about ረቡዕ ምሽት በመንፉሃ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ!

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ

December 26, 2013 09:30 am by Editor Leave a Comment

የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ክፍል አንድ ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫ ስለሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ የሚኖረውን ገጽታ እና ትርጓሜ ማስቀመጥ ያስቸግራል። አንዱ ሰው የሚፈራውን ነገር ሌላው ላይፈራው ስለሚችል ፍርሃት እንደ የግለሰቡ ባህሪ እና ጥንካሬ ወይም ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ የተለያየ መልክ ይኖረዋል። ይሁንና በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የሚጋሩት ባህልና ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ እንደመኖሩ ሁሉ የሚጋሩትም ፍርሃት ወይም ደስታ ወይም ሃዘን ወይም ድፍረት ወይም ሌሎች ባህሪያት ይኖራል። በዚህም ምክንያት አንዳንድ ሰዋዊ ባህሪያት ለአንድ ማህበረሰብ ወይም ለበርካታ ሰዎች የወል መገለጫ ተደርጎ ሲገለጽ ይስተዋላል። ‘የዚህ አካባቢ ሰዎች ጀግኖች ወይም ጸብ ፈሪዎች ወይም እሩህ ሩህዎች ወይም ጨካኞች ወይም ቂመኞች ወይም ገራገሮች ወይም ተንኮለኖች ወይም ጎጠኞች ወይም ሌላ ባህሪ ያላቸው ናቸው’ የሚል አገላለጽ … [Read more...] about የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የትግል ስም

December 25, 2013 08:20 pm by Editor 2 Comments

የትግል ስም

ለመግቢያ ያህል ሰሞኑን የበርካታ ሰዎችን የብዕር ስም አካፍዬአችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለትግል ስም በጥቂቱ አወጋችኋለሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎቻችን የሚጠሩባቸውን የትግል ስሞችም አካፍላችኋለሁ፡፡ ***** “የትግል ስም” ቃሉ እንደሚያመለክተው በትግል ዓለም ውስጥ ላለ ሰው ነው የሚያገለግለው፡፡ ታጋዩ በትግል ዓለም ውስጥ እያለ የሚጠቀምበት መጠሪያው ነው፡፡ ታጋዮች የትግል ስምን የሚጠቀሙት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ነው፡፡ ዋነኛው ምክንያት ግን ታጋዩ በትግል ዓለም ውስጥ ሳለ አደጋ እንዳይደርስበት ለመከላከል በሚል ነው፡፡ የትግል ስም እንደ ብዕር ስም በሚስጢራዊነት አይያዝም፤ ሰውዬው ድሮ የሚታወቅበትን ስም ተክቶ በስራ ላይ ይውላል እንጂ፡፡ ታጋዩ ወደ ትግል ዓለም ከገባ በኋላ የሚያገኛቸው የትግል ጓዶች በትግል ስሙ ነው የሚጠሩት፡፡ በመታወቂያም ሆነ በሌሎች ሰነዶች ጥቅም ላይ … [Read more...] about የትግል ስም

Filed Under: Politics Tagged With: Left Column

ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

December 25, 2013 10:18 am by Editor Leave a Comment

ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤ እንዲሁም በመላው UKየምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሁሉ። በስደት ላይ በሚገኘው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ጥረት፤ ድካምና ተጋድሎ አማካኝነት ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘረጋው የጎሳ ፖለቲካ ተጽዕኖ ሥር ሳትወድቅ በአስተዳደር ራሷን ችላ በመመራት ለከፍተኛ የዕድገት ደረጃ የበቃችው አንጋፋዋ የለንደን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅት ለወያኔ ባደሩ ጥቂት ባንዳ ካህናትና ተከታዮቻቸው አማካኝነት ገንዘብና ጉልበታቸውን አስተባብረው፤ ጥረውና ግረው የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ባለቤት ካደረጓት አባላቷ ተነጥቃ የወያኔ አገዛዝ ሹመኞችና ደጋፊዎች ንብረት እንድትሆን የሚካሄደው ጥረት ቀጥሎ … [Read more...] about ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

December 25, 2013 09:39 am by Editor 1 Comment

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አንምሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩ የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሙዋርቱ! ሪያድ በኢትዮጵያው አንምሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው «ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ» ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ ! ከ9 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ የውጭ ሃገር ዜጎች በጥገኝ ነት እንደሚኖሩባት የምትታወቀው ሳውዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካከሉ የተሰጠ የ 7 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ከ 3 መቶ ሺህ በማይበልጡ ኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ባነጣጠረው እርምጃ እስካሁን ቁጥሩ በወል ለማይታወቅ ወገናችን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት ስቃይ እና መከራ ምክንያት መሆኑ … [Read more...] about በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

ፖለቲካና ሃይማኖተኝነት የሚያቃርናቸው ነገር አለን?

December 24, 2013 06:38 pm by Editor 2 Comments

ፖለቲካና ሃይማኖተኝነት የሚያቃርናቸው ነገር አለን?

ፖለቲካ የሚለው ቃል የባዕድ ቃል ነው እምነተ-አሥተዳደር ማለት ነው፡፡ ከባዕድ ከመምጣቱም ቃሉንና ተግባሩን በመልካም ጎኑ ቀምሰን ሳናጣጥመው ወዲያውኑ ምሬቱን ስላሳየን ለቃሉና ለተግባሩ መልካም ስሜት የለንም፡፡ አንድ አባባልም ፈጥረንለት ከሥነ-ቃሎቻችን ቀላቅለንለታል ‹‹ፖለቲካንና ኮረንቲን በሩቁ ነው›› የሚል፡፡ በእርግጥ ግን ፖለቲካን ርቆ መራቅ ይቻላል? ለዚህ ቃልና ለተግባሩ ባለን ጥሩ ያልሆነ አመለካከት የተነሣ ፖለቲካ ያለውን የሀገርንና የሕዝብን እጣ ፈንታ የመወሰንን ያህል ግዙፍ አቅምና ሚና ዘንግተን ፖለቲካንና ፖለቲከኛነትን ጭንቅላታችን ውስጥ የጭራቅ ምስል ሥለን በመፍራት በመጥላትና በመሸሽ በዜግነታችን ለሀገራችን ልናበረክተው የሚገባንን ተግባርና አገልግሎት እንዳናበረክትና ሀገሪቱም በፖለቲካ ምክንያት ከሚከሰቱ ትብትብ ችግሮች እንዳትወጣ አድርጓታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ … [Read more...] about ፖለቲካና ሃይማኖተኝነት የሚያቃርናቸው ነገር አለን?

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና

December 24, 2013 01:53 am by Editor 4 Comments

ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና

በአማራ ክልል የተካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ የተሰጠው ሹመትና የሹም ሽሩ አካሄድ መነጋጋሪያ ሆነ። "በቃኝ አሉ የተባሉትን ባለስልጣን አውርዶ እንደገና መሾም የተነቃበት የህወሃት የማረጋጊያ ጨዋታ ነች" ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናገሩ። በሹም ሽሩ የአቶ ደመቀ መኮንን እጅ እንዳለበትና መንስዔውም "የቆየ ቁጭትና ቁርሾ" እንደሆነ ተጠቆመ። የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ከመንበራቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የመንግስት ልሳን መገናኛዎች እንዳመለከቱት አቶ አያሌው ከሃላፊነታቸው የተነሱት ታህሳስ 9/2006 በተጠራ አስቸኳይ የክልሉ ጉባኤ ነው። አዲስ ሹመት ያስፈለገው አቶ አያሌው ባቀረቡት "የመተካካት" ጥያቄ እንደሆነም ተመልክቷል። ምትካቸው የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነዋል። አቶ ገዱ ፕሬዚዳንትነታቸው በጉባኤ ተወስኖ ይፋ ከመደረጉ ጎን ለጎን ዜና … [Read more...] about ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ኢራፓ የስብሰባ ጥሪ

December 22, 2013 10:33 pm by Editor 2 Comments

ኢራፓ የስብሰባ ጥሪ

እሁድ ታህሳስ 13 ቀን 2006 ዓ/ም በኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ አዘጋጅነት በዋሽንግተን ዲሲ ዩኒፊኬሽን ቸርች 1610 Rd NW ውስጥ በተዘጋጀው የብሔራዊ/ሀገራዊ መግባባት አጀንዳ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ በፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ መሪነት በሚደረገው ህዝባዊ ውይይት በዋሺንግተን ዲሲና አከባቢው ያላችሁ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውይይቱ ታዳሚ እንድትሆኑ ኢራፓ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል:: ሰዓት ከ2:00 PM ጀምሮ Sunday December 22, 2013 … [Read more...] about ኢራፓ የስብሰባ ጥሪ

Filed Under: Opinions

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 315
  • Page 316
  • Page 317
  • Page 318
  • Page 319
  • …
  • Page 392
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • Defected Fano Spokesperson Alleges Orthodox Fano Is Pursuing Ties with Radical Islamist Groups Houthis and Al Shabaab November 24, 2026 06:38 am
  • “ፋኖ እንደ ሁቲ እና አልሸባብ ካሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር ለመሥራት ጥረት እያደረገ ነው” November 23, 2026 10:52 pm
  • በፋኖ ስም ከአማራ ገበሬና ከዳያስፖራ የሚሰበሰበው በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የጥቂት አመራሮች መበልጸጊያ ሆኗል November 20, 2026 08:54 am
  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
Copyright © 2026 · Goolgule