• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

December 25, 2013 10:18 am by Editor Leave a Comment

ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤ እንዲሁም በመላው UKየምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሁሉ።

በስደት ላይ በሚገኘው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ጥረት፤ ድካምና ተጋድሎ አማካኝነት ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘረጋው የጎሳ ፖለቲካ ተጽዕኖ ሥር ሳትወድቅ በአስተዳደር ራሷን ችላ በመመራት ለከፍተኛ የዕድገት ደረጃ የበቃችው አንጋፋዋ የለንደን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅት ለወያኔ ባደሩ ጥቂት ባንዳ ካህናትና ተከታዮቻቸው አማካኝነት ገንዘብና ጉልበታቸውን አስተባብረው፤ ጥረውና ግረው የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ባለቤት ካደረጓት አባላቷ ተነጥቃ የወያኔ አገዛዝ ሹመኞችና ደጋፊዎች ንብረት እንድትሆን የሚካሄደው ጥረት ቀጥሎ ይገኛል።

london 1ቀደም ሲል እነዚሁ ከሃዲ ካህናትና ተከታዮቻቸው ወያኔ ከጎሳው መርጦ ከሾማቸው ከአቡነ እንጦስና ከነ መጋቢ ተወልደ ጋር ግንባር በመፍጠር በ12 October 2013 ሁለት ጳጳሳትን ከኢትዮጵያ በማስመጣት ቤተ ክርስቲያኗን በወያኔ አገዛዝ ሹመኞችና ደጋፊዎች ቁጥጥር ሥር ለማዋል ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ይህ ሙከራቸው ግን ስደተኛው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝቤ ላይ የምትፈጽሙት ግፍ፤ በደልና ፍትሕ አልባነት አልበቃ ብሏችሁ በዚህ ነጻነትና ፍትሕ በሰፈነበት ሃገር ደግሞ ተመሳሳይ ድርጊት እፈጽማለሁ ብላችሁ አታስቡ በማለት ሰላማዊና ሕጋዊ ተቃውሞ በማድረግ ሙከራቸውን ሊያከሽፈው ችሏል።

ከዛም በመቀጠል የከሃዲዎቹ መሪ የሆኑት አባ ግርማ ከበደ አዲስ አበባ ድረስ በመሔድ ከወያኔ አገዛዝ ባለሥልጣኖችና የደህንነት ሰዎች ጋር በመምከር ለንደን በሚገኘው የወያኔ ኤምባሲና ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሃ.ት) ጽሕፈት ቤት እየተረዱ የጀመሩትን ተግባር እንዲያጠናቀቁ መመሪያ ተቀብለው ተመለሱ።

አባ ግርማ ከበደም ለወያኔ አገዛዝ ያላቸውን ታማኝነት ለማረጋገጥ ሲሉ ዜና ቤተ ክርስቲያን ለተሰኘው መጽሄት ለንደን ላይ የሚያስቸግሩኝ ግንቦት ሰባትና ቅንጅት ናቸው የሚል ክስ በማቅረብ ከነዚህ ሁለት ድርጅቶች ጋር ለሚያደርጉት ትግል ወያኔ ከጎናቸው እንዲቆምላቸው መጠየቃቸውን መጽሄቱ በእትሙ ላይ ካሰፈረው ለመረዳት ተችሏል።

በዚህ ድጋፍና መበረታታት በመታገዝ በአሁኑ ወቅት ደግሞ እነዚህ ባንዳ ካህናትና ተከታዮቻቸው የሃገሪቱን ሕግም ሆነ የቻሪቲን ሕግና መመሪያ አንቀበልም በማለት በኤምባሲ ተወካዮችና ለንደን ከደረሱ ካለፈው 7 ጀምሮ ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ደጃፏን ረግጠው በማያውቁት አቡነ እንጦስ አማካኝነት በ29/12/2013 ቤተ ክርስቲያኗን ከፍተው ለማስረከብ መዘጋጀታቸውን ይፋ ማስታወቂያ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ።london 2

ከዚሁ ጋርም በኤምባሲና በወያኔ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በለንደን ያሉና ከለንደን ውጪ ያሉ የሌላ ቤተ ክርስቲያን አባላት ተጓጉዘው መጥተው ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በብዛት በመገኘት ቤተ ክርስቲያኗን በወያኔ አገዛዝ ሹመኞችና በኤምባሲ ተወካዮች ቁጥጥር ሥር ለማዋል ኃይልና ጉልበት እንዲሆኗቸው ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን አቡነ እንጦስ በሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለጸሎት ለተሰበሰበው ሕዝብ ይፋ ቅስቀሳ አድርገዋል።

ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ ግን ለአካባቢው ፖሊስ የተሰጠው ምክንያት የጸሎትና የአምልኮት መብታችንን ይከበርልን ዘንድ ቤተ ክርስቲያኑን ስንከፍት አስፈላጊው ትብብር ይደረግልን የሚል በመሆኑ ፖሊስ ያሉትን አምኖ ተቀብሎ ትብብር ሊያደርግላቸው እንደሚችል ይገመታል።

በለንደንና በመላው UK የምትገኙ ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችና የማርያም ወዳጆች ሁሉ፡

መብትና ነጻነት ያለትግል፤ ድካምና መስዋዕትነት አይገኝምና ዛሬ የእምነትና የነጻነት ምልክታችን የሆነችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስደተኛው ኢትዮጵያዊ ሃብትና ጉልበቱን አስተባብሮ የንብረት ባለቤት ባደረጋት ማግስት የወያኔ ሹመኞች የውስጥ ባንዳዎችን በመሣሪያነት ተጠቅመው የሃይማኖቱን ማዕከል፤ ሃብትና ንብረቱን ነጠቁት ማለት ነገ በስደቱ ዓለም ነጻ የኮሚኒቲ ማዕከል፤ የፖለቲካ ተቋም፤ መኖር ቀርቶ በቤተሰብ ደረጃም ሆነ በግል ሰብ ሳይቀር በነጻነት ሃገር መብትና ነጻነትን አሳልፎ ለመስጠት ትለቁ በር ከፋች ስለሆነ ሁሉም የማርያም ወዳጅና ነጻነት ወዳድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በ29/12/2013 ከ0800 ሰዓት ጀምሮ በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ቤተ ክርስቲያኑን እንዲከላከልና በስደት ሃገር የተጎናጸፈውን መብትና ነጻነቱን እንዲያስከብር በእመቤታችን በቅድስት ማርያም ስም ጥሪአችንን እናቀርባለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

በ http://londondebretsion.org/ ተከታተሉን

በ ourchurchdebretsion@gmail.com ኢ-ሚየል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule