• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና

December 24, 2013 01:53 am by Editor 4 Comments

በአማራ ክልል የተካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ የተሰጠው ሹመትና የሹም ሽሩ አካሄድ መነጋጋሪያ ሆነ። “በቃኝ አሉ የተባሉትን ባለስልጣን አውርዶ እንደገና መሾም የተነቃበት የህወሃት የማረጋጊያ ጨዋታ ነች” ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናገሩ። በሹም ሽሩ የአቶ ደመቀ መኮንን እጅ እንዳለበትና መንስዔውም “የቆየ ቁጭትና ቁርሾ” እንደሆነ ተጠቆመ።

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ከመንበራቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የመንግስት ልሳን መገናኛዎች እንዳመለከቱት አቶ አያሌው ከሃላፊነታቸው የተነሱት ታህሳስ 9/2006 በተጠራ አስቸኳይ የክልሉ ጉባኤ ነው። አዲስ ሹመት ያስፈለገው አቶ አያሌው ባቀረቡት “የመተካካት” ጥያቄ እንደሆነም ተመልክቷል። ምትካቸው የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።

አቶ ገዱ ፕሬዚዳንትነታቸው በጉባኤ ተወስኖ ይፋ ከመደረጉ ጎን ለጎን ዜና የሆነው የሳቸው ሹመት ሳይሆን የአቶ አያሌው ስልጣናቸውን በፍላጎታቸው መልቀቃቸው ነው። አቶ አያሌው የ”በቃኝ” ጥያቄ ማቅረባቸው ከተሰማ ብዙ የቆየ ቢሆንም አሁን አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቶ የተወሰነበት ምክንያት ዜናውን አነጋጋሪ ያደረገው ጉዳይ ነው።

የአቶ አያሌው ከሃላፊነታቸው መነሳት ከግራና ቀኝ መነጋገሪያ በሆነ ማግስት ኢህአዴግ የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት እንደሰጣቸው ይፋ መደረጉም ሌላ ግርምት ፈጥሯል። በ”መተካካት” ሰበብ ከስልጣን ተነሱ የተባሉት አቶ አያሌው “ባለሙሉ ስልጣን” አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ደግሞ የሹም ሽር ተውኔቱን “ኮሜዲ” አሰኝቶታል ያሉና በማህበራዊ ድረገጾች መዝናኛ ያደረጉት ጥቂት አይደሉም።

ምክትላቸው የነበሩትና አሁን ዋናውን መንበር የጠቀለሉት አቶ ገዱ “ብዙ ጉድ አለባቸው” የሚሉ ወገኖች ወቀሳ መሰንዘርና መጠየቅ አለባቸው በማለት መከራከር ከጀመሩ ቆይተዋል። የአማራ ክልልን እንዳሻቸው ይጋልቡታል ከሚባሉት አቶ በረከት ስምዖን ጋር የጠነከረ ወዳጅነት እንዳላቸውና ከህወሃት የደህንነት ቁንጮ መዋቅር ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ የሚታሙት አቶ ገዱ “ጉዳቸው የተሸፈነው ባላቸው የታማኝነት መረብ (ኔትወርክ) ነው” በማለት የቅርብ ሰዎቻቸው ይከሷቸዋል።

gedu
ገዱ አንዳርጋቸው

በድርጅት በተወሰነ ውሳኔ አቶ አያሌው እንዲለቁ የተደረገውን ወንበር የተረከቡት አቶ ገዱ “ህወሃት ለሚያወርደው ማናቸውም መመሪያ ለመተግበር የፈጠኑና የታመኑ ከመሆናቸው በዘለለ ክልሉን የመምራት ብቃት እንደሌላቸው እናውቃለን” በማለት አስተያየት የሰጡ፤ የአቶ አያሌው ወንበር ለመነጠቁ ደረጃቸው በውል የማይታወቀውን ምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደ ምክንያት ያነሳሉ።

አቶ ደመቀ በክልሉ በግልጽ በሚታወቅ ስልጣን የአቶ አያሌው የበታች ሆነው የሚሰሩ ቢሆንም፣ የክልሉን የጸጥታና የደህንነት ጉዳይ ከህወሃት ሰዎች ጋር በመሆን ይሰሩ ስለነበር ከአቶ አያሌው ቁጥጥርና ትዕዛዝ ውጪ እንደነበሩ የሚጠቁሙት ክፍሎች “አቶ አያሌው በስብዕና ደረጃ እስካሁን በክልሉ ከተሰየሙት መሪዎች የተሻሉ፣ በባህሪያቸው ረጋ ያሉና ለክልሉ ህዝብም በንጽጽር ተቆርቋሪ የነበሩ” በማለት ይገልጹዋቸዋል። በዚህም የተነሳ “ሎሌ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አቶ ደመቀ ብዙም እንደማይፈልጓቸው፣ በዚህ ምክንያት የልብ ወዳጃቸውና ለህወሃት በታማኝነት በመታዘዝ የሚመሳሰሏቸውን አቶ ገዱን ለሃላፊነት እንዳበቋቸው ይገልጻሉ። በሌላም በኩል ለሱዳን እንዲሰጥ በተወሰነውና ሰሞኑንን የድንበር ማካለሉ ተግባራዊ እየሆነ እንዳለ የሚነገርለትን የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን እንዲሰጥ የተፈረመውን ስምምነት የሚያነሱም አሉ።

አቶ አያሌው ስምምነቱን አልፈርምም በማለታቸው ሳቢያ አቶ ደመቀ እንዲፈርሙና የኢትዮጵያን ህጋዊ መሬት ለሱዳን አጨብጭበው እንዲያስረክቡ በታዘዙት መሰረት ተግባራዊ ማድረጋቸው በክልሉ የተተፉ፣ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ደግሞ የተረገሙ አድርጓቸዋል። እኚሁ ከህወሃት በቀር ዘመድና ወዳጅ የላቸውም የሚባሉት አቶ ደመቀ “አያሌው ተገዶ መፈረም ነበረበት” በሚል ሲቆጩ እንደነበር የሚናገሩ አሉ። በባህር ዳር የሚኖሩና ለአቶ ደመቀ ቤተሰቦች ቅርብ የሆኑ “አቶ ደመቀ በኩራት የኢትዮጵያን ድንበር እልል ብለው በባንዳነት ወደውና ፈቅደው ካስረከቡ በኋላ ልጆቻቸው ፊደል ከሚቆጥሩበት የህጻናት ማሳደጊያ እንኳን መቀመጥ አልቻሉም ነበር” በማለት አቶ ደመቀ ላይ የደረሰውን የጥላቻ ስርና ጥንካሬ ያስረዳሉ። እንደ እኚሁ ሰው ገለጻ ከሆነ አቶ ደመቀ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው አዲስ አበባ እንዲዛወሩ የተደረገበት አንዱ ምክንያት ይኽው ልጆቻቸው ድረስ የዘለቀው ጥላቻ ጉዳይ ነው።

ከዚህ ማህበራዊ ቀውስ በኋላ አቶ አያሌውን በመልካም የማያይዋቸው አቶ ደመቀ የብአዴን ሊቀመንበርና ከአራቱ ጠ/ሚኒስትሮች መካከል አንዱ በመሆናቸው ጊዜ ወስደው አቶ አያሌው እንዲነሱ ጉባኤ ላይ ድምጽ ያሰጡባቸው፣ ድምጹንም አስቆጥረው ደስታቸውን የገለጹ፣ ወዲያውም ተመሳሳያቸውን መንበር አሰጥተው ደስታቸውን እጥፍ ድርብ ማድረጋቸውን ጉባኤው ላይ የነበሩ ለጎልጉል ገልጸዋል።

አቶ አያሌው በትክክል “ስልጣን በቃኝ፣ ለተተኪው ክፍል አስረክባለሁ” ቢሉ አምባሳደር ሆነው ባልተሾሙ ነበር የሚሉት እነዚሁ ወገኖች፣ “በቃኝ፣ ደከመኝ፣ ተኩኝ፣ ልተካ ብሎ የጠየቀ ባለስልጣን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አድርጎ በበነጋው መሾም ከሹም ሽሩ ጀርባ ችግር እንዳለ የሚያሳይ ነው” ብለዋል። አቶ አያሌው ባስቸኳይ ስብሰባ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ቅሬታ እንዳይፈጥርና ሌሎች ባለስልጣናት ላይ የመደናበር ስሜት እንዳያስከትል በሚል “ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር” ተደርገው መሾማቸውን ያመለከቱት ወገኖች “አካሄዱ የህወሃት የተቃጠለ ስልት ነው። ብአዴን ውስጥ ውስጡን እየጨሰ ነው። አቶ ገዱ ያበርዱት እንደሆን ለወደፊቱ የሚታይ ይሆናል” ሲሉ ከሁሉም ጨዋታ ጀርባ ሌላ ችግር መኖሩን አመላክተዋል። አቶ አያሌው የልማት አርበኞችን ከማፍራት አኳያ በስኬት ጉድለት አቶ ገዱን ክፉኛ መገምገማቸውም ይታወሳል። አቶ ደመቀ የትምህርት ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ስራው ከክልል የስለላ ስራ የተለየ አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ በሃላፊነታቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Hus says

    December 24, 2013 07:51 am at 7:51 am

    ዝብርቅርቅ ያላ,መላ ቂጡ የምታወቅ, ስሜታዊ መሰረተ ቢስ ወሬ!

    Reply
    • dawit says

      December 24, 2013 03:09 pm at 3:09 pm

      “ዝብርቅርቅ ያላ,መላ ቂጡ የምታወቅ, ስሜታዊ መሰረተ ቢስ ወሬ!” ስትል ምን ማለትህ ነው? ወንድሜ ሃሳብህን ብታፍታታው? አስተያየት ለመሰጠት ያመቸናል፤ አለበለዚያ የአቶ ደመቀ ወዳጅ ወይም የእሳቸው አምሳያነትህ የፈጠረብህ “ዝብርቅርቅ” ስሜት ያስመስልብሃል::

      Reply
  2. koster says

    December 24, 2013 08:35 am at 8:35 am

    All hodam collaborators will be thrown like dirt by woyane ethnic fascists sooner or later

    Reply
  3. በለው! says

    December 28, 2013 04:16 am at 4:16 am

    “ከአማራ ክልል የተቆረጠ ዱላ ወደ ቱርክ ተቀባበለ፦!”
    -“ሰሜናዊቷ ኮከብ” እየተባለች በምትሞካሸው መቀሌ ከተማ 3 ወር ሙሉ ውሃ አልነበረም “የውሃ እጥረቱ የተከሰተው ከከተማዋ ዕድገት ጋር ተያይዞ ነው” ብለው በቀላሉ ተገላገሉት (ይሄማ ከራዕዩ የቀጠለ ነው!)“ስኳር ለምን ጠፋ?”
    “ስኳር ቀምሶ የማያውቀው ገበሬ ስኳር መቅመስ ስለጀመረ!” ለምን ጤፍ ጠፋ? “ጤፍ በልቶ የማያውቀው ብሔር ብሔረሰብ ጤፍ መብላት በመጀመሩ ነው” እንግዲህ ቻይና ሕንድ ቱርክና ዓረብ ኢንቨስተሮች የጤፍ ቂጣ መብላት ስለጀመሩ ነው ለማለት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ። በሐረር ክልል መብራት ጠፍቶ ለጂቡቲ መብራት እንዴት ይሰጣል? “ለጂቡቱ የሰጠነው ከምሽቱ ፭ሰዓት በኋላ ነው። ግን ለ፻፶ሺህ በሳውዲ አረቢያ ለተሰደዱ ሌሊት በመብራት የሚሰራ ትንሽ ፋብሪካ ከፍተን ቢሆን ለምን እሰው ሀገር እጅ እግር አንገታቸው በሜንጫ ተቆርጦ ተደፍረው፣ ተደብድበው፣ የአዕምሮ በሽተኛ፣ ሆነው ውሻ እየተባሉ ወደ ኢትዮጵያ ይባረሩ ነበር? በኢትዮጵያ መብራት ተቋረጠ ሲባል በወር ሁለት ሳምንት ብቻ በፈረቃ ሲበራ ነው። መብራት ጠፋ የሚባለው እንጀራ ሊጋጋር ምጣዱ እየሰማ ሲጠፋና ለተከታታይ ሶስት ቀን ቆይቶ ሊጡ ሲደፋ ነው። በእውቀቱ ስዩም አገላላጽ ሱዳን መብራት ጠፋ የሚባለው የሳሎኑ ጠፍቶ መኝታ ቤት ሲበራ ነው።በመብራት፣ በውሃና በስልክ አገልግሎቶች አዲስ የተቆረቆርን አገር መሰልን አይደል? (ደቡብ ሱዳን እኮ ተሻለች!) “ከተማዋ ምስቅልቅል ላይ ናት…ግን የዕድገት ምስቅልቅል ነው!” … ይሄ ለሁሉ ነገር እንደ ፍቱን መድሃኒት የሚታዘዘው የ1ለ5 አደረጃጀት (በቤት ስሙ “ጥርነፋ!”) በቴሌ፣ በውሃና ፍሳሽ፣ እንዲሁም በመብራት ሃይል አልተሞከረም እንዴ? አቤት ሙቀት! አቤት መተፋፈን!አቤት መጨናነቅ!

    << ይህንና ሎሎችንም የሀገርና ሕዝብ ስቃይ ለማስቀጠል የሰሜናዊቷ ኮከብ ሀገር ነዋሪዎች በአይጋ ፎረም ድረገፃቸው ላይ የተለጠፈውን " ማንዴላን በማሳበጥ የመለሥ ራዕይ አይሟሽሽም!! ዮናስ 12/24/13" አንብበው ይተርጉሙ።የመልስ ራዕይን ለሟሟሸሽ መብራት የለም፣ ውሃ ጠፋ፣ ታፈንን፣ ታሰርን፣ ማለት …ታጋዩን እሬሳ እንደመናቅ ይቆጠራል ታጋይ አይሞትም!!
    *የመለስን ባለራዕይነትና አርበኝነት የሚያመላክተው ትልቁ አብነት ኢትዮጵን በቀጣዮቹ አሥርት ዓመታት የበለጸጉ ሃገሮችን ጎራ እንድትቀላቀል ያስቀመጠው ራዕይ ነው፡፡( ኒቆዲሞስ ዜናዊን ሚሊየነር! ኤዘብ ዜናዊ ጠላ ሻጭ! ፀጋዬ ዜናዊ ጢቢኛ ሻጭ! በለው!!
    **ሃገራችንንም ከተስፈኞች ጎራ ማውጣት አለብን። የሚል ፅኑ አቋም የነበረው ሲሆን ከዚህ አኳያ የሃገራችን እድገት
    ጎልቶ እንዲታይ ያደረጉት የከተማና የገጠር ልማት ፖሊሲዎችና የአፈፃፀም ስልቶች የመለስን የልማት አርበኝነት እና ጀግንነት በትክክል የሚያሳዩና የሚያረጋግጡልን ናቸው፡፡
    ***መለስ ብዝሃነትን ማክበር የአገሪቱ ህልውና መሠረት መሆኑን አጽንኦት ሠጥቶ አሥተምሯል፡፡ በገዛ አገራቸው ተዘንግተው የኖሩ የተናቁና ማንነታቸው እኩልነታቸው የተገፉ ወገኖች እኩልነታቸው ታውቆ በአገሪቱ ወሣኝ ተግባራት ተሣታፊና የውጤቱም እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በዚህም የአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ነፃና ህያው አካል እንዲሆኑ በሠፊው ተንቀሳቅሷል፡፡
    **የመለስ ገድልና ታምራት በዓለምና በአፍሪካም ተገልጧል፡፡ የአፍሪካ ድንቅ ልጅ የሚል ስያሜ ያተረፉለትን የተለያዩ ተግባራት አከናውኗል፡፡ የአፍሪካ ምርቶች ዋጋ እንዲሻሻል፣ ወደ አፍሪካ የሚፈሠው ኢንቨስትመንት ብድርና እርዳታ እንዲጨምር፣ አፍሪካውያን በአየር ንብረት መዛባት ለሚደርስባቸው ጉዳት ማካካሻ እንዲያገኙ እንዲሁም የዓለም ንግድ ሥርዓት ለአፍሪካ ዕድገት የሚያመች እንዲሆን ለማድረግ በተገኙት መድረኮች ሁሉ ታግሏል፤ ተሟግቷል፡፡
    ***የህዝቦች ሠቆቃ የሚያንገፈግፈው ለህዝቦች ጥቅምና ጀግንነት ለህዝቦች ሠላም ቀን ከሌት የሚጨነቅ መሆኑና ይህንን ፍቅሩንየሁሉም ተግባራቱ አንቀሣቃሽ ሞተር አድርጎ የሚጠቀም መሆኑ መለስን ጀግና አድርጎታል፤ አርበኛም አስብሎታል፡፡ ሃዋርያም ተብሎ ተጠርቶበታል፡፡ የህዝቦቹን ፍላጎት የሚያነፈንፍ ለህዝብ የቀረበ ልብ አለው፡፡ ለእኔ ሃገር ማለት ህዝብ ማለት ነው፡፡ የአገር ፍቅርም ማለት ከህዝብ ፍቅር ውጪ ትርጉም የለውም ይል ነበር።
    **በአጠቃላይ መለስ በአንድ ጊዜ የፖለቲካ ሳይንቲስት፣ የኢኮኖሚ ሊቅ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተንታኝ፣ የህግ ምሁርና የወታደራዊ ሣይንስና ጥበብ ቁንጮ ነበር፡፡ በዚህም ጀግና ቢባል ሃዋርያ ቢባል አርበኛም ቢሠኝ ቢያንስበት እንጂ የሚበዛበት አይደለም፡፡ ስለማያንስበትም ነው መላ ህይወቱን ለአመነበትና ለቆመለት ዓላማ መስዋእት የሆነውን ታላቅ መሪ ራዕይ ለማስቀጠል ሁሉም የሡን ራዕይ፣ የሡን ዓላማና ግቦች አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው፡፡ መለስ ህግ ሣይሆን ሃዋርያ ነው፤ የሕግ ተገዢ ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ አባይን የደፈረ ጀግና መሪ ምናልባትም በ፪ሺህ ዓመት አንዴ ብቻ ሊደገም የሚችል አርበኛና ሃዋርያ።

    **"አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ የአረንጓዴው ልማታዊ መንገስት" ለአረንጓዴው ችግኝ ተከላ የሞቱ መሪ ከአንድ ኮብል እስቶን ጠራቢ ደሞዝ ባታች እያገኙ ፫ነጥብ፫ ቢሊየን መቆጠብ የቻሉ የድሆች ተምሳሌት የአባታቸውን ተትረፈረፈ ሀብት ጥለው ድሃ ለመሆን ዋሻ የገቡ መሪ! " አቶ መልስ ዜናዊ አያት የተትረፈረፈ ሀብት ነበራቸው ተብለው የተጠየቁት ትግሬው ኢትዮጵያዊ አቶ ገብረመድክን አርአያ ሱመልሱ " የፈረስ ማጎሪያ ተፈቅዶላቸው ሲኖሩ አውቃለሁ ቤት ንብረት አልነበራቸውም ትግራይን እንኳን ሰውን ድንጋዩን አውቀዋለሁ!" ታዲያ ውረስ ሌላቸው አቶ ዜናወ እነዴት ሚሊየነር ነበሩ ተባለ? በእርግጥ ባንዳ(ሹምባሽ) {የሶላቶ እንቁላልና ዶሮ አቅራቢ} ሙስና በዚያ ግዜ የተፈጠረ ነውን?
    ***“የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሥአራቸውን ወደ ጎን ትተው በ፳፬ሰዓት ውስጥ በቱርክ የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት ተሰጣቸው” "new blood"? አዲስ ደም! ኢህአዴግ ከቻይና ከአረብ ከአውሮፓ ከአሜሪካ አዲስ ደም ማስገባት ጀመረ? "New generation" ? አዲሱ ትውልድ "young generation" ወጣቱ ትውልድ። በመጨረሻ … አንድ ጥያቄ አለኝ፡ አቶ አያሌው ጐበዜ ስልጣናቸውን የለቀቁበትን ምክንያት በፌስ ቡክ ላይ ይፃፉልን!! (“ኢህአዴግ ፌስ ቡክ መጠቀም ያበረታታል” ሲባል ሰምቼ እኮ ነው!!) የሀገሪቱ መብራት ውሃ ስልክ ኢንተርኔት ለተወሰኑ የሀገሪቱ ዜጎች ብቻ አለ ማለት ነው!? ድንቄም ፌስ ቡክ ምን ፊት አላቸው አይናቸውን በጨው አጥበው የበሉ ውሸታሞች ሁሉ "ፌዘራሊዝም ና ፌዝ ቡክ" ተጠቃሚዎች የበዙበት በተለጠጠ ወሬና አዲስ ደም የተበከለች ክልል በለው!። አቶ አያሌው ጎበዙ አቀበለ …….አቶ ጉድ አድርጋቸው እየሮጠ ነው! ““`…./////////''''''''\\\\\\\\\——-________

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule